ዳሽን ባንክ 🤝 ጎፈሬ 🤝 ታላቋ ቄራየጎፈሬ የፋይናንስ አጋር የሆነው ዳሽን ባንክ ለኢትዮጵያ እግርኳስ በርካታ ተጫዋቾች እንዲሁም ባለሙያዎችን ላፈራው የቄራ እና አካባቢው ቡድን "ታላቋ ቄራ" የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ አደረገ።
ዛሬ በአልማዝዬ ሜዳ በተከናወነው የትጥቅ ርክክብ ሥነ-ስርዓት በርካታ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ የስፖርት ወዳዶች እና ታላላቅ ባለሙያዎች የተገኙ ሲሆን ዳሽን ባንክ ለቡድኑ እና ለደጋፊዎች በድምሩ ከ500,000 ብር በላይ ወጪ የሚያወጡ ጥራት ያላቸውን የጎፈሬ የስፖርት ትጥቆች አስረክቧል።
ጎፈሬን ወክለው ለዳሽን ባንክ እና ለታላቋ ቄራ ቡድን ትጥቁን ያስረከቡት ምክትል ሥራ-አስፈፃሚያችን አቶ አቤል ወንድወሰን የቄራ እና አካባባቢውን የእግርኳስ እንቅስቃሴ ለማሳደግ ከፋይናንስ አጋራችን ዳሽን ባንክ ጋር በቀጣይም በጋራ እንደሚሰሩ አመላክተዋል።
@goferesportswear