💕 ፍቅርን በቃላት 💕


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


💞 ፍቅርን በቃላት 💞
♥️ይኼ ነው ለእኔ ፍቅር💟 ማለት፤
|➣ ያለምላሽ ወዶ መገኘት፤
|➣ በንጹህ ልብ ጠልቆ መዋኘት፤
|➣ ይኼ ነው ለእኔ ፍቅር ማለት💟
💝የፍቅር ቃላት ሁሌም አሸናፊ ናቸው💝
ለማስታወቂያ ሥራ ➢ @Naolviva
ғᴏʀ sᴘᴀᴍ 👇
@fkrn_be_kalat_bot
ᴇʏᴏʙ ᴍᴇᴋᴏɴɴᴇɴ 👇
@eyoba_king_of_reggaee

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter




ብለው ክፉኛ ቲያለቅሱ እኔና ተዋቡም በተቀመጥንበት መነፋረቅ ዠመርን።
ለቅሶአቸውን ጋብ አርገው•••
እናም ልጆቼ ተዛን ግዜ ጀምሮ የማውቃቸውም የማላውቃቸውም ባልና ሚስቶይ ተጣሉ ሲባል ውስጤ ይታመማል!። እረበሻለሁ!። እፈራለሁ!።
ክፋ ያለው እንኳን የምድሩን ሰው የላይኛችንም ከፋፍሎ ከመውደድ እንደማይመለስ አውቃለሁ።
እኔ ግን ክፉ ሆኜ አይደለም! አንተን ጠልቼ ልጄን ብወዳት አልጠቅማትም እሄን ጠንቅቄ አውቃለሁ።
ልጆቼ ተውቡ አንዳርጌ•••
ሰሞኑን እዚህ ቤት ውስጥ እናንተን የማያስደስት ውሳኔ የወሰንሁት እሄ ፍርሀቴ በፈጠረብይ መጥፎ ስሜት መሆኑን ተረድታችሁ ይቅር በሉይ።
መሀላችሁ በመግባት ብገፋችሁም ክፉ ካፋችሁ ሳይወጣ እክብራችሁ ትዛዜን ተቀብላኋልና እናንተም በልጆቻችሁ የተከበራችሁ ሁኑ ፣ ተከበሩ ! ፈጣሪ ያክብራችሁ!።
ልጆቼ እዚህ በቆየሁባቸው ቀኖች በብዙ መንገድ በመሀላችሁ ያለውን ጥልቅ ፍቅር መረዳት ችያለሁ።
ያ ክፉ ቀን የፈጠረብኝ ህመም እድሜዬን በሙሉ ሲያባንነኝ ነው የኖረው።
ዛሬም ድረስ ከውስጤ አልጠፋም ሴት ልጆቼ ተባላቸው ተጣሉ ሲባል ሳላውቀው ይቀይረኛል።እፈራለሁ። የህቴ ታሪክ ልጆቼ ላይ እንዳይደገም ስለምሰጋ እይ ክፉ ሆኜ አይደለም ።
ወድጄ አይደለም! ልጆቼ ወድጄ አደለም እያሉ ሲያለቅሱ ምድር ሰማዩ ተደበላለቀብይ።
ተዋቡም ታባቷ ስር ቁጭ ብላ እያለቀሰይ ነው ።
ተፈናጥሬ እግራቸው ስር ተደፋሁ።
"አይገባም የኔ ልጅ !" ብለው ቀና አርገው አቀፉይ ።
ሰውን ክፉ ነው ተማለቴ በፊት ለምን ክፉ ሆነ ብዬ ማሰብ እንዳለብይ የተስተማርሁት ዛሬ ነው ።
እስታሁን ለሆነው ሁሉ ይቅር በሉይ አባቴ የአካሌን ክፋይ፣ ያንድ ልዤን እናት ተዋቡዬን ውብ አለሜን ታሁን ቡሀላ እንኳን የከፋ ነገር ልፈጥምባት በክፉ አይን እንኳን እንደማላያት ቃል አገባሎታለሁ ።
እንደባል ብቻ ታይሆን እንዳባትም ሆኜ አኖራታለሁ ! እኔስ ያለሷ ማን አለኝ !!"
አልኋቸው ።
ግንባሬን ስመው አጥብቀው አቀፉይ!
ተዋቡዬም ተነስታ እኔና አባቷን እቅፍ አረገችን።

•••••••••••••••ተፈፀመ••••••••••••••

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
     @fkrn_be
_kalat
     @fkrn_be_kalat
╚═══❖•
🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴍᴍᴇɴᴛ         
       @fkrn_be_kalat_
bot
     ❥❥________⚘_______❥❥


👩◈ ሚስቴና አባቷ ◈👴🏻

       ክፍል - ዘጠኝ [፱]
የመጨረሻ ክፍል !

   ✍ (በጥላሁን ተስፋዬ)
.
.
.
ይህቺ ጉዷ እማያልቅ አሜሪካን ፎርጅድ ሚሽት ድራለት ነዋ ቲለኝ ግር አለኝ
ፎርጅድ ፎርጅድ ደግሞ ምን ማለት ነው እሱ? ትለው ሳቀብይ••••
ምን ያስቅሀል አንተው አለማወቅ ሀጥያት አይደለ! ባእድ ቋንቋ ቀላቅለህ ትታበቃ እኔ ላይ መሳቅ ምን ይሉታል በል ይልቅ እምታወጋይ ተሆነ ነገሩን እንዲገባይ በራሴ አፍ አውጋይ!'።
አልሁት ባሳሳቁ በሽቄ።ተዛ ቡሀላ ነገሩን እንዲህ ብሎ አጫወተይ•••
ዘመድ አዝማዷን ታይተዋወቅ እዛው አሜሪካን ተወልዳ ያደገች ጥቁር አሜሪካዊት ሴት ያገባል!
ዛድያ ተተጋቡ ቡሀላ እነሱ ዘንድ በመጣው ወንድሟ እና በሷ መሀል ያለውን የመልክ ልዩነት ቲያይ ለየቅል ብቻ ታይሆን ጭራስ ታንድ ማህጠን የወጡም አይመስሉ።
ወንዱሟን ቲያው ዝንጀሮ ቆሞ እምሄድ እይ ሰው ትለመሆኑ የሚያጠራጥር ሆኖ ሳለ እሷ ልቅም ያለይ ቆንጆ ነይ።
ታድያ ሁለቱ አጠገብ ላጠገብ ቁጭ ብለው ባያቸው ቁጥር እንዲሁ ቲያስገርመው!።
መገረም ብቻ አይደለም ቲያስደምመው!።
መደመምም ብቻ አይደለም አንዳንዴ እንደውም ቲያስደነግጠው ይቆይልሀል።
ማንን እንደሚጠይቅ ማንን እንደሚያማክር ግራ እንደተጋባ።
በዚህ መሀል አርግዛ ትወልዳለይ። ዛድያ ህጣኑ አደግ ቲል ወንድሟን መስሎ እርፍ።
ታክስቴ ልዥም ተሚሽቱም ምንም ያልወሰደ ጓጉንቸር ሆኖ ቁጭ።
የልዡ እና የወንድሟ መልክ መመሳሰል ውስጥ ውስጡን እየከነከነውም ቢሆን
ፈጣሪ የሰጠውን ልዥ በጠጋ ተቀብሎ ማሳደጉን ቀጠለ።
ያክስቴ ልጅ ለወንድሙ እንደነገረው ተሆነ•••
በመሀል ወንድማ የሚጠቀምበትን "ላብ ቶብ "ለብቶም"
የሚሉት "ኮምፒተሩን " ባጋጣሚ ክፍት ሆኖ አግኝቶት ኖራል ውስጥ ገብቶ ሲበረብር ተአመታት በፊት ሚሽቱ ተወንድማም፣ ተቤተሰቧም፣ ብቻዋንም የተነሳያቸውን ትክክለኛውን የቀድሞ መልኳን የየዙ ፎቶዋን ያያል! ክው አለ።
ያኔ በተፈጥሮ ተፈጣሪ የታደለይውን መልክ ዘመን አመጣሽ በሆነ "ቴክኖሎጂ" "የብላስቲካ ሴርጀሪ" ነው እሚባል ያለይ መሰል ብቻ በሱ ቴክኖሎጂ ገፅታዋን ሙሉ በሙሉ እንደቀየረይ ይደርስበታል።
ዝናቡ የፈረንጅ አፍ እየቀላቀሉበት ለሱ ያልገባውን ነገር ለኔ ሊያወጋይ ሲደክም ግራ እንደገባይ አይን አይኑን እያየሁ ታደምጠው አሁንም ቀጠለና•••
"የቀድሞ ፎቶዎቿን አንድ ባንድ እያሳየ ሲጠይቃት አይን ፍጥጥ !ጥርስ ግጥጥ!ዋሽታ እማታመልጠው ሀቅ ነውና አልካደይውም አመነይ። በጥቅሉ ያገባው በፈጣሪ የተሰራችውን ታይሆን በሰው የታደሰችውን ነው ስልህ!
ሲለይ ይበልጡን ተምያታብይ። ዝናቡ መዝነብ ተዥመረ መች ያቆማል አሁንም ቀጠለ•••
"ተዛ ቡሀላ የኛ ሰው ሀበሻ ያው እንደእልኸኛነቱ ሁሉ ተረታ /ታሸነፈ/ ቡሀላ ይቅር ባይነቱም የበዛ አይደል!
እውነቱን ታወቀ ቡሀላ ሁሉን ትቶ ይቅር ቢላትም በሷ ብሶ በጀ አላለይም። እውነቱ ተወጣ ቡሀላ ከሱ ጋር መቀጠሉ ጎረበጣት መሰል መፋታቱን መርጣ ተፋቱ። አንዳርጌ ሙት እሄን ስስማ ጉድ ጉድ ጉድ እያልሁ ጭንቅላቴን ይዤ ልጮህ ምን ቀረኝ!" ብሎ ያክስቱን ልጅ ታሪክ ቋጨ።
እንኳን የተዋቡ አባት እንዲህ ናላዬን አዙረውት በደናውስ ግዜ ቢሆን እንዲህ ለራሱ ያልገባውን ወሬ ለኔ አውርቶልዪ ቤት በኩል ይገባኛል።
ምናለ ሰው ለራሱ ያልገባውን ለሌላው ባያወራ
ምን እንዳናደደይ እንጃ ብቻ ብልጭ አለብይ•••
የነገሩ ባለቤት ያልጮኸውን አንተ ምን ቤት ነህ ጭንቅላትህን ይዘህ እምትጮኸው ጎበዝ??" ልለው አሰብሁና መልሼ ታጤነው ስንቱ በማያገባው እየጬኸም አይደል ብዬ•••
" እሄስ ያስጮሀል ዝንቡ ጮኽህ ቢወጣልህ ጥሩ ነበር ሙት!" አልኹት።
"ሙት እውነትህን ነው! ሳልጠጣ ሄጄ እንዢ ሞቅ ቢለኝማ መጮኼ አይቀርም ነበር አሁን ልጩህ እንዴ? አለዪ
ቆይ እኔ ልውጣና ትጮሀለህ ብዬው ሂሳቤን ከፍዬ ተጠጅ ቤቱ ወጣሁ።
ግቢ እንደደረስሁ መጠጡ በሰጠይ ድፍረት ትልቁቤት በር ላይ ቆምሁና ጮክ ብዬ ተዋቡ የኔ ብዬ ተጣራሁ።
በሩን በስሱ ከፈተይና •••
"በእጇ አባዬ ተኝታል አትጩህ!"
የሚል ምልክት አሳየችይ።
መስማታቸው አይቀርም ብዬ•••
ቅድም የሞተውን ሰው ስም በደንብ ሳላጣራ ስላስደነገጥሁሽ ይቅር በይይ ውብ አለም የስም ስተት ነው " ለጋሼ ዘርጋውም ንገሪልይ አልኋት።
በሩ ላይ እንደቆመይ አንገቷን አዙራ አባቷ ወደተኙበት ገልመጥ አረገይና።
በል አሁን ግባና ተኛ በቃ ደና እደር። አለችይ።
በጀ እያልሁ በሬን ከፍቼ እስትገባ ቆማ እያየችይ እንደሆነ ያወቅሁት የኔኑ ክፍል በር ልዘጋ ስዞር ነበር። ቆሜ ታያት እጇን አውለብልባ ተሰናበተችኝና ገብታ በሩን ጠረቀመችው።
በጥዋት ቁርስ ይዛልይ እንደገባይ።
ተዋቡ ላንድ ለሁለት ሳምንት ዘመድ ዘንድ ደርሼ እመለሳለሁ አንድ ሁለት ቅያሪ ልብስ ይዘሽልይ ነይ አልኋት።
ታፏ ቃል ታታወጣ ትክ ብላ እያየችኝ እንባዋ ሁለቱ አይኖቿ ላይ ግጥም ቲል ፊቷን መልሳ ተክፍሌ ወጣይ።
ትንሽ ቀየት ብሎ በሬ ቲንኳኳ ተዋቡ ልብሱን ይዝልይ መጥታ ነው ብዬ ማነው ታልል ብድግ ብዬ ብከፍተው አባቷ ናቸው።
ደንገጥ ብዬ ደና አደርህ ጋሼ ዘርጋው ምነው በጥዋት በሰላም ነው ብለው "ፈልጌህ ነው አንዳርጌ ለባብስና እላይ ቤት ና እጠብቅሀለው" ብሎኝ ተመለሰ።
ለምን ፈለጉይ ብዬ ፈራ ተባ እያልሁ ወደ ትልቁ ቤት ገባሁና ቁጭ አልሁ።
አንዴ አጠገባቸው ወደ ተቀመጠይው ተዋቡ አንዴ ወደኔ እየተመለከቱ •••
"ልጆቼ•••" ብለው መልሰው ዝም አሉ።
ገና መናገር ታይጀምሩ ፊታቸው ተቀያየረ።
ሁለመናቸውን የሀዘን ድባብ ጣለበት።
ልዦቼ እናቴ ገና የአስራ ሁለት አመት ልዥ እያለሁ ነው በወባ በሽታ የሞተችብይ።
ታድያ የናቴን ያህል የምወዳት አንድ ለናቷ የነበረይ አንድ ታላቅ ብቻ ነይ የነበረችይ።
ተዋቡ ትባላለይ ሲሉ እኔና የኔዋ ተዋቡ ግራ በመጋባት ተያየን።
ያንተን ሚሽት እቺ ልዤን ተዋቡ ያልኋት መልኳ ተሷ ጋር ስለሚመሳሰል ነው። እይ ጨቅላ ሆና እናቷ ያወጣይላት ሽም ሌላ ነበር።
አባታችን ብዙም ለልጅዥፊቱ የማይፈታ ሰው ነው። ስለዚህ እንደናትም ፣እንደህትም፣እንዳባትም የማያት ይችኑ እህቴን ነበር። ተራሴ በላይ እወዳት ነበር።
ማግባት አይቀርምና ባል ታገባይ ቡሀላ አባቴ ብዙም ስለማይቀርበይ ብቸኝነት ያጠቃይ ዥመር።
አብዛኛውን ግዜ እህቴ ዘንድ እየሄድኩ ብቀመጥም ባሏ አመለ ክፉ ነበርና ቲያሰቃያት እያየሁ ስለማያስችለዪ እሷን ሲያስለቅስብይ ሰድቤው ወደ ቤቴ እመለሳለሁ።
ግን አያስችለኝም አሁንም ስናፍቀኝ እሄዳለሁ አሁንም ተጣልቼው እመለሳለሁ።
በይህ ሁኔታ አመታት ቢቆዩም ልዥ አልወለዱም
ችግሩ ተሱ ይሁን ከሷ አላውቅም ብቻ ልዥ አልነበራቸውም።
ጠባቸው እየተደጋገመና እየከረረ ቲመጣ እህቴ ተባሏ በተጣላይ ቁጥር ወደኛ ዘንድ መምጣት ዥመረይ።
ስትመጣ አባቴ ልዥን ቀርቦ ? ምን ከፍቶሽ ነው? ሳይል ፣ ምንድን ነው በመሀከላችሁ ያለው ችግር?"
ብሎ የሚፈታ ችግር ከሆነ መፍትሄ እንዲያበጁለት መፍትሄ ከለለውና የሷ ምርጫ መለያየት ተሆነ እንዲለያዩ ፍላጎቷን ታይጠይቅ ፣ ከፍቷት በመጣች ቁጥር ሴት ልዥ ከቧላ ጋር በተጣላይ ቁጥር ሮጧ ወደቤተሰቦቿ የምትመጣ ከሆነ ደግ አደለም እያለ አሳቆ ሲመልሳት አለቅሳለሁ።
እኔ የባሏን ጠባይ አውቀዋለሁና ተጣልታ መጥታ ሂጂ ብሎ በሚያባርራት አባቴ እጅጉን እናደድ ነበር።
በመጨረሻም እሷው ጋር ሄጄ በሌላኛው ክፍል ውስጥ በተኛሁበት የገዛ ባሏ እህቴን በተኛችበት ገሏት ጠፋ።
ተንቅልፌ እንደተነሳሀ በተኛችበት ታርዳ የሞተይውን የገዛ እህቴን ሬሳ አየሁት።


Forward from: Bellato fashion official
✅ Air force

With different size and colour

AVAILABLE for pre order

Contact @Bellatofashion for more
Join our telegram channel
https://t.me/bellatoofficial


