የኢትዮ ፅንፈኛ ሙስሊሞች እፎይ የተሰኘው ወንድማችን ላይ ዘመቻ ከፍተዋል። ነፍሱን ለማጥፋት በየ ሚድያው ቅስቀሳ እያደረጉ ነው። ከትላንት ወዲያ ተሰብስበው ጥቃት ሊያደርሱበት ሞክረው ነበር። አንደኛ ነገር:- ኢትዮጵያ በሸሪአ ሕግ የምትተዳደር ሀገር አይደለችም። ሃይማኖት ላይ ጥያቄ አነሳ በሚል አንድን ሰው ተጠያቂ የሚያደርግ ሕግ የለንም። ሁለተኛ:- ልጁ ራሱ ጥፋተኛ ቢሆን በደቦ ፍርድ ጥቃት እንዲደርስበት መቀስቀስ በሕግ የሚያስጠይቅ ወንጀል ነው። ጥፋተኛን የሚቀጣ መንግሥት ባለበት ሀገር ከሕጋዊ ሂደት ውጪ አንድ ግለሰብ ላይ ጥቃት እንዲፈፀም መቀስቀስ ተጠያቂነትን ያስከትላል። ሦስተኛ:- ክርስትናን እንደ ልባቸው ሲሳደቡና ሲያንጓጥጡ የኖሩት የሀገራችን ሙስሊም ሰባኪያን በምን አንደበታቸው ሃይማኖታቸው እንደ ተነካ ስሞታ ሊያቀርቡ እንደሚችሉ ማሰብ ያዳግታል። የሰው ሃይማኖት መንቀፍ ጥፋት ከሆነ የመጀመሪያዎቹ ተጠያቂዎች እነርሱ ናቸው። የሆነው ሆኖ ይህ ወጣት እምነቱን ከመከላከል ውጪ ምንም ዓይነት ጥፋት አልፈፀመም። በእስላማዊ መጻሕፍት ውስጥ ያልተጻፈ ምንም ነገር ተናግሮ አያውቅም። ተናግሯል የሚል ሰው ካለ እስኪ አንዲት ነጥብቅ ይጥቀስ። ችግሩ እስላማዊ መጻሕፍት ሲገለጡ ብዙ አሸማቃቂ ጉዶችን የተሸከሙ በመሆናቸው ሳብያ ያለ ምንም ተጨማሪ ማብራርያ እንኳ የገዛ መጻሕፍታቸን ማንበብ ብቻውን በብዙ ሙስሊሞች ዘንድ እንደ ስድብ መቆጠሩ ነው። ሙስሊሞች ሃይማኖታቸው እንዲከበርላቸው ከፈለጉ አንደኛ:- የገዛ ነቢያቸውን የሚያንቋሽሹትን እነዚህን መጻሕፍት ሰብስቦ ማቃጠል፤ ሁለተኛ:- የሰው ሃይማኖት ሳይነኩ ዝም ብሎ መቀመጥ ያዋጣቸዋል። ችግሩ እዚያው እነርሱ ጋር በሆነበት ሁኔታ ሌላውን መወንጀል መፍትሄ አይደለም። ደግሞ ድሮ ድሮ ክርስቲያኖች እስልምናን ሳይጠቅሱ የራሳቸውን ሕይወት ሲኖሩ በነበሩባቸው ዘመናት ክርስትናን ሲሰድቡና ሲተቹ ኖረው መልስ ሲመለስላቸው ማለቃቀስ ምን የሚሉት ነው? ልጁ ዋሽቶ ከሆነ በአደባባይ ውይይት ገጥሞ ማሸነፍ፣ ያንን ማድረግ ከፈሩ ደግሞ በቪድዮ መልስ መስጠት። ሁለቱንም ማድረግ ካልቻሉ ሽንፈትን አምኖ መቀመጥ እንጂ የሰው ደም ለማፍሰስ መሯሯጥ የሃይማኖታቸውን ሐሰተኝነት ከመግለጥ የዘለለ ፋይዳ የለውም።