🎤🌼ድምፀ ተዋህዶ🌼🎤


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ድምጻችን ለተዋህዶ ሐይማኖታችን ለኢትትዮጲያ አገራችን

የእግዚአብሔር ሰላም የእናታች የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና ፀሎት የመላእክት ጥበቃና የቅዱሳን በረከት ከናንተ
ጋር ይሁን አሜን!

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


1GB ስንት MB ነው?


ከ17 ደቂቃ ቦኃላ ይጠፋል


የ 200 ብር ካርድ የሚያስሸልም ጥያቄ!

በኢትዮጵያ በጣም አስቸጋሪ የነበረዉ  ረሀብ መች አመተምህረት ነበረ




እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደርሳቹ❗️

ጥቅምት 5-ኑሮአቸው እንደሰው ያይደለ በምድረ በዳ እንደመላእክት የኖሩትና በዝቋላ ተራራ ባለው ባሕር ውስጥ 100 ዓመት ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ ሰዎች ምሕረትን የለመኑት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ ቃልኪዳን የተቀበሉበት ዕለት ነው፡፡ 

አባታችን አራት ሺህ እልፍ እየሰገዱ፣ 300 ጊዜ የቀኝ 300 ጊዜ ደግሞ የግራ ፊታቸውን በድንጋይ እየመቱ፣ መዝሙረ ዳዊትን እየደገሙ፣ 15ቱን መኅልየ ነቢያት፣ መኅልየ ሰለምንንና ውዳሴ ማርያም እየጸለዩ ለኃጥአን ምሕረትን ሲለምኑ ዕንባቸው እንደ ውኃ ይፈስ ነበር፡፡ ጌታችንም ‹‹በተወለድሁባት፣ በተጠመቅሁባትና ከሞት በተነሣሁባት ዕለት እልፍ እልፍ ነፍሳትን እምርልሃለሁ›› የሚል ቃል ኪዳን ሰጣቸዉ

አምላካችን በቃል ኪዳናቸው ይማረን


✝️#ድምፀ_ተዋህዶ ✝️


“አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው”ሲሉ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ገለጹ፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት 43ኛው ዓለም አቀፍ መደበኛ ጉባኤ መክፈቻ ላይ ለተገኙ ተሳታፊዎች መልእክት አስተላልፈዋል።

ቅዱስነታቸው በመልእክታቸው አሁን ባለን የአስተዳደር ክፍተቶችና በውስጣችን ያሉ ግልጽነት የጎደላቸው አሠራሮች ለአገልግሎታችን እንቅፋት እየሆኑብን ነው። በዚህ ጉባኤ በቤተ ክርስቲያናችን የሚታየውን  ችግር ለመፍታት በጥናት ላይ የተመሠረተ መፍትሔ ማምጣት ይገባል ሲሉ አፅዕኖት ሰጥተዋል፡፡

ቅዱስነታቸው ጨምረው እንደገለጹት ቅዱስ ሲኖዶስ ተግባራዊ እንዲሆን የወሰነውን የቤተ ክርስቲያን የ10 ዓመት መሪ ዕቅድ ውጤታማ ለማድረግ ሁላችንም በትብብር መሥራት ይገባናል ብለዋል።

በዛሬው ዕለት የተጀመረው 43ኛው አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ከሀገር ውስጥ እና ውጪ ከሚገኙ አህጉረ ስብከቶች፣ ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት አድባራት እና ገዳማት እንዲሁም ከተለያዩ መንፈሳዊ ማኅበራት የተወከሉ ተሳታፊዎች በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።

#ድምፀ_ተዋህዶ


✝️ቅዱስ እንጦንስ እንዲህ✝️ ይመክራል፦"
ደስታና ሰላምን የሚነጥቁ ሦስት የሰይጣን ወጥመዶች አሉ፦
➡️ስላለፈው መጸጸት፣
➡️ስለሚመጣው መጨነቅ እና
➡️ ስለ ዛሬው አለማመስገን ናቸው"

✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#ድምፀ_ተዋህዶ


📚አዲስ መፅሐፍ ምረቃ

✝️ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረኪዳን ግርማ አሐቲ ድንግል የተሰኘውን መጽሐፍት ሊያስመርቁ ነው

🫡ጥቅምት 2️⃣/2️⃣0️⃣1️⃣7️⃣ዓ.ም በቦሌ መድኃኔዓለም አዳራሽ ከቀኑ 7:30 ጀምሮ ⏰

መጽሓፉ 📚
ርእሰ ሊቃውንት የኔታ አባ ገብረ ኪዳን ግርማ:
1•የእመቤታችንን  ሕይወት  የያዘ ሙሉ የነገረ ማርያም  አስትምህሮ❔
2•በነገረ ድኅነት ያላት ድርሻ❔
3•ዕርገቷን የሚመለከቱ❔
4•እመቤታችንን የሚመለከቱ ጥያቄዎች❔
5•በእመቤታችን ፍቅር እንዴት መጽናትና ማደግ ይቻላል❔

የሚሉትን ዓበይት ጉዳዮች የሚተነትን ነው

628 ገጾች
12 ምእራፎች አሉት
✝️✝️✝️
#ድምፀ_ተዋህዶ
https://t.me/dmtse_tewaedo


​✝#ሰውን_ወዳጁና_ርህርሁ_እግዚአብሔር

ሰው ጨካኝ ሲሆን #እግዚአብሔር ግን ሁሉን የሚወድ ቸርና ርህርህ ነው፡፡ ለዚህም ነው ንጉስ ዳዊት ከሦስቱ ቅጣቶች መካከል አንዱን እንዲመርጥና አማራጩ ሲቀርብለት የተናገረው ቃል ድንቅ ነው፡፡ " ምህርቱ ብዙ ነውና በእግዚአብሔር እጅ እንውደቅ በሰው እጅ ግን አልውደቅ፡፡" 2ኛ ሳሙ 24 ፥ 14፡፡ ጻድቁ እዮብም በሦስቱ ባልደረበቹ እጅ በወደቀ ጊዜና እነርሱም እርሱን መውቀሳቸውን ባላቋረጡ ጊዜ እንዲህ ነበር ያላቸው ፡- "ነፍሴን የምትነዘንዙ በቃልስ የምታደቅቁኝ እስከ መቼ ነው? ይኸውም ስትሰድቡኝ አሥር ጊዜ ነው፡፡" ኢዮ 19 ፥ 2 - 3፡፡ #እግዚአብሔር ግን ከሰው በእጅጉ በተለየ መልኩ መሐሪና ርህርህ መሆኑን በሚከተሉት ውስጥ እንመለከታለን፡፡

#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ

#ድምፀ_ተዋህዶ
↗️ለወዳጆ ሼር ያድርጉ
https://t.me/dmtse_tewaedo


እንዳያመልጣችሁ ሊያመልጣችሁ አይገባም

     ከብዙ ወራት በፊት እነዚህን ሁለት ወንድሞች በአካል ሳገኛቸው በብዙ ልፋት እና ትጋት ውስጥ ሆነው ነበር ልባቸው ለአንድ አላማ ተሰልፎ የክርስቶስን አምላክነት ፈጣሪነት በመፅሐፍ ለማሳተም ሲደክሙ ተመለከትኳቸው ገና መፅሐፉ ወደ ማተማሪ ቤት ሳይገባ ያነሷቸውን ሀሳቦች ሲያወጉኝ ልቤ ተስፋን ሰነቀ ከዚህ በፊት በእስልምና  የእቅበተ እምነት ተከራካሪዎች ለሚነሱ ማናቸውም ጥያቄ በሚደንቅ ሁኔታ ምላሾችን ሲነግሩኝ ስለ እነርሱ አምላኬን አመሰገንኩ ። ወንድም ብሬ እና አቡ ወጣትነታቸውን ለእግዚአብሔር የሰጡ ዘመን ባፈራው የቴክኖሎጂ አገልግሎት በብዙ የሚያገለግሉ ብርቱዎች ናቸው ። የብዙ ጊዜ ልፋታቸው የማይደገሙ ምላሾችን የያዘው ድንቅ መጽሐፋቸው በቲክቶክ መንደር በአቡ ቤት ይመረቃል ።