ልሂድ አልሂድ እያልሁ እስተዛሬ ታመነታ ቆየሁ። ታመሪካን መጣ ሲባል አመሪካን እራሷን ይዞ መጣ የተባለ ይመስል ሁሉም ከያለበት እንኳን ደና መጣ ታይሆን እንኳን ደና መጣህልን ሊለው እየሄደ የድርሻውን ቲቦጭቅ።
ያክስቴ ልዥም አይደል እንኳን እኔ በደም ዝምድና ያለይ በስም የሚያውቀው የጎረቤት ልዥ ሁሉ ይሄድ የለ እንዴ!
የኔስ ድርሻ ተሚሻግት ሄጄ ብወስደው ምናለ አልሁና ለሳምንት የጠጅ ወጪዬን እንኳን የሚሸፍን ብር ቢሰጠይ ብዬ ሄድሁልህ ።
ሰላም ብዬው እንደተቀመጥሁ ቤተ ዘመዳ
ዘመዶቹ " አይ ዝናቡ ደና ነህ ግን እንደው በስንት ግዜ ዛሬ ተገናኘን !
ጠፋህ እኮ አንተው! እየመጣህ መጠየቁን ተተውከው ስንት ግዜ ሆነህ" ቲሉይ
እንደው ትለመጥፋቴ ያን ያህል የሚነዘንዙይ መጥፋቴ አሳስቧቸእ የናፍቆታቸውን ታይሆን እኛን ልትጠይቅ ታይሆን ዛሬ ልዣችን ተአሜሪካን መጣ ቲባል ነው የመጣህ እያሉ በነገር የሚሸነጉጡይ መስሎ ትለተሰማይ ውስጤን ጎረበጠይ።
ቢሆንም ሁለት ወዶ አይሆንም እና በአሽሙር የሚዘልፈይን ሰምቼ እንዳልሰማሁ ሆኜ ተቀመጥሁ።
ተቤተ ዘመዱ ጋር ታወጋ በወሬ መሀል ወደይህ የመጣው ታገሩ ተወንዙ የበቀለይውን ኮረዳ አግብቶ ሊወስድ መሆኑን ትሰማ ግር አለይ።
አጠገቤ ወዳለው ታናሽ ወንድሙ አንገቴን አዘመምሁና ስማ እንጂዢአንተው ተዛሬ ስንት አመት በፊት ወንድምህ እዛ አማሪካን ሚሽት አግብቶ መውለዱን ነግረኸይም አልነበር እንዴት ነው ነገሩ? ትለው።
ውይ ዝናቡ አልሰማህም እንዴ አየህ እሄን አለመስማትህ እራሱ ምን ያህል ግዜ እንደተጠፋፋን ነው እሚያሳየው በማለት በነገር ወጋ አርጎ ታለፈይ ቡሀሏ•••
" እሷን እማ ፈታት እኮ! አለይ ።
ምነው ምነው ተወለዱ ቡሀላ ምን አጋጠማቸው ጃል ? ትለው!
ይህቺ ጉዷ እማያልቅ አሜሪካን ፎርጅድ ሚሽት ድራለት ነዋ ቲለኝ ግር አለኝ
ፎርጅድ ፎርጅድ ደግሞ ምን ማለት ነው እሱ ? ትለው ሳቀብይ

•••••••ይቀጥላል

ክፍል - ዘጠኝ ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
     @fkrn_be
_kalat
     @fkrn_be_kalat
╚═══❖•
🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴍᴍᴇɴᴛ         
       @fkrn_be_kalat_
bot
     ❥❥________⚘_______❥❥


👩◈ ሚስቴና አባቷ ◈👴🏻

       ክፍል - ስምንት [፰]

   ✍ (በጥላሁን ተስፋዬ)
.
.
.
"እኔን ጥለህ አንዱ ? አታደርገውማ ይልቅ
ቆይ አንድ መላ መጥቶልኛል እነግርሀለሁ መጣሁ አለይችይና ቁርሱን አስቀምጣልይ ወጣይ።
ትንሽ ቆይታ መጣይና •••
••••"እሄውልህ አለሜ ትንሽ ቆይተህ ወደ ከተማ ትወጣና ድንገት ከናንተ ቀየ ወደይህ ከተማ የመጣ ሰው የሩቅ ዘመድህ መሞቱን መርዶ እንደነገረህ ሆነህ አዝነህ ትመጣለህ።
ተዛ ተያይዘን ለቅሶ ልንደርስ ሄድን ብለን እንወጣለን ።ያኔ አቡዋ መቸስ እሚያበስል እሚጋግር በለለበት ቤት ብቻውን አይቀመጥ ። ተሰናብቶን ወደ ቤቱ ተመሄድ ውጪ አማራጭ የለውም ።
ከተማ እንቆይና መሄዱን ሰው ልከን ታረጋገጥን ቡሀላ ተያይዘን ወደቤታችን!" አለችይ።
ምናለ እሄን መላሽን ያንን እኔኑ በሽተኛ ታረገዪ ከንቱ መላ በፊት ብትነግሪይ የኔ መለኛ አልኋት ፈገግ እያልሁ።
"ኪኪኪኪኪ ያኔ መች መጣልይ አለሜ?!" አለችይ እየሳቀይ።
በይ ሂጅ እኔም ልሂድ አልኋትና ከተማ ዘወር ዘወር ብዬ ትመለስ እግቢው ውስጥ ተዋቡ ቡና እያፈላይ እሳቸው ተፊቷ ቁጭ ብለው ያወጋለሁ።
ጥድፍ ጥድፍ እያልሁ ገባሁና አጠገባቸው ትደርስ በተማከርነው መሰረት የተረበሽው የደነገጥሁ መስዬ ቆምሁ•••
" ምን ሆነሀል አንዳርጌ ፊትህ ልክ አይደለም !?" አለችይ ተዋቡ ።
"መርዶ ሰምቼ ነው ተዋቡ !" ትላት።
"ውይ የምን መርዶ አለይና ብድግ አለይ !"
አወይ ተዋቡ የኔን አላውቅም እሷ ግን ማስመሰሉን እንዴት አድርጋ እንደምትችልበት እናንተው!
ይገርማል እኮ! ውሸት እንደሆነ እያውቅሁ አደነጋገጧ እኔኑ መልሶ ቲያስደነግጠይ እስቲ ምን ይባላል?"
እንደው ብድግ አለይና ደረቷንም እንደመድቃት እያረጋት••
"ማን ?የትኛው ነው አንተው? ያ ልዥ ነው እንዳትለይ አንዳርጌ! " አለችይ
"እኔ አፈር ልብላለት አዎ ተዋቡ ያ ባለፈው መታመሙን የነገርሁሽ ዘመዳችን ታያርፍ እይቀርም ለጉዳዩ ተነሱ መንደር ወይህ የመጣ ሰው ነውኮ አሁን የወተት ኪራይ ሂሳብ መጨመራችንን ለኮንትራት ደንበኞቻችን እየዞርሁ ትነግር ድንገት አግኝቸው ዥሮዬ ጭው እስቲል ድረስ መርዶዬን ያረዳይ አይ ሰው ከንቱ እንደው ለይህ እድሜ ነው እንግዲህ ተመዋደድ ይልቅ እየተጠላላን፣ ተመደጋገፍ ይልቅ እየተገፋፋን ፣ ተማስታረቅ ይልቅ እያጣላን ፣ አንዳችን ለአንዳችን መፍትሄ ታይሆን ሽግር እየሆንን ፣ የሰው ልዥን ህይወት ማቅለልን ታይሆን ማክበድን ስራየ ብለን የተያያዝነው! እንደው አሁን ያን የመሰለ ወጣይ እንዲህ ባጭሩ ይቀጫልይ ብሎ ያሰበና የገመተ ተዌት ይገኛል!? "
አልሁና እግረ መንገዴን የተዋቡን አባት በነገር ወጋ ወጋ አደረኋቸው።
"ውይይይይይ አቤት መልክ አይ ቁመና እንደው ምን አገኘው?
የኔ ለግላጋ! እይ ጫወታ ! አይ ፈገግታ! ምነው በግዜ ወሰድኸው ፈጣርዬ •••" እያለይ እንባ እንባ እያላት ትትብከነከን እኔ እራሱ እየተወነይ ይሁን የምሯን ለማወቅ ተምታታብይ።
እንደው ተዋቡን ታያት ተልቧ የተንገበገበይ እዪ እያስመስለይ መሆኑን እንኳን አባቷ እኔም ማወቅ ተሳነይ እንዴ ተረጋጊ እዪ ውባለም የተማከርነውን እይ እውነት አይደለም እኮ ልላት ምን ቀረይ እናንተው? ።
አባቷም ግራ ገብቷቸው አንዴ እኔን አንዴ እሷን እያዩ •••
"ታውቂው ኖሯል ተዋቡ "አሉ። እሷ መልስ ታትሰጣቸው •••
"በደንብ ነዋ! አሰምራ ነዋ እምታውቀው ተስንት ወር በፊት እይህ እኛ ዘንድ መጥቶ ጠይቆን ነበር እኮ የተዋቡ አባ !" አልኋቸው
ምኑን ጠጣሁት ቡናውም ይቅርብይ ልሰናዳና እንሄዳለን ብላ ብድግ ትትል።
"ለመሆኑ የት ነው ቦታው !"አሉ አባቷ። በልቤ ምን ሊሉ ይሆን እኝህ ሰው ጉዳቸው አያልቅ መቸስ እያልሁ ቦታውን ትነግራቸው።
" እ እዛ ነው እንዴ? እዛ ነው ልሰናዳና እንሂድ ያለይው? ወቅቱ እኮ ክረምት ነው ወንዝ ይሞላል፣ መሬቱ ረግረግ ነው!! በዛ ላይ መንገዱ ዳገት እና እሾህ የበዛበት አስቸጋሪ መንገድ እንደሆነ እውቃለሁ!
ዛድያ እዛ ነው ልዥ ይዘሽ እምትሄጅው ተዋቡ ለመሆኑ ቦታውን ታውቂዋለሽ አወይ ማበድ! አወይ አቅምን አለማወቅ እናንተው ! እንኳን ለሴት ልዥ ለወንድ በሚፈትን በያ መንገድ ልዥ ይዘሽ ይቅርና ሌጣሽንስ ትችይዋለሽ እንዴ ነገሩ ብታውቂው እግርሽን ለማንሳት ባልዳዳሽ!
በይ አሁን አርፈሽ ተቀመጭ እግርሽን እንዳታነሽ ተዋቡ!" ብለው ወደኔ ዞሩና
"አንዳርጌ ልጄስ መንገዱን ስለማታውቀው ልሂድ ትበል አንተ ግን ያን አስቸጋሪ መንገድ እያወቅህ ሚስትህንና ጨቅላ ልጅህን ይዘህ ለመሄድ አስበህ ነው ልሂድ ስትል ዝም ያልሀት! ያንተን ዘመድ ለመቅበር ሄዳ በዛው የሷ ቀብር እንዲፈጠም ነው አላማህ !? ብለው አፈጠጡብይ።
እምናገረው ጠፍቶይ አፌ ተለጎመ።
"ምንስ ቢሆን ታድያ ብቻውን አይሄድ!" አለይ ተዋቡ።
እሄን ግዜ ብድግ አሉና •••
" አንቺ ልዥ ••• ህጣን ልዥ ይዘሽ በዛ መንገድ መሄድ አትችይም አልሁ እንጂ ብቻውን ይሂድ መች ወጣይ ዘመድ አማች ጎረቤት እንደለለው ለምን ሲባል ብቻውን ይሄዳል !" ።አሉና •••
"መጣሁ ልብስ ልቀይር እኔና አንተ አብረን እንሄዳለን! አንዳርጌ አንቺ ግን አርፈሽ ተቀመጭ እኔው አብሬው እሄዳለሁ"
እያሉ ወደትልቁ ቤት ቲገቡ•••
እኔና ተዋቡ መላቅጡ ጠፍቶን ተፋጠጥን።
"ለብሰው ሊመጡ እኮ ነው ምን ይሻላል? ያልመተውን ሞተ ብዬ ታበቃ ወየት ይዣቸው ልሄድ ነው ተዋቡ ? አልኋት ጨንቆይ።
አይ መቸስ መለኛ አይደለይ ተመቅስፈት መፍትሄው ማምለጥ መሁኑን ወሰነይና ••••
"ሂድ ውጣ አምልጥ ታይወጣ ተግቢ ውጣና እሩጥ አንዳርጌ ! እኔ ገብቼ ተባራሪ ወሬ ስለሰማሁ አባትሽን እዛ ድረስ ወስጄ ሳላደክማቸው የሞተው እውነት እሱ መሆኑን ከሁነኛ ሰው አጣርቼ ልምጣ ብሎይ ወጣ እለዋለሁ !"አለችዪ።
እውነት ነው ሴት ልዥ መለኛ ነይ የሚባለው የኔ ተዋቡ ግን ትለያለይ እናንተው !።
እኔ አብሬህ እሄዳለሁ ሲሉ አንዴ የዋሸነውን ምን ብዬ እንደማስተባብል ማጣፊያው ቸግሮይ ትርበተበት ወድያው ምህንያት መፍጠራ ይገርማል ! እያልሁ
አባቷ ልብስ ቀይረው ታይወጡ ተግቢው በርሬ ጠፋሁ።
በዛው ወደ ጠጅ ቤት።
ጠጅ ቤት ቁጭ ብዬ ተማንም ሳልጫወት እና ሳላወራ እንደው ልብስ ቀይረው ቲወጡና ተግቢው ብን ብዬ መጥፋቴን ቲያውቁ ተዋቡ አለሜን ምን ብለዋት ይሆን ?" አልሁ በልቤ ።
ተማንም ታልቀላቀል ጥጌን ይዤ ጠጄን እየኮመኮምሁ ያባቷንም የሚሽቴንም ሁናቴ እና በይህ አስራ አመስት ቀን ውስጥ ያሳለፍነውን እያሰብሁ በሚያስቀው ትስቅ በሚያናድደው ትናደድ ቆየሁ•••
ብዙ ብቆይም ገና ሁለት ብርሌ ነው የጠጣሀት ሶስተኛውን አዝዤ ቀና ትል •••
ወሬ ተዥመረ እንደሀምሌ ዝናብ እኝኝ እያለ የማያባራው ዝናቡ ሞገስ ሲገባ አየሁት ብቻዬን ማሰብ ስለፈለክሁ ብደበቀው ደስ ባለይ።
ዝናቡ ሁሌም ደስ እማይለይ ስለማላውቀው ሰው ስለሚያወራይ ነው ።
በስምም በአካልም ስለማላውቀው ሰው በይህ ገባ በይህ ወጣ ብሎ ወሬ መስማት ብዙም ምቾት አይሰጠይም።
ገና ሲገባ አይቶያል። ቀጥ ብሎ ወደኔ መጣና•••
ዛሬ የገጠመይን ጉድ እስክነግርህ ቸኩያለሁ ።አለይ። ለማውራት ምላሱን እየሳለ•••
ምን አጋጠመህ አልሁት። ምን ቸገረዪ ዥሮ አይሞላ እስቲ ተንፍሶ እስቲገላገለው በመስማት ልተባበረውና ተንፍሶ ይገላገለው ብዬ••••
"እሄውልህ ያክስቴ ልዥ ታሜሪካን የመጣው ተሁለት ሳምንት በፊት ነው።


👩◈ ሚስቴና አባቷ ◈👴🏻

       ክፍል - ሰባት [፯]

