ethio tech tricks


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Telegram


ስማርት ስልኮችቻችን ላይ ለሚያጋጥሙን ችግሮች መፍትሄ እንዲሁም የሳይበር እና አጠቃላይ ቴክኖሎጂ ነክ የሆኑ መረጃዎችን የሚያገኙበት ቻናል!!!

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Telegram
Statistics
Posts filter


በ12 ሰከንድ ውስጥ 25 ሚሊዮን ዶላር የሰረቁት ወንድማማቾች‼️
አንተን ፔራሬ እና ጀምስ ፔራሬ የተሰኙት በአሜሪካዊያን የዓለማችን ምርጥ ተብሎ ከሚጠራው ዩንቨርሲቲ ማሳቹሴትስ ዩንቨርሲቲ በሒሳብ እና ኮምፒውተር ሳይንስ ተመርቀዋል፡፡

የ24 እና 28 ዓመት እድሜ ያላቸው እነዚህ ወንድማማቾች በ12 ሰከንዶች ውስጥ 25 ሚሊዮን ዶላር መዝብረዋል ተብሏል፡፡

ወንድማማቾቹ እውቀታቸውን ተጠቅመው 💰ኢቴሪየም የተባለ የክሪፕቶ ከረንሲ ድረገጽን ሰብረው በመግባት ገንዘቡን ወደ ራሳቸው አካውንት አዘዋውረዋል የተባለ ሲሆን ይህን ለማድረግ የፈጀባቸው ጊዜ 12 ሰከንዶች ብቻ ናቸው፡፡

እንደ ሲኤንቢሲ ዘገባ ወንድማማቾቹ ገንዘቡን የሰረቁት ከአንድ ዓመት በፊት ሲሆን እንዲህ አይነት ስርቆት ሲፈጸም በታሪክ የመጀመሪያው እንደሆነ የአሜሪካ ፍትህ ቢሮ አስታውቋል፡፡

የስርቆቱ መፈጸም በአሜሪካ ክሪፕቶ ከረንሲ ኢንዱስትሪ ላይ ተጽዕኖ እንደፈጠረ የገለጸው የሀገሪቱ ፍትህ ቢሮ ወንድማማቾቹ ገንዘቡን እንዲመልሱ ቢጠየቁም እንዳልሰረቁ እና ገንዘቡ የራሳቸው መሆኑን ለማሳየት ጥረቶችን አድርገዋል ተብሏል፡፡

የሀገሪቱ ወንጀል መርማሪዎች እንዳሉት መሰል የስርቆት ወንጀል ሲፈጸም እና ክስ ሲመሰረት ህ የመጀመሪያው ነው ያሉ ሲሆን ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር እንደዋሉ ተሰምቷል።


🖥Google play store በጣም በትንሽ ኔትዎርክ አፕሊኬሽኖችን አፕዴት የምናደርግበትን አሰራር እየሞከረ ነው።
የተለያዩ አፕሊኬሽኖችን play store ላይ update ለማድረግ ስንሞክር ኔቶርካችን ዝቅተኛ ከሆነ በቀላሉ update ማድረግ አንችልም ወይም ይቋረጣል። ይህን ችግር ለመቅረፍ google አዲስ "Update with limited amount of mobile Data" የሚል አማራጭ አካቷል።
ይህ አሰራር አሁን ላይ ለተወሰኑ የPlay store ተጠቃሚዎች ብቻ የተለቀቀ ሲሆን በቅርብ ጊዜ ውስጥ ለሁሉም እንደሚለቀቅ ተገልጿል።
ለመሞከር
✔️Play store ክፈቱና የፕሮፋይል ምልክታችሁን ንኩ።
✔️Settings ክፈቱ።
✔️Auto-update apps የሚል አማራጭ አለ እሱ ውስጥ ግቡ።
✔️መጨረሻ ላይ Update with limited amount of mobile Data የሚለውን on አድርጉት።
ከላይ እንደነገርኳችሁ ይህ ለጊዜው ለሁሉም ሰው ላይሰራ ይችላል።
ይህ አሰራር በተለይ ፈጣን ኔትወርክ በሌለባቸው የሃገራችን ገጠራማ አካባቢዎች ትልቅ ጥቅም ይኖረዋል።


🔥 ስልክዎ እንደተጠለፈ የሚያሳዩ #ሰባት ምልክቶች

1. የስልክዎ ፍጥነት ከቀነሰ

ተንቀሳቃሽ ስልክዎ ከሌላው ጊዜ በተለየ ትዕዛዞችን ለማከናወን ረዘም ያለ ጊዜ የሚፈጅ ከሆነ፤ ባዕድ ሶፍትዌሮች (ማልዌር) እያስቸገሩት ነው ማለት ነው።

እነዚህ ማልዌር የተባሉት ቫይረሶች ዋነኛ ሥራቸው የስልክዎን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ማዘግየት ሊሆን ስለሚችል፤ በአፋጣኝ ማስወገድ ተገቢ ነው።

