ኢብኑ ሰኢድ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


«ይህች መንገዴ ናት፡፡ ወደ አላህ እጠራለሁ፡፡ እኔም የተከተለኝም ሰው በግልጽ ማስረጃ ላይ ነን፡፡ ጥራትም ለአላህ ይገባው፡፡ እኔም ከአጋሪዎቹ አይደለሁም» በል፡፡ ዩሱፍ 108
~~~~~~~~

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


የአፋልጉኝ ማስታወቂያ


ጨረቃ ባለመታየቷ ኢድ አልፊጥር ረቡዕ ይሆናል።


ከውሸት እንራቅ!!
~
🔻ነብዩ (ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦[አደራ ውሸትን ተጠንቀቁ! ውሸት ወደ ጥመት ይመራል፤ ጥመት ደግሞ ወደ እሳት ይመራል።] ቡኻሪና ሙስሊም ዘግበውታል


🚫መውሊድ ቢድዓ ነው‼️

#መ መለያ ምልክት የሙብተድዕ አርማ
#ው #ውስጡን_የገነባ_በኹራፋት_ኮርማ
#ሊ ሊያጠወልግ ክብሩን የኢስላሜን ውበት
#ድ ድብቅ መርዙን ሊረጭ ሊያስቀረኝ ራቁት
#ቢ ቢያግበሰብስ ሙክት ሺወችን ቢያበላ
#ድ ድቤውም ቢያጓራ ቢወገር በዱላ
#ዓ ዓይኑ እስኪቀላ ቢቅም ቢያመነዥክ
#ነ #ነውና_ቢድዓ_የድን_ጠላት_እሾክ
#ው ውስጣችን ቁልፍ ነው🔐




Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ሰለፊይ ነን የምንል እህት ወንድሞች ልናዳምጠው የሚገባ ወሳኝ ምክር !


   የመልካም ነገር መክፈቻ ሁን !!

  ነቢዩ ሶለላሁ አለይሂ ወሰላም እንዲህ ይላሉ
" إِنَّ مِنَ النَّاسِ مَفَاتِيحَ لِلْخَيْرِ مَغَالِيقَ لِلشَّرِّ،

 "ከሰዎች መካከል ለኸይር መክፈቻ ቁልፍ የሆንና ሸርን ደግሞ የሚዘጋ አለ።"

እንደዚሁም
وَإِنَّ مِنَ النَّاسِ مَفَاتِيحَ لِلشَّرِّ مَغَالِيقَ لِلْخَيْرِ،
 "ከሰዎች መካከልም እንደዚሁ የሸርን በር የሚከፍቱ ወይንም ለሸር በር መከፈት ምክንያት የሆኑ ቁልፎችና የኸይር ወይንም የመልካም ነገር በር መዘጋት ምክንያት የሆኑ ቁልፎች አሉ።"

فَطُوبَى لِمَنْ جَعَلَ اللَّهُ مَفَاتِيحَ الْخَيْرِ عَلَى يَدَيْهِ،
"የኸይርን በር መክፈቻ በእጁ ያደረገለት ሰው፤ ይህ ትልቅ እድል አግኝቷል።"

وَوَيْلٌ لِمَنْ جَعَلَ اللَّهُ مَفَاتِيحَ الشَّرِّ عَلَى يَدَيْهِ "
"የሸር ቁልፎችንም በእጁ ያደረገበት ሰውም ወየውለት!።" ይላሉ።
ኢብኑ ማጃህና ሌሎች ዘግበውታል አልባኒ ሀሰን ብለውታል

  


🌾አሰላሙዐለይኩም ወራሐምቱሏሂ ወበረካቱህ
