አተ-ውሒድ.ኮም


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ተውሂድና ከሱ በመቀጠል ያሉ አምልኮዓዊ ትዕዛዛት መልዕክት ማሰራጫ ቻናል

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


ኢብኑልቀዪም (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦

﴿كانَ النَّبِيُّ ﷺ طويلَ السكوتِ لا يتكلمُ في غيرِ حاجة ، ولا يتكلمُ فيما لا يعنيه ، ولا يتكلمُ إلا فيما يرجو ثوابه ، وإذا كَرِهَ الشيءَ عُرِفَ في وجهه.﴾

“የአላህ መልዕክተኛ (ﷺ) ያለ ምንም ጉዳይ (ሐጃ) የማይናገሩና ዝምታቸው ረጅም፣ የማይመለከታቸውን ነገር የማይናገሩ፣ አጅር የሚያስገኝላቸውን ንግግር እንጂ የማይናገሩ፣ አንድን ነገር ሲጠሉ ፊታቸው ላይ የሚታወቅባቸው (ድንቅ) የአላህ መልዕክተኛ ነበሩ።”

📙 ዛዱል አል‐መዓድ፡ 1/175

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


ኢብኑልቀዪም (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦

﴿أَرْبَعَةٌ تَهْدِمُ الْبَدَنَ: الْهَمُّ، وَالْحُزْنُ، وَالْجُوعُ، وَالسَّهَرُ.﴾

“አራት ነገሮች አካልን በጣም ያጎዳሉ። ጭንቀት፣ ሀዘን፣ ረሃብ፣ በግዜ አለመተኛት።”

📙 ዛዱል አል‐መዓድ፡ 4/378

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


ዲናዊ ተግባር ምንግዜም በቁርዓንና ሀዲስ መልዕክት ላይ ብቻ ተገድቦ ይተገበራል። በግል አመለካከት የሚፈፀም ምንም አይነት የዲን ትዕዛዝ የለም!!

ዐሊይ ቢን አቡ ጧሊብ (رضي ﷲ عنه) እንዲህ ይላሉ፦

﴿لو كان الدينُ بالرأي لكان أسفلُ الخُفِّ أولَى بالمسحِ من أعلاهُ ، وقد رأيتُ رسولَ اللهِ ﷺ يمسحُ على ظاهرِ خُفَّيهِ﴾

“ዲን በግላዊ አስተያየት ቢሆን ኖሮ የስረኛው የእግር ክፍል ከላይኛው ይልቅ ሊታበስ ይገባው ነበር፡፡ ነገር ግን የአላህ መልእክተኛ (ﷺ) ሲያብሱ ያየሁት የላይኛውን ነው።”

📙 አውኑል መዓቡድ፡ 1/139

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


ሸይኹል ኢስላም ኢብኑ ተይሚያህ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦

﴿ومصيبة تقبل بك على الله
خير لك من نعمة تنسيك ذكر الله عز وجل.﴾

“የላቀውን አላህ እንድትረሳ ከሚያደርግ ኒዕማ (ፀጋ) ፊትህን ወደ አላህ እንድታዞር ያደረገ ሙሲባ (መከራ) ይሻላል።”

📙 ጃሚዑ አል‐መሳዒል፡ 9/287

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


የሰዎችን መብት ከማጎደል አደራህን!

ሶፊያን አስውሪ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦

﴿إن لقيت الله تعالى بسبعين ذنبًا فيما بينك وبين الله تعالى؛ أهون عليك من أن تلقاه بذنب واحد فيما بينك وبين العباد﴾

“ባንተና በባሪያዎች መካከል ያለ አንድ ወንጀል ይዘህ ከላቀው አላህ ጋር ከምትገናኝ ይልቅ ባንተና በላቀው አላህ መካከል ያለ ሰባ ወንጀል ይዘህ ብትገናኘው የቀለለ ነው። ”

📙 ተንቢሁል ጋፈሊን ሰመርቀንዲይ፡ 1/380

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


ሶፊያን ቢን ዑየይናህ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦

﴿لولا ستْر الله عزَّ وجلَّ ما جالسَنا أحدٌ﴾

“የላቀው አላህ ወንጀላችንን ባይደብቅልን ኖሮ፤ በዙሪያችን አንድም የሚቀማመጠን አይኖርም ነበር።”

📙 ሹዕበል ዒማን ሊልበይሃቂ፡ 6/290

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


📌 የዱዓችን ተቀባይነት ማጣት ምክንያቱ ምን ይሆን?