2. ስልክዎ በጣም የሚግል ከሆነ

ስልክዎት ከተለመደው ከፍ ባለ ሁኔታ የሚግል ከሆነ፤ ችግር አለ ማለት ነው። በፍጥነት እርምጃ ይውሰዱ አልያም ባለሙያ ያማክሩ።

3. የስልክዎ የባትሪ ኃይል ቶሎ የሚያልቅ ከሆነ

ስልክዎ ከፍተኛ ሙቀት አለው ማለት ደግሞ የባትሪው ኃይል ቶሎ ቶሎ ያልቃል ማለት ነው።

ምናልባት ስልክዎ አዳዲስ መተግበሪያዎችንና #ሶፍትዌሮችን ለማደስ በሚሞክርበት ወቅት የባትሪውን ኃይል ሊጨርስ ይችላል። ነገር ግን ምክንያቱ ይህ ካልሆነ ስልክዎ ተጠልፎ ሊሆን እንደሚችል ማሰብ አለብዎ።

4. ወደ ማያውቁት ሰው መልዕክት ከተላከ ወይም ከማያውቁት ሰው መልዕክት ከደረስዎ

ብዙ ጊዜ እርስዎ የማያውቋቸው መልእክቶች የሚላኩት በዋትሳፕና በመሳሰሉ መተግበሪያዎች በኩል ሲሆን፤ የሚላከው ደግሞ ወደ ጓደኛዎት አልያም ወደ የማያውቁት ሰው ሊሆን ይችላል።

ወደ እርስዎ የሚላኩ መልዕክቶች ደግሞ ብዙ ጊዜ ይህንን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ የሚሉ ማሳሰቢያዎች ይበዟቸዋል።

5. ከበይነ መረብ የሚመጡ ድንገተኛ መልዕክቶች

ስልክዎን በመጠቀም በይነ መረብን (ኢንትርኔት) በሚያስሱበት ወቅት #ወደ ሌላ ድረ-ገጽ የሚያሸጋግሩ መልዕክቶች በተደጋጋሚ የሚመጡ ከሆነ የስልክዎ መጠለፍ ነገር እውን ሊሆን ይችላል።

መልዕክቱን ሲጫኑ በአንድ ጊዜ ወደ ሁለትና ሦስት የድህ-ረገጾች አድራሻዎች የሚመራዎ ከሆነ በፍጥነት ይውጡ።

6. አጠራጣሪ መተግበሪያዎችና ገንዘብ ነክ ጥያቄዎች

አንዳንድ ጊዜ እርስዎ ያልገዙት ወይም ከበይነ መረብ ያላወረዱት መተግበሪያ ስልክዎት ላይ ሊመለከቱ ይችላሉ። ምናልባትም የሞባይል ዳታ እና የጽሁፍ መልዕክት ላይ የዋጋ ጭማሪም ሊያስተውሉ ይችላሉ።

የክሬዲት ካርድና የሞባይል ገንዘብ ማንቀሳቀሻ መንገዶችን የሚጠቀሙ ከሆነ ይህ ሁኔታ ለጠላፊዎች ምቹ አጋጣሚ ሊፈጥርላቸው ይችላልና ይጠንቀቁ።

ስለዚህ የይለፍ ቃሎችንና #የግል መረጃዎችን ስልክዎት ላይ ባያስቀምጡ ይመረጣል፤ አልያም በጠላፊዎች እንዳይገኝ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል።

7. ያልተለመዱ ድምጾች

የድምጽ ጥሪ በሚያደርጉበት ወቅት ያልተለመዱና ከዚህ በፊት ያልነበሩ ድምጾች የሚሰማዎት ከሆን ምናልባት ስልክዎ የጠላፊዎች ሰላባ ሆኖ ሊሆን ይችላል። ይባስ ብሎም የስልክ ጥሪዎችዎ እየተቀዱም ሊሆን ይቺላል።
#ማስታወሽ ከላይ የተዘረዘሩት ምልክቶች በሌላ የስልኩ ቴክኒካል ችግርም ሊከሰት ስለሚችል ምልክቶቹን አሳየን ማለት ስልኩ ሙሉ በሙሉ ተጠልፏል ለማለት አያስችልም!!!!!!
t.me/ethio_tech_tricks
t.me/ethio_tech_tricks_bot


