Forward from: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
ማክሰኞ ጠዋት! ሰኔ 20/2015 ዓ.ም የEMS ዐበይት ዜናዎች
1፤ በራያ አላማጣ አካባቢ ከ1 ሺህ 600 በላይ የመንግሥት ጡረተኞች ለከባድ ችግር መጋለጣቸውን መግለጣቸውን ቪኦኤ ዘግቧል። የመንግሥት ጡረታ ተከፋዮቹ፣ የሰሜኑ ጦርነት ከተቀሰቀሰ ወዲህ የጡረታ ክፍያቸውን እንዳላገኙና በዚሁ ሳቢያ በተከሰተ የምግብ እጥረት የቤተሰቦቻቸው አባላት ለሕልፈት እንደተዳረጉባቸው መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል። የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበራዊ ዋስትና አስተዳደር በበኩሉ፣ ያልተከፈሉ የጡረታ ክፍያዎችን ለመፈጸም መረጃዎችን እያጣራና እያመሳከረ መኾኑን እንደገለጠ የጠቀሰው ዘገባው፣ የጡረተኞቹ ተወካዮች የጡረተኞች ማኅደር ከማይጨው ወደ አማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን እንዲዛወርላቸው ጠይቀዋል ብሏል።
2፤ በትግራይ ክልል የሚገኙ የሃይማኖት መሪዎች በክልሉ ሰዎች በርሃብ እየሞቱ ስለመኾኑ መናገራቸውን ዶይቸቨለ ዘግቧል። የሃይማኖት መሪዎቹ፣ ዓለማቀፍ የረድዔት ድርጅቶች በክልሉ ያቋረጡትን የምግብ ዕርዳታ ባስቸኳይ እንዲቀጥሉ መማጸናቸውን ዘገባው ጠቅሷል። በክልሉ ለተረጅዎች የታሰበውን ዕርዳታ የዘረፉ አካላት ለሕግ እንዲቀርቡም የክልሉ የሃይማኖት አባቶች ጠይቀዋል ተብሏል።
3፤ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጀት ቋሚ ኮሚቴ ትናንት ባዘጋጀው ሕዝባዊ ውይይት ላይ መንግሥት በቀጣዩ ዓመት በጀት ለመንገድ ፕሮጀክቶች የመደበው በጀት አንስተኛ ስለመኾኑ አስተያየት ሰጪዎች እንዳነሱ "ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ዘግቧል። መንግሥት 300 ያህል ለሚገመቱ ለፌደራል መንገድ ፕሮጀክቶች የመደበው በጀት 68 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ሲኾን፣ ለ100 ያህል የመንገድ ፕሮጀክቶች ከ100 ሚሊዮን ብር ያነሰ በጀት እንደተመደበላቸው ከዝርዝር የበጀት ሰነዱ መመልከቱን ዘገባው ጠቅሷል። ገንዘብ ሚንስቴር አስተያየት ሰጪዎች ላነሷቸው ስጋቶች በሰጠው ምላሽ፣ ጉዳዩ "በበጀት አስተዳደር" ማለትም ለካፒታል ፕሮጀክቶች የተያዙ በጀቶችን በማሸጋሸግ እንደሚታይ ገልጧል ተብሏል።
4፤ ለኢትዮጵያ አዋሳኝ በኾነችው የሱዳኗ ብሉ ናይል ግዛት በሱዳን ጦር ሠራዊትና በአካባቢው በሚንቀሳቀሰው "የሱዳን ሕዝቦች ነጻ አውጪ ንቅናቄ - ሰሜን" በተሰኘው አማጺ ቡድን መካከል ግጭት ማገርሸቱን መስማቱን ሮይተርስ ዘግቧል። ተመድ፣ ከግጭቱ የሸሹ በመቶዎች የሚቆጠሩ የግዛቲቷ ነዋሪ ሱዳናዊያን ወደ ኢትዮጵያው ቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መግባታቸውን ገልጧል። በሌላ ዜና፣ የሱዳን ጦር ሠራዊት ባላንጣው ፈጥኖ ደራሹ ሠራዊት ካርቱም የሚገኘውን ግዙፉን የማዕከላዊ ተጠባባቂ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ዕሁድ'ለት መቆጣጠሩን አምኗል። ጦር ሠራዊቱ በከተማ የመንገድ ላይ ውጊያ ይሳተፍልኛል ብሎ የጠበቀው እስካፍንጫው የታጠቀውን ተጠባባቂ የፖሊስ ኃይል ነበር።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏
👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
t.me/emsmereja