✍️ጥር 18 - ቅዱስ ጊዮርጊስ
ዝርዎተ አጽሙ
"ያ ከሃዲ ንጉስ ዱድያኖስ ግንድ አምጥተው ቅዱስ ጊዮርጊስን በግንድ ላይ እንዲቸነክሩት አዘዘ፤ በላዩም ላይ ሰም አፍስሰው እሳት እንዲያነዱበት አደረገ ፤ ከዚህም በኃላ እንደ መጭመቂያ ሆኖ ከተሰራ የስቃይ መሳሪያ ላይ አወጡት ሰውነቱን እንዲሰነጥቁት እንዲጨምቁት አዘዘ፤ አንጀቱ ሁሉ ወጥቶ ከምድር ላይ እስኪዘረገፍ ድረስ እንዲሁ አደረጉበት ነፍሱ ከስጋው ተለየች የሰማዕቱን ሥጋ አቃጠሉት፤ ፈጩት አመድም ሆነ በቀፎ አድርገው ይድራስ ወደሚባል ተራራ ላይ በነፋስ ዘሩት።
ደብረ ይድራስ ማለት ምድረ በዳ ነው ወታደሮቹ የታዘዙትን ፈጽመው ተመለሱ። ያንጊዜም መብረቅ ነጎድጓድ ታላቅ ንውጽውጽታ ሆነ ምድርም ከመሰረቷ እስክትናወጽ ድረስ ከሰማይ ድምጽ ተሰማ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መላእክትን አስከትሎ በብሩህ ደመና ወረደ በተራራውም ላይ ተቀመጠ አራቱን የምድር ነፋሳት የሰማዕቱን ሥጋ እንዲሰበሰቡ አዘዛቸው። ከሞትም አስነሳው ኃይሉን አሳደረበት ባርኮትም ወደ ሰማይ አረገ።
ከዚህ በኋላ ቅዱስ ጊዮርጊስ እየሮጠ ወታደሮቹን ተከተላቸው ወንድሞቼ ቆዩኝ ከናንተ ጋር ልሂድ እያለ ተጣራ የነዚህ የወታደሮች ቁጥር አራት ነው ስማቸው ህልቶን፣ አግሎሲስ፣ ሶሪስና አስፎሪስ ነው፣ ይህንን ታላቅ ተአምራት አይተው አምነዋል፣ በኋላም በሰማዕትነት ሞተዋል፡፡
ይህ የሆነው ጥር 18 በዛሬዋ ቀን ነው ይህንንም ቀን "ዝርዎተ አጽሙ " ስትል ቤተክርስቲያን ሰማዕቱን አዘክራ ትውላለች፤ በስሙ በታነጹለት አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ታቦተ ህጉ ውጥቶ በደማቁ ተከብሮ ይውላል።
(ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ ምዕራፍ 6 ፤ 15 - 18)
ከሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ረድኤት በረከት ይክፈለን።
ከዲያቆን ዘማርያም ቴሌግራም ገጽ የተወሰደ።