በሥራ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ ባህሪያት
አሉታዊ ባህሪ ፤- ማለት ነገሮች ሁሉ መጥፎ ናቸው ብሎ መፈረጅ ወይም መፃኢን በመልካም ከመጠበቅ ይልቅ መጥፎ ሁኔታዎችን አስቀድሞ በማሰብ አጨልሞ የማየት ባህል ነው፡፡
አሉታዊ ባህሪያት ዓይነቶች ሞገደኝነት (Aggressive) እና የማይታገል /ቀሰስተኛ (Passive) በሚል የሚፈረጁ ሲሆን ዝርዝራቸው ቀጥሎ ቀርቧል፡፡
ሞገድኝነት (Aggressive Behaviors)
1. ነቃፊ፦
• ይህ ባህሪ የሚታይባቸው ሰራተኞች፡- ማንኛውንም ግለሰብ ገንቢነት በጎደለው መልኩ መተቸት፣ ለሁሉም ነገሮች መንገዱ/መፍትሔው አንድ ብቻ ነው ብለው የሚያምኑ እና ይህንንም መንገድ ለማሳመን ኃይልን አማራጭ አድርገው የሚወስዱ፤ ግጭቶችን በመፍጠር የሚታወቁና ለዚህ መነሻቸው ደግሞ ትኩረትና እንክብካቤ ከመፈለግ አኳያ ነው፡፡
2. ኃይለኝነት፦
• እነዚህ ሰራተኞች ቁጣን በጩኸት የሚያሰሙና ጩኸታቸውም እንደ ብራቅ የሆነ ይህን የሚያደርጉት ከዚህ ውጭ ሌላ መንገድ የለም ብለው ስለሚያስቡ/ስለሚያምኑ ነው።
3. አስመሳይነት፦
• በዚህ ባህሪ የሚገለጹ ሰራተኞች፡- ለማንኛውም ጉዳይ ቃል/ውለታ የሚገቡና በገቡት ቃል/ውለታ መሰረት የማይፈጽሙ ፣ውሸት መናገር የማይችሉ፣ “አሙቄ" በመባል ይታወቃሉ፣ ክትትልና ቁጥጥር እንዲደረግባቸው የማይፈልጉ ማሳፈርና ማሸማቀቅ የሚወዱ ናቸው፡፡
4. ብሶተኛ/ጨለምተኛ፦
• ይህ ባህሪ ያለባቸው ሰራተኞች፡-ባልደረቦቻቸውን መወንጀል የሚወዱ ፣በማንኛውንም ጉዳይ ላይ ቅሬታ የሚያሰሙ ፣ሁሉም ነገር የተሳሳተ /መጥፎ ነው የሚል አመለካከት የገነቡ፣ዓለም ከሰው ልጆች ቁጥጥር ውጭ ነች ብለው የሚያምኑና እነሱ ራሳቸውንም አቅመ ቢስ አድርገው የሚቆጥሩ፣ ናቸው፡፡
5. ጀብደኝነት/ጉራ:-
• በዚህ ባህሪ የሚፈረጁ ሰራተኞች፡-እራሳቸውን እንደ ጀግና /ጀብደኛ የሚቆጥሩ ፣ከማንኛውም ሰራተኛ በላይ ለተቋሙ ጠቃሚ ነኝ ብለው የሚያምኑ ፣ቀውስ /ትርምስ እንዲፈጠር የሚፈልጉ፣ናቸው፡፡
ቀሰስተኛ /ቀዝቃዛ ስሜት/ ባህሪያት (Passive/submissive Behavior)
1. ዝግ/ዝምተኛ/አይናፋር፦
• ይህ ባህሪ የሚታይባቸው ሰራተኞች፡- ለሚጠየቁት ጉዳይ ምላሽ የማይሰጡ ፣ምላሽ ከሰጡም አንድ ጊዜ ብቻ በአይናቸው ቀና ብለው በማየት ምላሽ የሚሰጡ ፣ ሙሉ በሙሉ ምላሽ የማይሰጡና እና የጥላቻ መንፈስ የተጠናወታቸው ናቸው፡፡