   ✍ (በጥላሁን ተስፋዬ)
.
.
.
ዘወር ብዬ ወደአመላከተችይ አቅጣጫ ትመለከት እመንገዱ ዳር ላይ ታለ አንድ ስጋ ቤት ነጭ እተቀባ ግርግዳ ላይ የተሳለ ትልቅ ጥቁር በሬ ነው !
እንደው አንዳርጌ ሙት ነው እምልህ ብልጭጭ አለብይ!"•••••
ቲለኝ አልቻልሁም ወሬውን እስኪያከትም አፍኜ የያዝሁትን ሳቅ እንደ ሀምሌ መብረቅ አንባረቅሁት ።
ካካካካካካ ያንተስ ለጉድ ነው ጃል
እና ምን ይሻልሀል ? ብለው•••
ታድያ እሄ ባልና ሚሽት ታንድ ወንዝ ይቀዳሉ ያለ ሰው ጥሁፍን እንዲህ ብሎ ያስተካክልልይ
ባልና ሚሽት ታንድ ወንዝ ይቀዳሉ ተዳምጠው እና ተሳቷ ሚሽቱ በስተቀር ብሎ ያስተካክልልይ።
ይህን ማድረግ የማይችል ተሆነ ግን ተሚስቴ ያፋታ እና ታለወንዟ የሄደይውን የኔዋን ያምጣልይ።
ይህም ታልሆነለት ያለክዳና ታልገጠምክ እያለይ ቲላት እስፓናቶ ቲላት አንጎል ፋቶ እያረገይ
አወላልቃ ታጨርሰይ የኔ ታትሆን የሷ ላረችይ ሚሽቴ የራሷን ግጣም አፈላልጎ ይስጣት።ይህም ተተሳነው ደግሞ•••
በእሳት ምላሷ ተጨጓራዬ ዥምራ በሷ ንዴት ስጠጣ ወደ ጉበቴ ፣ በሷ ብሶት ታጨስ ወደሳምባዬ እየመጣይ ተንቀሳቃሽ ሬሳ ካረገችይ ተይች ሴት እምገላገልበትን መንገድ ጠቁሞይ ፣ ተተቀዳሁበት የተቀዳይውን እማገኝበትን መላ ጀባ ይበለይ ።ያለበለዚያ አልፋታውም
ለሁሉም የማይሰራ ለሁሉም ቲተረት ደስ አይልማ ደስ አይልም!!! ቲለይ ሳቅ በላይ በላዩ እያፈነይ•••
"መፍትሄ ታልሰጠህስ ምን ትሆን ?" አልሁት።
"እሱማ ምን እሆናለሁ ወንድም አለም ነገሩን አጫወትሁህ እንጂ ከነፍጥርጥሯ እኮ ታንጀቴ አፈቅራታለሁ !"
"ካፈቀርካትማ ቻለው እንግዲህ እኔም ትለማፈቅራት እይ እንዳባቷ ጠባይ እማ ቢሆኔ እስታሁን ጥያት በጠፋሁ ነበር!" ብለው••
"ሀሳባችን ፍላጎታችን አልገጥም ቲል የጠላሁትን ትትወድ ፣ የወደድሁትን ትትጠላ ታንድ ወንዝ ተቀድተን ተሆነ በመሀላችን ፍቅር ታይጠፋ ለምን መንገድና ፍላጎታ ተኔ ታቃረነ ብዬ እይ ማፍቀርስ አፈቅራታለሁ።
ብታስከፋይኝም እሷስ በምን ምህንያት ይሆን እንዲህ ተኔ በተቃራኒው ለመሆን የበቃይው ብዬ አስባለሁ እይ አልነካትም።
ባይሆን አንዳንዴ ነገር ቲበዛ እና ትታስከፋይ ወጣ እልና ታፋፉ ላይ ቆሜ ብሶቴን በፉከራም በቀረርቶም ለዱሩም ለጫካውም እነግረዋለሁይ " አለይ።
"ምን እያልህ ነው እምትነግረው ጃል? ብለው እዛው ዠመረዋ •••
ኧ••••ረ ጎራው
ኧ•••••ረ ወንዱ
አረጎራው አረወንዱ
አረጎራው አረወንዱ•••
ተ••••ተሰውት በላይ እግምባር ሲወርዱ
ተ•••••ቆሰሉት በላይ ጠላት ሲያሳድዱ
እ•••••ልፍ ጀግና ወንዶይ በሴቶይ ነደዱ
ኧረ ጎራው
ኧረ ጎራው
ኧረ ወንዱ
ዳሩልይ ብላቸው የግራ ጎኔን
ዳሩልይ ብላቸው ውሃ አጣጪዬን
እ•••••ሳቷን አምጥተው ጠበሱዪ እኔን
እረ ጎራው
ኧረ ወንዱ
ኧረ ጎራው
ስንቱን ዥግና ነዪ ባይ እንዳላሯራጥነው
ስንቱን ወንድ ነዪ ባይ ገርፈን እንዳልጣልነው
ለ••••ፍቅር እጅ ሰጥተን ስንቱን አሳለፍነው
እረ ጎራው
ኧረ ወንዱ
ኧረ ጎራው
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ጀግና ቲመስለን ጡንቻ ያስነካ
ጀግና ቲመስለን •••
ስንት እንደጣለ ሬሳ ያስለካ
የራሷን ሳሰጥ የሰው ታትነካ
በፍቅር ገዳይ ሴት አለይ ለካ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
የዥግናው ልዥ ነይ የበላያ ዘር
ጓንዴ ቢተኮስ የማልበገር
መድፍ ቢንጣጣ የማልደነብር
ጠልፋ ጣለችይ በሀያል ፍቅር
ላገሬ ባልዘምት ባልወጣ ከዱር
ለሚስቴ ዘብ ነይ የቤት ወታደር
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
ዘራፍ አካኪ ዘራፍ
እጠጅ ቤቱ ውስጥ ያለው በሙሉ በመሀል በመሀል በወኔ እያጨበጨበ ቲያጅበው ቆየ ። ጨርሶ አጠገቤ ተቀመጠ።
እሄውልህ ወዳጄ አንተ ከፋም ለማም በፍቅርህም በጠብህም መሀል የሚገባብህ ሰው የለም እኔኮ የተጀገርሁት የራሳቸውን ሚሽት ፈተው የገዛ ሚስቴን ዘብ ሆኜ ታልጠበኳት በሚሉት አባቷ ነው።
"ያንተው ነገር ለሰሚውም ግራ ነው ኩለው ድረው ተሰጡ ቡሀላ ያንተ እንዢ የሳቸው እንዳልሆነይ አያውቁ ኖራል እንደው እሄን የሚነግራቸውስ ወዳጅ የላቸውም ? ሴት ልዥ እናት እና አባቷን ትተዋለይ ተባሏ ጋም ትተባበራለይ !"ቲባል አልሰሙም" አልይ።
ምን መስሚያ አላቸው እንደው ምን እንደማረግ ግራ ግብት ብሎያል ባክህ!" ብለው•••
" እኔን ቻለው እንዳልኸይ ቻለው ተማለት ውጪ ክፉ አልመክርህ እንግዲ መሄዴ ነው ውዳጄ ቻለው ብሎዪ ተጠጅ ቤቱ ወጣ።
ደሞ መለስ አለና ወደ ዥሮዬ ጠጋ ብሎ ችግር በጉልበት አልያም ጥፋተኛውን በመውቀስ ብቻ አይፈታም ብልሀት ያስፈልጋልይ እኔ ከሰሞኑ ተሞላ ጎደል በኔና በሷ መሀል ያለውን ሽግር እየፈታሁ ነው።
በምን እንደሆነ ታውቃለህ ለምን እንዲህ ትሆኛለሽ ለምን እሄን አደረግሽ ብዬ እምቧ ከረዩ በማለት እንዳይመስልህ ለሚሽቴ የምጠላውን እንደምወድ የምወደውን እንደምጠላ እያረግሁ ገለባብጬ በመንገር ነው ተያ ቡሀላ ተኔ በተቃራኒው የሄደይ መስሏት መስመራችንን ገጥማው ቁጭ አለይ!!
ኪኪኪኪኪኪኪ አሁንም ልድገምልህ በመሀላችሁ ያለውን ችግር ለመፍታት ብልሀተኛ መሆን አልያ መቻል ብቻ ነው ያለህ አማራጭ ቻለው ኪኪኪኪኪኪኪ"
መክሮይ ታይሆን ተሳልቆብይ የወጣ መስሎይ በገንሁ!።
ተጠጅ ቤት ወጥቼ ወደ ቤቴ የሚያደርሰይን መንገድ እንደዥመርሁት ነበር እንደእብድ ብቻዬን ማውራት የዠመርሁት።
ያው ለግዜውም ቢሆን ስካሩ እስቲበርድ እብድ እና ሰካራም አንድ ትለሆኑ ነው መሰል እንደእብድም እንደሰካራምን እያርገይ •••
"በየቤቱ ስንት ጉድ አለ እናንተው በኑሮ ጉያ ውስጥ እንቅፋት ቲመታይ ተሰው ዘር ሁሉ እኔን ብቻ መርጦ የሚመታይ እየመሰለይ ሳማርረው የቆየሁትን አምላኬን ይቅር በላይ አልሁት ።
ሁሉም በሂወቱ ውስጥ በፍቅር መሀል ፣ በስራ መሀል ፣ በጤና መሀል፣ በሰላም መሀል እያደናቀፈ የሚፈታተነው የየራሱ የሆነ እንቅፋት አለው ።
አንዳንዱ በእንቅፋቱ ተመቶ ይወድቅና ተሩጫው ይገታል ፣ አንዳንዱ በእንቅፋቱ ተንገዳግዶ ቆም ይልና መንገዱን ይቀጥላል፣ አንዳንዱ ተራሱ ተእንቅፋቱ ጋር ተላምዶ ሽግሩ ምን እንደሆን እንኳን በወጉ ታይለየው በፈጣሪው አልያም በሌላው ሰው ላይ ቲማረር ይኖራል።
አንዳንዱ እራሱን እንቅፋቱን ፈንቅሎ ይጥለውና ሌሎይንም እንዳይመታ መንገዱን ያቀናል ።
አሁን በኔ ሂወት እንቅፋት የሆኑብዪን የሚሽቴን አባት እንዴት ተኑሮዬ መሀል ፈንቅዬ እንደማወጣቸው ብቻ ነው ማሰብ ያለብይ።
እይ በሳቸው ምህንያት ተዋቡ ፍቅሬን እና ሴት ልዤን ጥዬ ዌትም አልሄድም ፣ ትዳሬን አልበትንም እያልሁ በሀሳብ እንደናወዝሁ ግቢ ደረስሁ።
በበነገው ታልጋዬ ላይ ታልነሳ ጥዋት ቁርስ ይዛልይ እንደመጣይ ወገቧን ይዛ ቁልቁል እያየችይ•••
"ለምን ሄድክ ትናንት ?" ትትለይ •••
"ተይይ እስቲ ተዋቡ በቃ ብስጭትጭት ቲያረገዪ ሄድሁ!
እየሆነ ያለው ነገር ቢያበሳጨይ በኔ ይፈረዳል?"
እንደውም ተሳቸው ጋር ክፉና ደጉን ተምነጋገር ወሩ እስቲሞላላቸው ድረስ ልብሴን ሸክፌ ዘመድ ጥየቃ ልሄድ ወስኛለሁ!" አልኋት።
"እኔን ጥለህ አንዱ ? አታደርገውማ ይልቅ
ቆይ አንድ መላ መጥቶልኛል እነግርሀለሁ መጣሁ አለይችዪና ቁርሱን አስቀምጣልይ ወጣይ።
ትንሽ ቆይታ መጣይና

•••••••ይቀጥላል

ክፍል - ስምንት ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

     ┈┈┈┈••●◉❖◉●••┈┈┈
       @fkrn_be_kalat
      ┈┈┈┈••●
❖◉●••┈┈┈


ትቼዋለሁ
=============================

ፍቅሬ ሶዬ ውዷ ባለፈው እለታ ያኔ ሲገጥምልሽ
ወርቅ ዳይመንድ ዕንቁ ብዬ አሽመንሙኜ ያልኩሽ
አሁን ትቼዋለሁ ሳስበው ሁሉንም አንቺ ትበልጪያለሽ

ለካ አንቺ የኔ ህይወት የሆንሺኝ መሰረት
አንድ ነገር አወኩ በደንብ አስቤበት

ወርቅም ሆነ ዳይመንድ አልማዝና እንቁ
በብር ይገዛሉ በሳንቲም ተሽጠው በግዜ ሚፋቁ

አንቺ ግን ህይወቴ በዳይመንድ የሌለሽ
በወርቅ ሚዛን ወተሽ አልማዝን የበለጥሽ
ከብር ተወዳድረሽ ሁላቸውንም በልጠሽ ህይወቴን ያበራሽ

አንቺ ማለት ለኔ ምንም ማይተምንሽ
ህይወቴ ሚለው ቃል በራሱ ሚያንስሽ
ብቻ ህ ይ ወ ቴ ነሽ

ብቻ አ ❤️ ፈ ❤️ ቅ ❤️ ር ❤️ ሻ ❤️ ለ ❤️ ሁ❤️ ሶዬ

ተፃፈ :- በሶፊ አፍቃሪ


"እምትናደድበት ነገር ቸግሮሀል መሰል ወዳጄ እሚካፈል ቢሆን ባከፈልኩህ ኧረ እንደውም ሁሉንም በሰጠሁህ
እንዴት
ምን እንዴት አለው አሁን እምትናደድበት አጥተህ ነው በዚህ እምትናደደው
"እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ
"ባልና ሚሽት ካንድ ወንዝ ይቀዳሉ" ብሎ ለመጀመሪያ ግዜ የተናገረው ወይ የጣፈው ግን ማን እንደሆን ታውቃለህ ? ""
ቲለኝ•••
አባቷ የጀመሩይን እሱ ሊጨርሰይ ነው እንዴ አልሁና በሆዴ!!
አብደሀል እንዴ አንተ ሰው እሄ ተስንት ዘመን ዥምሮ ቲወርድ ቲዋረድ የመጣ አባብልም እይደል እንዴ
እንደዛ ሲሉ እሰማለሁ እይ ማን እንዳለው በምን አውቃለሁ ዳምጤ !?" ብለው ።
"እሄን ሰው ባገኘው አንድ ጥያቄ እጠይቀው ነበር አንድ ብቻ !ሳልደግም ሳልሰልስ አንድ ብቻ ጠይቄው ምን እንደሚለኝ በሰማሁ "
ምን ብለህ ነው እምጠይቀው ጃል?አልሁት ለካ እኔ ብቻ አይደለሁም ቀልቤን ያጣሁት እያልሁ።
"ከነኝህ ከንድ ወንዝ ከሚቀዱ ወይ ከሚጨለፉ ባልና ሚሽቶች ስም ዝርዝር መሀል የኔና የሚሽቴን ስም ልታሳየኝ ትችላለህ ወይ ብዬነዋ?
እንደው ባገኘው ይህን ጠይቄ ጉዱን ነበር እማፈላው! መልሱ የናንተ ሽም የለም እንደሚሆን መች አጣሁት!•••
ቀኑን ተወው ሳምንቱን ፣ሳምንቱን ተወው ወርና አመቱን የኔና የባልተቤቴን ሽም ለማግኘት ቢኳትን አያገኘውም ስልህ••
ታይኔ ነው ብሎ መነጥር ቢደረግም፣ ተመነጥሩ ነው ብሎ አጉሊ መነጥር ቢገረግድ ያልሆነውን ተዌት ያመጣናል!"
ተው እይ ጃል ታንድ ወንዝ ባትቀዱ ምን አቆራኛችሁ እህል ውሃ ባንተና በሷ መሀል ባይጣፍ ስሜት ጋልቧችሁ ብትጋቡ እንኳ ተሶስት ወር በላይ አብራችሁ ባልዘለቃችሁ ? ብለው ቱግ ብሎ ተመቀመጫው ተነሳና•••
"እኔና ሚስቴ ነን ታንድ ወንዝ የተቀዳነው?
ስማ ትሰማኛለህ እኔና ሚሽቴ አይደለም
ታንድ ወንዝ ልንቀዳ ተሁለት የተለያዩ ወንዞይ እንኳ አልተቀዳንም
ምን ይላል እሄ •••" አለይ።ቱግ ሲል በረድ ብዬ
እንዴት ? ብለው "እንዴት ማለት ጥሩ ነው" አለና•••
ስለኔ እና ስለሚስቴ እውነቱን ማወቅ እምትፈልግ ተሆነ ልንገርህ አድምጠይ
እኔ እና አሷ ማለት እኔ ወንዝ ትሆን እሷ ተራራ ነይ ተራራ ታውቃለህ አደል
ወንዝ ተራራ ላይ ይወጣል??
በፍፁም አይወጣም! ቁልቁል ተሆነ ይሄዳል ብለው
"ልክ ብለሀል ብሄደም ሽቅብ ታይሆን ቁልቁል ተምዘግዝጎ ባናቱ መፈጥፈጥ ይሆናል እጣ ፋንታው
ዛድያ እሷ ተራራም አይደለይ እኔ ከሷ ጋር የምኖረው ሁሌ እየተፈጠፈጥሁ ስልህ ምን ነካህ ፊቴን ተመልከተው እይ
እውነቱን ተናገር እሄ ድሮ የምታውቀው የዳምጠው ፊት ነው ? በጭራሽ !•••
እሄውልህ የኔ ሚሽት ማለት አዘውትራ የምትለብሰው ልብሱን እኔ ያልወደድሁት እንደሆነ ብቻ ነው። አዘውትራ የምትሰራው ወጥም እኔ ባልበላው ደስ ይለኛል ያልኋትን ነው!"
ተው እንጂ ዳምጤ መስሎህ እንዳይሆን?
"መስሎህ እንዳይሆን ይለኛል እንዴ እሄ ሰው ምን ነካው ዛሬ?
እሄውልህ የኔ ሚስት አጥብቃ የምትይዛት ጋደኛ ምናልባት ይቺ ልዥ ምኗም አይጥመይ፣ ደስ አትለኝም ፣ ያልሁ እንደሆነ ነው!"
ኧረ ተው እታጋነው ዳምጤ! •••
"እስቲ ዝም ብልህ ስማይ ! •••
እኔ ነኝ ያለሁበትን ንዳድ የማውቀው ወይ ጉድ ገና ሲሶውን እንኳ መች ነገርኩህና የውልህ •••
ገብስማ ዶሮ አልወድም የሚል ቃል ታፌ ተወጣ ገብስማ ዶሮ ገዝታ ለመምጣት ተትናገርሁበት ቀን ቀጥሎ ያለውን አመትባል እንደሷ በጉጉት የሚጠብቅ ሰው በመላ ምድሪቱ እግርህ እስቲነቃ ብትፈልግ አታገኝም ስልህ ቲለኝ •••
ካካካካ ኦሮ አሁንስ በግድ ልታስቀይ ነው መሰል አንተ ሰው ብለው
ይልቅ ስማኝማ ለሳቁ ኋላ ትደርስበታለህ ብሎ •••
"ስማኝ ወዳጄ አንዳርጌ•••
ጥቁር በግ አልወድም ታልኋት መግዣ ገንዘብ ብታጣ ብታጣ ስታረግዝ ጠብቃ ጥቁር በግ አማረይ ትለኛለይ።
ያኔ የገባሁበት ገብቼ ተለቅቼም ቢሆን እልወድም ያልኋትን ጥቁር በግ እኔው ገዥቼ እየጎተትሁ ይዧላት እመጣለሁ።
ገና ጥቁሩን በግ ይዤ ስገባ እንዳየይ ደስታዋን እንዴት ብዬ ልግለጥልህ ጃል?
እንደው ተግር ጥፍራ እስተራስ ጠጉሯ ሁለመናዋ ጥርስ እስቲመስለይ ድረስ ስታገጥብይ ትውላለይ።
ዛድያ የገብስማ ዶሮውንም የጥቁር በጉንም ስጋ እንዲች ታልቀምስ ብቻዋን ቅርጥፍ አርጋነው የበላችው። ብትለምነኝም አልቀምሳት ። እየተጠየፍሁ ብብላውስ መች ሆዴ ውስጥ ይረጋልኝ እና•••
ምስር ወጥ ደስ አይለኝም ካልሁ ሳምንቱን ሙሉ ተምስር ወጥ ውጪ አትስራም ስልህ።
እየው አሁን ባለፈ ለት በዶሮው እና በበጉ ግዜ ጠብቃ የማልወደውን እየገዛይ ትታነደኝ ቆይታ የለ ሆን ብዬ ጥቁር በሬ በጣም ነው እምጠላው አልኋት ።
ተዌት ታምጣው ?እንዴት እርጋ ጥቁር በሬ አርዳ ታብግነይ ?
መንደሩን አስተባብራ እቁብ ሰብስባ ቅርጫ ልታሳርድም አሰበይ፣
ዛድያ በሬውን እሷ ሄዳ አትገዛው ነገር ። አልያም ገዥዎቹን
ጥቁር በሬ ታልሆነ ሌላ እንዳትገዙ ብትል ስንት ሰው ባዋጣው ብር ምን ብላ ብቻዋን ታዛለይ ?
ብትል እንኳ ገዥዎቹ ጥቁር በሬ ያለይው ምን አስባ ነው ?
እኛ ልንበላ እይ ለሷ ሰይጣን ልንገብር አላዋጣን ብለው ነገር እንደሚያጠሙባት ጠንቅቃ ታውቀዋለይ ።
ሁሉንም እኔን ሊያናድዱ የሚችሉ ነገሮችን አድርጋ ስታበቃ እሄን ማድረግ ተሳናት ስልህ።
እኔም በዚህ ተረታለይ ብዬ ደረቴን ነፋቼ ትንጎማለል ተቀናት ቡሀላ ዘመድ ጥየቃ ወደኸተማው አብረን ወጣን።
ድንገት እጥርግያው መንገድ መሀል •••
"ዳምጥዬ! "
አለይኝ ትከሻዬን ነካ አድርጋ ።
ሁሌም እንዲህ ብላ ትትጠራይ ለምን እንደሆን እንጃ ልቤ ትርክክ ትላለይ ብቻ ምን ልትለይ ነው ብዬ
"ወዬ!" አልኋት ••••
እስቲ በደንብ እየው ስሞትልህ ዳምጥዬ ያኛው በሬ ደስ አይልም በዲማው ጊዬርጊስ አለችይ።
ዘወር ብዬ ወደአመላከተችይ አቅጣጫ ትመለከት እመንገዱ ዳር ላይ ታለ አንድ ስጋ ቤት ነጭ እተቀባ ግርግዳ ላይ የተሳለ ትልቅ ጥቁር በሬ ነው !
እንደው አንዳርጌ ሙት ነው እምልህ ብልጭጭ አለብይ!"

