Ethio - ዜና 🇪🇹


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic


የመረጃዎች ቁንጮ የሆነውን Ethio ዜና ለሚወዱት ጓደኞችዎ እና ቤተሰብዎ ያካፍሉ። አንድ ላይ፣ ዘምነን እንቆይ!
ምርት እና አገልግሎታችሁን ገጻችን ላይ ለማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
@Ethiozenaa_bot

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Statistics
Posts filter


ሴዶ ማርሻል እስከ 1 ዓመት እስራት ሊቀጣ ይችላል» — ጠበቃ ሰብለ አሰፋ::

በETFC 2 Cage ውድድር ውዝግብ ዙሪያ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ሕጋዊ ማብራሪያ ሰጡ

አዲስ አበባ — በETFC 2 Cage ውድድር ዝግጅት ወቅት ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል "በተቃዋሚዬ ጆኒ ድግምትና መተት ተሰርቶብኛል" በሚል ምክንያት ከውድድሩ ራሱን ማግለሉን አስመልክቶ ጠበቃ ሰብለ አሰፋ ሕጋዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠበቃ ሰብለ አሰፋ በቪዲዮ በሰጡት መግለጫ፣ ሴዶ ያቀረበው "በእንቁላል መተት ተሰርቶብኛል" የሚለው አቤቱታ በህግ ፊት ተቀባይነት ያለው ማስረጃ ካልቀረበበት በስተቀር በጆኒ ላይ የተፈጸመ የሐሰት ስም ማጥፋት ወንጀል እንደሆነ ገልጸዋል።

እንደ ጠበቃ ሰብለ ገለጻ፣ በኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 613 መሠረት፣ አንድ ሰው ያለበቂ ማስረጃ በሌላው ሰው ላይ የሐሰት ክስና ውንጀላ በማቅረብ መልካም ስሙንና ክብሩን ካደፈረሰ ወይም በህብረተሰቡ ዘንድ ያለውን አመኔታ እንዲያጣ ካደረገ፣ በተጎጂው አቤቱታ አቅራቢነት እስከ አንድ ዓመት በሚደርስ ቀላል እስራት ሊቀጣ ይችላል።

በተጨማሪም ውድድሩ መሰረዙ ከተረጋገጠ ወይም የተወደዱ ተወዳዳሪዎች ባለመሰለፋቸው ምክንያት ቅሬታ ያላቸው የትኬት ገዢዎችና ተመልካቾች የውድድሩን አዘጋጆች ካሳ የመጠየቅ ሙሉ ሕጋዊ መብት እንዳላቸው ጠበቃ ሰብለ አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ደግሞ የውድድሩ አዘጋጆች (ETFC) ሴዶ ማርሻል በገባው ውል መሠረት ባለመወዳደሩ ምክንያት ለደረሰባቸው የወጪና የገቢ ኪሳራ እንዲሁም ለተመልካቾች ለሚከፍሉት ካሳ በፍትሐብሔር ሕግ መሠረት ከሴዶ ላይ የጉዳት ካሳ የመጠየቅ መብት እንዳላቸው ገልጸዋል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


ዛሬ ማለዳ በአዲስ አበባ  በደረሰ የመንገድ ትራፊክ አደጋ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ!

አደጋው የደረሰው ዛሬ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም ከጠዋቱ 1:50 ሠዓት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ11 ልዩ ቦታው ቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤ/ክርስቲያን አካባቢ ነው፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ እንዳሳወቀው የጉዞ አቅጣጫው ከኮዬ ፈቼ ወደ ጎሮ የሆነ የሠሌዳ ቁጥር ኮድ 3-05997 ትግ የሆነ ሚኒባስ ተሽከርካሪ በተጠቀሰው አካባቢ በመንገድ ስራ ላይ የነበረ ስካቫተር ማሽን መቆፈሪያው ወድቆበት በታክሲው ውስጥ ከነበሩ ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች መካከል 5 ወንዶችና 1 ሴት ህይወት አልፏል፡፡

