ግጥም ዘ ጦቢያ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ልበልሻ ታዲያ ጎጆ እና አለሜ
አንቺን የመግለጫ ቅኔ ነው ግጥሜ፡፡
Join join join
@gitmeyisdaw
@gitmeyisdaw
@gitmeyisdaw

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


Issac et:
ለውሻ የሚሆን ስጋ

አንድ ባለልኳንዳ በጣም የሚጠላው ሰውዬ ስጋ ሊገዛው ወደ መደብሩ ይመጣል::
ገዢው፦ ‹‹እስቲ ለውሻ የሚሆን ስጋ ስጠኝ››
ሻጭ፦ ‹‹ይዘኸው የምትሄደው ነው ወይስ እዚህ የምትበላው!››

@gitmeyisdaw

የኛ ሰፈር ቀልዶች - Application


Forward from: አማዶን
በመኖር ትርምስ ያለ እርጋታ ያህል
በህይወት መቀዝቀዝ የሞቀ ፍቅር ያህል
ህመም እንደሚያቀል
የበሰለ አባባል
ጥሎብኝ ’ወዳለሁ
"የአባቱ ልጅ!" መባል።

አማን@amadonart


👆👆👆👆👆

ሰላም ወዳጆቼ🙋‍♂


ኑ ለመልካምነት እንተባበር
#የፊታችን_ቅዳሜ_ለሊት_ለእሁድ አጥቢያ በየጎዳናው የወደቁትን ወገኖቻችንን በያሉበት ቦታ ተገኝተን #እንጠይቃቸው_እናልብሳቸው

#ሁለት_ሜትር_ሸራ_ለአንድ_ጎዳና_ተዳዳሪ


✍☞#ዘትዜ☜

#እባካችሁ እናስባቸው______?
ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ አያድርስባችሁና በእነዚህ በጎዳና ልጆች ቦታ እናንተ ብትሆኑ
ኖሮስ ምን ይሰማችሁ ነበር_____?
እስኪ ሁለት ሜትር ሸራ ለአንድ ልጅ እንስጥ መቼም 60 ብር ከኪሳችን ቢወጣ ይጎዳናል ብዬ አላስብም
2 ሜትር ሸራና ለክረምቱ የሚሆኑ ልብሶችን በማልበስ 4ኛ አመቱን የበጎ ፍቃደኞች ሰብስብ እንደ 3
አመታቶች ሁሉ ዘንድሮም ሸራና አልባሳት ለማልበስ ዝግት ለይ
ይገኛል ፡፡

👉👉እናም ልትደግፉን የምትሹ በእነዚህ ቁጥሮች ደውሉ፡፡

👇👇
☎️0913446413 ትዕዛዙ (ye tize masitawesha)

☎️0913952551 አቤል
በእነዚህ ቁጥሮች ደውሉልን

ወይም በውስጥ መስመር እኔን
🙋‍♂ @daveneneyedegualej
0923978812

👇👇👇👇👇👇
@daveyedegua👈
@daveyedegua👈
👆👆👆👆👆👆




🙏🙏🙏እነሆ የ 3 ቀን እድሜ ያለውን ግጥሜን ጋበዝኳችሁ፡፡🙏🙏🙏

የተፈጥሮ
የማየው ሰው ሁሉ አንቺን መሰሉብኝ
የፈገግታሽ መንፈስ በኔ ተጋብቶብኝ
ያስፈነድቀኛል እንደ ህፃናቱ
በውበትሽ ገለሽ አሸነፍሽኝ እቱ፡፡

የመዐዛሽ ጠረን ከሽቶሽ አይደለም
ጠቋራ ፀጉርሽም ያልተቀባ ቀለም
እጅሽ ለስላሳ ነው ህመም የሚያስረሳ
እጅግ በጣም አምሮ ለመንካት ሚያሳሳ፡፡

አይንሽማ ውዴ ከሁሉም ይለያል
በነጣ ወተት ላይ ያለ ቡና ይመስላል
የወገብሽ ቅጥነት ከዳሌሽ ተዳምሮ
ውብ አርጎ ፈጥሮሻል ፈጣሪ ቀምሮ፡፡