•••••••ይቀጥላል

ክፍል - ሰባት ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
     @fkrn_be
_kalat
     @fkrn_be_kalat
╚═══❖•
🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴍᴍᴇɴᴛ         
       @fkrn_be_kalat_
bot
     ❥❥________⚘_______❥❥


👩◈ ሚስቴና አባቷ ◈👴🏻

       ክፍል - ስድስት [፮]

   ✍ (በጥላሁን ተስፋዬ)
.
.
.
....ምን አቀበጠይ።
"ሳልታመም ታምሚያለሁ ብዬ የእውነት አደረከው ኧረ ይቅር በለኝ ጌታዬ !"••••
ሚሽቴምኮ አብራይ ተሰቃየይ ነገሩ አብረን ነን እሄን ተንኮል የሸረብነው ቢሆንም ማስታመም ተመታመም አይተናነስምና ለሷ ጭንቀት ስትል ማረይ!! " አልሁ ተልቤ።ጭንቁ ቲበዛብይ።
ተምሽቱ አንድ ሰአት አከባቢ የገባሁ ሁሉ ወጥቶ አለቀ መሰለይ ሁሉም ነገር ቀጥ አለ። ተሶስት ሰአት በላይ በተከታታይ ቲያሯሩጠኝ ስለቆየ ሁለ መናዬ ዝሎ እራሴን ስቼ እዛቹ ታጣፊ አልጋዬ ላይ እንደተዘረጋጋሁ እንቅልፍ ጣለይ።
ምን ያህል እንደተኛሁ እንጃ ብቻ ብንን ትል ተዋቡና አቧቷ እክፍሌ ውስጥ ተቀምጠዋል።
"ነቅቷል መሰለይ ወደላይ ቤት ይዘነው እንሂድ አደል አቡዋ?" አለች የኔ ተዋቡ።
ወባ ነች ያመመችው አልሁሽ እኮ ለኔና ላንቺስ ግድ የለም ለህጣና ልጅ አታስቢም ይልቅ ሂጂና እምኝታችሁ ላይ አጎበሩን ዘርጊና ተልጅሽ ጋር ተኚ ! ዛሬን እዚሁ ይደርና እስከጥዋት ለውጥ ከሌለው ከተማ ወዳለው ሀኪም ቤት ይዘነው እንሄዳለን። አሏት።
ውባ አለሜ እባቷ እንዲያ ሲሏት በሀፍረት ኩምሽሽ ብላ አይን አይኔን ትታየኝ አየኋት።
በንዴት እርርርርርይ ብዬ ልጬህ ምንም አልቀረይ።
ልጩህ ብልስ መድሀኒት ነው ብለው ያጠጡይ በሽታ አቅም አሳጥቶኛል በምን አቅሜ እጮሀለሁ።
"ወባ ነይ ብለህ ነው አቡዋ እኔ አይመስለኝም " አለይ ኮስተር ብላ።
እቅዳችን ትላልተሳካ እና እንዳለችው ይዛኝ ወደላይቤት እንዳንገባ የማይነቀል እንቅፋት በሆኑባት በገዛ አባቷ ተማፈሯም በላይ ተናደለይ።
"ወባ ነች አንቺ ነሽ እምውቂው እኔ ይልቅ ሂጂ ልጅሽም ተነስታለይ መሰለይ ድምጣ ይሰማል?" አሏት። እሄን ግዜ ብሽቅ አልሁና •••
"ወባማ አይደለም ያመመኝ!"አልሁ።
"እና እምትንቀጠቀጠው ጎጃምኛ እየጨፈርህ ኖሯል ምን ይላል እሄ!" አሉ አባቷ በቁጣ።
"ኧረ አልተንቀጠቀጥሁም መች ተንቀጠቀጥሁ!"
እንኳን አካልህ ድምጥህም እየተንቀጠቀጠ ነው ተወባ ውጪ እንዲህ የሚያደርግ በሽታ የታለ አንተ ልዥ ሰው የሚልህን ስማ!" አሉይ አይናቸውን አፍጠው"
ዝም አልኋቸው ። ሁለቱም ዝም ብለው ቲያዩኝ እሳቸውን ትቼ ወደምሽቴ ዞርሁና
"እንደኔ እንደኔ ተሆነ ግን
ያመመኝ ወባ ታይሆን ብርድ ነው ተዋቡ።
የዚህን ክፍል ግርግዳ እይው እስቲ ተሰነጣጥቋል እኮ!!!
ያን ግዜ እሄን ቤት ጭቃ ትናስመርገው ሳንቲም ቀነሰልን ብለን በማይረባ ሰው ነው ያስመረግነው።
ምርጉ አይረባ ልስኑ አይረባ ሞላ ግርግዳው እኮ ሽንቁር ብቻ ነው ።
ብርድ የማይገባበት ቀዳዳ የለም ስልሽ እግሬን ትሸፍን ታናቴ በኩል ይገባል፣ አናቴን ትሸፈን ተጎኔ በኩል ይገባል እሱ ነው በየቅጣጫው ትነፍስብይ ሰንብቶ ለበሽታ የዳረገይ!" አልሁ።
"ዛድያ አንተ ምን ቆራጣ ብርድልብስ የለበስህ ይመስል አንዴ እግርህን አንዴ አናትህን እያልህ በፈረቃ አሸፋፈነህ? ሁለመናህን ተሸፋፍነህ ለጥ አትልም አሉኝ አቶ ዘርጋው ።የተዋቡ አባት።
ኡፍፍፍፍ ሚሽቴን ባወራትም መልስ የሚሰጡይ እሳቸው ናቸው ። አሁንስ አበዙት እኝህ ሰው ብዬ በውስጤ ተልጌልጉሜ ታልጨርስ ቀጠል አረጉና•••
"ምርጉም ሆነ ልስኑ ሽግር ታለበት ደግሞ ተሽሎህ ስትነሳ እይሁ ግቢ ውስጥ እዛ እመውጫው በር በስተግራ በኩል ትቆፍርና ድንጋዩንም ጠጠሩም ለይተህ ለምርግ የሚበቃ አፈር ታዘገጀህ ቡሀላ ጭቃ ታቦካለህ።
በየሶስት ቀኑ እያሸህ ፣እያገላበጥህ እስቲበስል ድረስ ለሁለት ሳምንት በደንብ ታቦካኸው ቡሀላ ይህን የተሰናጣጠቀ ግድግዳ አፍርሰህ ወድያ ትጥልና ግጥም አርገህ ትመርገዋለህ ! እስታሁንስ ዝም ያልከው አንተ ለዚህ አንሰህ ነው አንዳርጌ ?
ባይሆን እኔም እስተዛው እዚሁ ስላለሁ ልሱኑ ላይ አግዝሀለሁ !" ሲሉይ •••
ሀሞቴ ፍስስ አለይ።
"በለፈለፉ ባፍ ይጠፉ " ያለይው ማን ነበርሳ ። እሳቸውን ተቤቴ ላበር በጠነሰስሁር ሴራ እኔኑ ሊያበሩኝ ነው መሰል አሁንስ።
"ለማንኛቸውም እኔ ብርድ እይ ወባ አላመመኝም አላመመኝም አበቃሁ !”
አልሁና ተሸፋፍኜ ተኛሁ አባትና ልጅ ተከታትለው ተክፍሌ ወጡ ። ተውጪ ዘጉብይ።
ጥዋት ላይ ተንቅልፌ ብንን ትል ተምኝታዬ ፊት የሚሽቴ አባት ቁጭ ብለዋል።
"ደና አደርህ አንዳርጌ? አዳርህ እንዴት ነው ለውጥ አለው?"
" ምንም አልል "አልሁ እየተንጠራራሁ።
"አይዞህ ለማንኛቸውም እንዳልኸው ብርድ ተሆነ የመታህ አንድ ተቡና ጋር የምትወሰድ ፍቱን ቅጠል አለይ ታች መንደር ወርጄ ይዤልህ ልምጣ!" ሲሉይ ገና ታያመጡት አንቀጠቀጠይ።
ኧረ በዲማው ጊዬርጊስ !!!
ተሽሎኛል እኮ! እንደኔ ጤነኛ አለ እንዴ!
ብርድ•••••
ኧረ የምን ብርድ ? ለሊቱን ነው በላብ ንቅል ብሎ የወጣልይ !
አብዋ አይድከሙ፣ እውነቴን ነው ምንም የህመም ዘር ውስጤ የለም።
እንኳን ሊበርደይ ሞቆኛል!"
አልኋቸው ቅጠል ላምጣልህ ቲሉኝ በድንጋጤ ያላበኝን እግንባሬ ላይ ችፍ ያለ ላብ እየጠረግሁ።
"ታልህ ይሁን አንዳንድ በሽታ ሄድ መለስ ይላልና መልሶ ታመመህ ንገረይ !"
ብለውይ ተክፍሌ ቲወጡ አንገቴን ሽቅብና ቁልቁል እያወዛወዝሁ በጀ አልኋቸው።
እንኳን የውሸት የእውነት ብታመምስ መች ለርሶ እነግሮታለሁ ሆሆ•••ቅጠል!! አልሄድ ብላቸው እዚሁ ሊገላግሉይ አስበዋል እንዴ እኝህ ሰው።
ሳልወድ በግዳጅ በሳቸው ውሳኔ ተተሰደድኩበት ክፍል ወጥቼ በህመም ሰበብ ወደቤቴ ልመለስ ፣ ስንት አውጥቼ ስንት አውርጄይ ባመጣሁት መላ የውሸት ብታመም መዳኒት ብለው ባጠጡይ ነገር የእውነት ታምሜ ለሶስት ሰአት ያህል ሽንት ቤት ተሯሯጥሁ።
ኪሎዬም ቀነሰ፣ ወዘናዬ ተመጦ ፊቴም ገረጣ፣ አቅሜም ተዳከመ ።
ታሁን ቡሀላ እኝህ ሰው እኔና ምሽቴ ተትዳራችን መሀል ገለል ይበሉ!!! ብለን ሰላማዊ ሰልፍ ታልወጣን በስተቀር ወር ታይሞላቸው ተዛች ቤት ንቅንቅ እንደማይሉ እርግጠኛ ትለሆንኩ ተስፋ ቆረጥሁ።
አዎ እኚ ሰው በመላም በበላም አይወጡም።
ሌላ መላ ለመፈለግ መባዘኑን ይቅርብይ አልሁና የተጎዳውን አካሌን ለመጠገን ለሁለት ቀን ተክፍሌ ታልወጣ ተቀለብሁ።
ተዋቡዬም ጥሩ ጥሩውን እየሰራይ ስለምታመጣልይ በሁለት ቀን ሰውነቴም ጉልበቴም መለስ አለ።
እቤት መጠጣትም በመስኮት እንደሌባ እየገቡ ሚሽቴን ማግኘትም ምርር አለይ።
አመሻሹ ላይ ተዋቡ ታታየኝ ወጥቼ ወደ ጠጅ ቤት ሄድሁ።
ገና ገብቼ አንድ ሁለት እንዳልሁ•••
" ምን ሆነሀል ጃል? ስትገባም ሰላም አላልከኝ፣ ከገባህ ቡሀላም ሀሳብ ገብቶሀል ።
እዚህ አካልህ ተቀመጠ እይ ቀልብህ የለም እኮ በደህና ነው?" አለይ ።
ተጀርባዬ የተቀመጠው ተጠጅቤት ጋደኛቼ መሀል አንዱ የሆነው ዳምጤ።
ቀደም ብሎ ነው መሰል የገባው ሞቅ ብሎታል !
"ደህና ነይ!" አልሁት።
"አሞህ ነበር እንዴ ?ፊትህም ጭር ብሏል ሰሞኑንም መጥተህም አታውቅም ሰላም ነህ ግን ወዳጄ?" አለይ ደግሞ።
ተወኝ እስቲ ዳምጤ አልሁና ያለሁበትን ሁናታ በግርድፉ ነግሬው
"ባልና ሚስት ካንድ ወንዝ ይቀዳሉ" ይባላል የኔ ሚሽት ግን ከኔ ጋር ታይሆን ካባቷ ጋር ሳይሆን አይቀርም ካንድ ወንዝ የተቀዱት አልሁት።
ታለበት ተነስቶ ተጎኔ በመቀመጥ ለወሬ ተመቻቸና •••
"ስማ አባቷማ አባት ነው ከሱ መወለዷ ካንድ ወንዝ ከመቀዳት አይበልጥም ብለህ ነው ? ግን እሄ አባብል በመሰረቱ አይጥመኝም በጣም ነው የሚያናድደኝ !" አለይ።
"የቱ? አልሁት ።ግራ ገብቶይ።
"እሄ •••ባልና ሚሽት ታንድ ወንዝ ይቀዳሉ" የሚሉት ነገር"" አለይ።