በቤት ውስጥ መወሰድ ያለባቸው የኤሌክትሪክ አደጋ ጥንቃቄዎች:-
===============
፩. የተላጡ ወይም ሊበጠሱ ያሉ ፓወር ኬብሎችን፣ቻርጀሮችን ወ.ዘ.ተ. መቀየር ወይም እንደ አስፈላጊነቱ በ ኢንሱሌተር መሸፈን አስፈላጊ ነው።
፪. ኤሌክትሪካል ሶኬቶችን ወይም ማከፋፈያዎችን ከአቅማቸው በላይ እንዲሰሩ አለማድረግ።
👉ኤሌክትሪክ ሶኬቶች ሲሰሩ መያዝ የሚችሉት የከረንት መጠን አለ ለምሳሌ ቤት ውስጥ የምንጠቀምባቸው ኖርማል ሶኬቶች መሸከም የሚችሉት እስከ 16 አምፔር ነው።
👉በተመሳሳይ ሰዓት ብዙ እቃ ብንሰካ እቃዎቹ የሚፈልጉትን የከረንት መጠን ማግኘት አይችሉም በዛ ላይ እሳት ሊፈጥር ይችላል።
፫. በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እቃዎችን፣ሶኬቶችን፣ማከፋፈያዎችን፣ ቻርጀሮችን ወ.ዘ.ተ. ከውሃ ማራቅ ምክንያቱም ቆሻሻ ውሃ ኤሌክትሪክ ያስተላልፋል።
👉ድንገት በውሃ ከረጠቡም ከመጠቀማችን በፊት የምንሰራበትን ቦታም ሆነ እቃዎችን ማድረቅ አለብን።
፬. ህፃናን ከኤሌክትሪክ አደጋ መጠበቅ:-
👉ህፃናት አጠገባቸው ባገኙት ነገር መጫወት ይወዳሉ። ስለዚህ የኤሌክትሪክ እቃዎችን ከህፃናት ማራቅ ና ክትትል ማድረግ አስፈላጊ ነው።
፭. በተቻለ መጠን ማከፋፈያዎችን አለመጠቀም:-
👉ማከፋፈያዎች መሸከም የሚችሉት የከረንት መጠን የተለያየ ነው።
👉በብዛት በቤታችን ውስጥ የሚገኙት ትንሺ ከረንት ለሚፈልጉ ለምሳሌ:- ስልክ ወይም ላፕቶፕ ቻርጅ ለማድረግ በቂ ሲሆኑ ለሌሎች ማሽኖች እንደ ልብስ ማጠቢያ፣ስቶቭ ለመሳሰሉ ከፍተኛ ከረንት ለሚፈልጉ እንጠቀማቸዋለን። በዚህ ጊዜ ከፍተኛ ሙቀት ይፈጥሩና ይቃጠላሉ። እሳት እስከመፍጠርም ይደርሳሉ።
👉በተቻለ መጠን ማከፋፈያ ከምንጠቀም ሶኬት አሰርቶ መጠቀም አስፈላጊ ነው።
፮. በእርጥብ እጅ በኤሌክትሪክ የሚሰሩ እቃዎችን አለመንካት:-
👉ከዚህ በፊት እንዳየነው የሰውነት ደረቅ ቆዳ (dry skine)የኤሌክትሪክ ፍሰት የመቃወም አቅሙ/ሪዚስታንስ 100,000 ኦም ሲሆን እርጥብ ቆዳ ወይም በውሃ የረጠበ ቆዳ ደግሞ ኤሌክትሪክ ፍሰት የመቃወም አቅሙ ወደ 1000 ኦም ይቀንሳል።
👉ኤሌክትሪክ ደግሞ ቆዳችን አልፎ መግባት ከቻለ ዉስጠኛው የሰውነት ክፍላችን የኤሌክትሪክ ፍሰት የመቃወም አቅሙ(300ኦም) ደካማ ነው።
👉ስለዚህ እጃችን ሳናደርቅ ማንኛውንም በኤሌክትሪክ የሚሰራ እቃን ከመንካት መቆጠብ አለብን።
፯. አፖል ስንቀይር ጥንቃቄ ማድረግ:-
👉አብዛኞቻችን የመብራት አፖል ሲቃጠልብን እጃችን ላይ ያለዉን ወይም ለመግዛት ሂደን የሰጡንን ገዝተን እንቀይራለን። ይሄ አግባብ አይደለም ከኤሌክትሪክ ፌክስቸሩ ዋት በላይ የሆነ አፖል ከቀየርን ፌክስቸሩ ላይ ከፍተኛ ሙቀት ይፈጥራል ከፍ ሲልም አምፖሉም ሆነ ፌክስቸሩ ይቃጠላል። ባጭሩ አምፖል ስንቀይር የአፖሉ ዋት ከፌክስቸሩ ዋት እኩል መሆን ወይም ማነስ ይኖርበታል። ፌክስቸሩ ከአንድ በላይ አምፖል የሚዎስድ ከሆነ የአፖሎች ዋት ድምር ከፌክስቸሩ ዋት መብለጥ የለበትም። ነገር ግንየዋቱ መጠን ቴክስቸሩ ላይ ካልተጠቀሰ የአፖሉ ዋት ለኢንካድሰንት ላምፕ ከ 60 ዋት፣ለCFL-ኮምፓክት ፍሎረሰንት ላምፕ ከ 12 ዋት እና ለLED-ላይት ኢሚቲንግ ዳይወድ ከ 10 ዋት መብለጥ የለበትም።
👉አምፖል ስንቀይር በሚገባ መታሰር አለበት ይህ ካልሆነ ግን ፍንዳታና እሳት ሊፈጥር ይችላል።
