እግር ጥሏችሁ ጃፓን ቶኪዮ ከተማ ብትደርሱ የዚህን ውሻ ሀውልት በአንድ ባቡር ጣቢያ ውስጥ ታገኙታላችሁ፡፡ ይህ ውሻ ለ10 አመታት ፍቅርን የሰበከ ታማኝነትን ያወጀ በመሆኑ ጃፓናውያን ይኮሩበታል ይወዱታል፡፡ በነገራችን ላይ የዚህ ውሻ ታሪክ ፊልም ሆኖ ተሰርቷል፡፡ "Hachi: a dogs tale" በ2009 የተሰራው ፊልም ነው።
ይህ ውሻ ስሙ ሀቺኮ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን የፕሮፌሰር ኢዛቡሮን ውሻ ነበር፡፡ ፕሮፌሰሩ ውሻውን በፍቅር አሳደጉት፡፡ ሁሌም ውሻው ጠዋት አብሮ ባቡር ጣቢያ ሄዶ ፕሮፌሰሩን ሸኝቶ ይመለሳል ማታ 11 ሰዓት ባቡር ጣቢያ ሄዶ ይቀበለውና ቤት ድረስ አብሮ ይመጣል፡፡
ታድያ ከእለታት ሁሉ በአንዱ ከፉ ቀን በግንቦት 21 - 1923 ዓ.ም ውሻው ፕሮፌሰሩን ሸኝቶ ማታ እንደልማዱ ሊቀበላቸው ባቡር ጣቢያ ቢጠብቃቸው ሰውዬው ለካ በልብ ድካም ሞተው ኖሯል ሳይመጡ ቀሩ፡፡
ውሻው ግን ይመጣሉ ብሎ ፕሮፌሰሩን ጠበቀ 1 ቀን ብቻ አደለም ጥቂት ወራትም አደለም ድፍን 10 አመት እንጂ እሳቸውን ጥበቃ እዛችው ባቡር ጣቢያው ጋር 10 አመት ጠብቆ እዛው ሞተ፡፡ እናም ሀቺኮ ወዳጁን 10 አመት በፅናት መጠበቁ አያስደንቅም?