"ተይው በቃ ተኝቶ እየቃዥ ነው ማለት ነው" አሉ አባቷ። ወድያው •••
" ማማማ •••ማ ነው" አልሁ ቀና ብዬ።
ድምጤን የታመመ ሰው ድምጥ ለማስመሰል እየሞከርሁ።
"እኔ ነዪ በሩን ክፈተው እስቲ" አለዪ ተዋቡ።
"ምን ሆነሀል አመመህ ወይ? አትይውም ከበሩ መከፈት ምን አለሽ !" አሉ ከፍቼላት ወደ ውስጥ እንዳትዘልቅ በሰበቡም አውርታኝ እንዳንታረቅ ሰግተው ነው መሰለይ።
"ምኑን ጠረ ፍቅር የሆኑትን አማች ሰጠኸኝ ፈጣሪዬ!"እያልሁ ተነስቼ በሩን ከፈትሁላትና ተጠቅልዬ ተኛሁ።
በሩን ገፋ አድርጋ ትትገባ ተከትለዋት ገቡ።
"አብዋ እያቃሰተ ነው ብሎኝ እኮ ነው ደናም አይደለህ እንዴ?" አለችይ።
አንዴ እሳቸውን አንዴ እኔን እያየይ።
"ኧረ አሞኛል! እንቅልፍ አልነሳችሁም ብዬ እንጂ እኩለ ለሊት እኮ ነው የጀመረይ።
መዥመሪያ እራስ ምታት ቲያነደኝ ቆየና ለጥቆ ደግሞ ተሆዴ ዥምሮ ብርድ ብርድ እያለ ያንሰፈስፈይ ገባ።
እሱን ቲጨርስ መላ አካላቴን በላብ የሚያጠምቅ ትኩሳት ለቀቀብይ ።
አሁን ተነጋ ደግሞ ቁርጥማት እና ብርድ ብርዱን አልቻልሁትም!"
አልሁ እንኳን ለተዋቡና ላባቷ ለሀኪምም የሚቸግር የህመም አይነት ደርድሬ ታበቃ ህመሙን በተግባር ለማሳየት ታገጬ ዥምሬ መላ አካላቴን ማንቀጥቀጥ ዥመርሁ።
"አውቂያታለሁ ያቺ እርኩስ ታትነድፈው አቀርም በይ አንቺ ሂጅና ትኩስ ትኩስ ነገር አዘጋጅለት!
እኔ ታች መንደር ልሂድና ለመድሃኒት የሚሆን ቅጠላ ቅጠል ፈላልጌ ላምጣለት"
ብለው ተክፍሌ ወጡ።
እኔና ተዋቡ ተያይተን ተሳሳቅን "በይ ሂጂ የደጁን በር ዝጊው " አልኋት።
"ኧረ ቆይ ትንሽ ራቅ ይበል !" አለችይ ፈገግ እንዳለይ።
"እዚህ ተመጡ ቡሀላ ለመዠመሪያ ግዜ ነው አይደል ግቢውን ለቀው ቲወጡ!" ስላት•••
"ሂድ ወድያ ብሽቅ!' ብላይ እየሳቀይ እሷም ተክፍሌ ወጣይና የደጁን በር ዘግታ ቁርስ ይዛልይ መጣይ።
እንደው ስከለከል ነው መሰል ተዋቡን ባየኋት ቁጥር ታሰኘይ ዥመር።
አባቷ ሰሙይ አልሰሙኝ ሳልል በነጣነት
እሷኑ ላጣጥማት ከጀልሁና ታመጣችልኝ ቁርስ በፊት እሷኑ ተሸክሜ
አልጋው ላይ•••የልባችንን አድርሰን ቁርሳችንን በልተን ትንጨርስ ሄዳ የደጁን በር ከፈተችው።
አባቷ ቲመለሱ ምን አዘጋጀሽለት?
እንዳይሏት ለይምሰል አንዳንድ ነገር ሰራርታ ወደ ክፍሌ ታመጣይ ቡሀላ •••
"በል እንግዲህ አብዋ እውነትም የታመምህ ስለመሰለው አመሻሹን እሱም "ወደላይኛው ቤት ይምጣ" ማለቱ አይቀርም እሱ ባይልም እኔው እያመመው እዚህ እንዴት ብቻውን ይተኛል እልና እላይ ቤት እንገባለን ።
እስተዛው መምጫው ስለማይታወቅ ዝም ብለህ ተኛ እኔ አሁን ስራ አለብይ ፣ ወደከብቶቹ ቤትም ተነጋ አልሄድኩም ወተቱን በወጉ አልበው ወደከተማ መውሰዳቸውን አረጋግጬ እመለሳለሁይ" ብላይ ወጣይ።
ትለደከመይ አፍታም ታልቆይ እንቅልፍ ጣለዪ።
አቧቷ እንደመጡ ተንቅልፌ ቀስቅሰው በወጉም ሳልነቃ ምሬቱ እንጥል የሚበጥስ የቅጠላ ቅጠል ዱቄት በጥብጠው ቲግቱኝ እንቢ ማለት አልቻልሁም።
ተጠጣሁ ቡሀላ አንገፈገፈይ።
እሄን ተምጠጣ እንኳን አንድ ወር አንድ አመትስ ተምሽቴ ባልተኛ ምናል አልሁ ።
እንደውም ጤነኛ የነበርሁት ሰውዬ ቅጠላ ቅጠሉን በጥብጠው ተጋቱዪ ኋላ አመመይ።
እንደገባ አጥወለወለይ ፣ ትንሽ ቆይቶ ታልወጣሁ እያለ ይተናነቀይ ገባ።
ተቀኑ ዘጠይ ሰአት ጀምሮ በየሰኮንዱ ወደሽንት ቤት ያሯሩጠይ ገባ ፣
መጣሁ ባለይ ቁጥር ወደ ሽንት ቤት መሮጡ ሰልችቶይ ፍራሼን ይዤ እሽንት ቤቱ በር ላይ መተኛት ተመኘሁ።
ምን አቀበጠይ ።
"ሳልታመም ታምሚያለሁ ብዬ የእውነት አደረከው ኧረ ይቅር በለይ ጌታዬ !"

•••••••ይቀጥላል

ክፍል - ስድስት ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
     @fkrn_be
_kalat
     @fkrn_be_kalat
╚═══❖•
🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴍᴍᴇɴᴛ         
       @fkrn_be_kalat_
bot
     ❥❥________⚘_______❥❥


👩◈ ሚስቴና አባቷ ◈👴🏻

      ክፍል - አምስት [፭]
.
.
.
በዚህ መሀል እኔና ሚሽቴ ካለንበትን ክፍል አባቷ ወደ ተኙበት ክፍል የሚያስገባው መሀለኛው በር የተንጠለጠለው መጋረጃ ገለጥ ሲል እኔም የኔ ተዋቡም እኩል አየነው ድምጣችን ብቻ ታይሆን ትንፋሻችን ጠፋ••••••
የተገለጠው መጋረጇ ወደ ቦታው ቲመለስ አይተውን ተመልሰው ሄደው ተኙ እንዴ? ብዬ ጆሮዬን ትቀስር ማንኮራፋታቸው ድምጡ ቢቀንስም አሁንም ጨርሶ አልጠፋም።
እያንኮራፉ ነው ።እሳቸው ተሆኑ መጋረጃውን የገለጡት ምንግዜ ተኝተው ምንግዜ ማንኮራፋታቸውን ቀጠሉ እያልሁ በመሀል ወደ ክፋሉ ወለል ትመለከት መጋረጃውን እንደሰው ገልጦ የገባው
ያ ጥላሸት የመሰለ የተዋቡ ድመት ሽቅብ እያየዪ ይንጠራራል።
ደንግጣ ወደ እምትቁለጨለጨው ተዋቡ ጆሮ ጠጋ አልሁን
"ኤድያ ቆሌውን ይግፈፈውና ያ ሻንቅላ ድመትሽ ነው ባክሽ ቄሌያችንን የገፈፈው እሄው እታች ቆሞ እየገላመጠኝ ይንጠራራል ፣ እኔማ አንዳንዴ አስተያየቱን ስመለከት እንደማልወደው ልቡ የነገረው እኮ ነው የሚመስለኝ ።
መጥቶ አጠገብሽ ሊተኛ አስቧል መሰል ሄዶ ላባትሽ ተማቃጠሩ በፊት ቦታ ልልቀቅለት "
ብያት በገዛ ቤቷ እንደልቧ የመሳቅ መብቷን የተነጠቀይው ተዋቡ ታፈናት ሳቅ ጋር ትትታገል እኔ ተነስቼ በገባሁባት መስኮት ወደ ክፍሌ ተመለስሁ።
መስኮቷን ስዘጋት ቅድም ትከፍታት ተጮኸችው በላይ
"ቀርርርርርርር እያለይ ትትጮህ ተሳቀኹይ ኧረ እሚያሳቅቅ ነገር ያሳቆት አቦ
ተዋቡ አቅሏን ስታ ስትጬህ አፏን አፈንኋት ይችን መስኮት ምኗን ላፍናት እናንተው?"
ጥርሴን መንከሴ ተጩኸት ያስጥላት ይመስል ጥርሴን ነክሼ ዘጋኋትና "ነግቶ ተዋቡ ትትነሳ ተውስጥ ትሸጉረዋለይ " እያልሁ ታጣፊዋ አልጋዬን ቁልቁል ታያት አስጠላችኝ።
በላብ ተሚያጠምቅ የፍቅር እሳት ተሚዘንብበት አልጋ ላይ አውርደህ በረዶ ላይ ያስተኛኸይ የተዋቡ አባት የስራህን ይስጥህ ብዬ ሽቅብ ተራገምሁና ተጠቅልዬ ተኛሁ።
ተሁለት ቀን ቡሀላ ዳግም መስኮቷን ከፈተችልይ። ተመግባቴ በፊት
"አባቷ ሰማ አልሰማ እያልሁ ታልሳቀቅ አልጋውንም ተዋቡንም እያስጮሁክ ታሰኛይ እኔም እየጮሁክ የልቤን በማድረስ አባቷ በብስጭት በውድቅት ለሊት በሮ እንዲጠፋ ታላረግሁ እኔ አንዳርጌ አይደለሁም !!"
ብዬ ፈክሬ ገባሁ። ተገባሁ ኋላ ግን ተዋቡ "ተው ቀስበል አለሜ አብዋ እንዳይሰማ !"
እያለይ ስለምነይ ለሷ ትል ተውሁት። አቧቷ በመሀል ድንገት ማንኮሯፋቱን አቁሞ መገላበጥ ቲያበዛ ተዋቡ •••
"ታይሰማን አይቀርም!" ብላ በጭንቀት ነፍሷ ልትወጣ ደረሰይ። እኔም የሷ ጭንቀት ትላስጨነቀይ በመሀል አቋርጬ ድምጣችንን አጥፍተን ትንሽ ቆየንና መገላበጡን አቁሞ ማንኮራፋት ቲጀምር ተነስቼ ወደክፍሌ ተመለስሁ።
ተስድስት ቀን በላይ በግዜ እየገባሁ እክፍሌ እያመሸው ብቆይም አባቷ ሀሳባቸውን ለመቀየር ፍንጭም ታያሳዩ ስለቆዩ ተበሳጨሁ።
እኝህ ሰው በምን ብልሀት ተኔም ተሚሽቴም አናት ላይ ሊወርዱ እንደሚችሉ ቁጭ ብዬ ታሰላስል ዋልሁ። አንድ ሀሳብ ስለመጣልይ ተዋቡ ማታ እራት ይዛ ክፍሌ ትትመጣ ያሰብሁትን ነገርዃት።
ምን አሰብሁ መሰለሽ ውብ አለሜ እኔ ሆን ብዬ ታምሚያለሁ ብዬ እተኛለሁ ። ያኔ አንቺ እንደተጨነቅሽ ሆነሽ •••
"እንዲህ ታሞማ ብቻውን እይህ ክፍል ውስጥ መተኛቱ ደግ አደለም እላይ ቤት ተኝቶ ላስታመው እይ ብለሽ ሀሳብ ታቀርቢያለሽ ።
መቼስ ሰው ናቸውና ታምሜ እያዩ አይሆንም አይሉም አደል?" ስላት።
"ኧረ አይልም አባዬ እኮ እንደሀይለኝነቱ ሁሉ ሩህሩህ ነው !" አለይ።
"ደግ እንግዲህ አንዴ እላይ ቤት ተገባሁ ቡሀላ ተሻለኝም አልተሻለኝም እይህ የሚቀመጡበት ምህንያት ስለማይኖራቸው መሄዳቸው አይቀርም"
"ልክ ብለሀል! አወይ አለሜ እንደው ምን ስትል እሄን መላ አሰብኸው በል !
ታብዋ ጋር ታንቀያየም በሰላም ችግራችንን የምንፈታበት ብልህ መላ ነው።
በል ነገ ተምኝታህም ሳትነሳ የታመምህ መስለህ ተኛ!" ብላይ ወጣይ።
አባቷ ጥዋት ጥዋት እኔ ታለሁባት ክፍል በር ላይ ጠሀይ እንደሚሞቁ አውቃለሁ ። ተንቅልፌ ቀደም ብዬ ብነቃም ሰአታቸው እስክትደርስ እዛው ትገላበጥ ቆየሁ።
ሁለት ሰአት ላይ ተምኝታዬ ተነስቼ በበሩ ፍንጭት ወደ ውጪ አጮለቅሁ።
እተለመደው ቦታ በርጬማቸው ላይ ተቀምጠው ጠሀይ እየሞቁ ዳዊት ቲደግሙ አየኋቸው••••
"ተሀምሳ ዳዊት የልብ ቅንነት" አለይ እምዋ
የኛን ትዳር እያሳመሙ ዳዊት ቢደግሙ ምን ዋጋ አለው።
ለሊቱን አብረን እንዳንሆን መከልከላቸው ታያንስ ቀንም እንደወንድ ወጣ ብለው ስለማይመለሱ እምንገናኝበትን ቀዳዳ ሁሉ ደፍነው በናፍቆት ርሀብ እየቀጡን ዳዊት ትለደገሙ ተቅጣት የሚያመልጡ መሰላቸው እንዴ?
ተመጡ ጀምሮ የለሊቱ ይሁን ቀን እንኳን ተቤት አይወጡም እኮ እናንተው
ተሁለት እስተ አራት ሰአት ጠሀይ ቲሞቁ ይቆያሉ ።
ጠሀይዋ አየል እያለይ ትትመጣ ተነስተው ግቢ ውስጥ ወዳለ አንድ ትልቅ ዛፍ ስር ይሄዱና ቆዳ ለበስ የሆነይ ራድዬናቸውን ከፍተው ምሳ ሰአት እስቲደርስ ጣብያ እየቀያየሩ የባጥ የቆጡን ቲሰሙ ይቆያሉ።
ምሳ በልተው ትንሽ እረፍት ይወስዱና ግቢ ውስጥ እየተንጎራደዱ እሚሰራ ስራ ቢያጡንኳ ምንም ያልሆነውን የግቢውን የንጨት አጥር ቲያጠባብቁ ይውላሉ።
የኛን የትዳር አጥር እያፈረሱ ምንም ያልሆነው የግቢያችንን አጥር ቲያጠባብቁ ታይ "እኝህ ሰው ግን ተቀልባቸው ጋር ታይጣሉም አይቀሩ!" እላለሁ።
በበሩ ፍንጭት መኖራቸውን ታረጋገጥሁ ቡሀላ ወድያው ወደ መኝታዬ ተመለስሁና እኔና ውብዬ ባቀድነው መሰረት እንዳመመው ሰው ማቃሰት ጀመርሁ።
"እህህህም •••እህህህም •••እትትትትት እህህህም•••" ለደቂቃዎይ እንዳቃሰትሁ እሳቸው ሰምተው ምንሆንክም ታይሉኝ እኔ ደከመይ ።
ዦሮዎትም አይስማ እንዴ የተዋቡ አባት አልሁና ትንሽ አረፌ ፣ ትንፋሽ ወስጄ ድምጤን ዘለግ አድርጌ ማቃሰቴን ቀጠልሁ ••• ።
ምንም ታይሉዪ ቆይተው ተዋቡ እምኝታ ቤቷ ሆኖ ሰምታዪ ነው መሰለዪ (መቸስ መስማቷ አይቀርም)
"ባሌ ምጥ ላይ እንዳለይ ሴት እሄን ሁሉ ቲያቃስት አባዬ ምንሆንክ የማይለው አልሰማሁም ለማለት ነው? " ብላ ነው መሰል ተትልቁ ቤት ብቅ ትትል እሳቸውም የሷን መውጣት ጠብቀው•••
"ተዋቡ እሄ ልዥ በደናው ነው?" ብለው ቲጠይቋት ትለሰማሁ ማቃሰቴን ገታ አድርጌ ምላሿን መጠበቅ ዠመርሁ።
እንዳልሰማይ ስትሆን ደግመው ጠየቋት።
" ማነው እሱ ?" አለይ እንዳላወቀይ መስላ።
"ያንቺው አንዳርጌ ነዋ !" አሉ የተዋቡ አባት አያ ዘርጋው።
ጉድ እኮ ነው እናንተ የሷ መሆኔን ታወቁ ዛድያ የሷን ነገር ለኔው ትተውልይ ብሄዱ ምናለ ያንቺው እያሉ ተሷ መነጠል ምን ይሉታል? ።
ባልና ሚሽት ማራራቅ ለትዳር ይጠቅማል የሚል ጥሁፍ ተይትኛው መጥሀፍ ላይ ነው ያነበቡት? እያልሁ በልቤ የኔዋ ተዋቡ•••
"ኧረ እንጃ ! ምን ሆኗል ? መችስ ተነሳ? ምን ሰማህ አቡዋ!?" ትትል ሰማሁ ። አይ ተዋቡ ያልተስተማረይ ምሁር ነይ እኮ እምዋን ይንሳይ።
"እኔ ምን አውቃለሁ ? እየቃዥ ይሁን አሞት ብቻ ሲያቃስት የሰማሁ መሰለዪ" አሏት።
"መች አሁን ነው?" አለይ ተዋቡ።
ኧረ እዚህ ተተቀመጥሁ ዥምሮ እያቃሰተ ነው በጤናውም አይመስለይ!"አሉ።
ጆሮዬን ማመን ተሳነይ ዛድያ ተተቀመጡ ጀምሮ እየሰሙዪ ኖሯል እንደዛ ትንፋሽ እስቲያጥረይዪ ታቃስት ዝም ያሉይ !! እኔስ በጤናዬ ነው እርሶ ግን ጤነኛም አይመስሉዪ አልሁ ባይሰሙኝም ንዴቴን ልትንፍሰው ብዬ።
"እስቲ ቆይ" አለችና ወደ በሬ ተጠግታ አንኳኳይ።
ቲያቀብጠኝ እንዴ ትድገመው ብዬ ዝም ስል•••


ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።


   ፈጣሪ አገራችንን ከክፉ ይጠብቃት!
    ₂₀₁₇ መልካም የደመራ በዓል!❤️

​​​​               ᴊᴏɪɴ ᴀɴᴅ sʜᴀʀᴇ
             🌼 ፍቅርን በቃላት 🌼
    ┄┄┄┄┉✽‌»‌🌼✿🌼»‌✽‌┉┉┄┄┄


አንቺ ታታለቅሽ አልጋው ምኔ ተነካ ብሎ ነው የሚያለቅሰው ውብ አለም !" አልኋት ጆሮዋን እየነከስሁ።
"አብዬ ሰምቶ ላባብለው እንዳይል ብዬ ነው" ትትለኝ•••
"አባትሽ ቲያንኮራፋ የሚያወጣው ድምጥ ታልጋው ለቅሶ ይከፋል እኮ አይሰማሽም እንዴ ?"እያልሁ ተስር የነበርይውን ተወቡን ብድግ አርጌ ተላይ እንድትሆን ታመቻቻት ተላይ ቁብ ብላ ትጋልበይ ጀመር ።
ትንሽ ቆይታ የአባቷን መኖር ረሳይው መሰለይ ተሚያንኮራፉት አባቷም ተሚያለቅሰው አልጋም በላይ መጮህ ትትዥምር መልሼ ታታች አረግኃትና እስትንጨርስ ድረስ አፍንጫዋን ትቸላት ባንድ እጄ አፏን በመላ አካላቴ መላ አካላን አፍኝ አስጨንቃት ዠመር።
ሁለታችንም ተንዘፍዝፈን ጣፋጭ ቆታችንን እንደቋጨን••• በጀርባችን ተንጋለን በፀጥታ በተግባር የቋጨነውን በሀሳብ ትናጣጥመው ቆየን ።
እዛው እንደተንጋለልሁ እንቅልፍ ሊወስደይ ቲከጅል ፋኖሷን መልሳ አበራቻትና•••
"አንተ እይሁ ልተኛ ነው እንዴ ተነስ እይ ወደ ክፍልህ ሂድ ሆሆሆሆ!" አለይ ። ድምጧ እንዳይሰማ አፏን ገጥማ እየሳቀይ።
ብድግ አልሁና ተመውጣቴ በፊት ወደ ጆሮዋ ጠጋ ብዬ•••
"ተወገኑ የተለየ አንበጣ ይሆናል ፌንጣ!" ትል ነበር እምዋ፣ እግዜር ይስጣቸው አባትሽ !
ታንቺ ተምሽቴ ለይተው ተባልነት በመስኮት እየዘለለ ወደ ሚገባ ውሽማነት ስለቀየሩይ አመስግኝልኝ እሺ?!"
አልኃት። ሊያመልጣት የሚታገላትን ሳቅ አፏ ውስጥ ብርድ ልብሱን ጎስጉሳ አስቀረችው።
በዚህ መሀል እኔና ሚሽቴ ካለንበትን ክፍል አባቷ ወደ ተኙበት ክፍል የሚያስገባው መሀለኛው በር የተንጠለጠለው መጋረጃ ገለጥ ሲል እኔም የኔ ተዋቡም እኩል አየነው ድምጣችን ብቻ ታይሆን ትንፋሻችን ጠፋ

•••••••ይቀጥላል

ክፍል - አምስት ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
     @fkrn_be
_kalat
     @fkrn_be_kalat
╚═══❖•
🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴍᴍᴇɴᴛ         
       @fkrn_be_kalat_
bot
     ❥❥________⚘_______❥❥


👩◈ ሚስቴና አባቷ ◈👴🏻

       ክፍል - አራት  [፬]

   ✍ (በጥላሁን ተስፋዬ)
.
.
.
ተዋቡም እራቴን ይዛልይ እንደገባች ሞቅ እንዳለይ አስተውላ ነው መሰል
እራቱን አስቀምጣ ተጣድፋ ልትወጣ ስትል ክንዷን ያዙሁና ጎትቼ ታጣፊዋ አልጋዬ ላይ አንጋለልኋት•••
አይኗን እያስለመለመይ ሽቅብ እያየችይ •••
"ምን ልትሆን ነው አንዳርጌ እንደው በልጃችን እንደው •••" እያለይ ተአርባ አራቱ ታቦት ያልጠራችው የለለ እስቲመስለይ ድረስ እንድተዋት ስለምነይ ሁለመናዬ አልታዘዝልህ አለይ።
እንኳንስ እንዲህ ለምናይ ደስ ታላላት በስተቀር ታለፍጎቷ ገላዋን መንካት መች ይሆንልኛል።
እንደለቀቅኋት ብድግ ብላ ልብሷን እና ሻሿን ማስተካከል ጀመረይ። ተመውጣታ በፊት አንድ ጥያቄ ልጠይቃት ከጀልሁና•••
"ተዋቡ !" ብላት
"ወዬ አለሜ!" አለይችኝ።
እሷን ውብ አለም ብዬ ትጠራት ደስ እንደሚላት ነግራኛለይ። እኔም ብሆን ለሷ ባልነግራትም "አለሜ!" ብላ ስትጠራይ ውስጤ ተጋግሮ የተቀመጠ የሚመስል አንዳች የፍቅር ስሜት ፍንቅል ሲል ይታወቀኛል።
ግን••••አልኃት። "ግን ምን ?" አለችይ ለመሄድ እየተቻኮለይ።
"ተቀናት በፊት መስኮትሽን ሳንኳኳ እየሰማሽ ነው አደል ዝም ያልሽኝ !?" ስላት•••
"ኪኪኪኪኪኪ ••••እና ብሰማህስ ምን እንድሆን ጠብቀህ ነበር እእእእ!?" አለይ ።
"ምናል መስኮቱን ብከፍችው ?"
"ሂድ ወድያ አንተ ብሽቅ ሆሆሆሆ•••ኧረ አንተስ ጉደኛ ነህ!" እያለይ ተክፍሌ ስተወጣ•••
ዛሬ ሳንኳኳ እንድትከፍችልይ አልኋት። መልስ ሳሰጠይ ወደ ትልቁ ቤት ገባይ።
እሷን እያሰብሁ፣ ሁኔታዋን እያስታወስሁ ያመጣይልይን እራት በልቼ፣ የቀረችኝን ጠጅ ጠጥቼ እንደጨረስሁ ተመተኛቴ በፊት መስኮቷን ጎተት አርጌ ሞከርኋት ። አልተከፈተይም። ትንሽ ቆይቼ በስሱ ኳኳኳ አረግሁና አልጋዬ ላይ ተንጋልዬ ድምጤን አጥፍቼ መጠባበቅ ጀመርሁ ።
ድምጥ የለም።መብራቱ ጠፋ ሳትከፍትልይ ተኝታለይ ። እኔም ተኛሁ።
ጥዋት እባቷ ተቤቱ ጓሮ ወዳለው ሽንት ቤት ቲሄዱ ጠብቃ መጣይ ።
ማታ ለምን እንዳልከፈተይልኝ ጠየቅኋት።
"እብድ!" አለችይ እየሳቀይ። እኔው ነኝ እብድ አልሁና••••
"ውብ አለሜ ግን እንደው በሌላ ነገር አትውሰጅብይና አባትሽ ግን እኔ ያልሁት ታልሆነ ተማለታቸውና ተጨቋኝ ባህሪያቸው ባሻገር ጤናቸው ተነ ሙሉ ክብሩ አብሯቸው ያለ ይመስልሻል ??" ስላትይ•••
"እእእእእ ምን ለማለት ፈልገህ ነው አንዳርጌ ? እስቲ ልትል የፈለግኸውን ግልጥልጥ አርገህ ንገረይ !?" አለችኝ እየተቆናጠረይ።
"ምነው ተናደድሽ እንዴ ተዋቡ !" አልኋት ነግሯ አላምርህ ቲለኝ ጥያቄዬን በንጭጩ ልቃጨው እያሰብሁ።
"ኧረ ምን አናደደይ ተደም ብዛት ውጪ ሌላ ምንም በሽታ እንደለለበት ነው የማውቀው አንተ የምታውቀው ታለ ንገረይ?! አለች ቆምጨጭ እንዳለይ።
"ሰው የሚያስበው በጭንቅላቱም አይደል ዛድያ እሄ ደም ብዛት የሚባል ህመም ተማሰብ ጋር የሚያቆራኘው ነገር ይኖር ይሆን እንዴ?
"ቆይቆይቆይቆይ ወዴት ወዴት አባትሽ ማሰቢያቸው ተቃውሷል ልክ አይደለም እብድ ናቸው እያልኸኝ መሆኑ ነው አንዳርጌ ነው ንገረይ !?" አለይ እንደመርገፍገፍ እያደረጋት።
ሁኔታዋ ታየው ነገር ነገር ሸተተይ ። ለምን እንዲህ ብሎ ጠየቀይ ብላ ትትንጨረጨር ገና በወጉ ሳንታረቅ መልሷ ልትጣለይ እያኮበኮበይ መሆኑ ታወቀይና
ኧረ እኔ እንደዛ አልወጣኝም ተዋቡ ምን ሆነሻል ፣ ለምን ነገር ነገር ይልሻል በይ!! እኔ እንዲሁ የምታውቂው ነገር ታለ ብዬ ጠየኩሽ እይ እብድ ናቸው የሚል ነገር ታፌ ወጥቷል ተዋቡ?!" አልኋት ። በረድ አለይና•••
"እኔ እንግዲህ ተደም ግፊት ነው ደም ብዛት ? ውጪ ሌላ ነገር ሲያመው አይቼም አላውቅ እሱም ሌላ በሽታ እንዳለበት አልነገረኝም !" አለች ፈርጠም ብላ።
"እሱማ እሳቸው እንዴት ይነግሩሻል? ማሰቢያውን የታመመ ሰው በምኑ አስቦ ህመሙን ያውቀዋል ? በዙርያው ያለ ሰው ነው እይ የሚረዳው አንቺ ታልነገርሻቸው ማን ይነግራቸዋል ? አልሁ በልቤ ታፌ አውጥቼ ብናገረው አጠገቧ ያለውን ማንቆርቆርያ አንስታ እንደምትወረውርብኝ መች አጣሁት።
እሷስ ትወርውር ተጠቡ ቡህላ ሌላ ሁለተኛ ወር ያባቷ ቅጣት ተሚመጣ አፌን ብዘጋ እና በውስጤ ብልጎመጎም ይሻላል ብዬ እንጂ።
"ምንድን ነው ዝም ብለህ የምታየኝ !?" በውስጤ እያወራሁ ሳፈጥባት ።
እንግዲህ በጤናቸው ሆን ብለው ተሆነ እንዲህ አይነት ፍርድ የፈረዱብን •••
እዚህ ሰው የለውም፣ መሬቱን ፣ የወተት ከብቶቹን ፣ ቤቱ እና ንብረቱንም እኔ ሰጥቿቸው ነው ትዳር የመሰረቱት !!
ስለይህ በትዳራቸው ላይ ተልጄ ባል በላይ እኔ ነኝ የምወስነው ብለው ነው ማለት ነው እንዲህ የሚሆኑት ግድያለም!
ልጄን ይዘህብይ አትሂድ እዚሁ ሁኑ ትላሉ እይ እኔ ትዳሬን ለማቆም የሚበቃ ወረት አጥቼ ነው ተዋቡ ? አንቺን ብዬ እንጂ እንደሳቸውማ ቢሆን ቤቱን ጥየላቸው በሄድኩ!" ስላት•••
አባትሽ እብድ ነው አልከይ ብሏ ቁጣ ቁጣ ሲላት የነበረይው ተዋቡ ወድያው ቁጣዋ ወደ ድንጋጤ ቲቀየር ፊቷ ላይ አየሁ። ክው አለይ። እንዲህ ስደነግጥ አይቼም አላውቅ።
"ውይ በስመአም የሰይጣን ጆሮ አይስማው!
የምን ሰይጣን ነው እንዲህ ያለውን መጥፎ ሀሳብ ሹክ ያለህ በል!?" አለይ።
"ተይኝ ተዋቡ እንዳንታረቅ መሀል ገብተው የፀብ እድሜ ከማራዘም በላይ ሰይጣን መሆን ተዌት ይመጣል?!።
አንዱዬ ሙት እንደዛ አስቦ አይደለም ያባዬን ጠባይ ስለማታውቀው ነው እሺ?!
አዳራ አለሜ ታሁን ቡሀላ እንዲህ እንዳታስብ !" አለችኝ። መጥታ ወገቤን አጥብቃ እያቀፈችኝ።
ምን ላርግ አለሜ አንቺ ጠጅን እይህ ድረስ ስላመጣሽልይ ብቻ ደስተኛ እምሆን ይመስልሿል!
ያንቺ ናፍቆት በምን ይተካል ? ናፍቀሽኝ እኮ ነው እንዲህ ንጭንጭ የሚያረገይ ውባለሜ!" አልኋት።ቃል ታትተነፍስ ደረቴ ላይ እንደተለጠፈይ ቆየይና •••
"ልሂድ በቃ" ብላ ልትወጣ ስትል እጇን ያዝ አድርጌ ዛሬስ መስኮቱን ከፍተሽው አተኝም ?" አልኋት።
ፈገግ እንዳለይ እጇን መንጭቃይ ወጣይ።
አባቷ እንቅልፍ እስቲጥላቸው እራቴ በልቼ ቀስ እያልሁ ጠጄን ታጣጥም ሰአት ገፋሁና
አልጋዬ ላይ ወጥቼ መስኮቷን ጎተት ታረጋት ከፈት እለይ።
አይ ውብአለም ተቸግረሽ እይ በኔ አጨክኝም እኮ እያልሁ ልብሴን አወላለቅሁና በቁምጣ እሷ ዘንድ ልሄድ ተሰናዳሁ። አልጋዬ ላይ ወጥቼ እስተመጨረሻው ልበረግዳት ጎተተተተተት
ታረጋት••••
"ቀርርርርር እያለይ ታሳብቃለይ ።
ያንቺ ማቃጠር ደሞ ምን ይሉታል?አልሁና•••
በብልሀት ድምጧ እንዳይጎላ አድርጌ ለመክፈት በሞክርም ታልጮህ አልከፈትም ትላለይ እንደፍጥርጥርሽ ብዬ እያንቃረርይ ከፈትሁና ዘልዬ ገባሁ። ትደናበር አቅጣጫ ስቼ አባቷ ታሉበት ክፍል እንዳልገባ ብላ ነው መሰል መብራቱን አጥፍታ ፋኖሱን በደበዘዝ ሀይል አብርታ ብርሀኑ ተሷ መኝታ ውጪ እንይሄድ ባንድ በኩል በጨርቅ ጋርዳዋለይ።
ድምጤንም ኮቴዬንም አጥፍቼ ተዋቡ ወደተኛይበት አልጋ እየተጠጋሁ። አባቷ እዛኛው ክፍል ተኝተው ቲያንኮራፉ ተሰማኝ።
አልጋ ውስጥ እንደገባሁ ፋኖሷን ደረገመቻት።
ተዘጋጅታ ስለጠበቀይኝ መሳብም ማውለቅም ታይጠበቅብይ " ግባ በሞቴ "
እያለ ተላይ እስተታች የጨርቅ ዘር ታይለብስ የተንጋለለውን ፣ ተሳምንት በላይ የናፈቀይን ፣ የተዋቡን ገላ እያተረማመስሁ አስጨንቀው ጀመር።
ተዋቡዬ ትንፋሿ ቁርጥ ቁርጥ እያለ•••
"አንተ ቀስ በል እይ አልጋው እስቲያለቅስ አትነቅንቀይ!" አለይ።


