⭐ሥላሴ ቅኔ ዘ ወልደ ገብርኤል (ራስ)
ዓለም እስከ ጊዜሃ፣ በሐብለ ዝንጋዔ ትስሕበነ፣ ወታወርደነ ካዕበ ኀበዘቀዳሚ መርገም።
ለዘተወለድነ በሥጋ ወደም፡፡
ዘአእማራስ ማእምር ለባዊ፣ ለኅልፈተ ዛቲ ዓለም::
ፍዳ ወይን ይስተይ ማየ ዝናም፡፡
ወህየንተ ልብስ ይትከደን ቆጽለ አእዋም፡፡
እስመ ዛቲ ጽላሎት ወሕልም፡፡
⭐ት ር ጉ ም
አለም እስከ ጊዜዋ በዝንጋታ/ ገመድ ትጎትተናለች . ሁለተኛም ወደቀደመ ርግማን ታወርደናለች በስጋና በደም የተወለድን እኛን ፤ የዚችን አለም አስተላለፍ ያወቃት ጥበበኛ ልበኛ ግን ስለወይን ፈንታ የዝናብ ወሃን ይጠጣ ፤ በልብስ ፈንታም የዛፎች ቅጠልን ይልበስ ፤ ይችው (አለም) ህልምና ጥላ ናትና ▪
⭐ም ስ ጢ ር
በግን የገዛች ሴት ወደ ወደደችው እንደምትስበው የባለበጊቱ ምሳሌ የሆነችው አለም የበግ ምሳሌ ሰውን እያታለለችና እያዘና ጋች የአዳምን ፍዳ እንዲቀበል ታደርገዋለች » ከዚህም ሌላ የኑ ሮን ልክ የሚያውቅ ባላገር በጠላ ፈንታ ውሃን እንደሚጠጣና ተራ ልብስን እንደሚለብስ ፡ እንደ አለም ከንቱነት ቢሆን የዝናብ ክታሪ ውሃን (ጨረቆን) ጠጥቶና ቅጠልን አገልድሞ መኖር ይገባ ነበርበማለት ባለቅኔው የአለምን ከንቱነት ያስረዳሉ ።
⭐ሙያ
ዓለም ----------- የቅኔ ባለቤት(የቅኔ በአለተቤት)
እስከ------አገባብ-ፍቺው-ድረስ-ሙያው ማንፀሪያ
ጊዜሃ-----------የማንፀሪያ ባለቤት
በ---አገባብ--ፍቺው-- በቁም ቀሪ-ሙያው ማድረጊያ
ሀብል-ዝንጋኤ -ምሳሌ---
ሀብል--------------ሰም
ዝንጋኤ-----------ወርቅ- ተመስሎ አድረጊያ ባለቤት
ትስሕበነ---------ማሰሪያ አንቀፅ ይስባል እንጂ አይሳብም
ወ----አገባብ--ፍቺው--ም--ሙያው ደጋሚ
ታወርደነ--በ ወ የተደገመ ማሰሪያ አንቅፅ ይስባል እንጂ አይሳብም
ካይበ--------ማድረጊያ የወጣበት
ኀበ-----አገባብ---ፍቺው---ወደ--ሙያው--መገስገሻ
ዘ-----ዘርፋ ደፊ ዘርፋ ደፊነቱ መርገመቀዳሚ የሚያሰኝ
ቀዳሚ----------የመርገም ዘርፋ
መርገም------------የመገስገሻ ባለቤት
ለ-------አገባብ---ፍቺው-በቁም-ቀሪ-ምስጢር አቀባይ
ዘ- በቂ ሁኖ የተጠቃሽ ባለቤት
ተወለድነ---እንዳያስር -ዘ ይጠብቀዋል
በ -አገባብ- ፍቺው -በቁም ቀሪ -ሙያው ማድረጊያ
ወ --አገባብ--ፍቺው--ና-ሙያው አጫፋሪ
ስጋ ደም በወ ተጫፍረው የማድረጊያ ባለቤቶች
ዘ---በወ ተደግሞ የደጋም ባለቤት
አእመራ---እንዳያስር ዘ ይጠብቀዋል
ሰ--አገባብ--ፍቺው--ግን--ሙያው--ደጋሚ
ማእምር /ለባዊ ----ምስሌ
ማእምር--------------ሰም
ለባዊ-------------------ወርቅ ተመስሎ የደጋሚ ባለቤት
ለ --አገባብ ---ፍቺው--- ን ሙያው --ተጠቃሽ ተጠቃሽነቱ አእመራላለው
ሕልፈት ----የተጠቃሽ ባለቤት
ዛቲ----------------------የዓለም ቅፅል
ዓለም-------------------የህልፈት ዘርፋ
ፍዳ -----------ማድረጊያ የወጣበት
ወይን -----------የፍዳ ዘርፋ
ይስታይ --በወ የተደገመ አስሪያ አንቀጽ ይስባል እንጂ አይሳብም
ማይ ----------- የይስተይ ተሳቢ
ዝናም ----------የማይ ዘርፋ
ወ----አገባብ--ፍቺው--ም--ሙያው ደጋሚ
ህየንተ-- አገባብ--ፍቺው ስለ ሙያው ማንፀሪያ
ልብስ ------------- የማንፀሪያ ባለቤት
ይትከደን------------እንዳያስር ህየንተ ይጠብቃል
ቆጽለ-------የይትከደን ተሳቢ
አእዋም--------የቆጽለ ዘርፎች
እስመ------አገባብ ---ፍቺው ና ሙያው አስረጅ አስረጅነቱ ይትከደን ላለው
ዛቲ-------ያስረጅባለቤት
ወ --አገባብ--ፍቺው--ና-ሙያው አጫፋሪ ጽላሎት ሕልም በወ ተጫፍረው እንዳያስሩ እስመ ይጠብቀዋል
(ሙያ አሰጣቱ እንደ ቤተ ጉባኤው ይለያያል)