Forward from: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
ሰኞ ምሽት! ሰኔ 19/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች
1፤ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድን ለአራት ዓመት ከመንፈቅ በሰብሳቢነት የመሩት ብርቱካን ሚደቅሳ "በጤና ችግር" ከነሃሴ 1 ጀምሮ በፍቃዳቸው ከሥራ እንደሚለቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ማሳወቃቸውን በፌስቡክ ገጻቸው ባሠፈሩት መልዕክት አስታውቀዋል። ብርቱካን ከሃላፊነት እንደምለቅ ሰኔ 5 ላይ ያሳወቅኹት፣ "ጤናዬን በሚገባ ለመጠበቅ የረጅም ጊዜ ዕርፍት የሚያስፈልገኝ" በመኾኑ ነው ብለዋል። ብርቱካን በኃላፊነት ላይ በሚቆዩባቸው ቀሪ ጊዜያት፣ ያልተጠናቀቁ ሥራዎችን እንደሚያጠናቅቁና አስተዳደራዊ ሽግግር እንደሚፈጽሙ ገልጸዋል። ብርቱካን ሃላፊነታቸውን "በፍትሃዊነትና ቅንነት" ሲያከናውኑ መቆየታቸውን በመልዕክታቸው ላይ ጠቅሰዋል።
2፤ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ፕሬዝዳንት ዮሃንስ አያሌው የባንኩ ያልተመለሰ ወይም መመለሱ አጠራጣሪ የኾነ የብድር ምጣኔ ወደ 9 በመቶ መውረዱን ለዋዜማ ተናግረዋል። ባንኩ "ባልተመለሰ ብድር ምጣኔ ከፍተኛ መሻሻል" ማስመዝገቡን የጠቀሱት ዮሃንስ፣ ይህ ምጣኔ ትግራይ ውስጥ ያለውን የብድር ኹኔታ እንደማያካትት ገልጸዋል። ዮሃንስ የባንኩ ያልተመለሰ የብድር ምጣኔ በሂደት የተሻሻለው፣ የብድር መክፈያ ጊዜን በማራዘም ሳይኾን ብድርን በመክፈል ብቻ ነው” ብለዋል። ባንኩ ለባለሃብቶች ካበደረው 73 ቢሊየን ብር ውስጥ 19 ቢሊዮኑ ብር ስለመመለሱ አጠራጣሪ የኾነ ብድር ሲኾን፣ ከዚህ ውስጥ 11 ቢሊየኑ ወለድን ሳይጨምር ትግራይ ውስጥ ለተሠሩ ፕሮጀክቶች የተሰጠ ነው። ከጥቂት ዓመታት በፊት የባንኩ ያልተመለሰ የብድር ምጣኔ 43 በመቶ ደርሶ ነበር። ብሄራዊ ባንክ ለልማት ባንክ ያስቀመጠው ያልተመለሰ የብድር ምጣኔ ጣሪያ 15 በመቶ ነው።
3፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፕላን፣ በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኬሚቴ ዛሬ መንግሥት ባቀረበው የቀጣዩ ዓመት ረቂቅ በጀት ላይ ተወያይቷል። ቋሚ ኮሚቴው ረቂቅ በጀቱን ገምግሞ ለምክር ቤቱ የማሻሻያ ሃሳቦችን የማቅርብ ሥልጣን ያለው ሲኾን፣ ምክር ቤቱም በቋሚ ኮሚቴው ምክረ ሃሳቦች ላይ ተወያይቶ በጀቱን እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። መንግሥት ለቀጣዩ ዓመት ያቀረበው የ801 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት፣ የ281 ቢሊዮን ብር ጉድለት አለበት።