〰〰〰
ጥያቄ
🔸ሴት ልጅ ግሩፕ ከፍታ ወንዶችንም ሴቶችንም ማስተማር እና በተለያዩ ቡድኖች ላይ ረድ መስጠት ከነሱ ጋር መከራከር ትችላለችን? አንዳንዴ በፅሁፍ አንዳንዴ በሪከርድ እየገባች
〰〰〰
መልስ:-በሸይኽ ሙሐመድ ዐረብ
~
https://telegram.me/daruselam


አነስ ኢብኑ ማሊክ (ረዲየላሁ ዐንሁ) እንዲህ ይላሉ፦
"ነቢዩ( ﷺ) ተሳዳቢ፣አስቀያሚ ንግግርን ተናጋሪ ሆነ ተራጋሚ አልነበሩም።"
📚【ቡኻሪ ዘግበውታል】


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
👉የሰዎችን አቋም ምንፈትነው በአህሉ ሱና ኡሱል ወይም በኢማምነታቸው ጥርጥር የሌለባቸውን መሻኢኾች ኢማም አህመድ ኢማም ሻፊዒ ኢማም ማሊክን ይመስል ነው።

👉በመንደር ሼኽና ኡስታዝ የሰውን ሱንይነት መፈተን አትችልም።
✍Dawud Ali AbuAsiya


🌾የጁምዓ እለት ትሩፋት

☞የጁምዓ እለት የሳምንቱ ምርጥ ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አላህ ዘንድ ከቀናቶች ሁሉ በላጩ የጁምዓ እለት ነው።» ብለዋልና በዚህ እለት ስራዎቻችንን ይበልጥ ማሳመር ይገባናል።
📚صححه الألباني في
السلسلة الصحيحة - رقم: (1502)
صحيح الجامع -  رقم: (1098)

☞የጁምዓ እለት በጀማዓ (በህብረት) የተሰገደ የፈጅር ሰላት ከየትኛውም ወቅት ሰላት በላጭ ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አላህ ዘንድ በላጩ ሰላት በጁምዓ እለት በጀማዓ የተሰገደ የሱብህ ሰላት ነው።» ብለዋልና ከየትኛውም እለት በበለጠ ቀድሞ ለመገኘት መጣር ይበልጥ ያስመነዳል።
📚السلسلة الصحيحة -
الألباني صحيح - رقم: 1566

☞የጁምዓ እለት ከሌሎች ቀናት በበለጠ በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋት የማውረጃ ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«በጁምዓ ቀንና በጁምዓ ሌሊት በኔ ላይ ሰለዋትን አብዙ። በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ላወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ያወርዳል።» ብለዋልና ትንሽ ሰርተን ከአስር እጥፍ በላይ ለማግኘት ከወዲሁ እድሉን እንጠቀም።
📚صحيح الجامع 
الألباني حسن - رقم: 1209

