"ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ" የተሰኘ የታሪክ መጸሓፍ ተመረቀ
****
የቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ "ሕይወቴና የኢትዮጵያ እርምጃ" የተሰኘ የታሪክ መጽሓፍ ተመረቀ።
መጽሐፉ በአማርኛ ቋንቋ ስለቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ የህይወትና የኢትዮጵያ የታሪክ ውጣ ውረዶችን የሚያትት ሲሆን በዛሬው ዕለት በአዲስ አበባ ዋቢ ሸበሌ ሆቴል ለምረቃ በቅቷል።
በመፅሐፍ ምረቃው ላይ ጥሪ የተደረገላቸው ታዋቂ ግለሰቦች፣ ተጋባዥ እንግዶች እንዲሁም የተለያዩ የሚዲያ ተቋማት ተገኝቷል።
የቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ፋውንዴሽን ሥራ አስፈጻሚ አቶ ንጉሴ አምቦ በመርሃ ግብሩ እንደተናገሩት፣ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር ፀንታ እንድትቆም ልጆቿና ንጉሰ ነገስቷዋ የተጓዙበትን ረጅም መንገድና የከፈሉትን መስዋዕትነት የሚዘክር ታላቅ መጽሐፍ ነው።
የመጽሐፉ ሽያጭ ለቀዳማዊ ዐፄ ኃይለ ሥላሴ መታሰቢያ ፋውንዴሽን ገቢ የሚውል ነው ተብሏል። የመጽሐፉ ሽያጭ በፋውንዴሽኑ አማካኝነት በመላ ሀገሪቱ በሁሉም መጽሐፍት መሸጫ መግዛት እንደሚቻል ገልጸዋል።
በቀጣይም ቅጽ ሁለት እንደሚታተም ተናግረዋል።
©ኢ ፕ ድ
መጻሕፍት መደብር
አድራሻ፦ ቁ.1 አ.አ ስታድየም ናሽናል ታዎር
ቁ.2. ሜክሲኮ ደብረ ወርቅ ታዎር
ስ.ቁ. 2519 11 00 6705