ማሰብ ጉዞ ነው፡፡ እምነት ግን በእኛ ሐገር ማረፊያህን ካገኘህ በኋላ የምታደርገው ጉዞ ነው፡፡ አምነህ ስለምትጀምር ብዙ ጊዜ አምላክን አታገኘውም፡፡ በሕይወትህ ውስጥ የሆነ ጥያቄ ሲመጣብህ ሮጠህ የሀይማኖት አባትህን ትጠይቃለህ እንጂ ለራስህ አታስበውም፡፡ ስትወለድ ተወልደሀል፡፡ አድገህበታል፡፡ ስሙን (ክርስቲያን ወይም ሙስሊም የሚለውን) ሰጥተውሃል፡፡ አምነሃል፡፡ የትም አትሄድም፡፡ ፍለጋ አታደርግም፡፡ “አንብበው እስቲ” ተብሎ የእምነት መጽሐፍ ቢሰጥህ እንኳን የምታነበው መልስ ለመስጠት እንጂ ለማመንና አለማመን አይደለም፡፡ ያመንከውን አምነሃል፡፡ እምነት ውስጥ ለምሳሌ “አምላክ አለ-የለም” የሚለው አይነት ሐሳብ አለ፡፡ ሐሳብ ውስጥ ግን እምነት የለም፡፡
ሐሳብ ጉዞ ነው፡፡ ሁሌ ታስባለህ፡፡ ፍፁም አይደለሁም” ነው የሚለው የሚያስብ ሰው፡፡ የሚያስብ ሰው ከሚያምነው በጣም የሚለይበት ጥሩ ጐኑ አሳቢው “ጐዶሎ ነኝ” ሲል አማኙ “ፍፁም ነኝ” ይላል፡፡ ትልቁ ልዩነታቸው ይህ ነው፡፡ አንድን አማኝ ስለ ኳንተምን ፊዚክስ አንሳና ጠይቀው እስኪ፡፡ “ሁሉም ነገር እኮ መጽሐፉ ላይ ተጽፏል፡፡ ምንም ያልተጻፈ ነገር የለም” ነው የሚልህ፡፡ ግን ምናልባትም መጽሐፉን አላነበበው ሁሉ ይሆናል፡፡ ቢያነብም አልመረመረውም ይሆናል፡፡ አምኖ መጀመር ማለት ይኼ ነው፡፡ የሃይማኖት መጽሐፉን በጥልቀት አንብቦ መፈተሽን እንደ ሐጢአት ነው የሚወስደው፡፡ አምኖ መጀመር ችግሩ ይሄ ነው፡፡ ካመንክ አምነሃል በቃ፡፡ ፍተሻ አያስፈልግህም፡፡ ስለዚህ ባታነብም፣ አንብበህ ባይገባህም “ልክ ነው” ብለህ ትወስዳለህ፡፡ አሳቢ ግን እንደዚያ አይደለም፡፡ ሁሌም አዲስ ሐሳብ እንዳለ ያስባል፡፡ አስር ገፅ እንዳነበበ ይጠይቃል፡፡ በሐሳብ በየቀኑ እያደግህ ትሔዳለህ፡፡ በኛ ሀገር በእምነት ውስጥ ግን በየቀኑ እያነስክ ነው የምትሄደው።
ቡርሃን አዲስ ነው ይህንን የነገረን