4፤ ባለፈው ሐሙስና ዓርብ አዲስ አበባ ላይ የመከረው የናይል ተፋሰስ አገሮች ከፍተኛ ስብሰባ የናይል ተፋሰስ የትብብር ማዕቀፍን በቶሎ ቶወደ ተግባር በማስገባት የናይል ቤዚን ኢንሼቲቭን ቋሚ በኾነና የጋራ የተፋሰስ ልማቶችን በሚያሳልጥ የናይል ወንዝ ተፋሰስ ኮሚሽን እንዲተካ በጋራ ባወጡት መግለጫ አሳስበዋል። አገራቱ፣ አፍሪካ ኅብረትና ቀጠናዊ ድርጅቶች ለድንበር ተሻጋሪ ወንዞች ፍትሃዊ አጠቃቀም ተቋማዊ አሠራሮችን እንዲፈጥሩም ጠይቀዋል። ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብጽ በሕዳሴ ግድብ ውዝግብ ዙሪያ በአፍሪካ ኅብረት አደራዳሪነት የጀመሩትን ድርድር በመቀጠል ያልተቋጩ ልዩነቶችን እንዲፈቱ የጠየቁት ተሳታፊ አገራት፣ ዓረብ ሊግ በናይል ወንዝ ዙሪያ በሚያወጣቸው "የላይኛው ተፋሰስ አገሮችን ሕጋዊ መብት በሚጋፉ" መግለጫዎች መከፋታቸውንና በተመድ ጸጥታው ምክር ቤትና ሌሎች መድረኮች ላይ የናይል ወንዝን "ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚደረጉ ሙከራዎች አፍራሽ መኾናቸውን" ገልጸዋል።
5፤ የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ሠራዊት የአገሪቱን ማዕከላዊ ተጠባባቂ የፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ መቆጣጠሩን አስታውቋል። የተጠባባቂ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያው ታንኮችን ጨምሮ ከፍተኛ የጦር መሳሪያ ክምችት የሚገኝበት ነው። ታማኝ የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት፣ በካርቱምና ኦምዱርማን አብዛኞች ቁልፍ መንግሥታዊ ተቋማትና አብዛኞቹ የኹለቱ ከተሞች ክፍሎች በፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ቁጥጥር ስር ወድቀዋል።
6፤ የተመድ ድርጅቶች ሩሲያና ዩክሬን በጥቁር ባሕር ወደቦች የዩክሬንን የእህል ምርቶች ለውጭ ገበያ ለማቅረብ የደረሱበት ስምምነት ካበቃ የአፍሪካ ቀንድ አገራት ላይ ከፍተኛ የምግብ እጥረት ቀውስ ያስከትላል ሲሉ ማስጠንቀቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል። የተመድ ረድዔት ድርጅቶች ይህን የገለጹት፣ ጀኔቫ ውስጥ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ነው። ሩሲያ ለውጭ ገበያ በምታቀርበው የእህል እና ማዳበሪያ ምርቷ ላይ ያሉ ዓለማቀፍ ማነቆዎች ካልተወገዱላት፣ ከስምምነቱ እንደምትወጣ ማስጠንቀቋን እንደቀጠለች ነው። በምሥራቅ አፍሪካ ሰባት አገራት፣ 60 ሚሊዮን ሕዝብ የምግብ እጥረት እንደገጠመው የረድዔት ድርጅቶች በመግለጽ ላይ ናቸው። በተመድና ቱርክ አደራዳሪነት ከሦስት ወር በፊት የታደሰው ይሄው ስምምነት፣ በሐምሌ አጋማሽ ይጠናቀቃል።
7፤ ንግድ ባንክ ዛሬ የአንድ ዶላር መግዣ ዋጋ 54 ብር ከ5506 ሳንቲም እና መሸጫ ዋጋው 55 ብር ከ6416 ሳንቲም ሆኖ እንደዋለ በድረገጹ ገልጧል። የአንድ የእንግሊዝ ፓውንድ መግዣ ዋጋ ደሞ 66 ብር ከ2086 ሳንቲምና መሸጫው 67 ብር ከ5328 ሳንቲም ሆኗል። በተመሳሳይ አንድ ዩሮ በ59 ከ3892 ሳንቲም ተገዝቶ፣ በ60 ብር ከ5770 ሳንቲም ሲሸጥ መዋሉን ባንኩ ገልጧል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏
👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
t.me/emsmereja