Ethiopian university Students


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: Education


ኢትዮጵያ ዉስጥ ስለሚገኙ ሁሉም ዩኒቨርሲቲወች እና ኮሌጆች ትክክለኛ መረጃወችን የምታገኙበት ቻናል ነው!!! You tube channel 👇
https://youtube.com/@temari_podcast?si=hKrtNc5CAe7NwS2I

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
Education
Statistics
Posts filter




#AdigratUniversity

በ2017 የትምህርት ዘመን ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የመግቢያ ቀናት ጥር 1 እና 2/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ወደ ዩኒቨርሲቲው ስትሔዱ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የወሰዳቹበት ማስራጃዎች፣ ፎቶግራፍ፣ የመኝታ አልባሳት እና የስፖርት ትጥቅ መያዝ እንደሚገባችሁ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡


@EthiopianUniversitystudents1


#WolloUniversity

በ2017 ዓ.ም ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለሪሚዲያል ፕሮግራም የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

የምዝገባ ቦታ፦
- የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ደሴ ግቢ፣
- የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ኮምቦልቻ ግቢ።

(የዩኒቨርሲቲው መልዕክት ከላይ ተያይዟል።)

@EthiopianUniversitystudents1


#BongaUniversity

ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ የ PhD ፕሮግራም መስጠት ጀምሯል፡፡

በዩኒቨርሲቲው PhD in Coffee Science የመጀመሪያ ቀን ትምህርት የመጀመሪያ Class በዛሬው ዕለት ተጀምሯል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በኢትዮጵያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ታሪክ በቡና ሳይንስ የ PhD ፕሮግራም በመጀመር ቀዳሚው ዩኒቨርሲቲ ሆኗል።

በቡና ሳይንስ የትምህርት መስክ በመጀመሪያ ዲግሪ ፕሮግራም ለመጀመሪያ ጊዜ ያሰለጠናቸው 34 ተማሪዎች ባለፈው ሰኔ ያስመረቀው ዩኒቨርሲቲው፤ በመስኩ በማስተርስ መርሐግብር ተማሪዎችን በማሰልጠንም ላይ ይገኛል።

@EthiopianUniversitystudents1


reading plan for Freshman course.pdf
103.1Kb
📘ለ2017 ሪሜዲያል ፈተና የሚሆን ምርጥ የጥናት ፕሮግራም አዘጋጀን!!!

ስለአተጋገበሩ ሙሉ መረጃ ለማየት ይህን video ተመልከቱ 👉
https://youtu.be/ahSCSmL4uyA

🎯JOIN US 👇👇

https://t.me/Freshman_tricks
https://t.me/Freshman_tricks






ዛሬ December 22 አለም አቀፍ የአጭር ሰዎች ቀን ነው።

አጭር ቁመት ያላቸው ከእንደ ማህተመ ጋንዲ ካሉ ታዋቂ መሪዎች እስከ ሲሞን ቢልስ ያሉ ታዋቂ አትሌቶች ታላቅነት በቁመት እንደማይለካ የሚያረጋግጡልን ምሳሌዎቻችን ናቸው።

ይህን ለአጭር ጓደኞቻችሁ አካፍሉ እና ምን ያህል ኃያላን እንደሆኑ አስታውሷቸው።



@EthiopianUniversitystudents1


#Wolaita_Sodo_University

በ2017 የትምህርት ዘመን አዲስ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች በሙሉ፡-

በ2017 የትምህርት ዘመን ከኢ. ፌ. ዴ. ሪ. ትምህርት ሚኒስቴር አዲስ ወደ ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች የ2017 የትምህርት ዘመን መግቢያ ቀን ታህሳስ 20 እና 21/2017 ዓ.ም መሆኑን እናስታዉቃለን፡፡

👉 ማሳሰቢያ 1

1.ምዝገባ (በአካል ቀርበው) ታህሳስ 21 እና 22 ቀን 2017 ዓ.ም
2.አጠቃላይ ገለፃ (orientation) ታህሳስ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
3.ትምህርት የሚጀመረው ታህሳስ 24 ቀን 2017 ዓ.ም መሆኑን እንገልፃለን፡፡

👉 ማሳሰቢያ 2

ሁሉም ተማሪዎች ሲመጡ፡-
1.የ8ኛ ክፍል ሰርተፍኬት (ዋናው እና ኮፒው)
2.ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕትና የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ኦርጂናልና የማይመለስ ሁለት ኮፒ
3.አንሶላ፣ የትራስ ጨርቅ እና የስፖርት ትጥቅ በመያዝ መምጣት ይጠበቅባቸዋል።

👉 ማሳሰቢያ 3
ከA አልፋበት አስከ Z ድረስ የስማችሁን የመጀመሪያ ፊደል በማየት በተፈጥሮም ሆነ በማህበራዊ ሳይንስ የተመደባችሁበትን ካምፓስ ከምስሉ በመለየት እንድትመዘገቡ፣ ገለፃ ላይ እንድትሳተፉ እና ትምህርት እንድትጀምሩ ዩኒቨርሲው ያሳስባል፡፡

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣ ተማሪን ዩኒቨርሲቲው አያስተናግድም፡፡

👉 የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራር ጽ/ቤት

@EthiopianUniversitystudents1


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
የማይሰማ የለም

“አስደናሽ” ወረርሽኝ


በኡጋዳ ምንነቱ ያልታወቀ እና ሴቶችን ብቻ ላይቶ የሚያጠቃ “የሚያስደንስ ወረርሽኝ” መከሰቱ ተሰምቷል። ኡጋንዳውያን “ዲንጋ ዲንጋ” እንደ ዳንስ መንቀሳቀስ ሲሉ የሰየሙት ወረርሽኙ እስካሁን በ300 ሴቶች ላይ መከሰቱንም የጤና ባለሙያዎች ተናግረዋል።

ወረርሽኙ ቡንዲቡግዮ በተባለ አካባቢ የተከሰተ ሲሆን፤ ከፍተኛ ትኩሳት እና መራመድ አለመቻልም የበሽታው ምልክቶች መሆናቸውን የጤና ዘርፍ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር ኬይ ክርቶፈር ገልጸዋል።

@EthiopianUniversitystudents1


🎯በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

📘 ጎንደር ዩኒቨርሲቲ - የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ ቀናት  ጥር 01 እና 02/2017 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል። የምዝገባ ቦታለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ መሆኑንም ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳውቋል።

📘 ቦረና ዩኒቨርሲቲ - በ2017 ዓ.ም ወደ ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 22 23/2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ብቻ በመሆነ· በተባለዉ ቀን ቦረና ዩኒቨርሲቲ ግቢ ዉስጥ በመገኘት ምዝገባ እንድታካሄዱ ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

📘 ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ - በ2017 ዓ.ም ወደ ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም ሲሆን የማመልከቻ ቀን ጥር 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡


For general knowledge 👇

በ 2024 በአፍሪካ ትልቅ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገሮች

@AFRIFLAME
@AFRIFLAME


#BorenaUniversity

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም ወደ ቦረና ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 22 23/2017 ዓ.ም ለተከታታይ ሁለት ቀናት ብቻ በመሆነ· በተባለዉ ቀን ቦረና ዩኒቨርሲቲ ግቢ ዉስጥ በመገኘት ምዝገባ እንድታካሄዱ ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

@EthiopianUniversitystudents1


#DiredawaUniversity

የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ

በ2017 ዓ.ም ወደ ድሬ ደዋ ዩኒቨርሲቲ በሪሜዲያል ፕሮግራም ትምህርታችሁን እንድትከታተሉ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ጥር 3 እና 4/2017 ዓ.ም ሲሆን የማመልከቻ ቀን ጥር 5/2017 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲዉ ያሳዉቃል፡፡

