ትዳር መደሰቻ ብቻ ሳይሆን ኃላፊነትም አለበት..
ኃያሉ አላህ እንዲህ ይላል..
يَٰنِسَآءَ ٱلنَّبِىِّ لَسْتُنَّ كَأَحَدٍۢ مِّنَ ٱلنِّسَآءِ ۚ إِنِ ٱتَّقَيْتُنَّ فَلَا تَخْضَعْنَ بِٱلْقَوْلِ فَيَطْمَعَ ٱلَّذِى فِى قَلْبِهِۦ مَرَضٌۭ وَقُلْنَ قَوْلًۭا مَّعْرُوفًۭا
የነቢዩ ሴቶች ሆይ! ከሴቶች እንደማናቸው አይደላችሁም፡፡ አላህን ብትፈሩ (ትበልጣላችሁ)፡፡ ያ በልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት እንዳይከጅል በንግግር አትለስልሱም፡፡ መልካምንም ንግግር ተናገሩ፡፡በቤቶቻችሁም ዉስጥ እርጉ እንደፊተኛይቱ መሃይምነት ጊዜ መገለጥም በማጌጥ አትገለጡ ሶላትንም በደንብ ስገዱ ዘካም ስጡ ..(አል_አህዛብ:32)
አንዲት የጋብቻ አማካሪ በዘመናችን ስላለዉ የትዳር ሁኔታ ሲገልጹ ሰዎች በትዳራቸዉ ደስተኞች እንዳይሆኑ ከሚያደርጓቸዉ ዋነኛ ምክንያቶች አንዱ ከትዳር አለም ከእዉነታዉ የራቀ ተስፋ ያላቸዉ መሆኑ ነዉ ይላሉ። ቀጥለውም ብዙ ባለ ትዳሮች ትዳርን እንደጠበቁት ሆኖ ሳያገኙት ሲቀረሩና የትዳር አጋራቸዉም ቢሆን እንዳለሙት አይነት ሰዉ አለ መሆኑን ሲገነዘቡ ግራ ይጋባሉ። በተጨማሪም በርካታ ሰዎች ትዳራቸዉን የሰመረ ለማድረግ ጥረት ሲያደርጉ ባይታይም ደስተኛ ትዳር እንዲኖራቸዉ ይጠብቃሉ። ትዳር ወዲያዉኑ ደስተኞች እንደሚያደርጋቸዉ አድርገዉ ስለሚያስቡ ደስታ ያለበት ትዳር ለመመስረት እጅግ አስፈላጊ የሆኑትን ነገሮች ማከናወን ማለትም ኃላፊነት መቀበልና ጠንክረዉ መስራት እንዳለባቸዉ ይዘነጋሉ። ከዚህም የተነሳ እዉነታዉን ሲገነዘቡ በተስፋ መቁረጥ ስሜት የሚዋጡ ከመሆኑም በላይ ግራ ይጋባሉ ።አብዛኛውን ጊዜ ከትዳር እጅግ ብዙ ነገሮችን ይጠብቁ ከነበረ ከእዉነታዉ ጋር ሲፋጠጡ የሚገጥማቸዉ ሃዘንም የዚያኑ ያክል የከፋ ይሆናል>ይላሉ.
ሃያሉ አላህ ታላቁን የህይወት መዋቅር {ትዳርን}አስመልክተዉ ወንዶች ሊከተሉት ስለሚገባቸዉ ስርአት እንዲህ ይላል..
يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ لَا يَحِلُّ لَكُمْ أَن تَرِثُوا۟ ٱلنِّسَآءَ كَرْهًۭا ۖ وَلَا تَعْضُلُوهُنَّ لِتَذْهَبُوا۟ بِبَعْضِ مَآ ءَاتَيْتُمُوهُنَّ إِلَّآ أَن يَأْتِينَ بِفَٰحِشَةٍۢ مُّبَيِّنَةٍۢ ۚ وَعَاشِرُوهُنَّ بِٱلْمَعْرُوفِ ۚ فَإِن كَرِهْتُمُوهُنَّ فَعَسَىٰٓ أَن تَكْرَهُوا۟ شَيْـًۭٔا وَيَجْعَلَ ٱللَّهُ فِيهِ خَيْرًۭا كَثِيرًۭا
እናንተ ያመናችሁ ሰዎች ሆይ! ሴቶችን ያስገደዳችሁ ኾናችሁ ልትወርሱና ግልጽን መጥፎ ሥራ ካልሠሩ በስተቀር ከሰጣችኋቸው ከፊሉን ልትወስዱ ልታጉላሏቸውም ለእናንተ አይፈቀድም፡፡ በመልካምም ተኗኗሩዋቸው፡፡ ብትጠሉዋቸውም (ታገሱ) አንዳችን ነገር ብትጠሉ አላህም በእርሱ ብዙ ደግ ነገርን ሊያደርግ ይቻላልና፡፡[አን-ኒሳእ:19]
"
ሙስሊም ምሁራን ስለዚህ የቁረአን አንቀጽ ማብራሪያ ሲሰጡ እንዲህ ይላሉ:-ይህ ማለት አንዲት ሴት ለትዳር አገሯ ጥሩ ስለሆነች እርሱም በአምሳያዉ ጥሩ ነገር ያድርግላት ማለት አይደለም ።ከዚያ እንኳን እርሱ መልካም ሊሆንላት ይገባል።ለባለቤትህ ጥሩ ባል ለመሆን ከፈለግክ መጀመሪያዉኑ ሃይማኖተኛዋንና ስነ_ምግባሯ ያማረዉን አግባ የሚስትህን ቁመናዋን ብቻ መስፈርት ካደረግህ አለቀልህ ማለት ነዉ።>
በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ ባሎች ሴቷን በጋብቻ ከቤተሰቦቹዋ ሲወሰዱ ልክ እንደባሪያ የገዟትና እንደፈለጉ ሊያደርጓት የሚያስችላቸዉ መብት ያላቸዉ የሚመስላቸዉ ናቸዉ።ይህን አይነት ተግባር በሚስት ላይ መፈጸም የእርሷን አደራ ማጥፋት መሆኑን ልብ አይሉም..አላህ እንዲህ በማለት እንዚህን ወገኖች ይገስፃቸዋል።
وَكَيْفَ تَأْخُذُونَهُۥ وَقَدْ أَفْضَىٰ بَعْضُكُمْ إِلَىٰ بَعْضٍۢ وَأَخَذْنَ مِنكُم مِّيثَٰقًا غَلِيظًۭا
ከፊላችሁ ወደ ከፊሉ በእርግጥ የደረሰ ሲኾንና ከእናንተ ላይም (ሴቶች) የጠበቀ ኪዳንን የያዙባችሁ ሲኾኑ እንዴት ትወስዱታላችሁ![አን_ኒሳእ:21]
ይህ የጠበቀ ኪዳን የተባለዉ ሌላ ሳይሆን
የጋብቻ ቃል ኪዳን ነዉ።
@eross_eross