TGStat
TGStat
Type to search
Advanced channel search
  • flag English
    Site language
    flag Russian flag English flag Uzbek
  • Sign In
  • Catalog
    Channels and groups catalog Search for channels
    Add a channel/group
  • Ratings
    Rating of channels Rating of groups Posts rating
    Ratings of brands and people
  • Analytics
  • Search by posts
  • Telegram monitoring
Grace Commission

7 Sep, 17:46

Open in Telegram Share Report

Prev Next
ይህ፣ ከግምቴም ከዕቅዴም ውጪ የኾነ የእግዚአብሔር ጒብኝት ነው። በርግጥ እግዚአብሔር የእኔን መጽሐፍ ሳይኾን የራሱን ወንጌል ርእስ ማድረግ እንደ ፈለገ ተረድቻለሁ። ሕንጸትም ለእኔ መጽሐፍ ሳይኾን ለወንጌል ተልእኮ ልዩ ትኲረት እንደ ሰጠ መቁጠር እፈልጋለሁ።

በነገራችን ላይ @ሕንጸት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ በእኔ የሥነ ጽሑፍ ሙያ (መጻፍ፣ ማርታት እና ማሔስ) ላይ ትልቅ ኢንቨስትመንት አለው። በዩቲዩብ ቪዲዮዎቹ አልቆኛል (Mentoring) አድርጎኛል። በጋሽ ፍትሐ አምላክ አቅራቢነት ያማርኛ ሥርዐተ ጽሕፈት ላይ አሰልጥኖኛል። ስለዚህ @ሕንጸት ከልብ አመሰግናለኹ።

በዚህ አጋጣሚ ስለ መጽሐፌ ወንጌል ይዘቱና አቀራረቡ ጥቂት ልበል፦ ዐሳቡ ለዓመታት ያስተማርኹትና በማኅበራዊ ሚዲያ የጮኽኹት ቢኾንም፣ ወደ መጽሐፍ የተቀየረው በዐጭር ጊዜ ነበረ። ይህም የኮነው በመንፈስ ቅዱስ ምሪት እና ድጋፍ ነበረ። የኅትመት ወጪውም ሙሉ በሙሉ የተሸፈነው በራሱ በእግዚአብሔር አቅርቦት ነበረ። አኹንም @በሕንጸት አማካይነት መልእክቱን ማጉላት የፈለገው ራሱ እግዚአብሔር እንደ ኾነ አምናለኹ።

ስለዚህ የወንጌልን ተልእኮ በማፈጠን ይህን የእግዚአብሔር ፍላጎት እንፈጽም ዘንድ በዚህ ታሪካዊ አጋጣሚ ጥሪዬን አቀርባለሁ። ይህ ወንጌል ወደ ውጪ ብቻ ሳይሆን ወደ ውስጥም መነገር አለበት። አቀራረቡ ደግሞ ሥነ መለኮታዊ ተፈጥሮውን የጠበቀ፣ ይዘቱን ያላሳሳ (የወንጌል ንጽሕናን የማያሳድፍ)፣ ዘመኑን ያስተዋለ (ዐውዳዊ)፣ ተገቢ ስልቶችን የሚጠቀም (ስልታዊ)፣ በቂ ዝግጅት የተደረገበት (ስንዱ የኾነ)፣ ወንጌል ተኰር ማኅበረ ሰብ መፍጠር እና እግዚአብሔርን ማክበርን ያለመ መኾን ይጠበቅበታል።

ከልብ አመሰግናለኹ!

በርናባስ ዘመነ
የወንጌል ይዘቱና አቀራረቡ ጸሓፊ
ነሐሴ 30፣ 2018 ዓ.ም.

760 0 4 6
Catalog
Channels and groups catalog Channels compilations Search for channels Add a channel/group
Ratings
Rating of Telegram channels Rating of Telegram groups Posts rating Ratings of brands and people
API
API statistics Search API of posts API Callback
Our channels
@TGStat @TGStat_Chat @telepulse @TGStatAPI
Read
Академия TGStat Telegram Research 2019 Telegram Research 2021 Telegram Research 2023
Contacts
Справочный центр Support Email Jobs
Miscellaneous
Terms and conditions Privacy policy Public offer
Our bots
@TGStat_Bot @SearcheeBot @TGAlertsBot @tg_analytics_bot @TGStatChatBot