በኢትዮጵያ ብቁ የሆኑ የሂሳብ ባለሙያዎች ቁጥር ከ500 አይበልጥም ተባለ !
በኢትዮጵያ የሰለጠኑ እና ብቁ የሆኑ የሂሳብ ባለሙያዎች ቁጥር እጅግ አነስተኛ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በመሆኑም የተመሰከረላቸውን የሂሳብ ባሙያዎች እጥረት ለመቅረፍ የሚያስችል ስልጠና ኤችኤስቲ ስኪል አካዳሚ መስጠት መጀመሩን አስታውቋል።
በተቋሙ በትምህርት እና ስልጠና ላይ ስትራቴጂክ ቢዝነስ ዩኒት ስኪል አካዳሚ ዳይሬክተር የቦርድ አባል እና የሪስክ እና ኦዲቲ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ ጎበዜ ደሳለኝ ከብስራት ሬዲዮ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደገለፁት በኢትዮጵያ በሂሳብ አያያዝ ቴክኒካል ብቃት ብቁ የሆኑ የሒሳብ ባለሙያዎች ቁጥር ከ500 አይበልጥም።ከዚህ ቀደም ስልጠናውን ለማግኘት ወደ ውጪ ሀገራት መሄድ አስገዳጅ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ጎበዜ ይህንን የሚያስቀር እና ከከፍተኛ ወጪ የሚያድን ስልጠና በሀገር ውስጥ በድረገጽ አማካኝነት እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል
ከ12ኛ ክፍል ጀምሮ በተለያዩ የስራ ሁኔታዎችም ሆነ የትምህርት ዘርፍ ላይ የሚገኝ ማንኛውም ሰው በየትኛውም ቦታ ላይ ሆኖ ስልጠናውን መውሰድ ይችላል። በማኔጅመንት፣ በኦዲት ፋይናንስ ታክስ፣ እንዲሁም በሌሎች የሙያ ዘርፎች በ12 የትምህርት አይነቶች ስልጠናው የሚሰጥ ሲሆን ትምህርቱን ለመማር ከ12 እስከ 18 ወራት ይወስዳል
ለአንድ የትምህርት ዘርፍ የ3ሺህ ብር የገንዘብ ክፍያ ብቻ የሚጠየቅ መሆኑን የገለፁት አቶ ጎበዜ አስራ አንድ ድርጅቶች ስልጠናውን ይሰጣሉ ሲሉ አክለዋልከእነዚህም መካከል ሶስቱ የግል ድርጅቶች መሆናቸው የተገለፀ ሲሆን አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ ስምንቱ ደግሞ የመንግስት ድርጅቶች ናቸው።የዩኒቨርሲቲ ተቋማት በቋሚነት ከሚሰጡት ትምህርት በተለየ መልኩ ስልጠናውን በተግባር እንደሚሰጡ ተነግሯል