‹‹በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ በግልጽ ሲዋጋን የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነበር››
‹‹አግበራ በምትባል አውራጃ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የታጸች አንዲት ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ በድላይ የተባለ አንድ አረማዊ ገዥ ወደ እርሷ በደረሰ ጊዜ ወደ ቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጥ በአመጽ ገብቶ ከሚስቱ ጋር ከሴሰነ በኋላ በእሳት አቃጠላት፡፡ ዳግማዊ ቆስጠንጢኖስ የተባለ ንጉሣችን ዘርዐ ያዕቆብም ይህን በሰማ ጊዜ በሰማዕቱ፣ በእመቤታችንና በተወዳጅ ልጇ ኃይል ይህን አረመኔ በድላይን ለመውጋት ተዘጋጀ፡፡
ከሃዲው በድላይም በበኩሉ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብን ለመውጋት ተነሣ፡፡ ውጊያውንም ለመጀመር በተነሡ ጊዜ በነጭ ፈረስ ላይ የተቀመጠ ፈረሰኛ ሰው በበድላይ የጦር ሠራዊት ውስጥ ታየ፡፡ ከኋላ ሆኖ ይነዳቸዋል፣ በሌላ ጊዜም ከፊት ሆኖ ይመራቸው ነበር፡፡ ከንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብ አጠገብ ባደረሳቸው ጊዜ ግን ያ ነጭ ፈረሰኛ ከበድላ ሠራዊት ተለይቶ የበድላይን ጦር ለመውጋት ከንጉሣችን ዘርዐ ያዕቆብ ሠራዊት ጋራ ተቀላቀለ፡፡ በክርስቲያኖቹና በአረማውያኑ መካከል ጦርነቱ በበረታ ጊዜ አረማውያኑ ተሸነፉ፡፡ አለቃቸው በድላይም በጦርነቱ መካከል በጦር ተወግቶ ወድቆ ሞተ፡፡
በድላይም ክፉ አሟሟት ሲሞት ባዩት ጊዜ ከሠራዊቱም መካከል ብዙዎቹ ‹‹በድላይ ከልቡ ትዕቢት የተነሣ ክፉ አሟሟት ሞተ፣ እግዚአብሔር ለእሥራኤል ይዋጋለቸው ነበርና በንጉሥ ሕዝቅያስ ዘመን ሰናክሬም እንደተዋረደ፣ በዮዲትም ዘመን ሆሎፎርኒስ እንደተዋረደ በድላይም ዛሬ ክፉኛ ተዋረደ›› ተባባሉ፡፡ ንጉሥ ዘርዐ ያዕቆብም በእመቤታችንና በሰማዕቱ በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የአረማውያንን ሬሣ ምድርን እስኪሸፍናት ድረስ በጦርነቱ አሸናፊ ሆነ፡፡ የሞቱትና ተማረኩትም ብዛታቸው በቁጥር አይታወቅም ነበር፡፡ ዘመናዊ የሆኑት የጦር መሣሪያዎቻቸውም እጅግ ብዙ ነበሩ፡፡ ራሱ ንጉሡ በድርሳኑ እንደገለጸው ‹‹ወደ ቤተ መግሥቴ የገባው የራሳቸው የሰዎቹና የፈረሶቻቸው ጌጥ በያይነቱ ሊናገሩት የማይቻል እጅግ አስደናቂ ነበር›› አለ፡፡ ሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስም አረማውያንን ስለመውጋቱ አረማውያኑ ራሳቸው ሲመሰክሩ ‹‹በነጭ ፈረስ ላይ ተቀምጦ በግልጽ ሲዋጋን የነበረው ቅዱስ ጊዮርጊስ ነበር›› አሉ፡፡ ክርስቲያኖቹም ‹‹ሰማዕቱ እረዳን›› በማለት ተደሰቱ፡፡
በዚያም የጦርነቱ ቀን ሌሊቱን ቅዱስ ጊዮርጊስ በስሙ በታነጸች ወደ አንዲት ሌላ ቤተ ክርስቲያን ሄደና የጦር መሣሪያ በታጠቀ አርበኛ ወይም ወታደር ተመስሎ ለአንድ ቄስ ተገለጠለት፡፡ ጦሩን በእጁ ይዟል፣ ፈረሱም በጣም አልቦት ነበር፡፡ የጦር መሣሪያ በታጠቀ አርበኛ አምሳል ለቄሱ የተገለጠለትም ‹‹ዛሬ ከበድላይ ጋር ጦርነት ውዬ መጣሁ›› አለው፡፡ ስለዚህም እኛ የክርስቶስ ወገኖች የቅዱስ ጊዮርጊስን የተአምራቱን ማረጋገጫ ምስክር ከራሱ አገኘን፡፡ የቅዱስ ጊዮርጊስ ጸሎቱ በረከቱ የረድኤቱም ሀብት የተዋሕዶ ልጆች የሆንን ሁላችን ይጠብቀን፡፡››
የዓሥራት ሀገሩን ቅድስት ኢትዮጵያን ከዘመኑ ጠላቷቿና ከሰፈሩባት የሰይጣን ልጆች ይጠብቅልን!!!
✞ ✞ ✞
(ምንጭ፡- የተስፋ ገብረሥላሴ እትም ገድለ ቅዱስ ጊዮርጊስ-ተስፋ ገብረ ሥላሴ፣ 1991 ዓ.ም)