🟢 🟡 🔴
ታኅሣሥ 15
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በዚች ቀን ያለ ደም መፍሰስ ሰማዕት የሆነ የአርማንያ ሊቀ ጳጳሳት ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዐረፈ።
ይህ ቅዱስ ንጉሡ ድርዳጥስ ስለሃይማኖቱ በጉድጓድ ጥሎት፣ በጉድጓዱ ውስጥም ቀሩንና ሐሩሩን ታግሦ ለ15 ዓመታት ቆይቷል። ምግቡንም አንዲት ቅድስት አሮጊት በእግዚአብሔር ትዕዛዝ ሁል ጊዜ ታመጣለት ነበር።
ኋላም ንጉሡ ከሠራዊቱ ጋር አብዶ ወደ አውሬነት ስለተቀየረ ቅዱሱን ከጉድጓድ አውጥተዉት ሁሉንም ፈውሷቸዋል። ኋላም ሊቀ ጳጳሳት ሆኖ የአርማንያን ሰዎች የክርስትና ጥምቀትን አጥምቋቸዋል።
ወደ ዕብራውያን 12:1-2
"እንግዲህ እነዚህን የሚያህሉ ምሥክሮች እንደ ደመና በዙሪያችን ካሉልን፣ እኛ ደግሞ ሸክምን ሁሉ ቶሎም የሚከበንን ኃጢአት አስወግደን፣ የእምነታችንንም ራስና ፈጻሚውን ኢየሱስን ተመልክተን፣ በፊታችን ያለውን ሩጫ በትዕግሥት እንሩጥ። እርሱ ነውርን ንቆ በፊቱም ስላለው ደስታ በመስቀል ታግሦ በእግዚአብሔር ዙፋን ቀኝ ተቀምጦአልና።"
አምላከ ቅዱሳን የቅዱሳኑን ልብና ቆራጥነት ያድለን!