@EthiopianUniversitystudents1


#UniversityofGonder

በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ተፈትነው በአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ለመከታተል ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ ተማሪዎች የማመልከቻ ቀናት 👉 ጥር 01 እና 02/2017 ዓ.ም. መሆኑን አሳውቋል።


የምዝገባ ቦታ፡- ለማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች ማራኪ ግቢ እና ለተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ ተማሪዎች አጼ ፋሲል ግቢ መሆኑንም ዩንቨርሲቲው ጨምሮ አሳውቋል።

@EthiopianUniversitystudents1






የራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎች የምግብ ወጪ መጋራት በሦስት ዓይነት አሠራሮች እንደሚተገበር ተገለፀ፡፡

በመንግሥት ምደባ በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ አገልግሎት ተጠቃሚ ከሆኑ የወጪ መጋራት ግዴታ እንደሚመለከታቸው በትምህርት ሚኒስቴር ከፍተኛ ትምህርት ዘርፍ የአስተዳደር ጉዳዮች ኃላፊ አብዱ ናስር ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

በራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲዎች ሦስት ዓይነት ተማሪዎች እንደሚገኙ የገለፁት ኃላፊው፤ ሙሉ ለሙሉ ክፍያቸውን የሚችሉ፣ ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እና የወጪ መጋራት የሚመለከታቸው መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የተማሪዎች ዝቅተኛው የትምህርት ቆይታ ጊዜ አራት ዓመት ሲሆን፣ በዚህ ጊዜ ውስጥ የአንድ ተማሪ የምግብ ወጪ መጋራት ሲሰላ 120,000 ብር እንደሚሆንና የሰባት ዓመት ቆይታ ያለው የሕክምና ትምህርት ደግሞ 210,000 ብር እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

የተማሪዎች የምግብ ወጪ መጋራት ተመን በየትምህርት ዘርፍ የዋጋ ልዩነት ያለው ሲሆን፤ ይህም በተማሪዎች የትምህርት ፕሮግራም ቆይታ ስሌት መሠረት እንደሚሆን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡

ራስ ገዙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘንድሮ 5,000 ተማሪዎች የተቀበለ ሲሆን፤ 2,500 በራሳቸው ከፍለው የሚማሩና ወጪ መጋራቱ የማይመለከታቸው ናቸው፡፡ የተቀሩት 2,500 ተማሪዎች ደግሞ መደበኛው የመንግሥት ወጪ መጋራት የማይከመለታቸው ሲሆኑ፤ ከእነዚህ ውስጥ ዩኒቨርሲቲው ወጪያቸውን የሚሸፍንላቸው እንዳሉ አስረድተዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ዕለታዊ የምግብ ወጪ ተመን ከታህሳስ 1/2017 ዓ.ም ጀምሮ 100 ብር እንዲሆን ተወስኗል። ትምህርት ሚኒስቴር ወጥ የሆነ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የምግብ ሜኑ በማዘጋጀት ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች መላኩም ይታወቃል፡፡ #ሪፖርተር

@EthiopianUniversitystudents1


#BahirDarUniversity

በ2017 ዓ.ም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ ከጥር 5-7/2017 ዓ.ም በዩኒቨርሲቲው ግሽ አባይ ግቢ እንደሚከናወን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ አራት 3x4 ጉርድ ፎቶግራፍ፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ ትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ።

@EthiopianUniversitystudents1


ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ2017 ዓ.ም ወደተቋሙ ለተመደቡ የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ጥሪ አላደረገም።

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ገጾች እየተዘዋወረ የሚገኘው ዩኒቨርሲቲው ጥሪ እንዳደረገ የሚገልፅ የጥሪ መልዕክት ስህተት መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

የ2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች የምዝገባ ጊዜ ወደፊት ይገለፃል ተብሏል፡፡

@EthiopianUniversitystudents1

20 last posts shown.