"እና የሳቸው ደም ብዛት እንዳይነሳ የኔ ደም እየተንተከተከ አንድ ወር ልከርም ነው ተዋቡ?
አንድ ወር ሙሉ በይህ ሁኔታ እንድንቀጥል አንቺም ፈረድሽ ተዋቡ?!" ስላት ።
ወደኔ ጠጋ አለይና ፁጉሬን እየደባበሰይ•••
"አንተም እኮ ተሱ ጋር እልህ የተጋባህ ነው እምትመስለው!
እስቲ አሁን እሱ እዚህ ተመጣ ቡሀላ ሁለት ቀን ሄዶ መጠጣት ምን ይሉታል ?! ያው ታፍህ ባታወጣውም ምን ታመጣለህ ጠጣለሁ እያልህ እኮ ነው እሚመስለው!
እንደው ለኔ ስትል እስቲ አንዱዬ ለትንሽ ቀን ጠጥተህ እና አምሽተህ መምጣትህን ተወው።
ምናልባት ያኔ እሱም መለስ ይልና ሀሳቡን ይቀይር ይሆናል!" ብላ አይናይኔን ስታየይ እኔም መልስ ሳልሰጣት ዝም ብዬ አየኋት።
"እእ እንደው በኔ ሞት ለትንሽ ቀን ተወው የኔ አለም እ ለኔ ስትል!!
ምናልባት አለመጠጣትህ እዚህ ብቻህን ትተኛ ተንዴቱ ጋር ተዳምሮ እንቅልፍ የሚነሳህ ተሆነ ደግሞ እኔ አንዳንድ ነገር ገዛለሁ እያልሁ ከተማ እወጣና በዛች ሶስት ሊትር በምትይዘው ቢጫ ጀርካን ሶስትም አራትም ብርሌ ጠጅ ተዛው ተምትጠጣበት ቤት ገዝቼልህ እመጣና አብዋ እንዳያይ ዘንቢሌ ውስጥ ሸሽጌ እዚሁ ክፍልህ ውስጥ አኖርልሀለሁ።
እራት ተበላህ ቡሀላ በርህን ዝግት አርገህ ትጠጣና ትተኛለህ እ አንዱዬ??•••አብዋም ያን ቀን እሄ ይመጣል ብዬ ታላስብ የንዴቴን ታወራ በጠጣህ ቁጥር እምትተናኮለይ ነው የመሰለው ለዛ ነው።
ትንሽ ቀን እንዲህ ብናረግ ሀሳቡን ይቀይር ይሆናል ብዬ እኮ ነው እሺ በለኝ ስሞትልህ !!"
ብላ ጉንጬን ሳም ስታረገይ እንደው አንዳች ስሜት መላ አካላቴን ነዘረይ ።
"እሺ እንዳልሽው እናረጋለን የኔ መለኛ!" አልኋት ፈገግ እያልሁ።
አብዋ ምሳ በልቶ ጋደም እንዳለ እንቅልፍ ጥሎታል ቲነቃ እንዳያጣይ ልሂድ በቃ እንደተባባልነው ተዛሬ ጀምሮ ጠጁን እኔው አመጣልሀለሁ እሺ የኔ ባል!" ብላይ ትትወጣ አንጀቴን በላችይ።
እንዳለችው ያንኑ ቀን ጠጁን ገዝታ ሸሽጋ አስገባችልይ ተራት ቡሀላ ጠጥቼ ተኛሁ።
በበነገው አምጥታ ክፍሌ ያስቀመጠችልኝን ጠጅ ግን ገና እራት ሳታመጣልኝ ቀደም ብዬ ጀምሬው ስለነበር እራት ይዛልይ ስትገባ ሞቅ ብሎይ ነበር።
ተዋቡም እራቴን ይዛልይ እንደገባች ሞቅ እንዳለይ አስተውላ ነው መሰል
እራቱን አስቀምጣ ተጣድፋ ልትወጣ ስትል ክንዷን ያዙሁና ጎትቼ ታጣፊዋ አልጋዬ ላይ አንጋለልኋት

•••••••ይቀጥላል

ክፍል - አራት ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
     @fkrn_be
_kalat
     @fkrn_be_kalat
╚═══❖•
🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴍᴍᴇɴᴛ         
       @fkrn_be_kalat_
bot
     ❥❥________⚘_______❥❥


👩◈ ሚስቴና አባቷ ◈👴🏻

       ክፍል - ሦስት [፫]

   ✍ (በጥላሁን ተስፋዬ)
.
.
.
ለሶስተኛ ግዜ አንኳኳሁ ሰምታኝ ነው መሰለኝ አይኗን ገልጣ እኔ ክፍል ውስጥ ሆኜ እሷን እያየሁ ወዳለሁበት መስኮት ተመለከተች ።የምታየኝ መስሎኝ ፈገግ አልሁ •••
አወይ መጃጃል! እንዲህ ጅል ላረጉይ አባቷ የስራቸውን ይስጣቸው አቦ እያልሁ እንደመንቀሳቀስ ስትል ተነስታ መስኮቷን በመክፈት አባቷ ታይሰሙ ልታስገባይ መስሎይ ትንፋሼን አጥፍቼ ትጠባበቅ ቀና አልይና መብራቱን ደረገመችው።
መብራቱን አጥፍታ ልከፍትልይ ይሆን ብዬ ብጠብቅም ድምጧን አጥፍታ ተሸፋፍና ተኛይ ።
"ያባቷ ልጅ!!"
አልሁና ታጣፊዋ አልጋዬ ላይ ሆድ ውስጥ እንዳለ ፅንስ ተጣጥፌ ተኛሁ።
በንጋታው ሆን ብዬ አባቷ ታይነሱ ቀደም ብዬ ተዋቡ ቁርስ በምታዘጋጅበት ሰአት ተነሳሁ።
ተዚህ በፊት እኔና ተወቡ የቱን ያህል ብንጣላ ተሁለት ቀን በላይ መኮራረፍ እንደማይሆንልን ጠንቅቄ ትለማውቅ በድፍረት ላናግራት ወሰንሁ።
ተትልቁ ቤት እኔ ታለሁበት በታች ወዳለው ማድ ቤት ሽር ጉድ እያለይ ቁርስ እያሰናዳይ ነው።
ለሽንት እንደሚወጣ ሰው ተክፍሌ ወጥቼ ሽንት ቤቱ ወዳለበት አቅጣጫ አንድ ሁለት እርምጃ ተራመድሁና ማድቤት መሆኗን አየት አድርጌ ታበቃ መለስ ብዬ ወደ ማድቤቱ ሄድሁ።
እማድቤቱ በር ላይ ቆም እንዳልሁ ቀና ብላ አየችይና ፊቷ ላይ ምንም ለውጥ ታታሳይ ምንም ታትለይ ስራዋን ቀጠለይ።
"ተዋቡዬ የኔ ድንብሽቡሽ እስቲ ንገርኝ እንደው እውነት አስችሎሽ ከልብሽ ጨክነሽ ነው እራት ቀን ሙሉ ጥርቅም አርገሽ የዘጋሽይ? አልኋት።
መልስ ሳትሰጠይ ዝምብላ ትንጎዳጎዳለይ።
"እኔ አሁን አንድ ነገር ብቻ ነው እምፈልገው እውነት ተልብሽ ተቀይመሽኝ ጠልተሽኝ ተሆነ ግልጡን ንገሪኝ ?! " ብላት አሁንም መልስ የለም ።
ብድግ ብላ ልትወጣ ትትል እግሬን ከፈት አርጌ መውጫ አሳጣኋትና •••
"ታልነገርሽኝ አታልፊም!" አልኋት።
"አንተ ወግድ ልለፍበት ኦሮ !" ብላ ያንን የበቆሎ እሸት የመሰለ ጥርሷን ብልጭ አድርጋ ፈገግ ትትልልይ ውስጤ እየፈገገ እግሬን ሰብስቤ አሳልፍኋትና ሽንቴን ልሸና ወረድሁ።
በቃ አበቃ እኔና ተዋቡ ታረቅን ። ድሮስ አባቷ ናቸው እይ የነገር እድሜ የሚያረዝሙት የኔ ተዋቡ በተጣላን እና በተናደደች ሰአት ንዴት እና እልኋ የምታረገውን ቢያሳጣትም፣ ንዴቷ ቲበርድላት ሁሉን ነገር ወድያው የምትረሳ ልቧ ውስጥ ለፍቅር እይ ለቂም የሚሆን ቦታ የሌላት፣ ገራገር ነይ።
ምን ያህል እንደማፈቅራትም ጠንቅቃ ታውቃለይ።
መነጋገር እንኳ ታያስፈልገን እኔና እሷ ተያይተን ብቻ የምንፈታውን ነገር ነው እንግዲህ ጠባችን እና መኳረፋችን ለወር እንዲራዘም የፈረዱብን እኛ አምባገነን አባቷ።
መሀላችን እንደጠብ ግድግዳ ተገሽረው ምን አርጉ እንደሚሉን እንጇ!።
ተሽንት ቤት ትመለስም ተያይተን ተሳሳቅን።
እንደጥዋት ጠሀይ ቀስ እያለ ደም በሚያሞቀው በተዋቡ ፈገግታ ደስ እያለኝ የጠባይ ማረሚያ እስር ቤት መስሏ ወደምትታየኝ ክፍሌ ገብቼ ጋደም አልሁ።
እኔና ተዋቡ ስለታረቅን ደስ ቢለኝም ተዋቡ "በቃ እኛ ታርቀናል ያንተ እዚህ መሆን አያስፈልግም!" ብላ አባቷን እንድሸኛቸው ብነግራት ደፈራ እንደማታደርገው እና እሺ እንደማትለኝ እያሰብሁ ምን ማረግ እንዳለብይ ታስብ ቆየሁ ።
እኔው እራሴው አሁኑኑ አባቷ ተንቅልፋቸው ሲነሱ ጠብቄ •••
"የተዋቡ አባት ! በቃ እኛ ታርቀናል እርሶ ተፈለጉ እዚሁ መክረም ታልያም መሄድ ይችላሉ እንደምርጫዋ!እኔን ግን ተንግዲህ ቡሀላ ተምሽቴ ጎን ተመተኛት ሊከለክሉይ አይችሉም ነው የምላችው !"
እያልሁ ትፎክር ቆየሁና እንደተነሱ አሁን እንዲህ ብላቸው •••
"ተደፈርሁ!! ክብሬ ተነካ ! "ብለው እንቧከረዩ ማለታቸው ታያንስ እኔ ያልሁት አንድ ወር እስቲሟላ ተዋቡ ልጄ እኔው ጋር ትቆያለይ ብለው ይዘዋት ተመሄድ የማይመለሱ መሆኑን ታስበው ፈርቼ ተውሁት።
ተዛ ይልቅ ተምሽቴ ጋር እንዴት አድርገን እንድሄዱ ማድረግ እንዳለብን ብንማከርባት እንደሚሻል ወሰንሁ።
ሁለት ቀን ተዋቡን አግኝቼ ላወራት ባደፍጥም አባቷ ለምን ቆየሽ እንዳይሏት ነው መሰል ምግብ እክፍሌ አምጥታልይ "እንዴት ነህ አንዱዬ?"
ብላ ፈገግታዋን ብልጭ እያረገይ አፍታም ታትቆይ ውልቅ ስለምትል ላወራት ቸገረይ።
አባቷን ያላከበረይ ባላን አታከብርምና ሚሽቴ ላባቷ ያላት ክብር ደስ ቢለኝም በትዳሯ በህይወታ መሀል ገብተው እኔ ያልሁት ታልሆነ እኔ የወሰንሁት ታልተተገበረ ቲሉ ተቀብላ ፍላጎታቸውን ለሟሟላት እየተሽቆጠቆጠይ ላማውራት እንኳን ግዜ ስታሳጣይ ስትቀር ዴሜ ፈላ።
በይህ ምክንያት አሁንም አባቷ ተመጡ በሰባተኛው ቀን ወደ ጠጅ ቤት ሄድሁ።
ሞቅ ብሎይ ተጠጅ ቤት እንደወጣሁ እቤት እስትደርስ የውስጤን ብሶት በንጉርጉሮ እየተነፈስሁ ሄድሁ።
ደርሼ ክፍሌ ተገባሁ ቡሀላም ዝፈን ዝፈን አለይ ። ዘፍናለኋ! በገዛ ክፍሌ አታንጎራጉር የሚለኝ ታለ አያለሁ እንግዲህ አልሁና
ተቀብል ብዬ ድምጤን ከፍ አድርጌ መዝፈን ጀመርሁ •••
እህህ ደማሙ እህህ ደማሙ
እህህ ደማሙ እህህ ደማሙ
እንኳንስ ላአንድ ወር ቢተኙ ላመት
ሰው አለ ተብሎ ይፈታል ወይ ሚስት!
እህህ ደማሙ እህህ ደማሙ(2)
እንኳንስ ሆድ ሆዴን ይብላው አንጀቴን
ባሌ አይደለም ወይ ያቆመው ቤቴን
ብላ እንድዘፍንልይ ብነግራት ሚሽቴን
ድምጧን አጥፍታለይ ፈርታ አባቷን!!
እህህ ደማሙ እህህ ደማሙ
እህህ ደማሙ እህህ ደማሙ
ጎመኑ ይቅርብኝ አውጪልኝ ከወጡ
ትናንት አጋብተውን ሊለያዩን መጡ
እህህ ደማሙ እህህ ደማሙ
እህህ ደማሙ እህህ ደማሙ
በተለ የመጨረሻዋን ይችን •••
ጎመኑ ይቅርብኝ አውጪልኝ ከወጡ
ትናንት አጋብተውን ሊለያዩን መጡ!
የምትለውን ቅኔ ሆን ብዬ እየደጋገምሁ እንቅልፍ እስቲጥለኝ ታዜማት ቆየሁና ተኛሁ።
በንጋታው ምሳ ሰአት አለፍ ታለ ቡሀላ ምሳ ይዛልይ የመጣይው ተዋቡ አልጋዬ ጠርዝ ቁጭ አለይና ።
አገጫን በግርምት በጇ መዳፍ ደግፋ እንደመሳቅ ቲቃጣት ።
ምንው ለምን ትታገይዋለሽ ሳቂና ይውጣልሽ አልኋት ማታ ሳንጎራጉር ሰምታይ እንደሆነ ገብቶኛል።
"ኪኪኪኩኩ እንድዬ ሙት እንዲህ ውብ ድምጥ እንዳለህ ትናንት ነው የሰማሁት "
ተይ እንጂ ድምጥ እንኳን የለኝም ምናልባት ሆድ የባሰው ሰው ተሆዱ ስለሚያንጎራጉር ድምጡ ሆድ ይበላ ይሆን እንደሆን እይ የለለውን ድምጥ ተዌት ያመጣዋል?
እሺ ድምጡስ ይሁን ግጥሙንስ ተዌት አመጣህው በል።
"ኬት አመጣዋለሁ እራሴው ነኛ የገጠምሁት ሰው ፍቅር ቲይዘውና ሆድ ቲብሰው ገጣሚ እንደሚሆን አታዉቂም።
አይ አንዱዬ የትናንት ማታው እማ የተለየ ነው። ተኝተህ ዝም እስትትል ድረስ እንዲሁ በተጋደምሁበት እየሰማሁህ ስስቅ እኮ ነው ያመሸሁት።አብዋም ተኝቶ አልሰማህም እይ ተመሳቅ ባልተመለሰ!"
" መች ስቀው ያውቁና? ይልቅ አንቺ ግን ሳቅሽ አደል? ሳቂ ምናለብሽ እኔ እንባ እንባ እያለኝ ታንጎራጉር መሳቅሽ ይገርማል!
ለኔ እንደቋጥኝ የከበደኝ ያባትሽ ውሳኔ ተስማምቶሻል ማለት ነው ተዋቡ ? 'ስላት።
"ምን ላድርግ የኔ አለም እስቲ ንገረኝ ምን ላድርግ?እኔም ሂድ አልለው ነገር ተቸገርሁ እኮ!ምን ላድርግ አለሜ እስቲ ንገረይ? አቡዋ እንደሁ አንድ ወር ይቀጣ ብሌ ተወሰነ ወሰነ ነው ፍንክች አይል እኛ ታርቀናል ሰላም ወርዷል ሂድ ብለው ያዋረድሁት ይመስለውና ይናደድብኛል ብዬ እይ ወድጄ መሰለህ ?
ተተናደደ ደሞ ታውቃለህ ያ መከረኛ ደም ብዛቱ ይጨምርና ሌላ ጦስ ይመጣብናል ብዬ ፈራሁ!"


ብቻ አንዳች ነገር •••"አንኳኳ አንኳኳ" ቲለኝ ፈራ ተባ እያልሁ በቀስታ••• ኳኳኳኳ አደረግሁ እና አይኔን ተሷ ላይ ታልነቅል ጆሮዬን እኔን እስወጥተው ሳሎን ወደተጋደሙት አባቷ ጣል አደረግሁ ። ድምጥ የለም።
ድምጡን ትንሽ ጨመር አድርጌ ደግሜ አንኳኳሁ።ገልበጥ አለይ ። ልቤ ዘለለይ።
አይኗን ጨፍናለይ ግን እንቅልፍ ጨርሶ የወሰዳት አትመስልም ፣ ደምግባት ታወዛው ጠይም ፊቷ ቁልቁል ትወርድ ተወለደችም ቡሀላ እንደልጃገረድ ጡት ተቀስረው አይን ተሚወጉት ሁለት ጡቶቿ መሀል አንደኛውን ተማስያዣው አምፆ በግልጥ አየሁት ።
አይ ተዋቡ የምርም ውብ እኮ ነሽ አልሁ ለራሴ ። ወድያው ግን በቀደም ትንጣላ ቆንጆ አይደለሽም ብዬ እንዳበሽቁሀት ትዝ አለይ።
ለሶስተኛ ግዜ አንኳኳሁ ሰምታኝ ነው መሰለኝ አይኗን ገልጣ እኔ ክፍል ውስጥ ሆኜ እሷን እያየሁ ወዳለሁበት መስኮት ተመለከተች ።የምታየኝ መስሎኝ ፈገግ አልሁ

•••••••ይቀጥላል

ክፍል - ሦስት ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
     @fkrn_be
_kalat
     @fkrn_be_kalat
╚═══❖•
🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴍᴍᴇɴᴛ         
       @fkrn_be_kalat_
bot
     ❥❥________⚘_______❥❥


👩◈ ሚስቴና አባቷ ◈👴🏻

       ክፍል - ሁለት [፪]