2. እኔ ብቻ አዋቂ ነኝ ባይ፦
• በዚህ የባሕሪ አይነት የሚገለጹ ሰራተኞች፡- ራሳቸውን እንደ ሊቅ የሚቆጥሩ፣ የዕውቀት ደረጃቸው ከፍተኛ ነው ብለው የሚያምኑ፣ ስራቸው ትክክል ነው መባልን የሚፈልጉ ፣ ለዚህም ሁልጊዜ አድናቆትን የሚፈልጉ ናቸው፡፡
3. ቢሮክራት፦
• ይህ የባህሪ አይነት የሚታይባቸው ሰራተኞች፡- ጉዳዮችን ለምን እንደምታከናውን እና እንደማታከናውን ሕጎችንና ደንቦችን አዘውትረው የሚጠቅሱ፣ ሥራዎችን ለማከናወን የሚያስችል አቅም የለኝም ብለው የሚያምኑ (ራሳቸውን አቅመ ቢስ አድርገው የሚቆጥሩ)፣ ናቸው፡፡
4. በራስ አለመተማመን፦
• በዚህ ባህሪ የሚፈረጁ ሰራተኞች፡- ውሳኔ ለመወሰን የሚቸገሩ ትክክለኛውን ሥራ ለመፈጸም የሚፈልጉ ነገር ግን ትክክለኛ ስለ መሆናቸው በራስ የመተማመን ችግር ያለባቸው ናቸው፡፡
5. ፋይዳቢስ፦
• የዚህም ባህሪ ባለቤት የሆኑ ሰራተኞች ለተቋሙ ምንም አይነት አስተዋጽኦ የሌላቸው ናቸው ፤ ማለትም በተቋሙ ውስጥ ቢኖሩም የሚጨምሩት የሌለ፣ ባይኖሩም የሚያጎድሉት የሌለ አይነት ናቸው፡፡
አሉታዊ ባህሪ ያለባቸው ሰዎች የሚታይባቸው የጋራ ባህሪያት
1. ሁልጊዜ ትኩረት የሚሰጡት ለመጥፎ ጎኖች ብቻ ነው፣ ሁሉንም በጥሩ ወይም በመጥፎ ፅንፍ/ጫፍ መመልከት (black or white)፣ ሁሉንም በአንድ ላይ መፈረጅና ስም መስጠት፣ ጉዳዩን በአግባቡ ሳይመረምሩ ድምዳሜ ላይ መድረስ፣ ጉዳዮችን ለግለሰቦች መስጠትና መወንጀል፡፡
2. ለአሉታዊ ባህሪያት መፈጠር መንስኤዎችና ውጤቶች ሁሉም አሉታዊ ባህሪዎች የሚመነጩት የዕወቀት/ግንዛቤ ማነስ፣ የአስተዳደግ ችግር፣ የባህል ተጽዕኖ፣ በራስ የመተማመን ችግር፣…ወዘተ ሲሆን ውጤቶቹም ሙገሳና አድናቆት መፈለግ፣ ቅቡልነትን/ተቀባይነትን መሻት፣ መገለልን/ጥላቻን መፍራት ናቸው፡፡
አሉታዊ ባህሪያትን በራስ አቅም ማስወገጃ መንገዶች፦
• ከሚገኘው ውጤት ጭምር ግብ ማስቀመጥ፦ ያሉብንን አሉታዊ ባህሪዎች መለየት እና ለእነዚህ አሉታዊ ባህሪዎች መቀነሻ /ማስወገጃ ስልት ወይም ተግባር ከሚገኘው ውጤትና ጊዜውን ጭምር ማስቀመጥ ማለት ነው፡፡
