PART 3
ሰላም የተወደዳችሁ!
OPAL/ኦፓል
በዛሬው ክፍል የምንመለከተው ስለ ኦፓሎች ነው። በብልጭልጭ ቀለማቸው አንጋፋነትን ከተላበሱት የተፈጥሮ ተአምራቶች መካከል ኦፓሎች ዋናዎቹ ናቸው። እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ የተፈጥሮ ትዕግስት የሚታየው በኦፓል ድንጋዮች ስርሪት ላይ ነው። እነዚህ ውብ ድንጋዮች በዝቅተኛ ቴምፕረቸር ላይ በሲሊከን ንጥረ ነገር የበለፀገ ውሃ ወደ መሬት ውስጥ ሰርጎ በሚገባበት ጊዜ በአለት ስንጥቆች ውስጥ ከብዙ ሚሊዮን የጂኦሎጂ አመታት በኋላ ወደ ጠጣርነት በመለወጥ በሴዲመንታሪ የአለት ስሪት ወደ ኦፓልነት ይቀየራል። ይህ ድንጋይ በተለያዩ የቀለም መደቦች ላይ በማይክሮስኮፒክ የሲሊከን ኳሶች ድርድር አማካኝነት ለአይናችን በሚማርክ መልኩ የቀለማትን ጭዋታ ያንፀባርቅልናል። ኦፓሎች በዋናነት ሰባት አይነት ቀለሞችን ይጠቀማሉ። ከዚህ በመነሳት ይህንን ድንጋይ በአራት ዋና ዋና ክፍሎች ከፍሎ ማየት ይቻላል። እነዚህም፦ White opal፣ Black opal፣ Fire opal እና Crystal opal ናቸዉ። የተወደዳችሁ ለዛሬ ይህንን ያክል ካነሳን ይበቃናል።
ስልጠና!
: የከበሩ መዓድናት አፈጣጠር
: የከበሩ ድንጋዮች ገበያ
: የድንጋዮች የሀገር ውስጥ ዋጋ ዝርዝር
: ዋና ዋና የከበሩ ድንጋዮች ጥልቅ ትንታኔ
: የድንጋዮችን ዋጋ የሚወስኑ ጉዳዮች
: የከበሩ ድንጋዮች የቤት ዉስጥ አፈታተሽ
# እየደወሉና በየግሩፑ ፎቶ እየለጠፉ የድንጋዮችን ምንነት ለማወቅ ሰዉ ከመለመን አሁኑኑ ተመዝግባቹ የዘርፉን ሚስጥር በጥልቀት ተማሩ።
ዋጋ 1000 ብር ብቻ
@et_gems