ﻣﺮ ﺇﺑﺮﺍﻫﻴﻢ ﺑﻦ ﺃﺩﻫﻢ ﺭﺣﻤﻪ ﺍللّٰه تعالى ﺑﺴﻮﻕ ﺍﻟﺒﺼﺮﺓ ؛ ﻓﺎﺟﺘﻤﻊ ﺍﻟﻨﺎﺱ ﺇﻟﻴﻪ، ﻭﻗﺎﻟﻮﺍ: ﻳﺎ ﺃﺑﺎ ﺇﺳﺤﺎﻕ: ﻣﺎ ﻟﻨﺎ ﻧﺪﻋﻮﺍ ﻓﻼ ﻳُﺴﺘﺠﺎﺏ ﻟﻨﺎ؟

ኢብራሒም ኢብኑ አድሀም (رحمه الله) በበስራ ገበያ ሲያልፉ ሰዎች ተሰብስበው ወደሳቸው ከበቧቸውና እንዲህ አሏቸው፦ ያ አባ ኢስሃቅ ዱዓእ አድርገን ዱዓችን ለምን ምላሽ አጣ?

ﻗﺎﻝ: لإﻥ ﻗﻠﻮﺑﻜﻢ ﻣﺎﺗﺖ ﺑﻌﺸﺮﺓ ﺃﺷﻴﺎﺀ!.

እሳቸውም፦ ቀልባችሁ (ልባችሁ) በአስር ነገሮች ሞታለች አሏቸው።

ﻗﺎﻟﻮﺍ: ﻭﻣﺎ ﻫﻲ؟ ﻗﺎﻝ:

እነሱም፦ ምን ምንድ ናቸው? ብለው ጠየቋቸው።
እሳቸውም፦

‏✅ﺃﻧﻜﻢ ﻋﺮﻓﺘﻢ ﺍللّٰه؛ ﻓﻠﻢ ﺗﺆﺩّﻭﺍ ﺣﻘّﻪ.
‏አንደኛ፡ አላህን አውቃቹት።ሐቁን አልተወጣችሁም።

‏ ‏✅ﺯﻋﻤﺘﻢ ﺃﻧﻜﻢ ﺗﺤﺒّﻮﻥ ﺭﺳﻮﻝ ﺍﻟﻠّٰﻪ (ﷺ) ﺛﻢ ﺗﺮﻛﺘﻢ ﺳﻨّﺘﻪ.
ሁለተኛ፡ ነቢዩን (ﷺ) እንወዳለን ብላችሁ ሞገታችሁ፤  ከዚያም ሱናውን ተዋችሁ።

‏ ‏✅ﻗﺮﺃﺗﻢ ﺍﻟﻘﺮﺁﻥ، ﻭﻟﻢ ﺗﻌﻤﻠﻮﺍ ﺑﻪ.
‏ሶስተኛ፡ ቁርኣንን አነበባችሁት አልሰራችበትም።

‏ ‏✅ﺃﻛﻠﺘﻢ ﻧﻌﻤﺔ الله، ﻭﻟﻢ ﺗﺆﺩّﻭﺍ ﺷﻜﺮﻫﺎ.
‏አራተኛ፡ የአላህን ፀጋ በልታችሁ ምስጋናውን አልተወጣችሁም።

‏ ‏✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥّ ﺍﻟﺸﻴﻄﺎﻥ ﻋﺪﻭّﻛﻢ، ﻭﻭﺍﻓﻘﺘﻤﻮﻩ.
‏አምስተኛ፡ ሸይጣን ጠላታችነው ብላችሁ ከሱ ጋር ገጠማቹ።

