“አንድ ሰው ተመልክቻለሁ.....
ያማረ እና የፈካ ውበት ያለው....የአይኖቹ ብሌን በጣም ጥቁር የሆኑ.... ሽፋሽፍቶቹ የረዘሙ ....ቅንድቦቹ ግጥም ያሉ....ፀጉሩ የጠቆረ....ፂሙ የበዛ እና ዘለላው ወፍራም የሆነ....ሆዱ እና ደረቱ አንድ አይነት መጠን ያላቸው....ድምፁ ውስጥ ሰኪና ያለ .....
በመልካም ስነምግባር ላይ ያለ...
ዝም ባለ ጊዜ ፊቱ ላይ እርጋታ የሚታይበት....
በተናገረም ጊዜም ወሬ የማያበዛም የማያሳንስም የሆነ...
ሲናገር ንግግሩ በደንብ የሚሰማ...
በንግግሩ ላይ የተዋበ እና ብልህነት የሚታይበት ....
ከሩቅ ሲታይ ከሰዎች ሁሉ ቆንጆ የሆነ...
ከቅርብ ሲሆን ደግሞ .... ይበልጥ መልከ-መልካም እና ምርጥ የሆነ ውበት ያለው...
አጭርም ረጅምም ያልሆነ....
ለሱ የሚከላከሉለት ባልደረቦችም አሉት....ሰዎች የሚሰባሰቡለት የሆነ ....
አንዲትን ቃል ባወራ ጊዜ በጥሞና ያዳምጣሉ....ትዕዛዝን ባዘዛቸው ጊዜ ደግሞ ለመፈፀም ይቻኮላሉ..!!
ያ ሰው አንድም ቀን ፊቱን አጨፍግጎ ተመልክቼው አላውቅም..... በሰዎች ላይ ወቀሳን ሲያበዛም አይቼው አላውቅም.....
ተንኮል የተባለ ነገር ሁሉም ደግሞ ከጠገቡ የራቁ ሰው ነበር..!!
ኡሙ መዕበድ አቲካ ቢንት ኻሊድ ረሱል ﷺ ስትገልፃቸው 😊❤
"وَليسَ يُشبِههُ في النَّاسِ من أحدٍ
فهُو الكريمُ رفيعُ الخَلْقِ والخُلُقِ" ﷺ
صلو عليه وسلموا تسليما
የተቀዳ
Te:
https://t.me/dawatulanbiya