ᗩ+ አካዳሚ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


🌟Hard work + Dedication pays off ᗩ+.
👉ለማስታወቂያ @Aplus_Gebeya
🎉 ADS: https://telega.io/c/aplusacademyy

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


💡Big ideas start small. Like Bill Gates, you can build the next big thing. Ready?

Apply here 👉 https://t.me/Founderacademyapplicationguide


#ESSLCE #Schedule

ነገ የሚጀመረው የ2017 ዓ.ም ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት መልቀቂያ ፈተና የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ዙር የፈተና መርሐግብር

በወረቀት እና በኦንላይን የሚሰጠው ብሔራዊ ፈተና ከሰኔ 23 እስከ ሐምሌ 08/2017 ዓ.ም ይቆያል።

ፈተናውን ለመውሰድ 608 ሺህ ተማሪዎች የተመዘገቡ ሲሆን፤ 150 ሺህ የሚሆኑት በበይነ መረብ የሚፈተኑ ናቸው።

✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy


" ተማሪዎች ውጤታቸውን በ https://aa.ministry.et/#/result ላይ መመልከት ይችላሉ " - ቢሮው

በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 88.8 % ያህሉ 50% እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በመዲናዋ የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት ይፋ ተደርጓል።

በ2017 ዓ.ም ፈተናውን ከወሰዱ 70,525 ተማሪዎች መካከል 88.8 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50% እና በላይ አስመዝግበው ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን ይፋ አድርጓል።

ዘንድሮው በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ተማሪዎች መካከል 13 የሚሆኑት በእቴጌ መነን የልጃገረዶች እና በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተማሩ መሆናቸው ተገልጿል።

የዘንድሮው ውጤት በ2016 ዓ.ም ከነበረው የ78.9% ወደ 88.8% ማደጉን በመግለጽ መምህራንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ቢሮው ምስጋና አቅርቧል።

ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ ተጠቁሟል።

ውጤት መመልከቻ ፦ https://aa.ministry.et/#/result

✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy


💡Big ideas start small. Like Bill Gates, you can build the next big thing. Ready?

Apply here 👉 https://t.me/Founderacademyapplicationguide


የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተፈታኞች የመውጫ ፈተና ውጤት ተለቋል። - ትምህርት ሚኒስቴር

የፈተና አገልግሎት ክፍያ (Exam Service Payment) የከፈሉ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውጤት ዛሬ ሰኔ 14/2017 ዓ.ም የተለቀቀ መሆኑን ከትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራር አረጋግጠናል።

በዚህም የፈተና አገልግሎት ክፍያ የከፈሉ ተቋማት የተፈታኞቻቸውን ውጤት እንዲያውቁት የተደረገ ሲሆን፤ የግል ተፈታኞች ወደ ተማሩበት ተቋም በመሔድ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ ተብሏል። 

✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy


PYSICS MODEL EXAMINATION.pdf
537.1Kb
1_G_12_APTITUDE_SAT_2ND_MODEL,_2017_E_C_LAST_EDITED_finalised.pdf
310.3Kb
MODEL                                                                                                  ✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy








ለትምህርት ልማት ስራ ውጤታማነት የሚረዳ ዲጂታል ላይብረሪ ተመረቀ።

(ሰኔ 4/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጄ ዩኒቨርስቲ VDI/virtual desk top infrastructure /የተሰኘ የማስተማሪያና መማሪያ ዲጂታል ላይብረሪ የትምህርት ሚንስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ፣ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ደረጄ እንግዳ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃድ እና ሌሎች አመራሮች በተገኙበት አስመርቋል።

ላይብረሪው የመማር ማስተማር ስራውን በይነ መረብ(online) ለማገዝ የሚያስችል እንዲሁም ዘመኑ የሚጠይቀውን የቴክኖሎጂ ከፍታ ያሟላና ተማሪዎች ከአንድ ዳታ ማዕከል የተለያዩ አጋዥ ግብዓቶችን ማግኘት የሚያስችል በ714 ኮንፒተሮችና በ21 ሰርቨሮች የተደራጀ መሆኑን የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጄ ዩኒቨርስቲ አይሲቲ ዳይሬክተር አቶ አደም ሽኩር ገልፀዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝደንት ዶ/ር ደረጄ እንግዳ የዲጂታል ላይብረሪውን ለስራ ሀላፊዎች ባስጎበኙበት ወቅት ላይብረሪው ከአንድ ማዕከል በአንድ ጊዜ የተለያዩ ፈተናዎችን ለመስጠት ፣ የትምህርት ለማስተማር ፣ ተማሪዎች ከአንድ ማእከል የተለያዩ ሶፍት ዌሮችን እንዲያገኙ እንደሚያግዝ እንዲሁም ከማዕከል በቪዲዮ ኮንትሮል ሩም የሚከናወኑ ተግባራትን ለመቆጣጠር እንደሚያግዝ ገልፀዋል። ✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy


የመምህራን መውጫ ፈተና!

