ከምድር ስር መጠለያዎች እንዳትወጡ:-እስራኤል ‼
የእስራኤል ጦር የአየር መከላከያዎች እስከ 20% የሚደርሱ ከኢራን የተወነጨፉ ባሊስቲክ ሚሳኤሎችን መጥለፍ አልቻልኩም ሲል የመጀመሪያ ጊዜ የስታቲስቲክስ መረጃ ሰኞ እለት ይፋ ማድረጉ ተገለፀ ።
እንደ ኢየሩሳሌም ፖስት ዘገባ ከሆነ ከኢራን የተወነጨፉ በሽዎች የሚቆጠሩ ሚሳኤሎች ከ80 እስከ 85 በመቶ የሚሆነውን 300 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኙ ሚሳዔሎችን መከላከል ይችላል የተባለው በዕብራይስጥ “ተዓምረኛው ዘንግ” በመባል የሚጠራው የዳዊት ወንጭፍ (ዴቪድስ ስሊንግ) “አሮው 2” (ቀስት) አይረን ዶም ጨምሮ ሌሎች ዘመናዊ ፀረ ሚሳዔል መከራ ከጥቅም ዉጭ ማድረጉንና ቀሪዎቹን ማክሸፍ ባለመቻሉ ኢራን ወደ እስራኤል የላቀ የአየር መከላከያ ስርዓት ውስጥ ዘልቆ በመግባት ዋና ዋና ከተሞችን የቴክኖሎጂ የሳይንስ ምርምር ጣቢያዎችን ኢላማ በመምታቷ የእስራኤል ጦር ስትራቴጂውን እንዲቀይር አስገድዶታል። ብለዋል ።
ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ኢራን የእስራኤልን የአየር ጥቃት አፀፋ ስታደርግ እንደ ቴል አቪቭ እና ሃይፋ ባሉ ትላልቅ ከተሞች ላይ በባለስቲክ ሚሳኤሎች መደብደብ ችላለች።
አብዛኛው የኢራን የሚሳኤል ጥቃት በቴል አቪቭ እና በማዕከላዊ እስራኤል፣ በሰሜን እስራኤል ሃይፋ አካባቢ እና በደቡብ በቤርሼባ አካባቢ ላይ ያተኮረ ነው እነዚህ ሚሳኤሎች የእስራኤል ባለ ብዙ ሽፋን እና ባለብዙ ቢሊዮን ዶላር የአየር መከላከያ ስርዓት ከአይረን ዶም - ዋናው አካል - ቀስት ፣ ዴቪድ ወንጭፍ እና የብረት ምሰሶ ፀረ ሚሳኤሎችን አልፈው መግባት እንደቻሉ ጥናት እያደረግን ነዉ ።ሲሉ ለእየሩሳሌም ፖስት ተናግሯል ።
እንደ ዘገባው ከሆነ ሠራዊቱ "ያለማቋረጥ ስልቶችን እያስተካከለ" ነው እና ኢራን ጥቃቷን እንዴት እንደምትፈጽም ለመረዳት እየሞከረና አዲስ ስታራቴጂ እየነደፈ ይገኛል እስከዛዉ ድረስም ዜጎች በምድር ስር በሚገኙ ደህንነቱ በተጠበቀ ክፍል ውስጥ እንዲጠለሉ አልፎ ተርፎም የማስጠንቀቂያ መልዕክቶችን ድምፅ እንዲከታተሉ መክሯል።
=====================
💎⬇️⬇️⬇️👇👇👇👇👇👇
የቴሌግራም ቻናላችንን join በማድረግ ወቅታዊ መረጃዎችን በቀላሉ ይከታተሉ፣ሊንክ👇
https://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2shttps://t.me/+Vl6V8k9V3YNEOp2s