☞የጁምዓ እለት መኖሩም መሞቱም ለሙስሊሙ ፀጋ ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«ማንኛውም ሙስሊም የጁምዓ ቀን ወይም የጁምዓ ሌሊት የሞተ እንደሆን አላህ ከቀብር ፈተና ሳያድነው አይቀርም።» ብለዋል።
 ስለዚህ በመጀመርያ የዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆን
☞አርካኑል ኢስላምን በስርዓቱ የተገበረ ሙስሊም እንሁን።
☞በማስከተልም አላህ በራህመቱ ከቀብር ፈተና እንዲጠብቀንና ለዚህ ሰበብም እንዲያበቃን ሁሌም እንለምነው።
📚حسنه الألباني في صحيح الترمذي - رقم: (1074) ، تخريج مشكاة المصابيح - رقم: (1316) الألباني :إسناده حسن أو صحيح لغيره

☞የጁምዓ እለት የሳምንቱ ከኃጢኣት መንፂያ ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«ከባባድ ኃጢኣቶች ኖረው ካልጋረዱት በስተቀር አምስቱ ሰላቶች እንዲሁም ከጁምዓ እስከ ጁምዓ በመሃከላቸው ያለውን ኃጢኣት ያብሳሉ።»¹ በሌላ ዘገባም «ከባባድ ኃጢኣቶች ኖረው ካልጋረዱ በስተቀር ከጁምዓ እስከ ጁምዓ በመሃከላቸው ላለው ማበሻ ናቸው።»² ብለዋል።

  ስለዚህ ከከባባድ ወንጀሎች በመራቅ ወይም ተውበት በማድረግ፣ አምስቱን እለታዊ ሰላቶች ጠብቆ በመስገድና የሳምንቱን ልዩ የስብስብ ቀን የጁምዓን ሰላት በመስገድ ተጨማሪ ግድፈቶቻችንን እናፅዳ።
¹📚صحيح مسلم - رقم: (233)
²📚الألباني - صحيح الجامع رقم: (3110)

☞ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የመከባበርያ ቀን ነው።

ሁሉም ሙስሊም ክቡር ነው። ሀብታም ከድሃ ታላቅ ከታናሽ፣ ገዢ ከተገዢ የሚለይበት ቦታ አየደለምና መስጂድ ሲደርስ ያገኘበት ክፍት ቦታ ሊቀመጥ ይገባዋል እንጂ ማንንም አስነስቶ ወይም እንዲነሳ አስደርጎ ሊቀመጥ አይገባውም። 

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አንዳችሁ በጁምዓ ቀን ወንድሙ የተቀመጠበት ቦታ ሊቀመጥ ብሎ እንዳያስነሳው። ነገር ግን ሰፋ ሰፋ አድርጉ ይበል።» ብለዋልና ኢማሙ ኹጥባ ያልጀመሩ እንደሆነ ሰዎችን እንዲጠጋጉለትና እንዲሸጋሸጉለት በስርዓት ማግባትም ይችላል።
📚صحيح مسلم - رقم: (2178)

☞ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የፅዳት ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ
«አንዳችሁ ወደ ጁምዓ ሲሄድ ይታጠብ።» ማለታቸው ተዘግቧል።
