ከአድናቆት የምናገኘው ትምህርት ..🤔
ከአድካሚ ውሎ በኋላ አንድ ቀን ምሽት ላይ እናቴ ለቤተሰቡ እራት አዘጋጀች። ለአባቴ በጣም ያረረ ዳቦ የተጠበሰ እንቁላል እና ሰላጣ አቅርባለት ነበር ። የቀለበውን ምግብ ስለመለከት ትኩረቴን ወዲያውኑ ወደ ዳቦው አረፈ። አባቴ ሐዘን፣ ንዴት ወይም የብስጭት ስሜት ይሰማዋል ብዬ በማሰብ እራሴን አዘጋጀሁ።
የሚገርመው ግን ፈገግ ብሎ መብላት ጀመረ። እንቁላሉን በዳቦው ውስጥ በደስታ እየጠቀለለ ስለ ውሏችን ይጠይቀንና ያጫውተን ጀመር።
እናቴ ስላረረው ዳቦ ይቅርታ ስትጠይቅ አባቴ የሰጠውን ሞቅ ያለ ምላሽ ግን ሁልጊዜ አስታውሰዋለሁ- "ውዴ፣ ፍጹም ደህና ነው። የምወደው ዳቦ እንዲህ ሲያር ነው።"
የዚያን ዕለት ምሽት አልጋ ላይ ተኝቼ ሳለ አባቴ ሊይናግረኝ መጣ። የማወቅ ጉጉት ስላደረብኝ ስለ ዳቦው የተናገረው ነገር እውነት መሆኑን ጠየቅሁት ። እቅፍ አድርጎ ከጎተተኝ በኋላ እንዲህ አለኝ- "እናትህ ረጅም፣ አድካሚ ቀን አሳልፋለች፣ ነገር ግን ለኛ ምግብ ለማዘጋጀት ድካሟ አላገዳትም። ያረረ ዳቦ መብላት እሷ ካሳየችው ፍቅርና ጥረት ጋር ሲወዳደር እዚህ ግባ የሚባል አይደለም።"
በዚያች ቅጽበት፣ ስለ ምስጋና እና በትንሽ ነገሮች ውስጥ ያለውን ውበት ስለማየት ጠቃሚ ትምህርት ተማርኩኝ።
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@eyetaye12