‌‏✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﺠﻨّﺔ ﺣﻖ، ﻓﻠﻢ ﺗﻌﻤﻠﻮﺍ ﻟﻬﺎ.
‏ስድስተኛ፡ ጀነት ሐቅ ናት ብላችሁ ለርሷ የሚሆን ስራ አልሰራችሁም።

‏ ‏✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﻨّﺎﺭ ﺣﻖ، ﻭﻟﻢ ﺗﻬﺮﺑﻮﺍ ﻣﻨﻬﺎ.
‏ሰባተኛ፡ የጀሀነም እሳት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሷ የሚዳርጋችሁት ስራ አልተዋቹም።

‏ ‏✅ﻗﻠﺘﻢ ﺇﻥ ﺍﻟﻤﻮﺕ ﺣﻖ، ﻓﻠﻢ ﺗﺴﺘﻌﺪّﻭﺍ ﻟﻪ.
‏ስምንተኛ፡ ሞት ሐቅ ነው ብላችሁ ለሱ አልተሰናዳችሁም።

‏ ‏✅ﺍﻧﺘﺒﻬﺘﻢ ﻣﻦ ﺍﻟﻨﻮﻡ، ﻭﺍﺷﺘﻐﻠﺘﻢ ﺑﻌﻴﻮﺏ ﺍﻟﻨﺎﺱ، ﻭﺗﺮﻛﺘﻢ ﻋﻴﻮﺑﻜﻢ.
‏ዘጠነኛ፡ ከእንቅልፋቹ ነቅታቹ፤ የራሳችሁን ነውር ትታችሁ በሰዎች ነውር ተጠመዳችሁ።

‏ ‏✅ﺩﻓﻨﺘﻢ ﻣﻮﺗﺎﻛﻢ، ﻭﻟﻢ ﺗﻌﺘﺒﺮﻭﺍ ﺑﻬﻢ
‏አስር፡ ሙታናችሁን ቀብራችሁ በነሱ አልተገሰፃችሁም።

📙 ጃሚዑል በያን ዓልዒልም ወፈድሊህ፡ 2/12

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


አላህ ሆይ! የስሜታችን ተከታይ (ባሪያ) አታድርገን!

ፉደይል ኢብኑ ዒያድ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦

﴿لَيْسَ فِي الأَرْضِ شَيْءٌ أَشَدُّ مِنْ تَرْكِ الشَّهْوَةِ﴾

“በዚህ ዓለም ውስጥ ስሜትን (የግል ዝንባሌን) አንደመተው የበረታ (የከበደ) የሆነ አንድም ነገር የለም።”

📚 [አል‐ሂሊያ (98/8)]

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


በርግጥም ትልቅ ተማፅኖ!

አብደላህ ቢን ዐምሩ (رضي ﷲ عنهما) እንዲህ በማለት አላህን ይማፀኑ ነበር፦

﴿اللهمَّ لا تَنْزعْ منِّي الإمانَ كما أَعْطَيْتَنيه﴾

“አላህ ሆይ! ኢማንን (እምነትን) ከሰጠኽኝ በኋላ ከኔ ላይ አትውሰድብኝ።”

📚 ኢብኑ አቢ ሸይባህ ሙሰነፍ ውስጥ ዘግበውታል፡ 30964

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


በሺር ቢን አል‐ሃሪስ (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦

﴿لا تعمل لتذكر: اكتم الحسنة كما تكتم السيئة﴾

“ለመታወስ ብለህ ስራን አትስራ። መጥፎ ስራህን እንደምትደብቀው ሁሉ ጥሩ ስራህንም ደብቅ።”

📚 [አሲየር፡ 10/476]

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


አቡ ኽልደህ አልበስሪ (رحمه الله)  እንዲህ ይላሉ፦

﴿أدرَكْتُ النَّاسَ وهُم يعمَلون ولا يقُولُونَ وهُم اليَومَ يقُولونَ ولا يعملُونَ﴾

“ሰዎች ላይ ደርሻለሁ (አግኝቻለሁ) እነሱ መልካም ስራ ይሰራሉ አይናገሩትም። ዛሬ ግን ያሉት ይናገሩታል ግን አይሰሩትም።”