📚صحيح البخاري - رقم: (882)


☞ጁምዓ የሳምንቱ ልዩ የቁርኣን ቀን ነው።

የአላህ መልእክተኛ ﷺ ቀጣዩን ብለዋል☞
«በጁምዓ ቀን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው በሁለቱ ጁምዓዎች መሃል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።»
📚حسنه الألباني في
تخريج مشكاة المصابيح - رقم:(2116)

በሌላም ዘገባ እኛ በተለምዶ ሐሙስ ማታ በምንለው የጁምዓ አጥቢያ ምሽቱን ሱረቱል ካህፍን ለቀራ ሰው አጅሩ እጅግ በጣም ሰፊ ነው።
«ለይለቱል ጁምዓ ሱረቱል ካህፍን ላነበበ ሰው በሱ እና በበይተል ዐቲቅ (በካዕባ) መካከል ያለውን ያህል ከብርሃን ያበራለታል።» ብለዋል።
📚صححه الألباني في
صحيح الترغيب -رقم: (736)

☞በተጨማሪም የጁምዓ እለት የማንንም ክብርና መብት የማንጥስበት፣ ከውስጥም ከውጭም በወሬም ሆነ በሌላ ጉዳይ ሰውን እንዳንረብሽ የተከለከልንበት ልዩ ቀን ነው። ይህንንም ለዒባዳ ብለን መስጂድ እንኳን መጥተን ክፍት ቦታ ፍለጋ ከሰው ትከሻ ላይ እየተረማመድን እንዳንሄድ ከልክለውናል። ኢማሙ ኹጥባ ላይ ሳሉ ምንም አይነት ቃል ትንፍሽ እንዳንል ተከልክለናል። ጣቶቻችንን ከመሰባበርም ሆነ ልብሶቻችንን ሆነ ሌላ ነገር አየነካካን እንዳንጫወት ተከልክለናል።

ማንኛውም ሰው በጁምዓ እለት ወደ መስጂድ ሲመጣ ክፍት ቦታ ከፊትለፊቱም ሆነ ከጎኑ ክፍተት እንዳይኖር ወደፊት መጠጋትን የመሰለ እንደገባ በማመቻቸት መቀመጥ አለበት። ምክንያቱም ከኋላ የሚመጡት ቦታ ፍለጋ ስህተት እንዳይፈፅሙና ክብሩንም እንዳይነኩ ይረዳልና። በመሰረቱ ቦታ ፍለጋ ከሰው ትከሻ ላይ መረማመድ ተከልክለናል። ኢማሙ ኹጥባ ላይ ሳሉ ምንም አይነት ቃል ትንፍሽ እንዳንልም ተከልክለናል። ጣቶቻችንን ከመሰባበርም ሆነ ልብሶቻችንን ሆነ ሌላ ነገር አየነካካን እንዳንጫወትም ተከልክለናል።
ባጠቃላይ
የሰው ትከሻ አትርገጥ~እንዳትወራገጥ
አርፈህ ተቀመጥ~በፀጥታ አድምጥ
ለጌታህ እጅ ስጥ
 
اللهم صل وسلم على نبينا محمد وعلى آله وأصحابه أجمعين


ሰዎችን በተብዲዕ ኢልዛም ማድረግ የሰለፎች መንገድ አይደለም፡፡
~~~~
☞መንሃጅ አንድ ሆኖ ኤከሌን ኤከሌ ሙብተዲዕ ብሎታል አንተ ኤከሌን ሙብተዲዕ ካለልክ አንተም ሙብተዲዕ ነህ የሚባለው ህግ የሰለፎች መንገድ አይደለም።
☞ኢኬሌን ሙብተዲዕ ካለልክ ብሎ ሰውን ማክሮፍ አለመናገር ይህ ከፊል እውቀት ያላቸው ሰዎች የሚያደርጉት ተግባር ነው ስለዲን ምንም አያውቁም፡፡