ከሟቾች በተጨማሪ በታክሲ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው የህክምና ክትትል በማድረግ ላይ የሚገኙ መሆኑን የገለጸው የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ የአደጋው መንስኤ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


ዓመተ ምህርት (ዓ.ም) የሚለው የዘመን አቆጣጠር የኢትዮጵያ አቆጣጠር (ኢ.አ) እንዲባል ስምምነት መደረሱ ተገለጸ

ዓመት ምሕረት (ዓ.ም) የሚለው የዘመን አቆጣጠር እንዲቀር የተለያዩ ምክረ ሀሳቦች ሲቀርቡ የነበረ ሲሆን፣ ለ4ሺሕ ጉባያተኞች ተነቦ ኮሚሽኑ በተረከበው ሰነድ፣ ዓ.ም የሚለው ቀርቶ የኢትዮጵያ አቆጣጠር (ኢ.አ) እንዲባል ስምምነት መደረሱን ተመካካሪዎች ገልጸዋል። ሒጅራ እንደ ካላንደር ይካተት ተብሎ መያዙም ተገልጿል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


አንድ የክርስቲያን እምነት ተከተይ የቁርዓን ውድድር አሸንፎ የዑምራ ጉዞ ተሸለመ

​በግብፅ የሚኖር ሚና የተባለ የክርስቲያን እምነት ተከተይ በቁርዓን አፈጻጸም ውድድር ላይ ተሳታፊ በመሆን አሸናፊ መሆኑ የመገናኛ ብዙኃን እና የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎችን ትኩረትስቧል።

​ሚና በውድድሩ የተሳተፈው ሙና የተባለችው ሙስሊም ጎረቤቱ ለውድድሩ ስታደርግ የነበረውን ጥረት ከተመለከተ በኋላ እሷን የመርዳት እና የማበረታታት አላማ ሰንቆ እንደነበር ተገልጿል።

የውድድሩ አሸናፊ በመሆን የተበረከተለትን የዑምራ (የመካ) ነፃ የጉዞ ሽልማት፣ እሱ በሃይማኖታዊ ምክንያት ሊጠቀምበት ስለማይችል ሙሉ በሙሉ ለጎረቤቱ ለሙና አበረክቶላታል።

​ይህ አርአያነት ያለው የእርስ በርስ መከባበር እና የጎረቤትነት ፍቅር ድርጊት በግብፅ እና በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ ከፍተኛ አድናቆትን እያገኘ ይገኛል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


#እንዲታወቅ
****
ከአያት 49 ወደ ፊጋ በሚወስደው መንገድ ላይ 72  ድልድይ አካባቢ የመንገድ ጥገና ሥራ ይካሄዳል።

በመሆኑም በተጠቀሰው ሥፍራ የሚካሄደውን የጥገና ሥራ በፍጥነት ለማከናወን፤ ከነገ ሰኞ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ መንገዱ በከፊል ለትራፊክ ዝግ ይደረጋል።

ስለሆነም አሸከርካሪዎች ጥንቃቄ በማድረግ ማለፍና እና አማራጭ መንገዶችን እንድትጠቀሙ  ትጠየቃላችሁ።
@ የአዲስ አበባ ከተማ መንገዶች ባለሥልጣን

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


“አንዲት ጠብታ ነዳጅ በሆርሙዝ አታልፍም” ኢራን

ኢራን ጎረቤቶቿ “በአሜሪካ የኢኮኖሚ ጫና ዘመቻ ላይ ከተሳተፉ ሆርሙዝ ሰርጥን ሙሉ ለሙሉ እዘጋዋለሁ“ አለች።

ጎረቤት ሀገራት ከአሜሪካ ጋር ግንባር ፈጥረው ኢኮኖሚያዊ አደጋ የሚያመጡ ከሆነ “አንዲት ጠብት ነዳጅ ከፐርዢያ ባህረ ሰላጤ አያልፍም አታልፍም“ ብላለች።