   ✍ (በጥላሁን ተስፋዬ)
.
.
.
እንደገቡ ሁሉንም ሰላም ብለው እኔን ዘለውይ ገብተው እንደተቀመጡ ወደኔ አፍጥጠው
"ገና ልጅ አንዳርጌ!" ብለው ቲጠሩይ ምን ሹክ እንዳለኝ እንጃ አንተ ባለጌ ብለው ሲሰድቡኝ የሰማሁ መስሎኝ
"ምን አጠፋሁ የተዋቡ አባት!?" ሰላም ኖት!? አልኳቸው እምይዝ እምጨብጠው ጠፍቶይ እየተደናበርኩ።
የተዋቡ አባት እየገላመጠይ "ምን አጠፋህ ወጣኝ !?"
አለና እኔን ትቶ ምን እንደተፈጠረ እንድትነግረው ተዋቡን ጠየቃት።
በቃ በእርቅ ሊፈጠም የነበረው የሽምግልና ጉዳይ አቧቷ ተመጣ ቡሀላ ሀ ብሎ ካዲስ ዥመረ ።
የኔዋ ሚሽት ነገሩን ተስርመሰረቱ አንስታ ተበደልሁ የምትለውን ሁሉ አውርታ እንዳበቃይ የልጁን ብቻ አድምጦ
የኔን ሀሳብ ሳይሰማ ከተጣላነው ከኔና ከሷ በላይ ነገሩን አክርሮ አክሮ ሲደነፋ ቆየና ለሽምግልና የተቀመጡትን ጎረቤቶቻችንን እንኳን ተቁብ ሳይቆጥር•••
"በል አንተም ወደ ቀልብህ እስክትመለስ መጠጥህን እስክትተው ፣ መጠጥ መተውህን በተግባር እስክታረጋግጥ ተነኝህ ከዋናው ቤት ጋር ተያይዘው ከተሰሩት ሁለት ሰርቢሶይ መሀል በአንደኛው ቆይ፣ እሷ ልጇን ይዛ በዚህ በትልቁ ቤት ትሁን እስከዛው መለወጥህን መስክራ መሀል ገብተን እርቅ እስክናወርድ አትድረስባት አትደርስብህም አበቃ !"
አለ።
እኔ ብቻ ሳልሆን ለሽምግልና የመጡትም አመዳቸው ቡን አለ። አንዴ አቧቷን አንዴ እኔን እያዩ ቆዩና ተመሀላቸው አንደኛው
"አይ እንደሱማ ደግ አደለም ይልቅ••••" ብሎ ገና ቀሪ ሀሳቡን ታይጨርስ •••
"በቃ ወስኛለሁ እናንተም መሄድ ትችላላችሁ! አሉ አቧታ ።
ሁሉም እኔን አየት እያደረጉ ተራ በተራ ቤቱን ጥለው ወጡ። ባይናገሩትም ካስተያየታቸው " በል ጥናቱን ይስጥህ አንዳርጌ!" እያሉኝ የሄዱ መሰለይ።
ሶስታችን ተፋጠጥን ቀረን።
እየተቃወመይ ይሁን እየደገፈይ ባይገባኝም ተዋቡ ሚስቴ •••
"ኦሮ ወደ ሰርቪስ ቤት መግባቱ ምን ፋይዳ አለው አመሉን ታልተወ ሰክሮ እየመጣ በሩን ትከፍች እንደሆነ ክፈች ታልሆነ ገንጥየው ነው እምገባ ማለቱ መች ይቀራል!" አለይ።
ያኔ አንባገነኑ አባቷ አመሉ እስኪሻሻል እኔ እዚሁ አንቺው ጋር ሳሎን ቤት ውስጥ እተኛለሁ ።
ተጥፋቱ ተምሮ ፣ ጠባዩን አርሞ፣መጠጡን አቁሞ ቤቴን ትዳሬን ይል እንደሆነ እስተ አንድ ወር እናየዋለን።
በአንድ ወሩ የጥሞና ግዜ ውስጥ እራሱን ገዝቶ ፣ መጠጡን ትቶ አደብ ታልያዘ ልጄ
ተይህ በላይ ተሱ ጋር በትዳር እንድቀጥይ አልፈቅድም ትፋታላችሁ" ብለው አረፉት።
ያሁኑ ይባስ!!!
ጭራሽ ተሚስቴ መኝታም መአድም ለይተው ተትልቁ ቤት አስወጥተው ጠባቧ ሰርቪስ ውስጥ ይግባ ማለታቸው ሳያንስ ለአንድ ወር እኔ እዚሁ እየተኛሁ እጠብቅሻለሁ ማለታቸውን ትሰማ ጭውውውውው አለብይ ።
እየቀለዱም መሰለይ ። ታሁን ታሁን ሀሳባቸውን ይቀይራሉ አልያም ተዋቡ ሀሳባቸውን ለማስቀየር የሆነ ነገር ትላለይ ብዬ እየጠበቅሁ••
እምለው ጠፍቶይ አንዴ ሚሽቴን አንዴ አባቷን እያየሁ ትቁለጨለጭ •••
"በቃ ጨርሰናል አንዳርጌ እሄው ነው! አሉይ። ያን እያረፈ የሚተኩሰውን፣ ለመተኮስ ትታስቡ ቀደም ብላችሁ ንገሩኝ የሚለውን ያረጀ ያፈጀ ጓንዴ መሳሪያቸውን ታጠገባቸው እያጋደሙ።
ውጣ ማለታቸው ነው መሰል አልሁና ብድግ ብዬ ስወጣ ያኔ ተሶስት አመት በፊት በሰርጋችን ሰሞን ጥጋቡ ስለእሳቸው ያለኝ ነገር ትዝ አለይ።
ተይ ከጎመኑ አርጊ ከወጡ
ትናንት አጋብተው ሊያፋቱን መጡ!!
ብሎ የተቀኘው እንደተዋቡ አባት አይነቱ ቢገጥመው ይሆን ? ኧረ በጭራሽ እንደኝህ አይነት ሰውማ የለም! እንደወጉ እንደልማዱ ተሆነ ባልና ምሽት ቲጣላ መሀል ገብቶ እሚያስታርቅ ሽማግሌ እይ መሀል ገብቶ እሚተኛ ሽማግሌ ተአለም ዙርያ ቢፈለግ ተምሽቴ አባት ውጪ እኔ አለሁ የሚል የሚገኝም አይመስለይም።
እንዲሁ በነገረ ስራቸው ትብሰከሰክ ለሶስት ቀን ጠጅም ታልጠጣ እነሱንም ታላናግር ከስራ መልስ ክፍሌን ዘግቼ እየተኛሁ ቆየሁ።
በአራተኛው ቀን ለሉት ግን በህልሜ ሁሉም ነገር ዛፉም ቅጠሉም መንገዱም ቀለሙ ቢጫ ሆኖ ታየኝ የጠጅ አምሮት የፈጠረው ህልም ነው መሰል።
እረወድያ ነገስ የመጣው ይምጣ እይ ሄጄ ጠጣለሁ አልሁ።
ነግቶልይ ጠጅ ቤት እስትሄድ ቸኮልሁ።
ተልጅነቴ ዥምሮ ተቤታችን ጠጅ ቢጠፋ ጠላ ጠላ ቢጠፋ ጠጅ አይጠፋም እምዋ በየሰበቡ ትጠምቃለይ ዛድያ እኔን ምን አርግ ይሉኛል።
እሳቸውም ቢሆኑ እድሚያቸው ቲገፋ በህመም ምህንያት ተው እንጂ ይጠጡ እንደነበር ተዋቡ ነግራኛለይ። ያበጠው ይፈንዳ እይ በጥም አልሞትም ዛሬ እሄዳለሁ አልሁ።
አመሻሹ ላይ ሄድሁ።በንዴትም በናፍቆትም እሄን ጠጅ ልፌ ልፌ ሞቅ ሲለይ ከግራ ወደ ቀኝ ደሞ ወደ ግራ ዚግዛግ እየሰራሁ
እቤት ደርሼ ግቢ እንደገባሁ ቀጥ ብዬ የትልቁን ቤት በር አንኳኩቻለሁ ለካ ብቻ •••
የ ተዋቡ አባት "ማነው" ብለው ቲጮሁ ስካሬ ተላዬ ላይ ብን ብሎ ጠፋ።
"ይቅር በሉይ የተወቡ አባት ቤቴን ረስቼ ነው ለካ ሰርቪስ ውስጥ ብቻዬን እንድተኛ ፈርደውብኛል ዘንግቸው ነው!" ትላቸው•••
ምናልክ አንዳርጌ?" አሉይ ።
"ኧረ ምንም ምንም አላልኩም አማቼ ሰላም አመሹ ወይ ? ነው ያልሁት አልሁና መልስም ባይሰጡይ ሰላም ይደሩ የተዋቡ አባት እያልሁ ፊቴን መልሼ የጠባቧን ክፍሌን በር ተመለከትኋት። ደሞ እኮ እኔው ነይ የሰራኋት።
እንደተጋባን አባቷ የሰጡን ቤት አሁን እሳቸው ሳሎን እሷ ጓዳ የተኛይበትን ሁለት ክፍል ብቻ ነው ።
ቤቱ ራቅ ብለው ቱያዩት አግድም የተኛ ቁምሳጥን ይመስላል።
በሳሎኑና በመኝታ ቤቱ (በጓዳው ) መሀል ጠበብ ያለይ መዝግያ በር ያልተበጀላት ደጃፍ አለይ።
ተሳሎን ቤቱ ወደመኝታ ቤቱ በግልጥ እንዳይታይ ወፈር ያለ የጨርቅ መጋረጃ ተሰቅላል ።
ተሳሎኑ ወደደጅ መውጫ በር በስተግራ እምኝታ ቤቱ ግርግዳ ላይ ወደውጪ የምትከፈት የንጨት መስኮት አለይ።
ተጋብተን መኖር ከጀመርን ቡሀላ አሁን እኔ ባባቷ ውሳኔ እምተኛባት ክፍል ሚስቴ የለችበት ክፍል መስኮት ባለበት ግርግዳ ላይ ተቀጥላ ነው ቁልቁል የተሰራይው።
ሚሽቴ ያለችበት ክፍል መስኮት ሰርቪሷ ተተሰራይ ቡሀላም ስላልተደፈነ መስኮቱን ከፍታ በመስኮት ብትዘል እጠባባ ክፍል ውስጥ አሁን እምተኛባት አልጋ ላይ ነው እምታርፈው።
ደና ደሩ አማቼ እያልሁ ክፍሌ ተገባሁ ቡሀላ••••
ጥግ ላይ በተዘረጋይው ታጣፊ አልጋ ላይ ጋደም ብዬ ሽቅብ የተዘጋይውን የሚሽቴን መኝታ ቤት መስኮት እያየሁ እንቅልፍ ሳይወስደይ ታንድ ሰአት በላይ ቆየሁ።
ድንገት አንድ ሀሳብ ብልጭ ቲልልኝ•••
ብድግ ብዬ አልጋዬ ላይ በጉልበቴ ተንበረከክሁና በእንጨት መስኮቷ ክፋይ ስንጥር ክፍተት ሚስቴ ወደታኛትበት አጮለቅሁ !•••
መብራቱን ትላላጠፋችው ወለል ብላ ታየችይ ። ልጄ ፊቱን ወደ ግርግዳው አዙሮ ተኝቷል። የኔዋ ተዋቡ ወደ ልጄ ዞራ ተለተኛይ የሚታየኝ ጀርባዋ ነው ።
ብርድልብሱን የለበሰይው እስተ ባቷ ብቻ ነው ። ተራስ ጠጉሯ ዥምሬ ረጅም ጠጉሯን ተንጠላጥዬ በወገቧ ላይ ተንሸራተትሁና ስስ ውስጥ ልብሷ በከፍል እሸፈነው መቀመጫዋ ላይ ትደርስ ብርድ ልብስ ወደሸፈነው ባቷ ታልሻገር እዛው ቀረሁ።
ለአመታት የዳበስሁት መቀመጫ አልመስልህ አለኝ ። መቀመጫሽ እንዲህ ወጣ ያለ ነበር እንዴ ተዋቡ ? ዛሬ ነው እንዲህ ጉብ ያለ መሆኑ የታየኝ አልሁ በልቤ።
ታላስበው ምራቄን ደጋግሜ እየዋጥሁ እንደሆነ የታወቀይ አፌ ውስጥ ቶሎ ቶሎ ምራቅ ቲመነጭ ነበር።


ነገሩ ያኔ ታይሽ ጠባዬ መልካም መስለሽይ ነበር ተጠባዩ ወይ ተመልኩ ታንዱም ያላደላት ሚሽት ማግባቴ የታወቀይ አሁን ነው •••
"መልከ ጥፉ በስም ይደገፍ "ነው ነገሩ ስም ብቻ ምን ይፈይዳል ስም ተማሪ ቤት ለመመዝገብ እይ ለመልክ አይሆን !"ብላት በንዴት እየተንተከተከይ•••
"እዛ ጠጅ ቤት ሰልካካዋን መልከመልካሟን ፍለጋ ነዋ ነጋ ጠባ የምትመላለስልይ ዛድያ ለምን እዛው አለደርህም ነበር ?" ስትለይ።
እጇን ለቀቅሁና " ተፈቀድሽ እማ ሄጄ አድራለኋ ምን ሽግር አለ ብዬ ራመድ ስል•••" እንደነብር ዘላ ተፊቴ በመምጣት ጥፍራን አንጨፍርራ ተከመረችብኝ።
ስትባጭረይ ! እኔም ብልጭ አለብይ።
ተዛ ቡሀላማ ዳር ቆሞ ፀቡ እስቲጀመር በጉጉት ምራቁን እየዋጠ ቲጠባበቅ የነበረው ሰይጣን በመሀል ፊሽካ እየነፋ የረፍት ሰአት ያውጅልናል መሰል እያረፍን ትንቧቀስ ቆይተን ቲደክመን ተኛን!
በጥዋት ተኔ ቀድማ ተነስታ ወጣይ ፣ ልጃችን እቤት ውስጥ ተኝቶ ስለነበር ከግቢያችን ጎን ወዳሉት ከብቶይ ሄዳ ሁለቱ ሰራተኛይ ወተቱን በጥዋት አልበው ለደንበኛቻችን መውሰዳቸውን አይታ ልመጣ ይሆናል ብዬ አሰብሁ።
ትንሽ እንደተኛሁ ተነስቼ ስወጣ እሷ ስትገባ ደጃፉ ላይ ተገናኘን ።
ይቅር በይኝ ተወቡ ብዬ ላናግራት ትሞክር ነብር አራስ ሆነችብይ። በቃ አምርራለይ አልሁና
ብድግ ብዬ ሁለቱ ጎረቤቶቻችን ጋር በመሄድ ሚሽቴን ማታ አድርጌው የማላውቀውን እጄን አንስቸባት አስቀይሚያታለሁና አማልዱይ ብዬ ለመንኋቸው ።
ግቢ ውስጥ ቆሜ ትጠብቃቸው ለሁለት ሰው ነግሬ ቴት እንደተጠራሩ እንጃ አምስት ሆነው ቲመጡ እንዳየሁ ደነገጥሁ።
ያልጠራኋችሁ ተመለሱ ልላቸው ምን ቀረይ።
አሁን ወሬ ማራባት ምን ይሉታል እኔ የነገርኋቸው ሁለቱ ብቻ ቢመጡ ምናለ
የድር ስብሰባ አለ የተባሉ ይመስል ተጠታርተው ይምጡ•••ጉድ እኮ ነው እናንተ" እያልሁ ትነጫነጭ ቆየሁና ገብተው እንደተቀመጡ ተከትያቸው ገባሁ።
ወድያው እሷ ተነስታ እንዲህ ብሎኝ እንዲህ አርጎኝ ፣ እንዲህ ደፍቶ፣ እንዲህ አንስቶ እያለይ የሞከርሁትም፣ የፎከርሁትንም የሰራሁትንም፣ ያልሰራሁትንም ሀጥያቴን ትታነበንብ••
ላስተባብል መሀል ትገባ •••
"ቆይ ዝም በል አንተ ትጨርስ !"
እያሉ እንዴት እንዴት ሆነው በአትኩሮት እንደሚከታተሏት ታይ ትክን እልሁ።
እሄን ግዜ አንድ ሰው ደግደጉን ወሬ እንዲህ እንደምሽቴ አንድ ሰአት ሙሉ ቆሞ ቢያወራ እንቅልፋቸው በመጣ ነበር።
የኔን ጉድ ለመስማት አይናቸው ፈጦ ጆሮቸው ተቀስሮ ታየው እኛ ተጣልተን ባንደርስላቸው በፀብ -ወሬ ጥም ሊሞቱ ተቃርበው ነበር እንዴ ?
በይህ አመት ይህን የመሰለ ጮማ ወሬ የሰሙም አይመስለይ ።
ተበዳዩን አጥናንተው፣ በዳዩን ገስፀው ወደ ሽምግልናቸው መቋጫ እኔን ተሷ በእርቅ ሊያቆራኙ አፍታ እንደቀራቸው •••
አሞራ ይንገረው ጅግራ ታይታወቅ ፣ የኔና የሚሽቴን መጣላት አጠገባችን ታሉት ጎሮቤቶቻችን ቀድሞ የሰማ የሚመስለው የሚሽቴ አባት ቴት መጣ ታይባል በሽምግልናው መሀል
በረጅም ቁመቱ ላይ ተመጥኖ በልኩ በተሰጠው ግዙፍ ሰውነቱ ጓንዴውን እጀርባው ላይ እንዳጋደመ ድንገት ዘው ብሎ ቲገባ •••
በድንጋጤ እጥዬ ዱብ አለይ !!••••
•••••••ይቀጥላል

ክፍል - ሁለት ... ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like❤️ ማድረግ አይርሱ።

የመወያያ ግሩፑን ይቀላቀሉን!
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group
t.me/ethio_lifes_group

╔═══❖•🌺🌸•❖═══╗
     @fkrn_be_kalat
     @fkrn_be
_kalat
     @fkrn_be_kalat
╚═══❖•
🌺🌸•❖═══╝
Ғᴏʀ ᴀɴʏ ᴄᴍᴍᴇɴᴛ         
       @fkrn_be_kalat_
bot
     ❥❥________⚘_______❥❥

20 last posts shown.