☞ሸይኽ ኢብኑ ባዝ በአጥፊዎች ላይ ረድ ያደረግ ነበር ነገር ግን የዚህን አይነት ነገረን አይከተልም ነበር፡፡
ሙሉ ኦዲዮን ያደምጡ!!
🔊🔊 ሸይኽ አብዱልሙህሲን አል-ዓባድ
~
https://telegram.me/daruselam


ሸይኽ ኢብራሂም ብን ሷሊህ አል-ሙሐይሚድ ለወራቤ ዩንቨርስቲ የላፕቶፕ ድጋፍ አደረጉ፡፡


የአሏህ መልዕክተኛ ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል:- ["ሙስሊም ማለት ሙስሊሞች ከምላሱ እና ከዕጁ (አደጋና ክፋት) የዳኑ (ሰላም የሆኑ)ሰው ነው"] ቡኻሪ ዘግበውታል


የጀናዛ ሰላት አሰጋገድ
አራት ጊዜ ተክቢራ ይደረጋል፤
☞ ከመጀመሪያ ተክቢራ በመቀጠል አል ፋቲሀ
(የመክፈቻው ምዕራፍ) ይነበባል። ከዚህም በተጨማሪ
አጠር ያለ የቁርአን ምዕራፍ ወይም አንድ ወይም ሁለት
አንቀፅ ቢያነብ ጥሩ ነው። ይህንን በማስመልከት
ከአብደላህ ኢብን አባስ የተዘገበ ትክክለኛ ሀዲስ ስላለ
ነው።
☞ ከዚያም ለሁለተኛ ጊዜ ተክቢራ ይደረጋል፤
ከተሸሁድ ቀጥሎ እንዳለው በነብዩ ላይ ሰለዋት
ያወርዳል። ከዚያም በሶስተኛው ተክቢራ ከተደረገ በኃላ
እንዲህ ይላል
( ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟِﺤﻴﻨﺎ ﻭﻣﻴﺘِﻨﺎ، ﻭﺷﺎﻫﺪﻧﺎ ﻭﻏﺎﺋﺒﻨﺎ، ﻭﺻﻐﻴﺮﻧﺎ ﻭﻛﺒﻴﺮﻧﺎ،
ﻭﺫَﻛَﺮِﻧﺎ ﻭﺃﻧﺜﺎﻧَﺎ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﻣﻦ ﺃﺣﻴَﻴﺘَﻪُ ﻣﻨﺎ ﻓﺄﺣﻴﻪ ﻋﻠﻰ ﺍﻹﺳﻼﻡ، ﻭﻣﻦ
ﺗﻮﻓﻴﺘﻪ ﻣﻨﺎ ﻓَﺘَﻮَﻓﻪُ ﻋﻠﻰ ﺍﻹﻳﻤﺎﻥ، ﺍﻟﻠﻬَﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟﻪ، ﻭﺍﺭﺣﻤﻪ،
ﻭﻋﺎﻓﻪ،
ﻭﺍﻋﻒ ﻋﻨﻪ، ﻭﺃﻛﺮِﻡ ﻧُﺰُﻟَﻪ، ﻭَﻭَﺳﻊ ﻣُﺪﺧَﻠَﻪ، ﻭﺍﻏﺴﻠﻪ ﺑﺎﻟﻤﺎﺀ
ﻭﺍﻟﺜﻠﺞ
ﻭِﺍﻟﺒﺮﺩ، ﻭﻧﻘﻪ ﻣﻦ ﺍﻟﺨﻄﺎﻳﺎ ﻛﻤﺎ ﻳﻨﻘﻰ ﺍﻟﺜﻮﺏ ﺍﻷﺑﻴﺾ ﻣﻦ ﺍﻟﺪَﻧﺲ،
ﻭﺃﺑﺪﻟﻪُ ﺩﺍﺭﺍ ﺧﻴﺮﺍ ﻣﻦ ﺩﺍﺭﻩ، ﻭﺃﻫﻼ ﺧﻴﺮﺍ ﻣﻦ ﺃﻫﻠﻪ، ﻭﺃﺩﺧﻠﻪ ﺍﻟﺠﻨﺔ،
ﻭﺃﻋﺬﻩ ﻣﻦ ﻋﺬﺍﺏ ﺍﻟﻘﺒﺮ، ﻭﻋﺬﺍﺏ ﺍﻟﻨﺎﺭ، ﻭﺍﻓﺴﺢ ﻟﻪ ﻓﻲ ﻗﺒﺮﻩ، ﻭﻧﻮﺭ ﻟﻪ
ﻓﻴﻪ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﻻ ﺗَﺤﺮﻣﻨَﺎ ﺃﺟﺮﻩ ﻭﻻ ﺗُﻀِﻠﻨﺎ ﺑﻌﺪﻩ )
(አላሁመ ኢግፊር ሊሐይና ወመይቲና ወሻሂድና ወጋኢቢና
ወሰጊሪና ወከቢሪና ወዘከሪና ወኡንሳና አላሁመ መን
አህየይተሁ ሚና ፈአህይሂ አለል ኢስላም ወመን
ተወፈይተሁ ሚና ፈተወፈሁ አለል ኢማን አላሁመ ኢግፊር
