በዚያ ብርቱ ቆራጥ ጀግና
ዛሬም ድረስ ሀገር ገ'ና
ገድል ሰርቶ ሲያልፍ ነፍሱ
"ታሪክ ስሩ" ነበር ጥቅሱ
ደሙ ፈሶ ለሀገር ገድል
ከንቱ ትውልድ የእኛ ዕድል
.
ከንቱ ትውልድ ጀብድ የራቀው
ዘረኝነት ያራራቀው
ምን ዋጋ አለው መሸለሉ
ምን ዋጋ አለው መፎከሩ
ተነካክሶ በሀገሩ!
.
አናስመስል አንካካድ
ግብራችን ነው ታሪክ መናድ
አናስመስል አንካካድ
የትኛችን ሀገር ወዳድ?
.
ባሪያ ሆነን በአዙር ግዝት
ዛሬም ቆመን የምንዝት
ከሩቅ ለሚያይ የበረታን
ሀቂቃው ግን የተረታን
.
በየቱ ትውልድ
ጨቅላ ህፃን ተደፈረ
በየቱ ዘመን
ሰው በቁሙ ተቀበረ
በየቱ ትውልድ
ልጅ እናቱን አቃለለ
በየቱ ዘመን
ንፁህ ወገን ተሰቀለ?
.
በእኛው ሆኖ ይህ እርግማን
በየቀኑ አዲስ ለቅሶ
አዲስ ሲቃ እየሰማን
እያወቅነው ሀቃችንን
አናሞኘው ልባችንን
.
የኛ አድዋ የእኛ ስኬት
መጨካከን ያለ ልኬት
የኛ አድዋ የእኛ አድራሻ
ከንፁህ ደም መፋሰሻ
.
አንሸነጋገል ዐቁ ይኼው ነው።
[ ጥሩቤል ]
@tirrubel
@ebuh_bhr
@ebuh_bhr
ዛሬም ድረስ ሀገር ገ'ና
ገድል ሰርቶ ሲያልፍ ነፍሱ
"ታሪክ ስሩ" ነበር ጥቅሱ
ደሙ ፈሶ ለሀገር ገድል
ከንቱ ትውልድ የእኛ ዕድል
.
ከንቱ ትውልድ ጀብድ የራቀው
ዘረኝነት ያራራቀው
ምን ዋጋ አለው መሸለሉ
ምን ዋጋ አለው መፎከሩ
ተነካክሶ በሀገሩ!
.
አናስመስል አንካካድ
ግብራችን ነው ታሪክ መናድ
አናስመስል አንካካድ
የትኛችን ሀገር ወዳድ?
.
ባሪያ ሆነን በአዙር ግዝት
ዛሬም ቆመን የምንዝት
ከሩቅ ለሚያይ የበረታን
ሀቂቃው ግን የተረታን
.
በየቱ ትውልድ
ጨቅላ ህፃን ተደፈረ
በየቱ ዘመን
ሰው በቁሙ ተቀበረ
በየቱ ትውልድ
ልጅ እናቱን አቃለለ
በየቱ ዘመን
ንፁህ ወገን ተሰቀለ?
.
በእኛው ሆኖ ይህ እርግማን
በየቀኑ አዲስ ለቅሶ
አዲስ ሲቃ እየሰማን
እያወቅነው ሀቃችንን
አናሞኘው ልባችንን
.
የኛ አድዋ የእኛ ስኬት
መጨካከን ያለ ልኬት
የኛ አድዋ የእኛ አድራሻ
ከንፁህ ደም መፋሰሻ
.
አንሸነጋገል ዐቁ ይኼው ነው።
[ ጥሩቤል ]
@tirrubel
@ebuh_bhr
@ebuh_bhr