ከአድዋ ድል ጋር የማገናኘው ሁሌ የሚያሳዝነኝ አንድ ታሪክ አለ፡፡
#Ethiopia | አሜሪካን ጨምሮ የነጮች የበላይነት ሰፍኖ የኖረበትን የዘር ስርዓት ሳስብ ህይወታቸውን ከፍለው ከጥቁርና ነጭ ቀለም የገዢ ተገዢነት ትርክትና ሰቀቀን የታደጉንን ጀግና አባቶቻችንን አከብራለሁ፡፡ አድዋ ላይ ተሸንፈን ቅኝ ተገዝተን ቢሆን ኖሮ r የኢትዮጵያና የህዝቦቿ ታሪክ ፣ የኛም ስነልቡና ዛሬ ያለው ቅርጽ አይኖረዉም ነበር፡፡
ከቀለም ፖለቲካ አዛሳኝ ታሪኮች አንዱን እነሆኝ!
በአሜሪካ ምናልባትም በዓለም የ20ኛው ክፍለዘመን የፍርድ ውሳኔ ታሪክ በእድሜ ትንሹ የሞት ፍርደኛ የ14 ዓመቱ ጆርጅ ስቲኔይ ጁኒየር ነው፡፡
ጆርጅ ስቲኔ ፍርድ ቤት የቀረበው የ11 እና የ7 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ቤቲና ሜሪ የተባሉ ሁለት ነጭ ህጻናትን ገድለሃል ተብሎ ነው፡፡
የሟቾቹ አስከሬን በመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ እንደተገኘ ትንሹ ጆርጅ ገዳይ ተብሎ ተጠረጠረና ፍርድ ቤት ቀረበ፡፡
ጉዳዩን ይመለከቱ የነበሩ ሁሉም ዳኞች ነጮች ሲሆኑ የሞት ፍርድ ሲወስኑበትም አጠቃላይ የፍርድ ሂደቱ ሁለት ሰዓት ብቻ ነበር የወሰደው፡፡ የመጨረሻው ቀን የፍርድ ውሳኔውን ያስተላለፈው ችሎት በተጀመረ በ10 ደቂቃ ተጠናቀቀ፡፡
ምስኪኑ ጆርጅ የተከሳሽ ሳጥኑ ውስጥ ቆሞ ሲያለቅስ ወላጆቹ አጠገቡ ቀርበው አይዞህ እንዳይሉት እንኳን በፍርድ ቤቱ ፖሊሶች ተከልክለዋል፡፡ ዳኞቹ በዚህ ምስኪን ጥቁር ህጻን ላይ ሞት ፈረዱበት፡፡
ጆርጅ ብቸኛ መጽናኛው በእጁ የያዘው መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ ነበር፡፡ ደጋግሞ መጽሃፍ ቅዱሱን እያሳየና እየማለ “እኔ አልገደልኳቸውም፣ ምንም ወንጀል አልፈጸምኩም” እያለ ቢማጸንም የሚሰማው አላገኘም፡፡
ጆርጅ ከፍርድ በኋላ ከሚኖርበት ከተማ 50 ማይል ርቆ ወደሚገኝ ወህኒ ቤት ሲወሰድ እናትና አባቱ ደግሞ በግድ ከመኖሪያቸው ለቀው ወደሌላ ከተማ እንዲሰደዱ ተደረጉ፡፡ ጆርጅ የሞት ፍርዱ አስኪፈጸምበት በእስር ቤት በቆየባቸው 81 ቀናት እናትና አባቱ ለስንብት እንኳን አንድም ቀን አይኑን እንዲያዩት አልተፈቀደላቸውም፡፡
የሚደንቀው ነገር ምስኪን ጆርጅ የፍርድ ውሳኔው ከተላለፈበት ቀን ጀምሮ ግድያው እስኪፈጸምበት ቀን ድረስ መጽሃፍ ቅዱሱ ከእጁ አልተለየም፡፡ የሚናገረውም አንድ ነገር ብቻ ነው፡፡
“እኔ ማንንም አልገደልኩም፣ ምንም አላጠፋሁም፣ እባካችሁ ልቀቁኝ”
በመጨረሻው ቀን ጆርጅ ስታኔይ ጁኒየር በ14 ዓመቱ ገዳይ ወንጀለኛ ተብሎ 5ሺህ 330 ቮልት ሃይል ያለው ኤሌክትሪክ ከእግር እስከጭንቅላቱ ድረስ ተለቆበት ተገደለ፡፡
ምሰኪን ጆርጅ ከተገደለ ከ70 ዓመታት በኋላ ግን አስደንጋጭ ታሪክ ተሰማ፡፡ የደቡብ ካሮላይና ፍርድ ቤት ዳኛ ያ ህጻን የተባለውን የግድያ ወንጀል እንዳልፈጸመ አረጋግጠው ንጽህናውን አወጁ፡፡
ነጮቹን ህጻናትን የገደላቸው 18 ኪሎ የሚመዝን የብረት ምሰሶ መሆኑንና ለንድ የ14 ዓመት ህጻን ይህን ያህል ክብደት ያለው ብረት ሰው ላይ መሰንዘር ቀርቶ ከመሬት አንስቶ ለመሸከም እንኳ የማይታሰብ መሆኑ በምርመራ ተረጋግጧል፡፡
በመጨረሻም ጆርጅ ላይ የተካሄደው ምርመራ ሆን ተብሎ የሟቾችን ገዳይ አገኘን ለማለት የተፈበረከ የሃሰት ክስ መሆኑም ታወቀ፡፡ “በጊዜው ምስኪኑን ጆርጅ ለሞት ያበቃው ብቸኛ ጥፋት ጥቁር መሆኑ ብቻ ነበር” ተባለ፡፡
ይህ አሳዛኝ ታሪክ ኋላ ላይ ስቴፈን ኪንግ የተባለው ደራሲ አድናቆት ያገኘውን "The Green Mile" መጽሃፍ እንዲጽፍ ምክንያት ሆኖት ነበር፡፡
ስቴፈን በመጽሃፉ ምን ይላል? “ቀደም ባለው ዘመን የነበረውም ይሁን አሁን ያለው የሰው ልጅ ጨካኝ ነው፡፡ ልዩነቱ ያኔ ጭካኔ ተደብቆ ይኖር ነበር ዛሬ ደግሞ የሚደበቅ ነገር ምንም የለም፣ ሁሉም ያውቀዋል”
‘’People were cruel then, just as they are now. The only difference is that before, cruelty was hidden, whereas now it is exposed for everyone to see’’
ስቴፈን እንዳለው "ዛሬ የሰው ልጅ የራሱን ጥቅም ከሰው ህይወት በላይ ለምን ያስቀድማል?" ብሎ መጠየቅ ልፋት ነው፡፡ ድሮም የሰው ልጅ እንዲያ ነበር፡፡ ልዩነቱ ያኔ ብዙ ነገር ተደብቆ ይኖር ነበር፡፡ ዛሬ የቱም የሰው ልጅ ጭካኔ ድርጊት በደቂቃዎች ልዩነት ጸሃይ ይሞቀዋል፡፡
እኔ ግን እላለሁ፡፡ በምድር ላይ በነጮች በተገዙ ጥቁሮች ላይ ከደረሰው በደል በላይ በሰው ልጅ የደረሰ ታሪክ የመዘገበው አስከፊ በደል የለም፡፡
እንኳን ለአንጸባራቂው የአድዋ ድል በዓል አደረሰን!!
Via መላኩ ብርሃኑ🙏🙏🙏🙏
Share @ethio_tksa_tks