ECWC/ኢኮሥኮ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


Official ECWC Telegram Channal
.የኮርፖሬሽኑ ዜናዎች
.የጨረታና የሥራ ማስታወቂያዎች
. በየወሩ የሚታተመው የዜና መጽሄት
. ፎቶዎች እና አጫጭር ቪዲዮች
.በየ 6ወሩ የሚታተመው የኮርፖሬሽኑ ዕይታ መጽሄት እና የኮርፖሬሽኑ ፕሮፋይል በዚህ ገጽ ላይ በየጊዜው ይቀርባል፡፡

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter








ኢኮሥኮ በሁለቱም ፆታዎች የመረብ ኳስ ቡድን ድል አደረገ።

ኢሠማኮ ባዘጋጀው የበጋ ወራት ስፖርት ዉድድር የኮርፖሬሽኑ የሴቶች መረብ ኳሰ ቡድን የውሀና ፍሳሽ አቻውን በስፖርታዊ ጨዋነት አብላጫ በመውሰድና ጭምር 2_0 ማሸነፍ ችላል።
በመቀጠልበ ሶስተኛው ዙር ውድድር የኢኮስኮ ወንዶች መረብ ኳስ ቡድን ከፉልውሃ አገልግሎት ድርጅት ጋር የነበረው ውድድርንም  በፎርፌ 3 ነጥብ ሊወስድ ችሏል።
ተወዳዳሪዎች በአግባቡ የስልጠና ጊዜያቸውን እንዲጠቀሙ መደረጉ ለውጤቱ መገኘት ጉልህ ሚና እንዳለው የጠቀሱት የመሰረታዊ ማህበሩ ም/ፕሬዝደንት አቶ መላኩ በቀጣይ ውድድሮችም ከውጤታማነት ጎን ለጎን ኮርፖሬሽኑን የማስተዋወቅ ስራ እንደሚሰሩም ተናግረዋል።


የኮርፖሬሽኑ መካከለኛ አመራሮች ስልጠና ወሰዱ
----------
'ስነ-ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልእኮ ስኬት' በሚል መሪ ቃል  የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን (ኢኮሥኮ) ከፌዴራል ስነ-ምግባርና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር  ያዘጋጁት ሁለተኛ ዙር ስልጠና ለኮርፖሬሽኑ መካከለኛ አመራሮች ተሠጠ።

በስልጠናው ወቅት ንግግር ያደረጉት  የኢኮሥኮ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ  ኢንጂነር ዮናስ አያሌው ከፍተኛ አመራሩ እስከ ሠራተኛው ድረስ ስነ-ምግባራዊ አመራርን የሚያጎለብቱ ስልጠናዎችን በመስጠት በኮንስትራክሽን ዘርፉ  ያለውን የጸረ ሙስና ትግል ማጠናከር ይኖርብናል ብለዋል።

በሁለተኛው ዙር ስልጠና ፕሮጀክት ሥራ አስኪያጆች፣ የአገልግሎት ሃላፊዎች  እና ቡድን መሪዎች ስልጠናውን ተከታትለዋል።

በመጀመሪያው ዙር የኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች   ከጥር 20 -21/2017አ.ም ስልጠናውን መውሰዳቸው ይታወቃል።


Invitation for Re-Bid
Tender No. ECWCT/NCB/PG/45/2017

The Ethiopian Construction Works Corporation (ECWC) here by invites registered eligible bidders for the procurement of Raw Materials Requirement (PVC-U, HDPE & Geomembrane  Raw Materials) under national competitive bidding (NCB).
1.  Interested Potential Bidders are required to present renewed relevant Trade License for the fiscal year, VAT Registration Certificate, Tax Clearance Certificate and Online Supplier list Registration Certificate together with the offer.
2.  Bidding document should be prepared in English language.
3.  Those bidders willing to participate for supply of any type of tonner must accompanied the bid with manufacturer authorization letter or manufacturer license.
4.  Interested Potential Bidders obtain a complete set of bidding document from the Procurement Office with Payment of none refundable fee of Birr 400.00(Four hundred birr).
5.  This invitation of bid is open to all interested potential bidders regardless of their nationality.
6.  Bid must be accompanied with a Bid Security an amount of Birr 300,000.00(Three hundred thousand birr only) in the form of certified check (CPO) or Bank guarantee. Bid Bond in the form of insurance bond or in any other form shall not be accepted.
7.  Bids must be delivered or deposited in the Tender Box situated at the office of the Procurement dep’t, before the closing date and time.
8.  The deadline for bid Submission shall be on February 06/2025 at 03:00 P.M.
9.  Bids will be opened on February 06/2025 at 03:30 P.M.  in Ethiopian Construction Works Corporation Procurement Department conference room, in the presence of bidders and/or their representatives who choose to attend.
10.  The Ethiopian Construction Works Corporation reserves its rights to reject any or all bids.
11.  Bidders may get further information at the following address:
                                          _________   
                                        Ethiopian Construction Works Corporation.
                                       Gurd Shola behind Athletics federation building and
                                          Infront of Andinet international College
                                               P. O. Box 21952/1000
                                                Telephone 011 8 96 29 91/01118 67 80 89
                                                Fax No. 251-11-6 67 60 90
                                                     Addis Ababa, Ethiopia




ስነ-ምግባራዊ አመራርን   የሚያጎለብት ስልጠና እየተሰጠ ነው
---------
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን(ኢ.ኮ.ሥ.ኮ) የስነ-ምግባር  መከታተያ ዋና መምሪያ  ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ  ስነ-ምግባር እና ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመሆን 'ስነ ምግባራዊ አመራርነት ለተቋማዊ ተልእኮ ስኬት' በሚል መሪ ቃል  ለኮርፖሬሽኑ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች  የተዘጋጀ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

በስልጠናው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት  የፌዴራል ስነ-ምግባርና እና ጸረ -ሙስና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አቶ ፈቃዱ ሰቦቃ  ስልጠናው ዘርፍ ተኮርና በተጨባጭ ችግሮች ላይ ትኩረቱን  የሚያደርግ በመሆኑ የጸረ-ሙስና ትግሉን  ለማቀጣጠል ከፍተኛ  ጠቀሜታ ይኖረዋል ብለዋል።

የኢ.ኮ.ሥ.ኮ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ዮናስ አያሌው በበኩላቸው  ኮርፖሬሽኑ በውስጥ አቅም ተከታታይ ስልጠናዎችን ሲሰጥ የቆየ  ቢሆንም  ከፌዴራል ሥነ -ምግባረና  ጸረ-ሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር የሚሰጠው ስልጠና የጸረ ሙስና ትግሉን  በተሻለ እውቀትና መረጃ  መምራት ያስችላል ብለዋል።

ስልጠናው በቀጣይም በየደረጃው ላሉ የኮርፖሬሽኑ አመራሮች እና ሰራተኞች የሚሰጥ ይሆናል።

8 last posts shown.