ኢትዮጵያ


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


ስለ ሀገራችን ታሪክ ፣ ባህል ፣ ጥንታዊ ቅርሶች ፣ ገዳማት ፣ መጎብኘት ስላለባቸው ስፍራዎች መረጃ ለማግኘት ካስፈለገ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ ። ኢሉሚናቲን እናወግዛለን። የዚህ ቻናል አላማ ትውልዱ ሐይማኖቱንና ታሪኩን ያውቅ ዘንድ እና ሙሉ ትውልድ ይሆን ዘንድ ማገዝ ነው ።
አንድነታችን ለህልዉናችን
@HISCULHEROFETHIOPIA

Related channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter






Forward from: ገድለ ቅዱሳን
ልደቱን ባከበረ ጊዜ ወለተ ሔሮድያዳ በዘፈን አጥምዳ አስማለችው:: እርሱም የታላቁን ነቢይ ራስ አስቆርጦ በወጪት አድርጐ ሰጣት:: አበው "እምሔሶ ለሔሮድስ ይብላዕ መሐላሁ - ሔሮድስ መሐላውን በበላ በተሻለው ነበር" ይላሉ:: የቅዱስ ዮሐንስ ራሱ በርራ ስትሔድ አካሉን ግን ደቀ መዛሙርቱ ቀብረውታል:: [ማቴ.፫፥፩ , ማር.፮፥፲፬ , ሉቃ.፫፥፩ , ዮሐ.፩፥፮]

- " አስማተ-ዮሐንስ መጥምቅ /የመጥምቁ ዮሐንስ ስሞች "

፩. ነቢይ
፪. ሐዋርያ
፫. ሰማዕት
፬. ጻድቅ
፭. ካሕን
፮. ባሕታዊ / ገዳማዊ
፯. መጥምቀ መለኮት
፰. ጸያሔ ፍኖት [መንገድ ጠራጊ]
፱. ድንግል
፲. ተንከተም [የብሉይና የሐዲስ መገናኛ ድልድይ]
፲፩. ቃለ አዋዲ [አዋጅ ነጋሪ]
፲፪. መምሕር ወመገሥጽ
፲፫. ዘየዐቢ እምኩሉ [ከሁሉ የሚበልጥ]

አምላከ ቅዱሳን በጥምቀቱ ይቀድሰን:: ከበረከተ ጥምቀቱም ያድለን::

🕊

[  † ጥር ፲፩ [ 11 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ በዓላት  ]

፩. በዓለ ኤጲፋንያ
፪. ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ
፫. አቡነ ሐራ ድንግል ጻድቅ
፬. አባ ወቅሪስ ገዳማዊ
፭. አባ ዮሐንስ ሊቀ ጳጳሳት
፮. ቅዱስ እንጣልዮስ ሰማዕት

[   †  ወርኀዊ በዓላት     ]

፩. ቅዱስ ያሬድ ካህን
፪. ማር ገላውዴዎስ ሰማዕት
፫. ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት
፬. ቅድስት ሐና ቡርክት

" ጌታ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ:: እነሆም ሰማያት ተከፈቱ:: የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ: በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ:: እነሆም ድምጽ ከሰማያት መጥቶ :- 'በእርሱ ደስ የሚለኝ: የምወደው ልጄ ይህ ነው' አለ::" [ማቴ. ፫፥፲፮]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖


Forward from: ገድለ ቅዱሳን
🕊

[  † እንኳን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ዓመታዊ የጥምቀት በዓል [ ኤጲፋንያ ] በሰላም አደረሳችሁ ፤ አደረሰን። †  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †

🕊  †  በዓለ ኤጲፋንያ  †    🕊

† "ኤጲፋንያ" የሚለው ቃል ከግሪክ [ጽርዕ] ልሳን የተወሰደ ሲሆን በቁሙ "አስተርእዮ: መገለጥ" ተብሎ ይተረጐማል:: በነገረ ድኅነት ምሥጢር ግን ኤጲፋንያ ማለት "የማይታይ መለኮት የታየበት: እሳተ መለኮት በተዋሐደው ሥጋ የተገለጠበት" እንደ ማለት ነው::

"ዘኢያስተርኢ ኅቡዕ እስመ አስተርአየ ለነ::
እሳት በላዒ አምላክነ::" እንዲል:: [አርኬ]

አንድም: ምሥጢር ሆኖ የቆየ አንድነቱ: ሦስትነቱ የተገለጠበት ቀን ነውና ዕለተ ጥምቀቱ ኤጲፋንያ ይሰኛል:: መድኃኒታችን ክርስቶስ አዳምንና ልጆቹን ያድን ዘንድ ከሰማያት ዙፋኑ ወርዶ: እንደ ሰውነቱ በሥጋ ማርያም ለ፴፫ [33] ዓመታት ተመላልሷል::

ጊዜው ሲደርስም በፈለገ ዮርዳኖስ: ከዮሐንስ ዘንድ ሊጠመቅ ሔደ:: መድኃኒታችን ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የወረደው ጥር ፲ [10] ቀን አመሻሽ ላይ ሲሆን በፍጹም ትