✅ጁምዓ ላይ መድረስ የሚቻለው በምንድን ነው?
ከኢማሙ ጋር አንድ ረከዓ ከደረሰ ጁምዓን በማግኘቱ የቀረውን አንድ ረከዓ ይጠበቅበታል:: ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ከጁምዓ አንድ ረከዓን የደረሰ ሰላት ላይ ደርሷል›› ኢማሙ ላይ የደረሰው ግን ከአንድ ረከዓ ባነሰ ከሆነ መሙላት ያለበት ዙህር ሰላትን ነው፡፡
✅የጁምዓ ሱና ሰላት
ከጁምዓ በፊት የሚሰገድ መደበኛ ሱና የለም፡፡ ነገር ግን ወቅቱ ከመድረሱ በፊት መደበኛ ያልሆነ ሱና ቢሰግድ ምንም ችግር የለውም ምክንያቱም ነብዩ (ﷺ) በጥቅሉ ሱና መስገድን አበረታተዋል፡፡ ከጁምዓ በኋላ ግን መደበኛ የሆኑ ሁለት፣ አራት ረከዓ ወይም ስድስት ረከዓ ሱናዎችን እንደሁኔታው ሊሰገድ ይችላል፡፡ ቡኻሪና ሙስሊም ባስተላለፉት ሀዲስ ‹‹ነብዩ (ﷺ) ከጁምዓ በኋላ ሁለት ረከዓ ይሰግዱ ነበር››ቡኻሪ 937 ሙስሊም 882 በሌላ ሀዲስ ደግሞ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ ከጁምዓ በኋላ አራት ረከዓ ሱናዎችን ስገዱ››ሙስሊም 881 ኢብን ዑመርም ከጁምዓ በኋላ ስድስት ረከዓዎችን ይሰግዱ እንደነበር ‹‹ነብዩ ይፈፅሙት ነበር››አቡዳውድ 113ዐ እንዳሉ አቡዳውድ ዘግበዋል፡፡ በዚህ መሰረት ከጁምዓ በኋላ የሚሰገድ መደበኛ ሱና ከፍተኛው ስድስት አነስተኛው ሁለት መሆኑን እንረዳለን::
✅የጁምዓ ሰላት አሰጋገድ
የጁምዓ ሰላት ድምፅ ከፍ በመደረግ የሚሰገዱ ሁለት ረከዓዎች እንደሆኑ በነብዩ (ﷺ) ተግባርና በዑለማዎች ስምምነት የተረጋገጠ ነው፡፡ በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሃ በኋላ ሱረቱል ጁምዓ በሁለተኛው ረከዓ ደግሞ ሱረቱል ሙናፊቁንሙስሊም 877 ወይም በመጀመሪያው ረከዓ ከፋቲሃ በኋላ ሱረቱል አዕላ በሁለተኛው ሱረቱል ጋሺያ እንደሚነበብም ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) በተግባር አስተምረዋል፡፡ሙስሊም 878
✅በጁምዓ ዕለት የሚሰሩ ሱና ስራዎች
1. ከፍተኛ ምንዳ ለማግኘት በግዜ ወደ ጁምዓ መስጂድ መሄድ አቡ ሑረይራ ባስተላለፉት ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ የጁምዓ ሰላት ገላውን ታጥቦ በመጀመሪያው ሰዓት የተጓዘ ግመል እንዳቀረበ ነው፣ በሁለተኛው ሰዓት የተጓዘ ከብት እንዳቀረበ ነው፣ በሶተኛው ሰዓት የተጓዘ ቀንዳማ በግ እንዳቀረበ ነው፣በአራተኛው ሰዓት የተጓዘ ዶሮ እንዳቀረበ ነው፤ በ አምስተኛው ሰዓት የሄደ እንቁላል እንዳቀረበ ነው፤ ኢማሙ ሚንበር ላይ ሲወጣ መላእክት ኹጥባ ለማድመጥ ይቀመጣሉ››ቡኻሪ 881 ሙስሊም 85ዐ 1. ገላን መታጠብ
✅2. ከላይ ባሳለፍነው ሀዲስ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ የጁምዓን ዕለት ገላውን ታጥቦ ….›› በየሳምነት ጁምዓ ገላ መታጠብ ሱና ሲሆን በተለይ የሠውነት ጠረን ባለበት ሰው ይበረታል፡፡ አንዳንድ ዑለማዎች ‹‹ጁምዓን ዕለት መታጠብ እያንዳንዱ አቅመ አዳም የደረሰ ሰው ላይ ግዴታ ነው››ቡኻሪ 879 ሙስሊም 486 የሚለውን ሀዲስ መሰረት በማድረግ በጁምዓ ገላ ትጥበት ግዴታ (ዋጂብ) ነው ይላሉ፡፡
✅3. ከትጥበት ውጭ ያሉ ሌሎች ፅዳቶችንም ማከናወን፡፡ ለምሳሌ፡- ሽቶ መቀባት ጥፍርን መቁረጥ፣ የብብትና የሀፍረተ ገላ አካባቢ ፀጉርን ማፅዳት፣ ቀድሞ ቀመስን ማሳጠር እና የመሳሰሉት፡፡
✅ 4.ከልብሶቹ ጥሩውን መልበስ: ኢብን ዑመር ባስተላለፉት ሀዲስ ‹‹ዑመር ኢብን ኸጣብ መስጂድ በር ላይ ከሰይራዕ የመጣ ካባ ተመልክተው ‹‹ የአላህ መልዕክተኛ ሆይ ይህንን ካባ ገዝተው ለጁመዐና እንግዶች ሲመጡ ቢለብሱት?›› ም አል ቡኻሪ ይህንን ሀዲስ በጁምዓ ዕለት ጥሩን ልብስ መልበስ ሱና ስለ መሆኑ መረጃ አድርገው የተጠቀሙበት ሲሆን አልሃፊዝ ኢብን ሀጀር መረጃ ሊሆን የቻለው ነብዩ (ﷺ) የዑመርን ሀሳብ ባለመቃወም ስለተቀበሉት እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ ነብዩም (ﷺ) ‹‹ለስራ ከምትለብሷቸው ሁለት ልብሶች(ሁለት ልብሶች ማለት ከወገብ በታችና ከወገብ በላይ አንድ ጊዜ የሚለብሱትን ማለት ነው) ውጪ ለጁምዓ የሚለበሱ ሁለት ልብሶችን መልካም ነው›› ብለዋል::አቡዳውድ 1ዐ78 ኢብን ማጃህ 1ዐ95
✅5. በነብዩ (ﷺ) ላይ ሰላትና ሰላም ከሌላው ቀን በበለጠ መልኩ ማስፈን ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹ በጁምዓ ዕለት በይበልጥ እኔ ላይ ሰላት አውርዱ››አቡዳውድ 1ዐ47 ነሳኢይ 3/91
✅6. የጁምዓ ሱብሂ ሰላት ላይ በመጀመሪያው ረከዓ ሱረቱ ሰጅዳህ በሁለተኛው ሱረቱል ኢንሳን ማንበብ የነብዩ (ﷺ) ተደጋጋሚ ተግባር ስለነበር ሱና ነው፡፡ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ደግሞ ሱረቱል ከህፍን ማንበብ፡፡ቡኻሪ 891ነ ብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል‹‹በጁምዓ ዕለት ሱረቱል ከህፍን ያነበበ ዕለተ ቂያማ ከእግሩ እስከ ሰማይ ጫፍ የሚያበራ ብርሐን ይኖረዋል፡፡ እንዲሁም ከዕለቱ ጁምዓ እስከ ቀጣዩ ጁምዓ የሚፈፀም ኃጢአት ይማርለታል››ሃኪም 2/368
✅7. መስጂድ ገብቶ ከመቀመጡ በፊት ሁለት ረከዓ መስገድ ነብዩ (ﷺ) ያዘዙትቡኻሪ 93ዐ ተግባር ሲሆን ኢማሙ ኹጥባ ላይ ከሆነ ግን ሰላቱን ቀልጠፍ አድርጎ መስገድ አለበት::
✅8. ጁምዓ ዱዓ ይበልጥ ተቀባይነት ያለው ወቅት በመሆኑ ዱዓ ማብዛት፡ ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል ‹‹በጁምዓ ዕለት አንድ ሰው እየሰገደ ሊገጥመው የሚችል ልዩ ሰዓት አለ፡፡ በዚያ ሰዓት አንድ ሰው አላህን አንድ ነገር ቢጠይቅ ወዲያው ይሰጠዋል፡፡››ቡኻሪ 935 ሙስሊም 852
ቻናላችን ይቀላቀሉ
ለሌሎችም ያስተዋውቁት
@alfiqhulmuyser