 ከዘማሪ ዲ/ን ሰለሞን አቡበከር ቴሌግራም ገጽ የተወሰደ
#ድምፅ ተዋህዶ


"በሰማይ የምትኖር ሆይ፥ ዓይኖቼን ወደ አንተ አነሣሁ፤ እነሆ፥ የባሪያዎች ዓይኖች ወደ ጌታቸው እጅ እንደ ሆኑ፥ የባሪያይቱም ዓይን ወደ እመቤትዋ እጅ እንደ ሆነ፥ እንዲሁ እስኪምረን ድረስ፡ ዓይናችን ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር ነው'' መዝ. 122:1-3

#ድምፀ_ተዋህዶ

▫️https://t.me/dmtse_tewaedo


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ከእስልምና ወደ ክርስትና 5ቤተሰብ
😍“ኢየሱስም፦ እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ በእኔ በቀር ወደ አብ የሚመጣ የለም።”
  — ዮሐንስ 14፥6
#ድምፀ_ተዋህዶ




#እንኳን #ለፆመ_ጽጌ በሳላም አደረሳቹህ

✤ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው (ከሰዓትም ቅዳሴ የሚቀደሰስባቸው አካባቢዎች አሉ (ጎንደር )፡፡
በግዕዝ ጸገየ ማለት   አበበ ፤ አፈራ ፣ በውበት ተንቆጠቆጠ ማለት ነው፡፡ 
በማኀሌቱም ወቅትን እመቤታቸንን 3 ዓመት ከ6 ወር እስከ ግብፅ ከዚያም የአሥራት ሀገሯ  በሆነችው በኢትዮጵያ የተሰደደችበትን ወቅት በማሰብ  በጽጌና በአበባ እመቤታቸንን እና ጌታቸንን በመመሰል ሲያመሰግኗት ፣  ከልጇ ጋር ያየችውን መከራ  እያሰቡ  እና  ምልጃዋን ሲለምኑ ያድራሉ ፡፡

✤እምግብጽ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን፤ ለቅዱሳን ክብር ልጄን ከግብጽ ጠራሁት››
በማለት ነቢዩ ሆሴዕ በምዕራፍ ፲፩ ቍጥር ፩ እና ፪ ላይ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልጅነቱ ወደ ምድረ #ግብጽ (ምስር) የተሰደደው የነቢያት ትንቢት ይፈጽም ዘንድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕፃናትን በመፍጀት ከሚታወቀው ከአረመኔው ንጉሥ ከሄሮድስ ለማምለጥ ነው፡፡ አምላካችን ክርስቶስ ያለጊዜው (ዕለተ ዓርብ) #ደሙ #አይፈስምና፡፡ ስለዚህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ይፈልጋልና›› ብሎ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ለዮሴፍ በነገረው ቃል መሠረት ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ምድር ተሰደደ፡፡ ይህንን ስደት አስመልክቶ #ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ካህናቱ በሚያሳዝን ዜማ ያደርሳሉ፤ ያቀርባሉ፡፡

#በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሕፃናትን ሄሮድስ አስፈጅቷል፡፡ ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ለቅሶና ብዙ ዋይታ፡፡ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፡፡ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና›› የሚለው ትንቢትም ተፈጸሟል፡፡

#ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ የግብጽ ስደት በኋላ ሊቃውንቱ፡- ‹‹ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ›› እያሉ ከስደት መመለሷን ያበሥራሉ፡፡ ትርጉሙም፡- ‹‹ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና›› ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በዐርባው ቀን (በዘመነ ጽጌ) ወቅት የማርያምን የሽሽትና የመመለስ (የሚጠት) ታሪክ እያነሡ ውዳሴ የሚያቀርቡትና ማኅሌት የሚቆሙት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ለእመቤታችን ክብር ሲባል የፈቃድ ጾም የሚጾሙ ምዕመናንና ምዕመናትም ብዙዎች ናቸው በመሃል ኢትዮጵያ  በፈቃድ ጾምነት ሲጾም ; በሰሜኑ አካባቢ ተጹሞ ከሰዓት ይቀደሳል ሌሎች ጋር ግን ጠዋት ያበቃል፡፡