ደጋግሜ ባይሽ ትሆኛለሽ አዲስ
እንደገና መጣች በፀሃይ ወጋገን
ከወዲያኛው አድማስ
በዝግታ እየሄድሽ መሬቱን እረግጠሽ
እኔም ሳፈጥብሽ አንቺም ፈገግ እያልሽ፡፡

@gitmeyisdaw
✍✍✍ @yisdaw1


DagRo:
😒😒ምኑ ነው ቅለቱ😏😔
ሰዎችን ሸሸሁኝ ከራሴ አርቄ
ውስጤንም ጠላሁት እያወቅኩ አውቄ
ለምን ይሆን ይሄ በጣም የከበደው
ከልቦና ይልቅ ህሊና የላቀው
ምን ይሆን ምክንያቱ ልቤን የማጣቴ
ዝም ብዬ እጓዛለው ያለ ፍላጎቴ
እሺ ለምንድን ነው ማስተዋል ያቃተኝ
በማይሆን መንገድ ላይ የሚያመላልሰኝ
ሰላም ወይስ ጠብ ነው የሚጫወትብኝ
በፀጥታ መኖር እንዴት ነው የሚቻለው
ማንም ሳይደርስብኝ ጭንቄን የምሽረው
ልቤ እየከዳኝ ህሊናዬ ርቆኝ
እንዴት ነው የራስ ሰው የማያስፈልገኝ
ሰው እንዴት ይኖራል ያለፍላጎቱ
መምረጥ እየቻለ ሁሉን ከ አይነቱ
ለሰዎች ቀላል ነው ለኔ ግን ከብዶኛል
ህይወቴ ጠማማ ዳገት ሆኖብኛል
ቀለል አርገሽ ኑሪ ይለኛል ሰው ከንቱ
ኑሮው በጣም ከባድ ምኑ ነው ቅለቱ።
🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵


ፀሀፊ ✍✍ቃልኪዳን ምህረቴ✍✍

Join as @DaggRodas


ትማርኪኛለሽ

እንደ አብይ ንግግር እንደ ማር ወለላ

እንደ ባርሳ ጨወታ እንደ ወይን ዘለላ

ስራ እንደመቀጠር Dv እንደመድረስ

ቶምቦላን ቆርጬ ገንዘብ እንደማፈስ

እንደ ፅገሬዳ እንደ አቦል ቡና

ባየር እንደመብረር ተጭኜ ደመና

ትማርኪኛለሽ እንደ አደይ ፍካት

ባየር ላይ ተጉዞ ጨረቃ እንደመውጣት
@gitmeyisdaw
@samson994


LikeBot:
❤️🙏 በልቤ ሳስበው 😍👌

ፍቅር(×3) ሁሌ ስለ ፍቅር
ሲተረክ ሲነገር አኔስ ይለኛል ቅር
ያኔ በፊት ነበር ስለ ፍቅር ሲወራ
ቢሆንልኝ ብዬ በባዶ ስቅራራ
ፍቅር ሲሆንብኝ የማያልፍ ተራራ
አገኘው ይሆን ስፈራ ስተባ
የት ይሆን የኔ ሰው ኸረ ወዴት ልግባ

ፍቅር ምን ማለት ነው ብዬ አስብና
ቀስብዬ አውቀዋለሁ መልሼ እልና
የፍቅርን ትርጉም ለመረዳት ብዬ
ሁሌ እመኝሀለው በሀሳቤ ስዬ
የወደፊት ፍቅሬን ያሁኑን ሀሳቤን
ብዬ አስብና ምን ይመስል ይሆን
ቆንጆ እና ተጫዋች የዋህ እና አዋቂ
ጨዋና ወንዳወንድ በፍቅሩ አስጨናቂ
አሁን ግን.........
ሀሳቤ ተሳክቶ ይኸው አገኘሁት
ያኔ በንፁህ ልብ በሀሳብ ያለምኩት
ፈጣሪ ይመስገን ''በልቤ ያሰብኩትን'' አሁን አገኘሁት ።

