አሏህ ከባሮቹ የተብቃቃ ነው አሏህ ለባሮቹ በጎ ሰሪ ፤ ከባሮቹ የማይፈልግ ፣ በራሱ የተብቃቃ ነው፤
ቸር ፣ አሸናፊ ፣ አዛኝ የሆነ ጌታ ነው።
ከባሪያው የማይከጅል ከመሆኑ ጋር ፣ ለባሪያው በጎ ይሰራ ፣ ለባሪያው መልካምን ይሻል ፣ ከባሪያው ላይ ጉዳትን ያስወግዳል። ይህን የሚፈጽመው ከእርሱ በሆነ እዝነትና በጎ አድራጊነት እንጅ ከባሪያው ጥቅምን ሽቶ ፣ (የሚመጣ) ጉዳት ኖሮ ጉዳትን ከእርሱ ላይ እንዲከላከሉለት ፈልጎ አይደለም።
አሏህ ፍጡራንን የፈጠረው እርሱ አነስተኛ ሆኑ ቁጥሩን ለማብዛት አይደለም ወይም የሚዋረድ ሆኖ በእነርሱ ልቅና ለማግኘት አይደለም ወይም እርሱን ለመመገብ ፣ እርሱን ለመጥቀም አይደለም ወይም ከእርሱ ላይ ጉዳትን እንዲከላከሉለት አይደለም።
አሏህ የሚከተለውን ተናግሯል :-وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ
مَا أُرِيدُ مِنْهُم مِّن رِّزْقٍ وَمَا أُرِيدُ أَن يُطْعِمُونِ
إِنَّ اللَّهَ هُوَ الرَّزَّاقُ ذُو الْقُوَّةِ الْمَتِينُ
"ጅንንና ሰውንም ሊግገዙኝ እንጅ ለሌላ አልፈጠርኳቸውም፡፡ ከነርሱም ምንም ሲሳይ አልፈልግም፡፡ ሊመግቡኝም አልሻም፡፡ አላህ እርሱ ሲሳይን ሰጪ የብርቱ ኀይል ባለቤት ነው፡፡"(ዛሪያት 56-58)
አሏህ የሚከተለውን ተናግሯል :وَقُلِ الْحَمْدُ لِلَّهِ الَّذِي لَمْ يَتَّخِذْ وَلَدًا وَلَمْ يَكُن لَّهُ شَرِيكٌ فِي الْمُلْكِ وَلَمْ يَكُن لَّهُ وَلِيٌّ مِّنَ الذُّلِّ ۖ وَكَبِّرْهُ تَكْبِيرًا
«'ምስጋና ለአላህ ለዚያ ልጅን ላልያዘው፣ ለእርሱም በንግሥናው ተጋሪ ለሌለው፣ ለእርሱም ከውርደት ረዳት ለሌለው ይገባው' በልም፡፡ ማክበርንም አክብረው፡፡»(ኢስራእ :111)
አሏህ ወዳጆቹን የሚወደው ከእርሱ በሆነ በጎነትና እዝነት ነው።
አሏህ የሚከተለውን ተናግሯል:-وَاللَّهُ الْغَنِيُّ وَأَنتُمُ الْفُقَرَاءُ ۚ
"አላህም ሐብታም ነው፡፡ እናንተም ድሆች ናችሁ፡፡" (ሙሀመድ :38)
ፍጡራን እርስ በርስ የሚደጋገፉት ድሃ በመሆናቸው ነው። አፋጣኝ ወይም ዘግይቶ የሚገኝ ጥቅም ሽተው ነው። ጥቅምን ታሳቢ ባያደርጉ ኖሮ አንዱ ለሌለው በጎ ባልሰራ ነበር።
በሀቂቃ ካየነው የሰው ልጅ ለሌሎች በጎ የሚሰራው ከእነርሱ ጥቅም ለማግኘት መዳረሻ መንገድን ለማመቻቸት ነው።
የሰው ልጅ በጎ የሚሰራው በዚህ አለም የመልካም ዋጋውን ፈጥኖ ለማግኘት ወይም ለበጎ ስራው ለውጥ ፈልጎ ወይም ከሌላው ምስጋና እና ውዳሴን ጠብቆ ነው
ወይም በአኼራ ከአላህ ዘንድ ምንዳ ለማግኘት ፈልጎ ነው። በዚህ ምክንያት እርሱ ለነፍሱ በጎ ይሰራል።
ይሁን እንጅ ደካማ ሳይሆን በሚጠቅመው (አሏህ በፈቀደው) ነገር ላይ መጓጓቱ እርሱን የተሟላ ያደርገዋል እንጅ የሚያስወቅሰው አይደለም።
አሏህ የሚከተለውን ተናግሯል :- إِنْ أَحْسَنتُمْ أَحْسَنتُمْ لِأَنفُسِكُمْ ۖ
"መልካም ብትሠሩ ለነፍሶቻችሁ መልካምን ሠራችሁ፡፡" (ኢስራእ :7)
አሏህ የሚከተለውን ተናግሯል وَمَا تُنفِقُوا مِنْ خَيْرٍ يُوَفَّ إِلَيْكُمْ وَأَنتُمْ لَا تُظْلَمُونَ
"ከገንዘብም የምትለግሱት ሁሉ (ምንዳው) ወደናንተ ይሞላል፡፡ እናንተም አትበደሉም፡፡"(በቀራ :272)
አሏህ በሀዲሰል ቁድስ የሚከተለውን ተናግሯል:-(يا عبادي! إنكم لن تبلغوا نفعي فتنفعوني ، ولن تبلغوا ضري فتضروني ، يا عبادي! إنما هي أعمالكن أحصيها لكم ، ثم أوفيكم إياها ، فمن وجد خيرا فليحمد الله ، ومن وجد غير ذلك فلا يلومن إلا نفسه)
أخرجه مسلم (٢٥٧٧)
(ባሮቸ ሆይ! እናንተ እኔን መጥቀም (ብትፈልጉ) መጥቀም አትችሉም ፤ መጉዳት (ብትፈልጉ) መጉዳት አትችሉም ፤ ባሮቸ ሆይ ! እርሷ ስራችሁ ነች፣ ለእናንተም እዘግባታለሁ ፤ ከዚያም እርሷን እመነዳችኋለሁ። መልካምን ያገኘ አላህን ያመስግን ፤ ከእርሱ ውጭ ያገኘ ፣ ነፍሱን እንጅ ሌላን እንዳይወቅስ) "ጢቡል ቁሉብ : 227-228)
https://t.me/alateriqilhaq كن على بصيرة