ለሁ ወግሲልሁ ቢልማኢ ወሰልጂ ወልበረዲ ወነቂሂ
ሚነል
ዙኑቢ ወል ኸጣያ ከማ ዩነቀ ሰውቡል አብየዲ ሚነደነሲ
ወአብዲልሁ ዳረን ኸይረን ሚን ዳሪህ ወአህለን ኸይረን
ሚን አህሊህ ወአድኺሉሁል ጀነተ ወአዒዙሁ ሚን ዓዛቢል
ቀብሪ ወዓዛቢ ናር ወፍሰህ ለሁ ፊ ቀብሪሂ ወናዊርለሁ
ፊህ አላሁመ ላተህሪምና አጅረሁ ወላቱዲለና ባዕደሁ።)
ትርጉሙም: “አላህ ሆይ በህይወት ያሉትንም፣
የሞቱትንም፣ በቅርብ ያለውንም ሩቅ ያለውንም፣
ትልልቆችንም፣ ትንንሾችንም፣ ወንዶችንም ፣ ሴቶችንም
ማርልን። አላህ ሆይ ከመካከላችን የምትገለውን በእምነት
ላይ እንዲሞት አድርገው። አላህ ሆይ ምህረት
አድርግለት፣
እዘንለትም፣ ከእሳት ጠብቀው፣ ይቅርም በለው፣
መስተንግዶውን አሳምርለት፣ መግቢያውንም አስፋለት፣
አጢአቱንም በውሃ፣ በበረዶና በቀዝቃዛ ውሃ እጠብለት፣
ነጭ ልበስ ከቆሻሻ እንደሚፀዳው የእርሱንም ወንጀል
አፅዳለት፣ ከቤቱ የተሻለ ቤት ከሚስቱ የተሻለ ሚስት
ቀይርለት። ወደ ገነት አስገባው፣ ከቀብር ውስጥ ቅጣትና
ከእሳትም ቅጣት ጠብቀው ቀብሩንም አስፋለት፣
አብራለት። አላህ ሆይ ምንዳውን አትንፈገን ከእርሱም
በኃላ እጣችንን ጥመት አታድርግብን።” ማለት ነው።
☞ ከአራተኛው ተክቢራ በኃላ በቀኝ ጐኑ ብቻ
“አሰላሙአለይኩም” በማለት ይጠናቅቃል።
ተክቢራ በሚደረግበት ጊዜ እጅን ማንሳት ይወደዳል።
√ ሴት ከሆነች ዱዓው ላይ እንዲህ ይባላል፤
( ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟﻬﺎ . . ) (አላሁመ እግፊርለሃ)
√ ሁለት ከሆኑ ደግሞ ( ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟﻬﻤﺎ . . . ) (አላሁመ
እግፊር ለሁማ)
√ ከሁለት በላይ ከሆኑ ደግሞ ( ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﻏﻔﺮ ﻟﻬﻢ . . )
(አላሁመ እግፊር ለሁም) ይባላል።
√ ሟቹ ህፃን ከሆነ ለእርሱ ምህረትን በዱዓው ውስጥ
ከመለመን ይልቅ እንዲህ ይባላል።
( ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺍﺟﻌﻠﻪ ﻓﺮﻃﺎ ﻭﺫُﺧْﺮَﺍ ﻟﻮﺍﻟﺪﻳﻪ، ﻭﺷﻔﻴﻌﺎَ ﻣُﺠَﺎﺑﺎ، ﺍﻟﻠﻬﻢ ﺛﻘﻞ
ﺑﻪ
ﻣﻮﺍﺯﻳﻨﻬﻤﺎ، ﻭﺃﻋﻈﻢ ﺑﻪ ﺃﺟﻮﺭﻫﻤﺎ، ﻭﺃﻟﺤﻘﻪ ﺑﺼﺎﻟﺢ ﺳﻠﻒ ﺍﻟﻤﺆﻣﻨﻴﻦ،
ﻭﺍﺟﻌﻠﻪ ﻓﻲ ﻛﻔﺎﻟﺔ ﺇﺑﺮﺍﻫﻴﻢ ﻋﻠﻴﻪ ﺍﻟﺼﻼﺓ ﻭﺍﻟﺴﻼﻡ، ﻭَﻗِﻪِ ﺑﺮﺣﻤﺘﻚ
ﻋﺬﺍﺏ
ﺍﻟﺠﺤﻴﻢ )
(አላሁመ ኢጅዓሉሁ ፈረጠን ወዙኽረን ሊዋሊደይሂ ፤
ወሸፊዓን ሙጃበን አሏሁመ ሰቂል ቢሂ መዋዚነሁማ፤
ወአዕዚም ቢሂ ኡጁረሁማ፤ ወአልሂቁሁ ቢሷሊሂ
