ስንክሳር ዘወርኀ ጥር ፯
አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥር ሰባት በዚች ቀን የከበረ አባት የሮሜ ሀገር ሊቀ ጳጳሳት ሶል ጴጥሮስ አረፈ። ይህንንም አባት ስለ ተጋድሎው ገናናነት ስለ አገልግሎቱም ስለ ትሩፋቱ ስለ አዋቂነቱና ስለ ደግነቱ ከእርሱ በፊት የነበረ ሊቀ ጳጳሳት አባ መልጥያኖስ ከአረፈ በኋላ መርጠው ሊቀ ጵጵስና በሮሜ ሀገር ላይ ሾሙት ። በሐዋርያት አለቃ በጴጥሮስ ወንበር በተቀመጠ ጊዜ የዕሌኒ ልጅ የሆነ ንጉሥ ቈስጠንጢኖስን የክርስትና ጥምቀትን አጠመቀው ከከሀድያን ጋር ስለሚያደርገው ጦርነት ምክንያት ገና አልተጠመቀም ነበርና የጣዖታትንም ቤቶች አፍርሶ የእግዚአብሔርን አብያተ ክርስቲያናት ሠራቸው። የዚህም አባት የሶል ጴጥሮስ ገድሉ እጅግ ብሩህ የሆነ ነው እርሱ ሁል ጊዜ ሕዝቡን ያስተምራቸዋልና ከልቡናቸውም ከሰይጣን የሆነ ጥርጥርንና ክፉ ሐሳብን ያርቃል። ከእነርሳቸው ሥውር የሆነውንም የመጻሕፍት ምሥጢር ተርጕሞ ያስገነዝባቸዋል። አይሁድንና ዮናናውያንን ሁል ጊዜ ይከራከራቸው ነበር ከእርሳቸውም ብዙዎችን መልሶ ወደ ቀናች ሃይማኖት አስገባቸው የክርስትና ጥምቀትንም አጠመቃቸው ስሙም በምእመናን ዘንድ ፈጽሞ የሚያስፈራ እግዚአብሔርን ስለ ማወቅና ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ብዙ ድርሳናትን ደረሰ። በተሾመ በሰባተኛውም ዓመት ስለ አርዮስ በኒቅያ ከተማ ሃይማኖታቸው የቀና የሦስት መቶ ዐሥራ ስምንት የከበሩ አባቶች የአንድነት ስብሰባ ሆነ ይህም አባት ሶል ጴጥሮስ ከእርሳቸው አንዱ ነበር አርዮስንም ከተከታዮቹ ጋር ረገመው አውግዞም ለየው በሹመቱም ዐሥራ አንድ ዓመት ኖረ መልካም ተጋድሎውን ፈጽሞ እግዚአብሔርንም አገልግሎ በሰላም አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
አርኬ
ሰላም ለከ ጴጥሮስ ሶል። መጥምቀ ቈስጠንጢኖስ ንጉሥ ከሣቴ መስቀል። መዋዕለ ዕብሬትከ ኮነ ዕብሬተ ርትዕ ወሣህል። እስመ ተቀጥቀጠ ዳጎን ወወድቀ ቤል። በከመ ቀዳሜ ኢሳይያስ ይብል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በዚችም ዕለት የቅዱስ ኤፍሬም መታሰቢያው ነው፤ በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን ።
አርኬ
ሰላም ለከ ኤፍሬም አብ።
ምሉአ ጥበብ ። ፈሪሆተ ክርስቶስ ምልአኒ ከመ ማህየብ። በአልባቢሆሙ ለዘይፈርህዎ ሕዝብ። እስመ አድኀኖቱ ተብህለ ለአምላክ ቅሩብ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በዚችም ቀን የሰሎሞን የጎርጎርዮስ የማርቆስ የአትያኖስ የሉያ የመልይን የሱስዮስ የማርትይ መታሰቢያቸው ነው። በረከታቸውም ከእኛ ጋር ትኑር ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን አሜን ።
ጥር ፯ ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
፩.በዓለ ሥሉስ ቅዱስ
፪.ቅዱስ ሶል ዼጥሮስ
፫.ቅዱስ ኤፍሬም
፬.ቅዱስ ሰሎሞን
ወርኀዊ በዓላት
፩.አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
፪.አባ ሲኖዳ (የባሕታውያን አለቃ) ፫.አባ ዳንኤል ዘገዳመ ሲሐት ፬.አባ ባውላ ገዳማዊ
፭.ቅዱስ አትናቴዎስ ሐዋርያዊ ፮.ቅዱስ አግናጥዮስ (ለአንበሳ የተሰጠ)
የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋ: የእግዚአብሔርም ፍቅር: የመንፈስ ቅዱስም ኅብረት ከሁላችሁ ጋር ይሁን ። አሜን ። (፪ኛ ቆሮ. ፲፫፥፲፬)