📚 [«አልኪታቡ ሰምት» ሊኢብን አቢ ዱኒያ (678)]

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


ሶፊያን አስውሪ (رحمه الله) እንዲህ ይሉ ነበር፦

﴿إذا عرفتَ نفسَك لم يضرَّكَ ما قيلَ لَكَ،﴾

“አንተ ስለራስህ የምታውቅ ከሆነ፤ ስላንተ የሚባለው የሰዎች ንግግር አይጎዳህም።”

[«አልሙኽለሲያት» ሊአቢ ጣኺር አልሙኽለስ (1626)]

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


ኢማሙ ኢብኑልቀዪም (رحمه الله) እንዲህ ይላሉ፦

﴿الصدقة تأثيرٌ عجيب في دفع البلاء ودفع العين ودفع شر الحاسد﴾

“ሰደቃ መከራን በመከላከል ላይ የሚገርም ተፅዕኖ አለው። እንዲሁም በአይን የሚመጣን ችግር፤ በክፋትና በምቀኝነትም የሚመጣን ችግር ይከላከላል።”

📚 በዳዒዑል ፈዋዒድ: (2/234)

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM


ረቢግፊርሊ!

ሉቅማን አል‐ሀኪም ለልጃቸው እንዲህ አሉት፦

﴿يا بني عود لسانك رب اغفر لي فإن لله ساعات لا يرد فيها سائل﴾

“ልጄ ሆይ! ምላስህ ረቢግፊርሊ ‘ጌታዬ ሆይ ምህረትን ለግሰኝ’ በማለት ላይ የሙጥኝ ይበል፤ የላቀው አላህ የጠያቂዎችን ጥያቄ መልስ የማይመልስበት (የሚቀበልበት) ወቅት አለና።”

[ሹዕበል ዒማን: 1120]

ጆይን፦ https://t.me/ATWHIDCOM








Forward from: የቡኻሪና ሙስሊም ሐዲሶች በአማርኛ
#የሰማህውን ሁሉ አታውራ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

كَفى بالمَرْءِ كَذِبًا أنْ يُحَدِّثَ بكُلِّ ما سَمِعَ

“ለአንድ ሰው ውሸታም ለመባል በቂው ነው የሰማውን ሁሉ ማውራቱ።”

📚 ሙስሊም ዘግበውታል: 309

ጆይን፡‐ https://t.me/BuhariMuslimAmhari


Forward from: የቡኻሪና ሙስሊም ሐዲሶች በአማርኛ
#አላህን የማውሳት ትሩፋት!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

إنَّ (الحمدَ للهِ، وسُبحانَ اللهِ، ولا إلهَ إلّا اللهُ، واللهُ أكبرُ) لَتُساقِطُ من ذُنُوبِ العبدِ كما تَساقَطَ ورَقُ هذه الشجرَةِ

“አልሀምዱሊላህ፣ ወሱብሃነላህ፣ ወላኢላሃ ኢለላህ ወላሁ አክበር የሚሉት ንግግሮች (አዝካሮች) ልክ ከዛፋ ላይ ቅጠሎች እንደሚረግፉት የባሪያውን ወንጀሎች ታራግፋለች።”

📚 ሶሂህ አተርጊብ: 1570

ጆይን፡‐ https://t.me/BuhariMuslimAmharic


Forward from: የቡኻሪና ሙስሊም ሐዲሶች በአማርኛ
#ከንፍቅና ባህሪያት ራስህን አፅዳ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿ إنَّ أثقلَ الصَّلاةِ على المنافقين صلاةُ العشاءِ والفجرِ ولو يعلمون ما فيهما لأتوْهما ولو حبوًا﴾


“በሙናፊቆች ላይ እንደፈጀር እና ዒሻእ ሶላት የሚከብድ የለም። ጥቅሟን ቢያወቁ ኖር እየተንፏቀቁም ቢሆን ወደ መስጂድ ይመጧት ነበር።”

📚 ቡኻሪ (657) ሙስሊም (651) ዘግበውታል

ጆይን፡‐ https://t.me/BuhariMuslimAmharic

20 last posts shown.