ምጽዋት የፊት መብራት ናት፡፡ አንድ ሰው በጨለማ ሲጓዝ ከኋላው መብራት ቢያበሩለትም እንኳ ከፊቱ የሚቀድመው የገዛ የአካሉ ጥላ እንቅፋት እየሆነበት ይጥለዋል፡፡ ወደ ፊት ያለውን መንገድ አጥርቶ እያየ ያለ ስጋት ለመሄድ እንዲችል የግድ የፊት መብራት ያስፈልገዋል፡፡ ጾም፣ ጸሎት እና ሌሎች መንፈሳዊ ትሩፋት እንደ ኋላ መብራት ናቸው፡፡ የፊት መብራት የተሰኘች ምጽዋት ካልታከለችባቸው እነዚህ ብቻቸውን ዋጋን አያሰጡንም፡፡ ከምጽዋት በላይ ታላቅ ነገር እንደሌለ ልንረዳ ይገባል፡፡"*
*ኢትዮጵያዊው አፈወርቅ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ*
“ለድሃው ልብሶቹ ቢያድፉበት በውሃ እጠብለት አዲስም ልብስ ገዝተህ አልብሰው፤ ደሃው ወደ ቤትህ የገባ እንደሆነ እግዚአብሔር ወደቤትህ ይገባል፤ በመኖሪያህም ያድራል፡፡ ከመከራ ከስቃይ ላላቀቅኅው ለዚያ ድሃ እግዚአብሔርም አንተን ከሚመጣብህ መከራና ስቃይ ያላቅቅሃል፡፡
የእንግዳውን እግር አጠብክን? የበዛ ሃጢአትህን አጥበህ አስወገድከው፡፡ ለድሃው ይመገብ ዘንድ ማዕድን አቀረብክለትን? እነሆ እግዚአብሔር አብ ከማዕድህ በላ፤ ክርስቶስም ለደሃው ካቀረብክለት ውሃ ጠጥቶ ረካ፤ መንፈስ ቅዱስም ማደሪያ ቤቱ አደረገህ፡፡
ደሃው ባቀረብክለት ማዕድ በልቶና ጠጥቶ ደስ አለውን? ጌታ ክርስቶስን ደስ አሰኘኅው፤ እርሱ ያደረክለትን መልካም ችሮታ የሚረሳ አይደለምና በመላእክትና በሰወች ፊት ያከብርሃል፡፡ ከረሃቡ እንዳሳረፍከው በመጨረሻው ቀን ይመሰክርልሃል፡ ለጥማቱ የሚጠጣ ስላቀረብክለት በመላእክቱ ፊት ያመሰግንሃል፡፡
ልጄ ሆይ መልካም ዘርን በደስታና እግዚአብሔርን ተስፋ በማድረግ ዝራ ልፋትህም ፍሬ ይስጥህ”
(ከስብከት ወተግሳፅ ዘቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ መጽሐፍ የተወሰደ)