በክረምት የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ለቆዩ 5,521 መምህራን የመውጫ ፈተና ይሰጣል። - ትምህርት ሚኒስቴር

በክረምት የመምህራን ስልጠና መርሐግብር ትምህርታቸውን በተለያዩ የመንግሥት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሲከታተሉ የነበሩ 5,521 መምህራን የመውጫ ፈተና እንደሚወስዱ ተገልጿል።

መምህራኑ የመውጫ ፈተናውን በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተዘጋጁ 35 የፈተና ማዕከላት ሰኔ 10/2017 ዓ.ም እንደሚወስዱ በሚኒስቴሩ የአካዳሚክ ጉዳዮች መሪ ስራ አስፈጻሚ ኤባ ሚጀና (ዶ/ር) ተናግረዋል።

መምህራኑ የመውጫ ፈተናውን ስልጠና በተከታተሉባቸው 24 የትምህርት ፕሮግራሞች እንደሚወሰዱ መሪ ስራ አስፈጻሚው ገልፀዋል።

ተፈታኞቹ ወደ ፈተና ማዕከላት ሲሔዱ ብሄራዊ መታወቂያ (ፋይዳ) መያዝና በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የፈተና ፕሮቶኮል ማክበር ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy


#MoH

ግንቦት 22/2017 ዓ.ም የተሰጠውን የተግባር ምዘና ፈተና (OSCE) የወሰዳችሁ የአንስቴዥያ ተመዛኞች ውጤታችሁን ኦንላይን መመልከት ትችላላችሁ። - ጤና ሚኒስቴር

የአንስቴዥያ ተመዛኞች http://hple.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት ሙሉ ስም እና የፈተና መለያ ቁጥራችሁን በማስገባት የፈተና ውጤታችሁን መመልከት የምትችሉ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

በውጤታችሁ ላይ ቅሬታ ያላችሁ ተመዛኞች ከሰኔ 3/2017 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አስር (10) ተከታታይ የሥራ ቀናት በስልክ ቁጥሮች 0115186275 / 0115186276 በመደወል ጥያቄዎቻችሁን ማቅረብ ትችላላችሁ ተብሏል።

ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ዛሬ ሰኔ 4/2017 ዓ.ም ስም ዝርዝራችሁ ወደ ክልል ተቆጣጣሪ አካላት የሚላክ በመሆኑ፥ ሌሎች ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት የሙያ ፍቃድ ማውጣት የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል።

✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy


Sene 5, 2017 Management Session 3.xlsx
59.8Kb
#AAU #ExitExam

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋም ዕጩ ተመራቂና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የ Management መውጫ ፈተና ተፈታኝ ሆነው ነገ ሰኔ 2/2017 ዓ.ም የሚወስዱ ተፈታኞች ዝርዝር ላይ ስምዎ ከሌለ ሰኔ 5/2017 ዓ.ም በፈረቃ 3 ተፈታኞች ዝርዝር ላይ ስምዎን ይፈልጉ።

✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy


#AAU #ExitExam

በርካታ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ተፈታኞች ፈተናቸውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ይወስዳሉ።

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና በየቀኑ በሦስት ፈረቃ መርሐግብር እንደሚሰጥ ተገልጿል።

ተፈታኞች በተመደቡበት ካምፓስ እና የፈተና ክፍል ብቻ ፈተናቸውን መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።

(የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ቀን የ Management ፈተና መርሐግብር ከላይ ተያይዟል)

✅ ፈረቃ 1: ጠዋት 2:30-5:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 2: ረፋድ ከ 5:30-8:00 ሰዓት
✅ ፈረቃ 3: ከሰዓት 8:00-9:30 ሰዓት

ተፈታኞች ከፈተናው ከሚጀመርበት ሰዓት 30 ደቂቃ አስቀድመው በመፈተኛ ክፍል መገኘት ይጠበቅባቸዋል።

ፈተናውን ለመውሰድ ወደተመደቡበት የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ካምፓስ ሲሔዱ የፋይዳ መታወቂያዎን መያዝ ይኖርብዎታል። ስልክ እና ሌሎች የተከለከሉ ነገሮችን የያዘ/የያዘች ተፈታኝ ወደ ግቢው እንዲገባ/እንድትገባ አይፈቀድላቸውም።

🔔 ስምዎ ከላይ በተያያዘው ዝርዝር ውስጥ ከሌለ የ Management and Business Management ተፈታኞች ሰኔ 5/2017 ዓ.ም በፈረቃ 3 ተፈታኞች ዝርዝር ላይ ተካተዋል።

✨ Share with your  Friends
 
    🎖📖🎖
@aplusacademyy
@aplusacademyy



15 last posts shown.