• አወንታዊ ባህሪን ማሳደግ (Develop assertive behavior)፦ ይህ ባህሪ ሃሳብን፣ ስሜትን፣ አስተያየትንና ፍላጎትን፣ …ወዘተ በቀጥታ፣ ቅንነት በተሞላበትና ህግና ሥርዓትን አክብሮ የመግለጽ ክህሎትን የማሳደግ ሂደት ነው ፡፡ የዚህ ባህሪ ባለቤት የሆኑ ሰዎች የራሳቸውን መብትና ግዴታ በአግባቡ የሚረዱና የሚተግበሩ እንዲሁም የሌሎችንም መብት የሚያከብሩ ናቸው፡፡ በመሆኑም የርስበርስ ግንኙነት የተቃናና ውጤታማ በማድረግ በኩል የተዋጣለት መንገድ ነው፡፡
• የመደማመጥ/የማድመጥ ክህሎትን ማሳደግ፦ የማድመጥ ክህሎት ከዋና ዋና የቋንቋ ክህሎቶች ውስጥ በከፍተኛ ደረጃና ልናሳድጋቸው ከሚገቡ ክህሎቶች በግንባር ቀደምትነት ይጠቀሳል፤ ለዚህም በምክንያትነት የሚጠቀሰው ጉዳዮችን በአግባቡ ማድመጥ ከሌለ ተገቢውን ምላሽ መስጠት የለም፡፡ ለተገቢው ሃሳብ ትክክለኛው ምላሽ መስጠት ካልተቻለ ደግሞ መግባባት የለም፣ ካልተግባቡ አብሮ መስራት አይቻልም፣ አብሮ መስራት ካልተቻለ ደግሞ የሚጠበቀውን ውጤት በሚጠበቀው ደረጃ ማስመዝገብ አይቻልም፡፡
• መቆጣጠር/መፈታት በሚቻሉ ጉዳዮች ላይ ብቻ ማተኮር፦ የፓሬቶ ህግ/መርህ በመባል የሚታወቀውን 80/20 መተግበር ነው፡፡ ይህ መርህ የሚያስገነዝበው 80 በመቶ የሚሆነውን አቅም፣ ጊዜ ፣ሃብት፣…ወዘተ 20 በመቶ ለሚሆኑት ወሳኝ ጉዳዮች/ችግሮች በማዋል አብዛኞቹን ችግሮች መፍታት ነው፡
• የመወያየት ባህልን ማዳበር፦ የውይይት ባህልን ማዳበር ከላይ ከተገለጸው የማድመጥ ክህሎትን ማሳደግ ከሚለው ሃሳብ ጋር ተመሳሳይነት ውጤት ያለው ነው፡፡ተወያይቶ ጉዳዮችን የመፍታት ክህሎትና አቅም ማሳደግ መልካም የሆነ የቡድን ስሜትን ለመፍጠር ያስችላል፣ የመከባበርና የመቻቻል ስሜትን ያሳድጋል፣ ሥራዎችን በተሻለ ደረጃ ለማከናወን ያስችላል፡፡
• በመደበኛም ሆነ መደበኛ ባልሆኑ መድረኮች /ግንኙነቶች ላይ ገንቢነት የሌላቸውን አስተያየቶች አለመስጠት፦ አፍራሽ የሆነ አስተያየት የሰዎችን የመወያየትና የማድመጥ ፍላጎት የሚዘጋና የርስ በርስ ግንኙነትን የሚያሻክር ተግባር ነው ፤ በመሆኑም አስተያየት የመስጠት ባህላችን ከአወንታዊ ጎኖች በመነሳት ድክመት የሚታይባቸውን ደግሞ ሊያስተምርና አስተያየት ተቀባዩ በሙሉ ፍላጎቱ ሊቀበለውና ወደፊት ሊያስተካክለው በሚችል አግባብ መሆን አለበት፡፡ይህ ሲሆን ሰዎች ከድክመታቸው የመማርና የመሻሻል እድላቸው የሰፋ ይሆናል ፣ለሌችም አርዓያ ይሆናሉ፡፡
• አብረውን ያደጉ መጥፎ ልምዶችና አስተሳሰቦችን ማስወገድ ናቸው።
🙏መልካም ምሽት ይሁንላችሁ🙏