🏷በሶላት ላይ እጅ የሚነሳባቸው ቦታዋች
ዐብደሏህ ኢብኑ ዑመር - ረዲየሏሁ ዐንሁማ - ስለ ነብዩ - ﷺ - አሰጋገድ ሲያወራ እንዲህ ይላል ፦ [ ከሁለት ረከዓዎች ሲነሱ እጃቸውን ያነሱ ነበር። ] (ቡኻሪ ፥ 739).
♦️በጥቅሉ እጅ የሚነሳባቸው ቦታዎች አራት ናቸው ፦
1.ተክቢረተል ኢሕራም ሲያደርግ
2.ወደሩኩዕ ሊወረድ ሲል
3.ከሩኩዕ ሲነሳ እና
4.ከመጀመሪያው ተሸሁድ ሲነሳ. ከነዚህ ውጭ እጅ የሚነሳበት ቦታ የለም።
💢የእጅ አነሳስ💢
🛑ሶላት ስንጀምር በተክቢረተል ኢሕራም ጊዜ (አላሁ አክበር በምንል ጊዜ)፤
እጃችንን በትከሻችን ወይም በጆሯችን ትክክል በምናደርግ ጊዜ፤
የእጆቻችን ውስጣዊ ክፍል (መዳፎቻችን) የሚዞሩት ወደ ፊታችን ሳይሆን፣
ወደ ቂብላ አቅጣጫ ነው።
🛑ብዙዎቻችን ግን ሳናውቅም ይሁን ሳናስበው በመርሳት፤
ብዙ ጊዜ የእጆቻችን መዳፍ ወደ ቂብላ ፊት ለፊት የተቅጣጨ ሳይሆን፣
ወደ ፊታችን የተገለበጠ ነው።
🛑 እጆች ሲነሱ ጣቶች ተጠጋግተው መሆን እንዳለባቸው የሚያስገነዝብ ትክክለኛ ሀዲስ ተዘግቧል።
🛑ሴቶችም እንደ ወንዶች በተመሳሳይ መልኩ እስከ ትከሻቸው ወይም እስከ ጆሯቸው ድረስ እጆቻቸውን ማንሳታቸው ሱንና ነው። ከዚህ በተቃራኒ ያሉ እይታዎች "እኔ ስሰግድ እንዳያችሁኝ አስመስላችሁ ስገዱ" ከሚለው ወሳኝ ነብያዊ መርህ ጋር የሚጣረስ አቋም ነው። ኡሙ ደርዳእ እስከ ትክሻዋ ድረስ እንደምታነሳም ተዘግቧል።
🛑 እጆችን እስከ ደረት/ጡቶች ድረስ ብቻ ከፍ ማድረግ፣ በራስ ቅል ትይዩ እስከሚሆኑ ከፍ ማድረግ፣ እጆችን ወደ ጎን አራርቆ ማንሳት፣ ጣቶችን በታትኖ ወይም ጣቶችን ጨብጦ ከፍ ማድረግ፣ መዳፍን ወደጆሮ ወይም ወደ ፊት ማዞር እነዚህ ሁሉ ሱንናውን የሚጻረሩ ተግባራቶች ናቸው።
#ሼር ያድርጉ
••••••••••📚📚•••••••••••
rel='nofollow'>Https://t.me/alfiqhulmuyser/181