አማራጭ መስመሮችን ሊጠቀሙ ቢችሉም ወታደራዊ ዕርምጃ እንደምትወስድም ኢራን ዝታለች።

ቴህራን ይህን ሀሳቧን ይፋ ያደረገችው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ዋና ፀሐፊ ስኮት ቢሰንት ሀገራት አሜሪካን እንዲደግፉ እና በኢራን ላይ ብርቱ ምጣኔ ሀብታዊ ጫና ለመፍጠር ጥሪ ካቀረቡ በኃላ ነው ።

የዋሽንግተን አጋሮች እና ሌሎች ሀገራትም ዘመቻውን እንዲቀላቀሉ ራሳቸው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ማሳሰቢያ መስጠታቸው የሚዘነጋ አይደለም።

እንደቻይና ያሉ ሀገራት ደግሞ የአሜሪካን ጥሪ አንቀበለውም በሚል ውድቅ አድርገውታል።

ከቴህራን ጋር ንግድ የሚለዋወጡ ሀገራትም ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዋይት ሀውስ አስጠንቅቋል።

የኢራን ከፍተኛው ብሄራዊ ደህንነት ምክር ቤት ሀኃላፊ ሞህሰን ረዛኢ ከአሜሪካ ጎን በምጣኔ ሀብታዊ ዘመቻው ላይ ለመሰለፉ የሚሞክሩ ሀገራት “አደብ ቢገዙ መልካም ነው “ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

የትኛወም ሀገር በዚህ ጉዳይ ላይ እንዳይሳተፉ ብለዋል።

ከዋሽንግተን ጋር አብረው የሚሰሩ ካሉ ቴህራን እንደጠላት ትቆጥራቸዋለች  ብለዋል ሞህሰን ረዛኢ ሲሉ አር ቲ እና አልጀዚራ አስነብበዋል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


ከኢትዮጵያ የተነሳ ድሮን ተመቷል-ሱዳን‼️
የሱዳኑ መከላከያ ሚኒስቴር "ከኢትዮጵያ የተነሳ የጠላት ድሮን በብሉ ናይል (ሰሜናዊ ናይል) ክልል ውስጥ በኩርሙክ አካባቢ ሲበር በመታየቱ መትተን ጥለነዋል" ሲል ጦሩ ገልጿል።

የሱዳን ጦር ዋና አዛዥ በዛሬው ዕለት ነሐሴ 17/2018 ዓ.ም እለት በሰማያዊ ናይል ግዛት በስተደቡብ አንድ ስትራቴጂካዊ ድሮን ከኢትዮጵያ ወደ ሱዳን የአየር ክልል በመግባቱ ተመቶ መውደቁን አስታውቋል።

የጦር ኃይሎች ኦፊሴላዊ ቃል አቀባይ ጽህፈት ቤት ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳመለከተው ድሮኑ የተመታው ከዲንዲሮ ደቡብ ምስራቅ በብሉ ናይል ግዛት ሲሆን ከኢትዮጵያ አቅጣጫ የሱዳንን ድንበር አቋርጦ ከገባ በኋላ ነው ብሏል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


ከጆኒ ጁጁትሱ ጋር ያደርገዋል ተብሎ በብዙዎች ዘንድ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የትግል ውድድር ሊካሄድ ጥቂት ቀናት ሲቀሩት፣ ተወዳዳሪው ሴዶ ማርሻል አርት «ድግምትና መተት ተሰርቶብኛል» በሚል ምክንያት ከውድድሩ ማለፉን ባሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ አድርጓል።

ሴዶ ባስተላለፈው መልእክት፣ በተቃዋሚው ወገን በእንቁላል አማካኝነት ድግምት እንደተደረገበትና ንቃተ ህሊናንም ያሸነፈው በዚሁ ሁኔታ መሆኑን ገልጾ፣ በዚህ አይነት ሁኔታ ውስጥ ገብቶ መወዳደር እንደማይፈልግ አስታውቋል።

ውድድሩን ለሚከታተለው የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ለትኬት ገዢዎች እና ለስፖንሰሮች ይቅርታ የጠየቀው ሴዶ፣ አዘጋጆቹ ሌላ ተወዳዳሪ ካቀረቡለት ለመግጠም ዝግጁ መሆኑን ጠቁሞ፣ የውድድር አዘጋጁን ኢቲኤፍሲ (ETFC) ቲሸርት በካሜራ ፊት አውልቆ በመጣል ከውድድሩ መውጣቱን አረጋግጧል።

ሴዶ ይህንን መልዕክት ያስተላለፈው፤ በቀልድ መልክ ይሁን በትክክለኛ ውድድሩን ለማቋረጥ፤ እስካሁን ከውድድሩ አዘጋጆች የታወቀ ነገር የለም።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


ከሚሰራበት ድርጅት የተቆራረጡ ፌሮ ብረቶችን በሁለት እግሮቹ አስሮ  ይዞ የወጣው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት።

ወንጀሉ የተፈጸመው ሐምሌ 24/2018 ዓ/ም ከቀኑ 11:00 ሠዓት በንፍስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ  ወረዳ1 ለቡ መብራት አካባቢ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪ አስታውቋል።

ተከሳሽ በሪሁን ሰፈፈ በተጠቀሰው አካባቢ ከሚገኝ አንድ ሪል ስቴት ውስጥ  በቀን ሰራተኛነት ተቀጥሮ ሲሰራ የነበረ ሲሆን በስራ መውጫ ሰዓት የድርጅቱ ንብረት የሆነውን ቁርጥራጭ ፌሮ ብረት በሁለት እግሩ ከቁርጭምጭሚቱ በታች ፌስታል በመጠምጠም ከእግሮቹ ጋር አስሮ እና ሱሪውን ከላይ በመልበስ ይዞ ሊወጣ ሲል በድርጅቱ ጥበቃዎች ተይዞ ክስ እንደ ተመሰረተበት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ፖሊስ ዋና መምሪያ የለቡ ፖሊስ መምሪያ ገልጿል።

ህይወታቸውን ለመቀየር ቀን ከሌሊት በታማኝነት የሚሰሩ የቀን ሰራተኞች እንዳሉ ሁሉ አንዳንዶች ደግሞ ወንጀልን ለመፈጸም አቅደው እና አስበው የሚንቀሳቀሱ እንደማይጠፉ ፖሊስ አስታውቋል።

አሰሪ ድርጅቶች ሰራተኞችን ተገቢ በሆነ መንገድ መቅጠር እና ቁጥጥር ማድረግ ይኖርባቸዋል ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ዋና ጠቅላይ መምሪያ መልዕክቱን አስተላልፏል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


“አይፎን 15” ካልገዛችሁልኝ ያለው ወጣት ራሱን ጨምሮ የቤተሰቡን ነፍስ ቀጥፏል።

በህንድ ማሃራሽትራ ግዛት ዕድሜው 18 ዓመት የሆነ ወጣት አዲስ “አይፎን 15” (iPhone 15) ስልክ እንዲገዛለት ያነሳው ጥያቄ ቤተሰቦቹ ባለመቀበላቸው፣ ከፍ ያለ ቦታ ላይ በመውጣት እራሱን ከገደል አፋፍ ላይ አቁሞ ቆይቷል።

ወላጆቹ ለሰዓታት ሲለምኑት እና ለማሳመን ሲሞክሩ ከቆዩ በኋላ አባቱ ሊያድኑት ወደ እሱ ሲጠጉ፣ ወጣቱ አባቱን ጨብጦ በመሳቡ ሁለቱም ከገደል ወድቀው ህይዎታቸው አልፏል።

ልጇን እና ባለቤቷን በድንገት ያጣችው እናቷም በደረሰባት ከፍተኛ ሀዘን እና ድንጋጤ ከተመሳሳይ የገደል አፋፍ ላይ እራሷን በመጣሏ የሷም ህይወት ማለፉ ተዘግቧል።

ይህ አሳዛኝ ክስተት በዛሬው ዕለት በርካቶች ሲመለከቱት፥ በወጣቶች የአዕምሮ ጤና ዙሪያ ያለውን ስጋት አጉልቶ ያሳየ ስለመሆኑ ተነግሯል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


💥በመገናኛ የካ ክፍለ ከተማ (ዲያስፖራ አደባባይ) የሚገኘውን የቴምር ፕሮፐርቲስ ዘመናዊ አፓርትመንት ሽያጭ መረጃ በአጭሩ እንደሚከተለው ቀርቧል፦

የክፍያ አማራጭ፦ በ40/60 አከፋፈል (40% አሁን፣ ቀሪውን 60% ቤት ሲረከቡ) ወይም ቀሪውን 80% እስከ 15 ዙር ያለምንም ወለድና የዕቃዎች ጭማሪ መክፈል ይቻላል። ለ40% ከፋዮች የ10% ቅናሽ አለ እንዲሁም 100% ለከፈለ 35%ቅናሽ አለው

ስቱዲዮ (32 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 4,160,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 832,000 ብር።
100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ=2,704,000

1 መኝታ (60 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 7,800,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 1,560,000 ብር።
100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ=5,070,000

2 መኝታ (90 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 11,700,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 2,340,000 ብር።
100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ=7,605,000

3 መኝታ (112 ካሬ)፦ ሙሉ ክፍያ 14,560,000 ብር | 20% ቅድመ ክፍያ 2,912,000 ብር።
100% ሲከፍሉ 35% ቅናሽ =9,464,000

ልዩ ማሳሰቢያ፦ ይህ ዋጋ ከ1ኛ እስከ 7ኛ ፎቅ ላለው ሲሆን፣ ፎቁ ከፍ ሲል ዋጋው ይቀንሳል።

ሌሎች ሳይቶች፦ በሳርቤት፣ አዋሬ፣ ቡልጋሪያ፣ ፒያሳ እና ገላን የመኖሪያና የንግድ ሱቆች/ቢሮዎች ይገኛሉ።

ለበለጠ መረጃ :-

☎️ +251953577265 ይደውሉልን።
                      


የመከላከያ ሰራዊት የልዩ ዘመቻዎች ዕዝ ማሰልጠኛ ማዕከል 45ኛ ዙር የኮማንዶ ሠልጣኞችን አስመረቀ

ማሰልጠኛ ማዕከሉ በሥነ ምግባር፣ በፅናትና በሀገር ፍቅር የታነጹ የ45ኛ ዙር የ"ፅናት ኮርስ" መሠረታዊ የኮማንዶ ሠልጣኞችን በዘመኑ የውጊያ ባህሪ ላይ የተመሠረተ ሁለገብ ወታደራዊ ሳይንስና የኮማንዶ ቴክኒክ ዘርፍ አሰልጥኖ ማስመረቁን አስታውቋል።

የሥልጠናው የትኩረት መስኮች፦

የፀረ-ሽምቅ፣ የመደበኛና የከተማ ውጊያ፣ የፀረ-ሽብር እንዲሁም ዓለም አቀፍ ግዳጆችን መሠረት ያደረጉ በተለያዩ የመሬት ገጽታዎችና የአየር ሁኔታዎች የሚከናወኑ ወታደራዊ ክህሎቶች፤

የቀንና የሌሊት ሥልጠናዎች፣ የእጅ በእጅ ውጊያ፣ የጅምናስቲክ እና ተፈጥሯዊና ሰው ሠራሽ መሰናክሎችን የማለፍ ከፍተኛ ብቃት፡፡

የዘንድሮ ተመራቂዎች በራሳቸው ተነሳሽነትና ፈጠራ ከኪሳቸው ገንዘብ በማዋጣት ለማዕከሉ 5 የመሰብሰቢያ "አንፊ-ትያትሮችን" ገንብተው ማስረከባቸን ሚኒስቴሩ አስታውቋል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


የአዲስ አበባ ጉዳይ‼️
የኦሮሚያ ክልል ያቃረበውን ቅሬታ የተመለከተው የአሸማጋይ ቡድን  አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ ከተማ መሆኗ በህገ መንግስት ይጻፍ የሚል ምክረ ሃሳብ አቅርቦ፤ የ500 ቡድን አዲስ አበባ የፌደራል መንግስት አካል ናት በሚል የተስማማበት ቀርቶ "ተጠሪ" በሚል እንዲተካ ምክረ ሃሳብ አቅርቦ ምክክሩ ተጠናቋል።
አዲስ አበባን በተመለከተ በሁለት ጎራ ከፍሎ ሲያከራክር የቆየው ጉዳይ አሁንም በልዩነት ተመካካሪዎች ካሳለፏቸው 4 ምክረ ሃሳቦች ውስጥ አንዱ ነው።

አዲስ አበባን በተመለከተ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም. ለርዕሰ ቡድን ተመካካሪዎች በንባብ የቀረበው ሰነድ "አዲስ አበባ የፌደራል ከተማ ትሁን፤ ራሷን በራሷ ታስተዳድር" በሚለው ላይ ሁሉም ከስምምነት መድረሱን ያስረዳል።

ክልሉ ከከተማው አስተዳደር ልዩ ጥቅም ማግኘት ስላለበት የሚደነግገው የሕገ መንግሥቱ ክፍልም "የጋራ ጥቅም" በሚል እንዲሻሻል ከስምምነት መደረሱን ያክላል።

አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል ዋና መቀመጫ ትሁን ከሚለው ጋር በተያያዘ ግን የ500 ቡድን ሁለት ምክረ ሃሳቦችን አቅርቦ ተንቦ ነበር።

እነሱም፦ ክልሎች የራሳቸውን መቀመጫ መወሰን እንዲችሉ በሕገ መንግሥቱ ይካተት የሚለው አንደኛው ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 47 (ወይም አግባብ ያለው አንቀጽ) ላይ የሰፈረው አዲስ አበባ የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ከመሆኗ ጋር በተያያዘ ከተማዋን እና ክልሉን የሚመለከቱ ጉዳዮች በሕግ ይወሰኑ የሚል ድንጋጌ ይካተት የሚሉት ናቸው።

ይሁንና የኦሮሚያ ክልል ተወካዮች ይህን ጉዳይ በተመለከተ ቅሬታ አቅርበው ኮሚሽኑም ይህን ችግር የሚፈታ የክልል ጉባዔ ጠርቶ ከዚያ ውስጥ አሸማጋይ ቡድን አቋቁሞ የነበረ ሲሆን፣ የቡድኑንም ውሳኔ የምክክር ኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዮናስ አዳዬ ለ4,000 ጉባዔተኞች ትናንት ምሽት በንባብ ማቅረባቸው ታውቋል።

በተነበበው መሠረት አሸማጋይ ቡድኑ በሕገ መንግሥቱ "የኦሮሚያ ርዕሰ ከተማ አዲስ አበባ ናት" የሚል ድንጋጌ ይጻፍ የሚል ምክረ ሃሳብ መስጠታቸውን እና ከተማዋ "የፌደራሉ አካል ናት" የሚለው ተስተካክሎ "ተጠሪ" በሚል እንዲተካ ምክር ማቅረቡን ውሳኔውን ያነበቡት ኮሚሽነር ዮናስ አስረድተዋል።

ኮሚሽኑ ግን ከቀረቡት ምክረ ሃሳቦች ውስጥ የየትኛውን እንደሚቀበል ለጊዜው አላስረዳም።

ነገር ግን በምን መስፈርት እንደሆነ ባልዘረዘረው ሁኔታ ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበሩ ውሳኔዎችን መርምሮ "ለሀገር የሚበጅ" ያለውን ውሳኔ እንደሚያሳልፍ ተናግሯል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


"ከአጠቃላይ 591.6 እና ከሴቶች ደግሞ 583 ከፍተኛ ውጤት ተመዝግቧል"
**

በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ይፋ ሆነዋል።

በዚህም መሠረት በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ በወንዶች አዳማ ኦዳ ስፔሻል ቦርዲንግ ትምህርት ቤት ተማሪ ከ600 ውስጥ 591.6 በማስመዝገብ ከፍተኛውን ውጤት የተመዘገበ ሲሆን፤ በሴቶች ደግሞ ከእንጅባራ አገው ምድር ትምህርት ቤት ተማሪ ከ600 ውስጥ 583 በማምጣት የላቀ ውጤት አስመዝግባለች።

በማህበራዊ ሳይንስ ከወንድ 576.2 ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ት/ቤት እና ከሴት 569.1 ቦሌ ሱፐር ሆሊሴቪየር ት/ቤት ተመዝግቧል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


ከሀገሬ መቼም አልሸሽም-ኮሚሽነሩ‼️
ከሀገሬ አለሸሸሁም፣መቼም አልሸሽም፣ወደ አሜሪካ የሄድኩት በሀዘን ምክንያት ለቀብር ስነስርዓት ነው-የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርአያ።
በአንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች ኮሚሽነሩ ከአገር እንደሸሹ ሲወራ ነበር።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


ጄኔራል ባጫ ደበሌ ወደ አዲስ አበባ ሊመጡ ነው

በኬኒያ አምባሳደር በመሆን የስራ ዘመናቸውን ያጠናቀቁት አምባሳደር ጄኔራል ባጫ ደበሌ የክብር ሽኝት ሥነ-ሥርዓት በናይሮቢ ተካሂዷል።
ጄኔራሉ በፌደራል መንግስቱ ለአንድ ከፍተኛ ስልጣን እንደታጩ ታውቋል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


ተጠናቀቀ‼️ደሴ❗ጅማ❗ደብረ ማርቆስ❗
ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ፣ ጅማ፣ ደብረ ማርቆስ እና ነቀምቴ የሚዘልቁ የፍጥነት መንገዶች የአዋጭነት ጥናት ተጠናቀቀ።

የኢትዮጵያ የመንገድ መረብ ባለፉት 8 ዓመታት በ53,000 ኪ.ሜ ማደጉን እና በቀጣይ 5 ዓመታት 245,000 ኪ.ሜ ለማድረስ ዕቅድ መያዙን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡

በተጨማሪም በሚቀጥሉት 10 ዓመታት የሀገሪቱን የፍጥነት መንገዶች ርዝመት ወደ 1,600 ኪሎ ሜትር ለማሳደግ ታቅዶ፣ ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ፣ ጅማ፣ ደብረ ማርቆስ እና ነቀምቴ የሚዘልቁ 4 አዳዲስ የፍጥነት መንገዶች የአዋጭነት ጥናት መጠናቀቁንም ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ቁልፍ መረጃዎች፦

🛣 የመንገድ እድገት፦ በ2010 ዓ.ም ከነበረበት 126,773 ኪ.ሜ በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ወደ 180,232 ኪ.ሜ አድጓል፡፡ ባለፉት 8 ዓመታት +53,000 ኪ.ሜ አዲስ መንገድ ተገንብቷል።

