Forward from: Hulu media (ሁሉ ሚዲያ)
የአልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኞች ለ29 ወራት ደሞዝ ስላልተከፈላቸው በረሃብ እየሞቱ ነው ተባለ
በትግራይ ክልል አድዋ ከተማ የሚገኘው አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኞች፤ ለ29 ወራት ደሞዝን ጨምሮ ምንም ዓይነት ክፍያ ስላልተከፈልቻቸው በረሃብ እየሞቱ ነው ተብሏል።
የፋብሪካው ሠራተኞች ለአዲስ ማለዳ እንደገለጹት፤ የትግራይ ክልል ብልጽግና ፓርቲ በክልሉ ሥራ ጀምሮ በነበረበት ወቅት ብቻ ለአራት ወራት ደሞዝ ተከፍሏቸው የነበረ ሲሆን፣ ከመጋቢት 2013 ጀምሮ እስካሁን ወርሃዊ ደሞዝና ጥቅማጥቅም ሙሉ በሙሉ ተቋርጦባቸዋል።
በዚህም ከ30 ያላነሱ የፋብሪካው ሠራተኞች በረሃብና በበሽታ መሞታቸውን ጠቅሰው፤ በዚህ ወቅት ሴቶች በልመና፣ ወንዶች ደግሞ አቅም ያላቸው ወደ መሀል አገር ሲሰደዱ ሌሎች ወደ ገጠር ሄደው ከቤተሰቦቻቸው ጋር በችግር እየኖሩ ነው ብለዋል።
“ፋብሪካው የክልሉ መንግሥት የልማት ድርጅት በመሆኑ እንደ ሌሎች ሠራተኞች ለእኛም ደሞዝ ይከፈለን ስንል በተደጋጋሚ ብንጠይቅም ሰሚ አጥተናል።” ነው ያሉት።
“መቀሌ ድረስ ተጉዘን ለክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ችግራችንን ብንገልጽም፤ “በፋብሪካው ላይ ጉዳት ያደረሰው አካል ካሳ ሲከፍል ነው የእናተም ጥያቄ መልስ የሚያገኘው” የሚል ምላሽ ሰጥቶናል።” ሲሉ ተደምጠዋል።
“ለፌደራል መንግሥት ጥያቄያችንን እናቅርብ አሳልፉን ስንልም የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፈቃደኛ አይደለም።” ብለዋል።
በተለይ በክልሉ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መቋረጡ ችግሩን ይበልጥ አስከፊ አድርጎታል ያሉት ሠራተኞቹ፤ ከዚያ በፊትም የቀበሌ መታወቂያ ለሌለው ሰው እርዳታ የማያገኝ በመሆኑ፣ እርዳታ ከተሰጣቸው ሰዎች እየለመኑ ይኖሩ እንደነበር ተናግረዋል።
ሠራተኞቹ አክለውም" በ“ኢፈርት” ውስጥ ካሉ የክልሉ መንግሥት 22 የልማት ድርጅቶች ውስጥ የ17ቱ ሠራተኞች ደሞዝ እየተከፈላቸው ነው ካሉ በኋላ፤ ለእኛ የማይከፈልበት ምክንያት ሊኖር አይችልም ሲሉ ተደምጠዋል።
አልመዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ከ5 ሺሕ 200 ያላነሱ ቋሚ እና 400 ገደማ ጊዜያዊ ሠራተኞች እንደነበሩት የተገለጸ ሲሆን፤ ብዙዎች የቤተሰብ አስተዳዳሪ መሆናቸውን ታሳቢ በማድረግ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር እና ከፌደራል መንግሥቱ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል።
በጦርነቱ ወቅት ዝርፊያ፣ ውድመት እና የአየር ጥቃት ተፈጽሞበታል የተባለው ፋብሪካው፤ እስካሁን ምንም ዓይነት ጥገና እንዳልተደረገለት እና መቼ ወደ ሥራ እንደሚመለስም እንደማይታወቅ ተመላክቷል።
አዲስ ማለዳ ሠራተኞ ባቀረቡት ቅሬታ ላይ ከትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ምላሽ ለማግኘት ያደረገችው ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
መረጃ ህይወት ነው፣ ይህንንም መረጃ ለጓደኞቻችሁ#Share በማድረግ ተባበሩን🙏
👉ወሳኝ መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት የቴሌግራም ቻናሉን ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇👇👇
t.me/emsmereja