ስላሴ ክፍል_(#ሁለት)
፨ በእግዚአብሔር መጽሐፍ ፈልጉ አንብቡም፤ አፌ አዝዞአልና፥ ኢሳ 34 ፡16፨
#መለኮታዊ #ባህርያት (Divine Essenc )
መለኮታዊ ባህርያት ስንል፣ ፍፁም አምላክ ከሆነው ከእግዚአብሔር(አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ) በስተቀር ማንም ፍጡር የሆነ በራሱ ሊኖረው የማይችል የእግዚአብሔር ባህርያት(ችሎታ) ማለት ነው።
መፅሐፍ ቅዱሳችንን በጥንቃቄ ስናጠና፣ እግዚአብሔር አብ፣ እግዚአብሔር ወልድ፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዳቸው እነዚህን ፍፁም መለኮታዊ ባህርያት አሟልተው እናገኛቸዋለን። (ዘፍ 1÷1) (ዮሐ 1÷3 ) ፤ (1ኛ ተሰ 3÷11-13) (ሐዋ 5÷3) (1ኛ ቆሮ 2÷10-11) (ሮሜ 8÷11)
እንግዲህ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሶስት የተለያዩ አካላት (አብ አባት፤ ወልድ ልጅ፤ እና መንፈስ ቅዱስ) መኖራቸውን ግልፅ ሲሆን እነዚህም አካላት ፍፁም መለኮት ለመሆን እነዚህን ባህርያት ሊያሟሉ ይገባቸዋል ማለት ነው።
በሶስቱም አካላት ተመሳሳይ የሆነውን የመለኮት ባህርያት እንዳላቸው አንድ በአንድ እንመለከታለን።
1) #ሁሉን #ማወቅ(Omniscience)፦
ሁሉን ነገር ማወቅ አምላክ ብቻ ሊኖሩት የሚችል ባህርይ ሲሆን፣ ሶስቱም አካላት ይህን የመለኮት ባህርይ ያለ ልዩነት እኩል ያሟላሉ።
#አብ (አባት)፦
ሮሜ 11፡33፤ የእግዚአብሔር ባለ ጠግነትና ጥበብ እውቀቱም እንዴት ጥልቅ ነው፤ ፍርዱ እንዴት የማይመረመር ነው፥ ለመንገዱም ፍለጋ የለውም። (ሮሜ11÷33) (1ኛ ሳሙ 2÷3) (መዝ 139÷1-5)
#ወልድ(ልጅ)፦
ዮሐንስ 16 ፡30፤ ሁሉን እንድታውቅ ማንምም ሊጠይቅህ እንዳትፈልግ አሁን እናውቃለን፤ ስለዚህ ከእግዚአብሔር እንደ ወጣህ እናምናለን፡ አሉት። (ዮሐ 2÷24, 16÷30) (ሉቃ 6÷8)
#መንፈስ ቅዱስ፦
1 ቆሮንቶስ 2 ፡10፤ መንፈስም የእግዚአብሔርን ጥልቅ ነገር ስንኳ ሳይቀር ሁሉን ይመረምራልና ለእኛ እግዚአብሔር በመንፈሱ በኩል ገለጠው። (1ኛ ቆሮ 2÷10)
2) #ሁሉን #ማድረግ #መቻል(Omnipotent)
#አብ (አባት)፦
ኢዮብ 42፡2፤ ሁሉን ታደርግ ዘንድ ቻይ እንደ ሆንህ፥ አሳብህም ይከለከል ዘንድ ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ። (ዘፍ 17÷1) (ኢዮ 42÷2) (ኤር 32÷27)
#ወልድ(ልጅ)፦
ዮሐንስ 1፡3፤ ሁሉ በእርሱ ሆነ ፥ ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም። (ዮሐ 1÷3) (እንዲሁም በመጽሐፍ ውስጥ ያሉ ተዓምራት በሙሉ)
#መንፈስ ቅዱስ፦
ዘካ 4፡6፤ .... በመንፈሴ እንጂ በኃይልና በብርታት አይደለም፥ .... (ሉቃ 1÷35) (ዘካ 4÷6)
3) #በሁሉ #ቦታ #መገኘት(Omniprescence)
#አብ (አባት)፦
ኤርምያስ 23፡23፤ እኔ የቅርብ አምላክ ነኝ እንጂ የሩቅ አምላክ አይደለሁም። (መዝ 139÷7-11) (ኤር 23÷23)
#ወልድ(ልጅ)፦
ማቴዎስ 18፡20፤ ሁለት ወይም ሦስት በስሜ በሚሰበሰቡበት በዚያ በመካከላቸው እሆናለሁና። (ማቴ 28÷20, 18÷20) (ቆላስ 1÷27) (2ኛ ቆሮ 3÷17)
#መንፈስ ቅዱስ፦
መዝሙር 139፡7፤ ከመንፈስህ ወዴት እሄዳለሁ? ከፊትህስ ወዴት እሸሻለሁ? (መዝ (139)÷7)
4 ) #ፈጣሪነት ( Creator )
#አብ (አባት)
ዘፍ 1 ፡1፤ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን ፈጠረ። (ዘፍ 1÷1) (ኢሳ 40÷28, 44÷24)
#ወልድ(ልጅ)፦
ዕብ 1፡10፤ ....... ደግሞ፦ ጌታ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ምድርን መሠረትህ፥ ሰማዮችም የእጆችህ ሥራ ናቸው፤ (ዮሐ 1÷3) (ቆላስ 1÷15-16) (ዕብ 1÷10)
#መንፈስ ቅዱስ፦
ኢዮብ 33 ፡4፤ የእግዚአብሔር መንፈስ ፈጠረኝ፥ ሁሉንም የሚችል የአምላክ እስትንፋስ ሕይወት ሰጠኝ። (ዘፍ 1÷2), (መዝ 104÷30) (ኢዮ 33÷4)
5 #ዘላለማዊነት ( Eternal)
#አብ (አባት)
ኢሳይያስ 41፡4፤ ይህን የሠራና ያደረገ፥ ትውልድንም ከጥንት የጠራ ማን ነው? እኔ እግዚአብሔር፥ ፊተኛው በኋላኞችም ዘንድ የምኖር እኔ ነኝ። (ኢሳ 41÷4, 44÷6) (መዝ 90÷2)
#ወልድ(ልጅ)፦
ራእይ 22፡13፤ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ። (ራዕ 1÷17, 22÷13)
#መንፈስ ቅዱስ፦
ዕብራውያን 9፡14 ......በዘላለም መንፈስ
አንባቢው ልብ ሊለው የሚገባው....የአምላክ ዘላለማዊነት ከፍጥረት የሚለየው እግዚአብሔር ከዘላለም እስከ ዘላለም ( የነበረና የሚነኖር ) ሲሆን ለፈጥረት ሆነ ለሰው ልጆች የተሰጠው ዘለዓለማዊነት ግን ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የሚኖረው የወደፊቱ ዘለዓለም ብቻ መሆኑን ማስተዋል ይገባል።
እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ #አምላካችን እግዚአብሔር #አንድ እግዚአብሔር ነው፤ ዘዳግም 6፡ 4
የመገለጥ እና የጥበብ መንፈስ ለሁላችንም ይብዛ።አሜን
ይቀጥላል 👇👇