ሰለፊልሙእሚኒን፤ ወጅዓልሁ ፊ ከፋለቲ ኢብራሂመ
አለይሂ ወሰላቱ ወሰላም ወቂሂ ቢራህመቲከ አዛበል
ጀሂም)
√ ትርጉሙም “አላህ ሆይ በወላጆቹ (በወዲያኛው
ህይወት) ቀደሞ ሄዶ የሚያመቻች፣ ለችግር ቀን አለኝታ፣
ተሰሚነት ያለው አማላጅ አድርግላቸው፣ አላህ ሆይ
የመልካም ስራቸው ሚዛን ማክበጃና የምንዳቸው ማብዣ
አድርገው፣ ከደጋግ ምእመናን ጋርም አስጠጋው ከነብዩ
ኢብራሂም u እንክብካቤ ስር አድርገው፣ በችሮታህም
ከጀሐነም እሳት ጠብቀው።”
☞ ኢማሙ በሟች ላይ ለመስገድ ሲቆም ወንድ ከሆነ
በጭንቅላቱ አቅጣጫ ሴት ከሆነች በሰውነቷ መሀል
አቅጣጫ መቆሙ ሱና ይሆናል።
☞ አስክሬኑ ወንድና ሴት ከሆኑ ወንዱ ወደ ኢማሙ
በኩል
ሴቷ ወደ ቂብላ በኩል ይደረጋሉ::
አስክሬኖች ጋር ህፃናት ከሉ መጀመሪያ ወንዱ ህፃን
ቀጥሎ ሴት ቀጥሎ ህፃን ተደርጎ አቀማመጡም በዚህ
መሰራት ይሆናል።የሰውዬውና የህፃኑን ጭንቅላት እኩል
ማድረግ ከዚያም የሴቷንና የህፃኗን ጭንቅላት እኩል ማድረግ
ነው።ኢማሙ ተከትለው የሚሰግዱ ሰዎች በአጠቃላይ ከኢማሙ
ጀርባ ይሆናሉ።ነገር ግን ከእነሱ መሀከል ቦታ ያጣና የቀረ ካለ
ከኢማሙ በስተቀኝ በኩል ይቆማል።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ከሀዳዲዮች ባህሪ መካከል
🔊🔊ሸይኽ ረስላን


ሸይኽ ፈውዛን እንዲህ ተብለው ተጠየቁ:-
“አንዳንድ ዱዓቶችን ተብዲዕ በማድረግ ሰዎችን የሚያስገድዱና ይህን መሰረት አድርገው የሚወዳጁና የሚጠሉ፣ ተብዲዕ ያላደረገን የሚያኮርፉ ሰዎች ብይናቸው ምንድን ነው?”
መልስ:-
“ይህን እንዳትይዝ። በዚህ ላይ እንዳትታዘዛቸው። እኔ ከዚህ የጠራሁ ነኝ። አላህ ከዚህ ጠባቂዬ ነው። በዚህ ውስጥ አልገባም። ስለዚህ ምንም አላውቅም በል።” [ደርሱ አተፍሲር ቢል ሐረም፡ ረጀብ 14/433]


◼️የአላህ መልክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል፦
💎 "ፀሀይ ከወጣችበት እለት ሁሉ በላጩ የጁምዓ ቀን ነው"
📙 ሙስሊም ሰሒሕ ብለውታል


ماهي البدع التي وقع فيها الحجوري_؟
لشيخ العلامة محمد بن عبد الوهاب الوصابي
የሕያ አል ሓጁሪይ ቢድዓ ላይ የወደቀበት ወይም ሙብተዲዕ የተባለበት ጉዳይ:-
"በኢጅቲሃድ ጉዳይ ላይ(እከሌ ሙብተዲዕ ነው ወይስ አይደለም በሚለው ጉዳይ) ላይ
ሰዎችን በመጥላቱ፤
በመሳደቡ፤
በእዚህ የተነሳ ሰዎችን ሁለት ቦታ በመክፈሉ፤
☞በጥመት ወይ በቢድዓ በመፈረጁ፤
☞ሂዝቢይ በማለቱ
☞በዚህ ጉዳይ እሱን ያልተቀበሉ ሰወችን ጀርባ በመስጠቱ........