👉ሌላው ደግሞ ስለ አምፖሎች ለምን ቶሎ ቶሎ ይቃጠላሉ? ምን አይነት አምፖል ይሻላል? የሚሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ። ሌላ ሰፊ ፕሮግራም ይኖረናል ለጊዜው ግን ስለተለያዩ የአምፖል አይነቶች፣የሚጠቀሙት የሀይል መጠንናየሚሰጡት የብርሃን መጠን ቆጥሎ ያለው ፎቶ ላይ ይመልከቱ።
፰. ለሁሉም የቤተሰብ አባላት ግንዛቤ መፍጠር:-
👉ዋናው ብሬከር ወይም ቆጣሪ የት ጋ እንዳለ እና እንዴት ማብራትና ማጥፋት እንዳለባቸው ሁሉም የቤተሰቡ አባል ማወቅ አለባቸው። ድንገት አደጋ ቢፈጠር ቤት ዉስጥ ያለ ሰው ማንንም ሳይጠይቅ ማጥፋት ይኖርበታል።
👉አፖል ስንቀይርም ሆነ ሌሎች የኤሌክትሪክ ስራዎችን ስንሰራ መብራቱን ማጥፈትና ኤሌክትሪክ መከላከያ እንደ ጓንት፣ሴፍቲ ጫማና ሌሎችን መጠቅም። መብራት እንዳይለቁብን እየሰራን መሆኑን ለሁሉም የቤተሰብ አባል ማሳወቅ ተገቢ ነው።
👉ብረት ነክ መሰላል የምንጠቀም ከሆነ መሰላሉን ስናንቀሳቅስ ከኤሌክትሪክ መስመር ጋ እንዳይገናኝ ጥንቃቄ ማድረግ።
፱. በሙያው በሰለጠኑ ሰወች ማሰራትና የባለሙያውን ትክክለኛነት ማረጋገጥ:-
👉ህይወታችን ከኤሌክትሪክ ጋ የተቆራኘ ነው። ስለዚህ ሁሉም ሰው ስለኤሌክትሪክ መሰረታዊ እውቀት ሊኖረው ይገባል። ቀላልና ራሳችን ልንሰራቸው የሚገቡ ነገሮችን መለየትና መስራት አለብን ነገር ግን እራሳችን ለአደጋ የሚያጋልጡ ነገሮችን በሙያው በሰለጠኑ ግለሰቦች ወይም ድርጅቶች ማሰራቱ ተገቢ ነው።
👉የምናሰራቸውን ሰወች የሙያ ሁኒታ፣ ፈቃድ፣ፈቃዱን የሰጠውን አካል ማወቅ ይኖርብናል። ምክንያቱም :-
👉አደጋ ቢፈጠር ስራውን የሰራውም ያሰራዉም ሁለቱም ወንጀለኞች ናቸው።
👉ኤሌክትሪክ ምንም ቢደረግ ሉፕ እስከሰራ ድረስ ለጊዜው ኤሌክትሪክ ያስተላልፋል። ነገር ግን ብዙ ታሳቢ መደረግ ያለባቸው ህጎች፣መመሪያዎችና ስታንዳርዶች አሉ። እነዚህን ካላሟላ ወይም ካልጠበቀ ወዲያዉኑ ይበላሻል አደጋም ሊፈጥር ይችላል። እቃወቻችንም ሊይቃጠሉብን ይችላሉ። ስለዚህ የሚሰሩልን ሰወች የሙያ ሁኔታ ማወቅ ይኖርብናል።
👉ሌላው ዋናውና በሀገራችን ያልተለመደው ቅድመ/መከላከል ጥገና/prevantive maintenance የምንለው ነው። ይህ አሁን ላይ አንዳንድ ቤቶች (ሆቴሎች፣ድርጅቶች፣አንዳንድ መኖሪያ ቤቶች ወዘተ) ላይ እየተሰራ ሲሆን በጣም ጠቃሚና ብዙ እቃወችን ከብልሽት የሚታደግ ነው። ብልሽት ከማስተናገዱ በፊት መጠገን ያለብት እንዲጠገንና መቀየር ያለበት እንዲቀየር ያስችላል። የንብረትም ሆነ የህይዎት አደጋ ሳያስከትል ቀድሞ ምላሽ ለመስጠት ዋነኛ መፍትሄ ነው። ስለዚህ ቋሚ ሙያተኛ ይዞ በሆነ የጊዜ ልዩነት ቸክ አፕ እንዲያርግልን ማድረግ አዋጭ ነው።
👉ሌላው ከጅምሩ የሚያምር ህንፃ ልሰራ አስበን ኤሌክትሪኩንና የሳኒታሪ/ቧንቧ ስራዉ ላይ ግድ የለሾች ነን። በዚህም የተነሳ ስንት ነገር ወጪ አርገን የሰራነው ቤት አንድ አመት እንኳን ሳይሞላው ኤሌክትሪክ ገመድ በዉጭ በኩል ተሰርቶና ተልጣጥፎ እናያልን። ስለዚህ ከጅምሩ ትኩረት ሊሰትምጠው ይገባል።
👉የመጨረሻው ደግሞ ወጪ ላለማውጣት ሲባል ስታንዳርዱን ሳይጠብቅ ቤታችን ዉስጥ ባለው ነገር እንዲሰራ የሚያስገድዱ ግለሰቦች አሉ። ይሄ አግባብ አይደለም ሙያው በሚፈቅደው መልኩ መሰራት አለበት ይህ ካልሆነ የከፋ አደጋ ያስከትላል።
ሌሎችም አሉ ለጊዜው ግን እነዚህ በቂ ናቸው ።