💑💑💑👨‍❤️‍👨👨‍❤️‍👨👨‍❤️‍👨💏💏💏👩‍❤️‍💋‍👩👩‍❤️‍💋‍👩

✍😸 ማህሌት ታደሰ 😹✍


Dinsefa:
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟

👍ፈጣሪ ይምርሃል የማይምርህ የሰው ልጅ ብቻ ነው።ፈጣሪ እኮ ይቅር በለኝ ስትለው ከነበርክበት የዘቀጠ ህይወት አፅድቶ ወደ እርሱ ያቀርብሃል። የሰው ልጅ ግን ከባድ ነው። ዛሬ ጥሩ ስትሆን ለማስመሰል ነው ይልሃል...ክፉ ከሆንክ የለመደው ነው ይልሃል። ላጠፋኸው ጥፋት ይቅርታውን ስትከጅለው ባለፈ ማንነትህ ያሸማቅቅሃል!!
ፈጣሪ መልካምነትን በውስጣችን ያኑርልን።
ነገን ስለማታውቃት ክፉ አትሁን‼
/////የዛሬ መልዕታችን ነው\\\

🌹መልካም ቀን💎
★★★★★@DaggRodas

🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟


ግጥም ዘ ጦቢያ:
😂😂😂አስጨነቀኝ😁😁😁
የሆነ ነገር እረበሸኝ
እልፍ ብሎ ሚያስጨንቀኝ
ሚያስፈራራኝ
ፌለፊቴ ሚነካካኝ
ከጀርባዬ ሚዳብሰኝ
ከኋላዬ ይመጣና
ጎኖቼ ስር እየገባ
ያዝ ለቀቅ እያረገኝ
የሆነ ነገር እረበሸኝ
ጓዴ በጣም ኮረኮረኝ
አስለቅሶ እያሳቀኝ፡፡
share,invite friends
Read more.....
@gitmeyisdaw


Forward from: Nadbis Generations (Nadbis film production PLC)
ሰላም ዉድ ቤተሰቦቼ ሰኔ 24 የኪነ ጥበብ ድግስ ከስለ እናት ማህበር ጋር ጋር በመተባበር ይቀርባል በለቱ ታዋቂ የጥበብ ሰዎች ይገኛሉ

መግቢያ 1 ደርዘን የመማሪያ ቁሳቁስ
በለቱ የትም መሔድ የለም እዛው ስለ እናት ማህበር እንገናኝ፡፡ ሚዲያ ከቨር ማረግ ይቻላል::
ለበለጠ መረጃ
0944026145 ታይን ኤልዶን የናድቢስ የጥበብ መንደር መስራች
@Tayin inbox


✈ ሺ ሰማንያ ✡
መቼም ላንለያይ ገፃችን አንድ ሆኖ
ከአንድ እናት ተወልደን ደማችን ተቀድቶ
በግራና በቀኝ ጡቷን ምገን አድገን
ጭቃ አቡክተን ግድብ ሰርተን
ተደባድበን በአንድ በልተን
ፍቅራችን አይሎ ላንጣላ ምለን
እየኖርን ነበር ፍቅርን አስቀድመን
የቀን "ጎዶሎ" ነው እኛን የለያየን.......
:
:
:
:
:
እንጂ መች ተጣላን
አሁንም አንድ ነን....!!

ዳግማዊ በየትም ✍(ዳግሮ)✍
@DagRo




Rãhél:
አ .ል .ወ .ድ .ሽ .ም .እ .ን.ጂ!!!!!