የእመቤታችን ምልጃ ና ጸሎት አይለየን

#ማኅሌተ_ጽጌ
✤የማኅሌተ ጽጌ  የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ አባ ጽጌ ድንግል ነው ፡፡
  ገዳሙም ትልቅና ሰፊ የኾነ የፍልፍል ዋሻ ሲኾን ወሎ ወግዲ ወለቃ ወንዝ አጠገብ በረሃ ላይ (ከጋሥጫ ገዳም የ4 ሰዓት የእግር መንገድ) ይገኛል፡፡
✤✤ በየዓመቱ ሳይመረገዱ ያመይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ፤
      እጅጉን በምንወደው የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ላይ በየዓመቱ ሳይመረገዱ የማይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ
( ከማኅሌተ ጽጌ፤ ጽጌ አስተርአየ(የመጀመሪያው ሳምንት)፣ በከመ ይቤ መጽሐፍ፣ ትመስል እምኪ ማርያም፣ ዘኒ ስብሐተ ወዘኒ ማኅሌተ፣ ኢየሐፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ እና ኅብር ሐመልሚል (የመጨረሻው ሳምንት)ናቸው፡፡
✤ ከሰቈቃወ ድንግል፤ በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ፣ ብክዩ ኅዙናን፣ እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ እና አብርሂ አብርሂ ናቸው፡፡
✤ከማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እና ክበበ ጌራ ወርቅ በየሳምንቱ (በኹሉም ዓመታት) ይመረገዳሉ፤ ዚቁ ግን በዓሉን በተመለከተ ይኾናል፡፡
✤ ከላይ ካየናቸው ውጪ የሚገኙት #የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ክፍሎች ግን #በየሰባት ዓመት አንዴ ነው የሚመረገዱት፡፡
( የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤

የቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኀኔ ዓለም ወደብረ ትጉሃን ቅዱስ ገብርኤል ቤ.ክ የማኅሌት ቁመትም የላይ ቤትን አብነት የተከተለ ሲኾን የዚቁ ወረብ ግን የደብሩን የራሱን (የሸዋን) የተከተለ ነው፤
( የላይ ቤት ቁመት የሚቆሙ አድባራት #ዘግምጃ ቤት የሚለውን እንዲከተሉ፤ የታች ቤትን #ቁመት የሚቆሙ አድባራት ዘበዓታ የሚለውን እንዲከተሉ፡፡ የዚቁ ወረብን ግን የቀጨኔ ደብረ ሰላም
የቤቱን ቀለም አስቀድመን ቀጥሎ ደግሞ ዓዲ (ወይም) በማለት የጎንደርን ስላስቀመጥነው እንደ ደብራችሁ ይትበሃል መርጣችሁ  ተጠቀሙ፡፡

/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ ::/

    #ድምፀ_ተዋህዶ

https://t.me/dmtse_tewaedo




ይህችን ቅደስት ቤተ ክርስቲያን ካሰባችሁላት ተዋት!

ለልጆቻችሁም ካሰባችሁ ተውን!

ይህ ሕዝብ በጦርነት ዜና፣ በኑሮ ውድነት በሌላም ብዙ ጭንቀት አለበት። እንደአባትነታችሁ ሰላምን ባትሰጡት እንኳ ሌላ ወከባ አትጨምሩበት።

እንደፖለቲከኛ የያዛችሁት ሽኩቻ ሰልችቶናል።

ተናግራችሁና ሠርታችሁ አርአያ መሆን ካልቻላችሁ ዝም በማለት አርአያ ሁኑን!

