በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲካሄድ የቆየው የ2016 ዓ.ም የተማሪዎች የሒሳብ ትምህርት ውድድር የማጠቃለያ መርሀ ግብር ተካሄደ።
ውድድሩ ''ጉብዝና ያሸልማል!'' በሚል መሪ ቃል ከ3ኛ እስከ 12ኛ ክፍል በሚማሩ ተማሪዎች መካከል ማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ በተሰኘ ድርጅት አዘጋጅነት ሲካሄድ ቆይቶ በዛሬው እለት በሚሊኒየም አዳራሽ የማጠቃለያ መርሀ ግብሩ መካሄዱ ተገልጻል።
የ2016 ዓ.ም የተማሪዎች የሒሳብ ትምህርት ውድድር በአምስት ዙር ሲካሄድ ቆይቶ ለዛሬው የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድር መብቃቱን የውድድሩ አዘጋጆች ገልጸው በዛሬው የማጠቃለያ ውድድር ከ50 ከተሞች የመጡ ተማሪዎች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ውድድሩ የሒሳብ ትምህርት ከባድ ነው በሚል የሚታሰበውን የተሳሳተ አመለካከት በመቅረፍ ተማሪዎችን በትምህርት አይነቱ ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መሆኑን የማይ ሶሮባን ኢትዮጵያ መስራች አቶ ከበደ አጥናፉ ገልጸው ውድድሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ እና ኮተቤ ትምህርት ዩኒቨርሲቲ በመጡ የዘርፉ ምሁራን ዳኝነት መካሄዱን አስታውቀዋል።
ቀደም ሲል በየአከባቢያቸው በተደረገ ውድድር አሸናፊ ሆነው ለዛሬው የማጠቃለያ ውድድር የደረሱ ተማሪዎች የዋንጫ እና የሜዳልያ ሽልማት በክብር እንግዶች የተበረከተ ሲሆን የአሸናፊዎች አሸናፊ ውድድሩ በየክፍል ደረጃው እስከ መጪው ረቡዕ ተካሂዶ ለአሸናፊዎች ዕውቅና እንደሚሰጥ ተገልጿል።
#share#share #share
#ሼር #ሼር
https://t.me/ethio_addis_mereja