የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤትን ለማሻሻል መከናወን በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ ሙያዊ ክርክር(professional debate) ተካሄደ።
በመርሀ ግብሩ የቢሮው ማኔጅመንት አባላትን ጨምሮ የአላማ ፈጻሚ ስራ ክፍል ዳይሬክተሮች ፣ ቡድን መሪዎች እና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከቀናት በፊት የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርትን ለማሻሻል በተዘጋጀ ስትራቴጂክ እቅድ ዙሪያ ተመሳሳይ ውይይት መካሄዱ ይታወቃል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በመርሀ ግብሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የተማሪዎችን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤት ለማሻሻል ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ቢሮ ድረስ መከናወን በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ ሙያዊ ውይይትና ክርክር በማድረግ በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ መርሀ ግብሩ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።
ኃላፊው አያይዘውም ተማሪዎች በሁለቱ የትምህርት አይነቶች በሚፈለገው ደረጃ ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ከስርአተ ትምህርት አተገባበር ጀምሮ ከፈተና ዝግጅት ጋር በተገናኘ ባለው አሰራር ላይ የነጠረ ሀሳብ በማቅረብና የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ ሁሉም የስራ ክፍል የሚጠበቅበትን ኃላፊነት በአግባቡ መወጣት እንዲችል ታስቦ ሙያዊ የክርክር መርሀ ግብሩን ማዘጋጀት ማስፈለጉን አስረድተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል የመምህራንን አቅም በማሳደግና ፍትሀዊ የምዘና ስርአት በማስፈን የተማሪዎችን የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤት ለማሻሻል በትኩረት እንደሚሰራ ሲጠቅሱ ስርአተ ትምህርቱ በአግባቡ ተግባራዊ እንዲሆን ተገቢውን የክትትል ስራ በመስራትም ሆነ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ ሌሎች ውጤታማ የሚያደርጉ አሰራሮችን ተግባራዊ በማድረግ ተማሪዎችን በሁለቱ የትምህርት አይነቶች ውጤታማ ለማድረግ እንደሚሰራ ምክትል ቢሮ ኃላፊዋ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ አመላክተዋል።
በመርሀ ግብሩ የቢሮው የፈተና ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ የ6ኛ እና 8ኛ ክፍል የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት የውጤት ትንተና እንዲሁም በስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ በ2017 ዓ.ም የሒሳብና እንግሊዘኛ ትምህርት ውጤትን ለማሻሻል የተዘጋጀ ስልታዊ እቅድ ቀርቦ ተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶችን እና ጥያቄዎች አንስተው በኃላፊዎችና ጉዳዩ በሚመለከታቸው ባለሙያዎች ምላሽ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠቃሏል።
#share#share #share
#ሼር #ሼር
https://t.me/ethio_addis_mereja