📣 የተለያዩ አኒሜሽን ቪድዮዎች የሚሰራልን ምርጥ ዌብሳይት❗️

በተጨማሪም
➖Instagram Story
➖Instagram Reel
➖Instagram Post
➖TikTok Video
➖Facebook Story
➖YouTube Video
➖YouTube Thumbnail
➖YouTube Banner
እነዚህን ሁሉ ይሰራልናል።

🔗 https://www.adobe.com/express/


የግል ዋይፋያችን #WiFi እንዳይጠለፍ እና ለመረጃ ጥቃት እንዳያጋልጠን በምን መልኩ መከላከል እንችላለን?
ብዙ ጊዜ ለቤት ዉስጥ አገልግሎትም ሆነ ለመስሪያ ቤት ያስገጠምነዉ ዋይፋይ እኛ ላሰብነዉ አገልግሎት እየሰጠ ከሆነ ስለ ደህንነቱ ብዙም ትኩረት ስንሰጥ አይስተዋልም፡፡ ይህም በአንድ በኩል ከቸልተኝነት ወይም የሚያስከትለውን ጉዳት በውል ካለመገንዘብ ሲሆን፤ በሌላም በኩል የግል ዋይፋያችንን ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችል እውቀትና ግንዛቤ በአግባቡ ካለመያዝም ሊሆን ይችላል፡፡
ከዚህ አኳያ ለዋይፋዮቻችን ተገቢውን የደህንነት ስርዓት ተግባራዊ የማናደርግ ከሆነ የሳይበር ወንጀለኞች አውታረ-መረቡን /networks/ በመጠቀም ሚስጥራዊ መረጃዎችን መመንተፍ እና ዋይፋዩን በሚገባው ፍጥነት እንዳንጠቀም ሊያስተጓጉሉብን ይችላሉ፡፡
በመሆኑም ከአገልግሎት መስተጓጎል እና ከጠላፊዎች ለመጠበቅ የሚከተሉትን አማራጮች መጠቀም ይመከራል፡፡
1. ጠንካራ የይለፍ ቃል /password/ ይጠቀሙ
የዋይፋይ ራውተሮች ሲመረቱ ነባሪ መጠቀሚያ ስም /default username/ እና ሚስጥራዊ የይለፍ-ቃል ይኖራቸዋል። የራዉተሩ አምራች ከታወቀ እነዚህን የዲፎልት መጠቀሚያ ስሞችን እና ሚስጥራዊ የይለፍ-ቃላትን ለመገመት በጣም ቀላል ነው፡፡ በመሆኑም የግል ዋይፋዮቻችን ደህንነት ለማረጋገጥ “default username” በመቀየር ጠንካራ የይለፍ-ቃሎችን መጠቀም ይገባል፡፡
2. የበይነ-መረብ አገልግሎት መስጫ መለያ ይቀይሩ /service set identifier - SSID/
እያንዳንዱ ራውተር ከነባሪ መጠቀሚያ ስም /default/ ጋር ስለሚመጣ የአውታረ መረባችንን አገልግሎት መስጫ መለያ ስም /SSID/ መለወጥ ያስፈልጋል። ይህንን በራውተራችን ገመድ አልባ መሰረታዊ ቅንብር ገጽ /wireless basic setting page/ በመሄድ መጠሪያውን በመለወጥ የዋይፋያችንን ተገማችነት በማስቀረት ለጥቃት እንዳንጋለጥ ማድረግ እንችላለን፡፡
3. አውታረ-መረባችንን መመስጠር
የዋይፋይ ራውተራችን ከመረጃ ጠለፋ እና የአገልግሎት መስተጓጎል ለመከላከል የአውታረ-መረብ ምስጠራን መተግበር አስፈላጊ ነዉ፡፡
4. ሎጊንግ መፍቀድ (Enable Logging)
ሎጊንግ አማራጭን ስንፈቅድ (Enable) ስናደርግ የዋይፋይ ኔትወርካችንን እንዳይጠለፍ ለማድረግ ከሚያግዙ መንገዶች አንዱ ነዉ፡፡ በዋይፋይ ራውተራችን ውስጥ ያለው የመለያ ባህሪ ሁሉንም የአይፒ አድራሻ ይመዘግባል፡፡ እንዲሁም ሁሉንም የግንኙነት ሙከራዎች ዝርዝር ይሰጣል። ምንም እንኳን ይህን ተግባራዊ ማድረግ ዋይፋያችንን ከጠላፊዎች የማይጠብቅ ቢሆንም ማንኛውንም አጠራጣሪ እንቅስቃሴ ለመከታተል ይረዳናል፡፡ ይህንን ስርዓት "Enable" ማድረግ ይገባናል፡፡
5. የዋይፋይ ሲግናል ማስተካከል
የዋይፋይ ሲግናላችን ጠንካራ እና በአጭር የቆዳ ስፋት ብቻ ለመጠቀም የዋይፋዩን ሲግናል አቅም መቀነስ ይኖርብናል፡፡ ይህን ለማድረግ የራውተራችንን ሞድ 802.11n ወይም 802.11b ምትክ 802.11g መጠቀም ይመከራል፡፡
6. የራውተራችንን ፈርምዌር ማዘመን
ራውተራችን ፈርምዌር /Firmware/ ጊዜው ያለፈበት እና በወቅቱ ያልዘመነ ከሆነ ለአንዳንድ የደህንነት ስጋቶች የተጋለጠ መሆኑ አይቀርም፡፡ ምንም እንኳ የዘመናዊ ራውተሮች ፈርምዌር በራሳቸው የሚያዘምኑ ቢሆንም እርግጠኛ ለመሆን በየጊዜው መዘመናቸውን ልናረጋግጥ ይገባል፡፡
7. የራውተራችን ፋየርዋል ማንቃት
የራውተራችንን ፋየርዎል /firewall/ ማንቃት ይኖርብናል፡፡ ይህን በማድረጋችን ሊከሰት ከሚችል ተጨባጭ የሳይበር ጥቃቶች እራሳችንን መከላከል ያስችለናል፡፡
credit INSA