ይህ ምእመን ቤተ ክርስቲያን ላይ ለደረሰው ሁሉ ዝም ያላችሁ ከላይ እስከታች ስላላጠፋችሁ አልነበረም።

አሳልፈው የሰጡት አባቶች ከመካከል እንደነበሩ ጠፍቶትም አይደለም። ግን ስለማእተቡና ስለቀደሙት አባቶቹ የደም ሰማእትነት ሲል ብዙ እየተደረገ በብዙ ዝም አለ።

እናንተ የተቋም መሪዎቻችን እንጂ ሃይማኖታችን አይደላችሁምና መሠረቱን ክርስቶስን አስቦ ታገሰ!

እናንተ ግን ተጸፅታችሁ ወደ አንድ መጥታችሁ ከውጫዊ ጥቃት ልትጠብቁት ይቅርና እያደረ አዲስ የውስጥ ፈተና ትጠራላችሁ።

ሙስናው፣ መልካም አስተዳደር ችግርና ውጫዊ ፈተናችን ብዙ ነው አይካድም።

የእናንተ የአደባባይ ንተርክ ግን እውነት ለቤተ ክርስቲያን ለውጥ አስባችሁ ነው? ወይስ ለክብራችሁ? ወይስ ስልጣናችሁን ለማጽናት?

ራሳችሁን በጾም በጸሎት የወሰናችሁ ብፁዓን አባቶችስ እስከመቼ ጥግ ይዛችሁ ታያላችሁ? ጸሎት ከሁሉም የበለጠ ኃይል እንደሆነ ብናምንም ተስፋ እንዳንቆርጥ ተግሳጻችሁን እንመኛለን!

እናም ጽሑፉ የሚመለከታችሁ ብፁዓን አባቶች የአደባባይ መዘላለፉን ትታችሁ በውስጥ ተሟገቱ። የውጭ ፈተናችን ይበቃናል። እንደተከታታይ ድራማ እናንተን መከታተል ደክሞናል።

እንዳው በልጅነት የምጠይቃችሁ ድፍረት አይሁንብኝና ከቻላችሁ ወደ ገዳም ገብታችሁ አረፍ በሉ። የጥሞና ጊዜ ጥሩ ነው ብላችሁ አስተምራችሁን የለ?

እስኪ እኛም ካለእናንተ አይነት መሪዎች ቤቱ ምን እንደሚሆን እንየው!

(ከድፍረት ያልሆነ በመድከም የተጻፈ)

✍️ መስከረም

#ድምፀ_ተዋህዶ



16 last posts shown.

111 142

subscribers
Channel statistics
Popular in the channel

መስከረም  ፲፮ በዚች ቀን በኢየሩሳሌም አገር ንግሥት ዕሌኒ የገለጠቻቸው የከበሩ ቦታዎች ሁሉ የተሠሩበትና የከበሩበት ሆነ ። ቆስጠንጢኖስ ከነገሰ በኋ...
# ልዩ የመሰቀል ደመራ ፕሮግራም !!      ✝️✝️✝️ #የሶዶ_ወረዳ_ቤተክህነት_ልዩ_የደመራ_ዝግጅት በምሥራቅ ጉራጌ እና ማረቆ ልዩ ወረዳ ሀገረ ስብከ...
ታስሯል ይሄ ልጅ ስሙ ብሩክ ኦዶ ሲሆን በሚዲያ ስሙ ባሮክ 21 በመባል ይታወቃል በቲክቶክ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ተከታይ አፍርቷል በሚዲያው ለእምነቱ ...
መስቀል ሃይላችን ነው ፣መስቀል መፅናኛችን ነው ፣ መስቀል የነፍሳችን መድሃኒት ነው፣ መስቀል ቤዛችን ነው ። አይሁድ ይክዱታል እኛ ግን እናምነዋለን ያመነ...
🐐#ፍየል #ወዲህ🐐              ------------------- 🐝ትንኟ ኅይለኛ የሆነውን ⛈ ዶፍ ዝናም በዝሆን ጆሮ ውስጥ ታሳልፋለች። ዝናቡ አልፎ...