®.በኢጂቲሃድ ጉዳይ ዱኒያ ልተቆማት አይገባም እሱ ግን በዚህ ጉዳይ ዱኒያን አቆማት፡፡
የፋይል መጠን:-4.79 MB
የሚፈጀው ጊዜ:-13:18 ደቂቃዎች
🔊🔊በሸይኽ ሙሓመድ ቢን አብዱል ወሓብ አል ወሳቢይ
~~~~
https://telegram.me/daruselam


🤝 የእውነተኛ ወንድማማችነት መገለጫ

*▪قال عمر بن الخطاب رضي الله عنه :

🔹 አሚሩል መእምኒን ኡመር ቢን ኸጧብ "ረዲየሏሁ አንሁ" እንዲህ ብሏል:

*《إذا رأيتم أخاً لكم زلّ زلة ، فسددوه ووفقوه وادعوا الله أن يتوب عليه ، ولا تكونوا عوناً للشيطان عليه .》*

🔶 【አንድ ወንድማችሁ ተንሸራቶ ባያችሁት ጊዜ; ወደ እውነት መልሱት, እውነትን እንዲገጥም እርዱት, አላህ ለተውበት እንዲመራው ዱአ አድርጉለት, በሱ ላይ ለሸይጧን አጋዥ አትሁኑለት።】

*📚 حلية الأولياء (٤٩٥٩)*

*▪قال عبدالله بن مسعود رضي الله عنه :
🔹 አብዲላህ ቢን መስኡድ "ረዲየሏሁ አንሁ" እንዲህ ብሏል:

*《إذا رأيتم أخاكم قارف ذنباً ، فلا تكونوا أعواناً للشيطان عليه ، تقولوا أخزاه الله ، قبحه الله ، ولكن قولوا تاب الله عليه ، غفر له .》*

💎 【አንድ ወንድማችሁን ኃጢአት ሲፈፅም ካያችሁት; አላህ ያዋርድህ, አላህ አስጠሊታ ያድርግህ ብላችሁ በመራገም በሱ ላይ ለሸይጧን አጋዥ አትሁኑለት, ይልቁንስ ; አላህ ለተውበት ይምራው አላህ ይማረው ብላችሁ ዱአ አድርጉለት።】

*📚 رواه ابن المبارك في الزهد (٨٩٦)*

*▪قال أبو الدرداء رضي الله عنه :

🔶 አቡ ደርዳእ "ረዲየሏሁ አንሁ" እንዲህ ብሏል:
*《إذا تغير أحد إخوانكم وأذنب ، فلا تتركوه و لا تنبذوه ، وعظوه أحسن الوعظ ، واصبروا عليه ، فإن الأخ يعوج تارة ويستقيم أخرى .》*

💎【አንድ ወንድማችሁ በፊት ከነበረው አቋሙ ተለውጦና ኃጢአት ሲፈፅም ካያችሁት! አትተውት እንዲሁም አታጥላሉት, ይልቁንስ መልካም በሆነው ተግሳፅ ገስፁት, በሱ ላይ / በመምከር ላይ/ ታገሱ, ምክኒያቱም ወንድም አንዳንዴ ይወላገድና ሌላ ጊዜ ደግሞ ይቃናል!!】

*📚 حلية الأولياء (٢٣٢/٤)*

Copy

20 last posts shown.

562

subscribers
Channel statistics