***

አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ያዩሽም አይኖሩ ይቅርና የነኩሽ::
አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽማ
አደባባይ ቆሜ ከመሃል ከተማ
በጂጉ በሚልቅ ከወፎቹ ዜማ
አዜምልሽ ነበር ህዝብ ሁሉ እንዲሰማ::
ያው እንደነገርኩሽ
አልወድሽም እንጂ እኔ ከወደድኩሽ
ፅሀይ ትቆማለች ጨርቃም አትወጣም
ነፋሱም ፅጥ ይላል ብርዱም አይበረታም::
ወንዞችም አይፈሱም ቆመው ይሰማሉ
የፍቅራቸው ነገር ዕፁብ ነው እያሉ::
ከፍቅራችን በላይ እጅግ የሚገርመው
እኛ ስንጎዳ ህዝቡን ነው የሚያመው::
አልወድሽም እንጂ !
አልወድሽም እንጂ !
እኔ ከወደድኩሽ
ያው እንደነገርኩሽ
አመት አንድ ቀን ነው በፊትሽ በፊቴ
ምድርም አንድ እርምጃ ላንቺ ና ኔ ኮቴ::
እኔማ ስወድሽ
ሰማይ ትጠባለች በፍቅራችን ደስታ
እኛ ከፈለግን ቀን ይሆናል ማታ::
እምልልሻለሁ "አልወድሽም እንጂ ከወደድኩሽ ብዬ"
ደስ አሰኝሻለሁ ሰጎንን ቀድሜ አንበሳን ታግዬ::
እኔ ከወደድኩሽ
እየተራመድን ነፋስ እንቀድማለን
እየተናገርን ዓለት እንሰብራለን
ከደመና መሃል ደመና እንፈጥራለን ::
አትጠራጠሪ
አልወድሽም እንጂ የወደድኩሽ ዕለት
ብረት እና ሳት ነን አንቺ ና ኔ ማለት::
እሳት ና ብረት ግጥም እና ዜማ
ንጉስ እና ንግስት እግር እና ጫማ
አንድ መሆን ታውቂያለሽ አንድ መልክ አንድ ቀለም
እኔ አንችን ስወድሽ የሚመስለን የለም::
ግን
እኔ ከማልኩልሽ በሚበልጥ መሃላ
ከምድራዊው ፍቅር ባይደለ በሌላ
አለት በሆነ ልብ በማይጎድል ተስፋ
በማይናድ ፅናት ቅፅበት በማይጠፋ
በውበትሽ ሰክረው ቅኔ እየዘረፉ
በነበልባል ፍቅርሽ ነደው እየጠፉ
የሚወዱሽ አሉ
እኔ ከወደድኩሽ ታዲያ እነዚህ ሰዎች ምንድን ይሆናሉ።


የበላይ በቀለ ወያ እይታዎች:
"ለምን ሞትህ" ቢሉት ...
አልሞትኩም እያለ ፣ ትውልድ ይሟገታል
ድሮስ
ኖሮ የማያውቅ ህዝብ ፣ ምን ሆኖ ይሞታል?!!!
።።።።።
(በላይ በቀለ ወያ ©)
👇👇👇👇👇
@yBelay
@yBelay
👉share


Zare yezih group andu abale yehonw ye NEBA lidet nw esky like bemarge melkam lidet belut


g:
DagRo:
DagRo:
😔😒ፍቅርዬን አራኳት😝🙈
በስሞች አጅቤ በቃላት ድርደራ
ለመጥራት በሚመች በሆሄ ስደራ
ሁለት ሶስት አራት ስም
በራሴ አርቅቄ አውጥቼ አውርጄ
ስሟንም ሠየምኳት ጨረቃዬ ብዬ
በገዛ ፈቃዴ ፍቅርዬን አራኳት
ሰማይ ላይ ሰቅዬ..........::
🙄🙄🙄🙄🙄🌝🌛🌜

✍ዳግሮ✍
@DagRo
@daggbot




ልበልሻ ታዲያ ጎጆ እና አለሜ

አንቺን የመግለጫ ቅኔ ነው ግጥሜ፡፡

Join join join
@gitmeyisdaw
@gitmeyisdaw
@gitmeyisdaw


Issac et:
💋💋💋እጠብቅሻለው💋💋💋
ቃልሽን አላፈርስ የኔና ያንቺ ነገር
በልብሽ በልቤ ዘላለም ነው ሚቀር


መጣው ለአንድ አፍታ ብለሽ ስትወጪ
መስሎኝ ነበር እኔም በቶሎ ምትመጪ

ምነው ውዴ ታዲያ ከሰዓቱ አረፈድሽ
የገባሽውን ቃል የኔ ፍቅር አጠፍሽ

ቃል ቃል ነውና አንቺ ብታፈርሺው
ቃልኪዳኔን ውዴ እኔማ አከብራለው
ትመጫለሽ ብዬ ደጃፉን አያለው
ከሱቅ እስክትመጪ እጠብቅሻለው፡፡

@gitmeyisdaw
@gitmeyisdaw
@gitmeyisdaw

20 last posts shown.

425

subscribers
Channel statistics