እግዚአብሔር ልጅ አንተ ነህ፣በመስቀልና በትንሣኤ ተስፋን የሰጠኽን የእግዚአብሔርና የሰው ልጅ አንተ ነህ።
እኔስ ከሊቁ ከቅዱስ አባ ጊወርጊስ ዘጋስጫ ጋር ሁኜ እንድህ እላለሁ
በአምላኩ ደም የተቀደሰ ከፈጣሪው ጎን በወጣ ውኃ የተጠመቀ ዕፅ እንዴት ያለ ነው !
ለገነት ዛፎች አክሊል ለገዳም ዛፎችም ክብር የሆናቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው !
ለአሸናፊ እግዚአብሔር በግ መሠዊያ የሆነው ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
ለእሥራኤል አምላክ የፋሲካው መሠዊያ የሆነ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
የጎልጎታዊው የምሥጢር ወይን ማፍለቂያ የሆን ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
ከእርሱ ምእመናንን ለማተም የሚሆን የሕግና የሥርዓት ደምን ያንጠባጠበ ዕፅ ምን ዓይነት ነው!
ብሩካን በጎችን ለማጠቢያ የሚሆን ምንጭን ያወጣ ዕፅ ምን ዓይነት ነው !
ምድርን የቀደሳት ሰማይንም ያማተበበት ዓለምንም ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ በረከት የባረከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
ሰማያውያንን ከምድራውያን ያስተባበራቸው ዕፅ እንዴት ያለ ነው !
አዳምን ከስሕተት ያዳነው ሔዋንን ከሞት ጻዕረኛነት ነጻ ያወጣት ዕፅ እንዴት ያለ ነው !
ስለእርሱ አስቀድሞ በኦሪትና በነቢያት የተነገረየሰበሰባቸው በሐዋርያትም በገሐድ የተሰበከ ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
የተከተሉትን የበተናቸው ያመኑትንም ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
ቤቴ ክርስቲያንን በኢየሱስ ክርስቶስ ሃይማኖት ላይ የመሠረታት ዕፅ እንዴት ያለ ነው!
አልጫውን ያጣፈጠ ርኩሱንም ያነጻ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
ድኻውን ከፍ ከፍ ያደረገ በደለኛውን ያጸደቀ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
ደካማን ያበረታ ሕመምተኛውንም ያዳነ ዕፅ እንደምን ያለ ነው !
ጥቂቱን ያበዛ ሰነፉንም ጥበበኛ ያደረገ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
መካኗን ወላድ ያደረገ ጨለማውን ያበራ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
የዓለም ሁሉ መመኪያ የሆነ ዕፅ እንደምን ያለ ነው!
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር
@felgehaggnew@felgehaggnew