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🅰️🔠

በAlibaba ካምፓኒ ተሰርቶ EMO የሚል ስያሜ የተሰጠው ኖርማል ፎቶዎችን ወደሚናገር ተንቀሳቃሽ ምስል የሚቀይረው A.I model ይፋ ተደርጓል።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
Remote work በ construction ዘርፉም በጣም እየተራቀቀ ነው !!
ሰውየው ከ video እንደምትመለከቱት መኖሪያ ቤቱ ላይ ቁጭ ብሎ በኮምፑተሩ እያዘዘ excavatoru field ላይ ስራውን በአግባቡ እየሰራ ነው።


Official የቴሌግራም ዋሌት የዜና ቻናል @wallet_news ከላይ የምታዩትን image ቻናሉ ላይ አጋርቷል። May 16 NOT Coin ላይ አዲስ ነገር መኖሩ አይቀርም።


⭐️ Video to Animation AI Website

✅️የቀረፃችሁትን ቪድዮ ወደ አኒሜሽን ቪድዮ የሚቀይርላችሁ የኤአይ ድረ-ገፅ❗️


🔗 https://lensgo.ai/style-transfer


ethio tech tricks በሌላ አማራጮች ቢመጣ ምን ይመስላችኋል? እስኪ ምርጫችሁን አሳዩኝ!


call waiting ጥቅሙ ምንድነው? እንዴትስ በቀላሉ activate ማድረግ እንችላለን?
===============================
ወደ መልሱ ስሄድላችሁ call waiting ስልክ መስመራችን ሌላ ሰው ጋር እያወራን ሁለተኛ ስልክ ቢደወልልን እንዲጠራልን ማድረጊያ ስልት ነው ቀድመን እያወራን የነበረውን hold አድርገን የገባውን ስልክ ማውራትም እንችላለን
በአንጻሩ ይህ setting off ከሆነ ደግሞ መሰመሩን እያወራንበት ሌላ ከተደወለ ለኛ አይጠራም ለደዋዩም መስመር ተይዟል ሚል የ oprerator መለክት ይደርሰው እና ይዘጋል ማለት ነው
ሌላው ደግሞ እንዴት ይሄን setting በቀላሉ activate እናደርጋለን ሚለው ነው
በቀጥታ *43# ብለን መደወል ብቻ 😎
t.me/ethio_tech_tricks
t.me/ethio_tech_tricks_bot


Delete የተደረገ message እንዴት ማንበብ እንችላለን?

🌐Telegram፣ 🌐WhatsAppና 🌐Facebook Messenger ላይ ሰዎች ሚሴጅ ፅፈውላችሁ እናንተ ሳታዮት delete ቢያደርጉት እንዴት ማንበብ እንደምትችሉ ላሳያችሁ።

ስልካችሁ Samsung ከሆነ
⚫የስልካችሁ Settings ላይ ትገቡና Notifications የሚለውን ምረጡ።
Advanced settings የሚል አማራጭ ውስጥ Notification history የሚለውን on አድርጉት።

በዚህ መሰረት ካስተካከላችሁት በኋላ ማንም ሰዉ message ፅፎላችሁ ካጠፋው እዚህ notification history ውስጥ ገብታችሁ ታገኙታላችሁ።


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የ ስልኮች የለውጥ ሂደት ከ 1991 እስከ አሁን
ወደፊት ምን አይነት ስልኮች ይመጡ ይሆን?


የ ethiotelecom ussd አገልግሎት የሚሰጡ ኮዶች ክፍል 1(part 2)
1👉 *Zam Zam bank service
2👉 *602# ወይም *683# E-Birr
3👉 *611# Ahadu bank service
4👉 *617# NIB BIRR ussd service
5👉 *623# call signeture service በተለይ ለ ቢዝነስ እና ፕሮሞሽን ስልክ ስትደውሉ ወይም ሲደወልላችሁ ለደዋዮች የሚነበብ text
6👉 * 626# sub wallet birr
7👉 *636# ethio tel 100 second game
8👉 *641# gaada bank service
9👉 *644# coming soon😍
10👉 *653# vision fund MFI
11👉 *669# sinqee bank service
12👉 *674# kacha
13👉 *676# E-SAHAL wallet
14👉 *681*recivers phone No*amount# በ E-Birr ገንዘብ ለመላክ
15👉 *685# abyssiniya bank apollo service
16👉 *690# amhara bank mobile banking
17👉 *693# HALAL pay wallet
18👉 *698# Zam Zam mobile banking service
=====part 3=ክፍል (3) ይቀጥላል=====
t.me/ethio_tech_tricks
t.me/ethio_tech_tricks_bot