🚗 የፍጥነት መንገዶች፦ ከ2010 ዓ.ም በፊት የነበረው ሽፋን 84.7 ኪ.ሜ ብቻ የነበረ ሲሆን፣ የሞጆ-መቂ-ባቱ-አርሲ ነገሌ እና ድሬዳዋ-ደዋሌ አዳዲስ የፍጥነት መንገዶች (+450 ኪ.ሜ.) ተገንብተዋል፡፡

🏗 የፕሮጀክቶች አፈጻጸም፦ ባለፉት 8 ዓመታት 182 ፕሮጀክቶች ወደ ግንባታ የገቡ ሲሆን 71 ግዙፍ ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለትራፊክ ክፍት ሆነዋል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


ውጤት መቼ ይታያል❓

ተማሪዎች ውጤታቸውን ከሰኞ ጠዋት ወይም ማክሰኞ ከሰዓት ጀምሮ መመልከት ይችላሉ።

በውጤታቸው ላይ ቅሬታ የሚኖራቸው ከሆነም 5/6 ቀናት ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ የሚሰጣቸው ይሆናል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


የ2018 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዋና ዋና መረጃዎች‼️

📊 የማለፊያ ውጤት
• 70,544 ተማሪዎች ፈተናውን አልፈዋል።
• ይህም 12.8% የማለፊያ ምጣኔ ነው።
• 565 ትምህርት ቤቶች አንድም ተማሪ ማሳለፍ አልቻሉም።

🏫 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች
• አምና — 62
• ዘንድሮ — 88
➡️ በዚህ ዓመት 26 ትምህርት ቤቶች ጨምረዋል።

💻 በፈተና አሰጣጥ ዘዴ
• በኦንላይን የተፈተኑ — 18.37% አልፈዋል።
• በወረቀት የተፈተኑ — 4.2% አልፈዋል።

🏆 የክልሎች የማለፊያ ምጣኔ
🥇 አዲስ አበባ — 32.4%
🥈 ሀረሪ — 22.76%
🥉 አማራ — 15%
• ድሬዳዋ — 11.92%
• ትግራይ — 11.2%
• ጉምዝ — 10.53%
• ደቡብ — 9.2%
• ሶማሌ — 9%
• ሲዳማ — 6.95%
• ጉምዝ — 6.1%
• ደቡብ ኢትዮጵያ — 4.2%
• 3.74% — የክልሉ ስም አልተጠቀሰም።

🎯 ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ
• 591/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ወንድ — ኦዳ ትምህርት ቤት
• 583/600 — ተፈጥሮ ሳይንስ፣ ሴት — አገው ምድር ትምህርት ቤት
• 576.25/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ወንድ — ዶዶላ ኢፋ ቦሩ ትምህርት ቤት
• 569/600 — ማህበራዊ ሳይንስ፣ ሴት

📌 በአጠቃላይ፦ የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የማለፊያ ምጣኔ 12.8% ሲሆን፣ አዲስ አበባ 32.4% በማስመዝገብ ከፍተኛውን የክልል ደረጃ ይዟል። በተጨማሪም 100% ያሳለፉ ትምህርት ቤቶች ከ62 ወደ 88 ከፍ ብለዋል።
" ዘንድሮ ካለፉት ዓመታት ውጤት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ተማሪ ቁጥር ያለፈ በመሆኑ የምንቀበለው የሬሚዲያል ተማሪ ቁጥር ይቀንሳል። ስንት ይሆናል የሚለውን በተመለከተ ግን መቁረጫ ነጥቡ ወደፊት የሚገለጽ ይሆናል።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23


ከፍተኛ ውጤት !

በተፈጥሮ ሳይንስ ወንድ 591.6 ከ600 ተመዝግቧል። ተማሪው የኦዳ ስፔሻል ቦርዲንግ - አዳማ ተማሪ ነው።

ከሴት ደግሞ 583 ከ600 ሲሆን ከእንጅባራ አገው ምድር ትምህርት ቤት ነው።

https://t.me/Ethio_Zena23
https://t.me/Ethio_Zena23

20 last posts shown.