ዜጎች ተደራጅተው የሚሰሩበት ልዩ የሥራ ዕድል!
የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ለዜጎች በሚፈጠር የሥራ እድል ዳቦ በልቶ ከማደር በላይ እንዲሆን ለማስቻል ብዙ ሥራዎችን ከግልና መንግስታዊ ከሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ሲሰራ ቆይቷል። በዚህም ወደ ውጪ ሃገር ሄደው መሥራት ለሚፈልጉ ዜጎች በውጪ ሃገር የሥራ ስምሪት ተጠቃሚ መሆን እንዲችሉ ለማድረግ ብዙ ሥራዎች ተከናውነዋል።
አሁንም በከፊል በሰለጠነ እና በቤት ውስጥ ሥራ ከምናሰማራቸው ዜጎች በተጨማሪ የሰለጠኑ ዜጎችንም ለመላክ የሚያስችል ሥራ ለመሥራት ብዙ ጥረት ተደርጓል ወደ ተግባርም እየተገባ ይገኛል።
በውጪ ሃገር ሥራ ስምሪት ላይ ብዙ ተግባራት እየተከናወኑ እንደመሆናቸው ሁሉ በሃገር ውስጥ ደግሞ የራሳችን ሃሳብ አለን፣ በቡድንም ሆነ በግል ተደራጅተን መስራት እንፈልጋለን ለምትሉ ዜጎች ሌላኛውን አማራጭ ዕድል አቅርበናል።
ይህም ዕድል በኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት በመመዝገብ በተዘረጋው የ(Enterprise Development System) ስርዓት የፋይናንስ እና የሥልጠና ድጋፍ ማግኘት ነው።
በመሆኑም ይህንን ዕድል መጠቀም የምትፈልጉ ዜጎች ሁለት ነገር ማድረግ ይጠበቅባችኋል የመጀመሪያው በኢትዮጵያ ሥራ ገበያ መረጃ ስርዓት መመዝገብ ሲሆን በመቀጠል የሳይኮሜትሪክ ምዘና በመውሰድ የትኛው ሞያ ውስጣችሁ ካለው ተሰጥኦ ጋር እንደሚስማማ ካረጋገጣችሁ በኋላ የፋይናንስና የሥልጠና እንዲሁም ልዩ ልዩ ድጋፍ የሚደረግላችሁ በመሆኑ ውጤታማ የሆነ ኢንተርፕራይዝ መመሥረት የምትችሉበት እድል ይፈጠራል።
የሥራ ባለቤት እርስዎ ነዎት!