የ ethiotelecom ussd አገልግሎት የሚሰጡ ኮዶች ክፍል 1(part 1)
1👉 *803# LIB banking አገልግሎት
2👉 *804# cheek balance(የሞሉትን ሒሳብ ለማዎቅ)
3👉 *805# ሂሳብዎን ለራስዎ ለመሙላት ከሚመጡት አማራጮች 1 ን በማስገባት ለሌላ ሰው ለመሙላት ደግሞ 2ን በማስገባት መሙላት ይችላሉ።
4👉 *806*phone number*amount to transfer*1#  ሌላኛው ለሰው ካርድ የምንሞላበት አማራጭ
5👉 *809# for balance recharge and transfer
6👉 *810# for airtime crredit( ካርድ በብድር ለመሙላት)
7👉 *811# Hibir mobile banking
8👉 *812# Abay bank S.C አገልግሎት
9👉 *815#bank of Abyssiniya አገልግሎት
10👉 *817# Gize pay service
11👉 *819#   hallo cash አገልግሎት
12👉*820#   bunna international bank S.c አገልግሎት
13👉 *822# የጥሪ ማሳመሪያ አገልግሎት
14👉  *827# hijra mobile banking አገልግሎት መስጫ
15👉*836#...........
16👉*840# oromia international bank አገልግሎት መስጫ
17👉 *841#......
18👉 *844#  Zemen mobile banking አገልግሎት
19👉 *845# Enat bank S.C service
20👉 *847# comertial bank of ethiopia(CBEBirr) አገልግሎት
21👉 *866#*Wegagen bank አገልግሎት
22👉 *868# ሞባይል ቀፎ ከ sim card ጋር ለማቆራኘት ይህ አገልግሎት ስልካችሁ ቢጠፋ ከናተ ውጪ ማንም እንዳይጠቀምበት ለማድረግ ያስችልችኋል። ምክንያቱም አንዴ ካቆራኛችሁት  ሞባይል ቀፎው ያን ሲም ብቻ ነው የሚያነበው።
23👉 *870# Addis international bank service
24👉 *873# Sahay wallet service
25👉 *877# Gada bank ussd service
26👉 *881#  Birhan bank service
27👉  *889# ussd banking service center for commrecial bank of ethiopia
28👉 *895# Amole
29👉 *898# bank service
30👉 *900# ......
31👉 *912# ......1 delala 2movie 3bill 4CBO 5lucy bill 6 MFO 7walia services
32👉 *922# .......
33👉*928# change telecommnication service language
34👉 *961# Amhara bank service
35👉 *985#..........
36👉*100# ወይም *107# IMSI ቀጥር ለማዎቅ
37👉 *111# sim card ቁጥሩን ለማየት
38👉 *127# ቴሌ ብር አገልግሎት ለማግኘት
39 👉 *994*3*2# መቼ ካርድ እንደሞላን እና ምን ያክል ብር እንደሞላን ያሳየናል።
40👉 *994*2*2# የተዘጋ ሲም ለመክፈት
41👉 *994*2*1# የጠፋን ሲም ለማዘጋት ሌላ ሰው አላግባብ ሲማችን እንዳይጠቀምበት
42👉*999# ኢትዮ ገበታ አገልግሎት ማእከል።
======ክፍል (2) ይቀጥላል=====
t.me/ethio_tech_tricks
t.me/ethio_tech_tricks_bot


✳️ ሀሰተኛ ፎቶዎችን ወይም ምስሎች እንዴት መለየት እንችላለን❗️

🔺በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ የሚያጠራጥራችሁን ፎቶ ስትመለከቱ በቀላሉ የትኛውንም ሚዲያ ወይም ግለሰብ እንዲያጣራላችሁ ሳትጠብቁ በእጅ ስልካችሁ ማረጋግጥ ትችላላችሁ።

🔺በቅደሚያ ሀሰተኛ የመሰላችሁን ፎቶ/ምስል ወደ ስልካችሁ Save አድርጉት።

🔺በቀላሉ ስልካችሁ ላይ "Google Chrome App" ክፈቱት፦

-ወደ Desktop Site ቀይሩት

-በቀኝ በኩል ከላይ Image የሚለውን ምረጡ

-በመቀጠል የካሜራ ምልክቱን ተጫኑ

ለማጣራት የፈለጋችሁትን ፎቶ Choose file የሚለው ላይ ፎቶውን Upload አድርጉት፤ ከዛ ውጤቱን አጣርቶ ይነግራቹኋል።
@ethio_tech_tricks
@ethio_tech_tricks_bot


✅የስልካችን password ወይም pattern ቢጠፋብን 📲 ካለ ምንም ኢንተርኔት🌐 እና ምንም መረጃ ሳናጠፋ እንዴት መክፈት እንደምንችል እናቀርባለን. ..

🔆ኣስፈላጊ ነገሮች👇

1 aroma file manager በ ሌላ ስልክ📱 ማውረድ ኣለብን

2 ሚሞሪ ካርድ (ያወረድነውን app
የምንናስቀምጥበት)

3 የተዘጋው ስልክ📲

~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~

Step1️⃣ aroma file manager ካወረዳቹ ወደ ሚሞሪ ካርዱ ጫኑት እና ካርዱ ወደ ተዘጋው ስልክ ኣስገቡት

Step2️⃣ ከዛ ስልኩ #power_off እናረገው እና የ recovery stock ወይም ስልካችን ካጠፋነው ቡሃላ የ power እና የ ድምፅ መጨመርያ ኣንድ ላይ ተጭነን እንቆያለን( እንደ የ ስልኩ ኣይነት ሊለያይ ይችላል)

Step3️⃣ ወደ recovery mode ከገባን ቡሃላ የ ድምፅ መጫኞቹ ወደ ላይ እና ታች የ power መጫኛው ደሞ እንደ ok ሁነው ያገለግላሉ

Step4️⃣ recovery mode ላይ install zip from sd card የሚለውን ላይ ok/power button እንጫን እና aroma file manager ያስቀመጥንበት folder ገብተን #install እንለዋለን

Step5️⃣ ከዛ aroma file manager ከከፈታቹ ቡሃላ ወደ #nevigate የሚለውን ትወርዱ እና automount all devices on start የሚለውን ተጭናቹ ከዛ ዝጉት📵

Step6️⃣ step4 ላይ እንዳደረጋችሁት step6 ላይም ድገሙት

Step7️⃣ aroma file manager እንደገና ሲከፈት ወደ data folder ከዛ system folder ትገቡ አና 'gesture.key' or 'password.key' የሚል ታገኛላቹ

Step8️⃣ ከዛ ያገኛችሁት gesture.key or password.key ኣጥፉት ከዛ ስልካቹ reboot ኣድርጉት

Step9️⃣ ስልኩ📲 ሲከፈት የማትረሱትን pattern ወይም password በማስገባት መክፈት ትችላላቹ
https://t.me/ethio_tech_tricks
https://t.me/ethio_tech_tricks_bot


✳️ ይህን ሞክረውታል

🔺ስልክን በሚስጢራዊ ቁጥሮች በፓተርን ወይም በፊት ቅርጽ፣ በአሻራ የመቆለፊያ መንገዶች በመጠቀም የግል መረጃዎችንና ልዩ ልዩ መተግበሪያወችን መቆለፍ ወይም ደብቆ ማስቀመጥ እንደሚቻል የታወቀ ነው፡፡

🔺ነገር ግን በስልካችን ውስጥ የሚገኙ በአፋጣኝ የምንፈልጋቸውን መተግበሪያዎች ስልካችን እንደተቆለፈ መጠቀም የምንችልባቸው ዘዴወች አሉ፡፡ ለምሳሌ ያክል እንደ ጎግል እና ሴሪ (Google Assistant and Siri) ፎቶ ማንሳትና የአደጋ ጊዜ ስልክ ጥሪ ማድረግ (emergency calls) ያስችለናል።

🔺አንድሮይድ ስልክ ያለው ሰው መጀመሪያ የጎግል መተግበሪውን (Google Assistant app) ይከፍታል፡፡ ከዚያም በታች ቀኝ በኩል የሚገኘውን የኮምፓስ ምልክት መንካት በላይኛው የግራ ክፍል በመሄድ (Settings
Assistant and Phone) የሚሉትን መምረጥ ከዚያም የድምጽ ማመሳሰያ ምልክቱን ማብራት ከዚህ በፊት ስልኩ የተጠቃሚውን ድምፅ የማያውቅ ከሆነ መጀመሪያ ስልኩ ድምፅ መለየት (voice recognition) እንዲችል ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ አንድ ጊዜ ይህ ከተስተካከለ በኋላ የ Google Assistant ለማግኘት "Hey Google" ወይም "Okay Google" ማለት ብቻ ነው የሚጠበቅብን፡፡ ከዚያም የምንፈልገውን አገልግሎት ማግኘት እንችላለን፡፡
@ethio_tech_tricks
@ethio_tech_tricks_bot


ምናልባት ጓደኞቻችን ወይም ሌላ ሰው ስልካችን ላይ telegram plus ውስጥ ቢገባ  እንዲያይብን  የማንፈልጋቼውን freind chat channel እንዲሁም Group መርጠን   መደበቅ  እንችላለን? አዎ እንችላለን
እንዴት?
step 1✅ telegram plus ስንከፍት በግራ በኩል ከላይ የምናገኛትን 3 መስመር ጫን እናደርጋለን።
step 2✅ ከሚመጡልን አማራጮች ውስጥ plus setting የሚለውን እንጫናለን።
step 3✅ ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ privacy and security የሚለውን እንጫናለን።
step 4✅ ከሚመጡልን አማራጮች ውስጥ enable hidden chats የሚለውን on እናደርጋለን። ሌሎችንም እንደየ ፍላጎታችሁ on ማድረግ ትችላላችሁ ለምሳሌ  unlock with fingerprint ሚለውን on ብታደርጉት   የምትደብቁት chat ወይም group የምትከፍቱት በጣታችሁ አሻራ ነው ማለት ነው እንዲሁም passcode ሚለውን on ካደረጋቹት  step 7 ላይ የደበቃቹትን chat,group ወይም channel ለማየት search🔎  ምልክቷን ተጭናችሁ ስትይዟት password ይጠይቃቿል።
step 5 ✅ on ካደረግን በሗላ   መደበቅ ወደምንፈልገው chat, group ወይም channel እንገባለን። ለምሳሌ እኔ ከ Gashaw shimelash  ጋ ማዎራውን መደበቅ ፈለኩ ከዛ Gashaw shimelash ሚለው ውስጥ በቀኝ በኩል ከላይ ሶስት ቁልቁል የተደረደሩ ነጥቦች አሉ እሱን እጫናለሁ ማለት ነው።
step 6❇️ሶስቱን ነጥቦች ስንጫን ከሚመጡት አማራጮች ውስጥ hide የሚለውን ስንጫን ይደበቃል ማለት ነው።
step 7❇️  ከዛ የደበቅነውን ማየት ስንፈልግ   search 🔍 የሚለውን ምልክት ለተዎሰኑ ሰከንዶች ጫን አድርገን ስንይዘው የደበቅናቸውን ያመጣልናል ማለት ነው😻🤭

20 last posts shown.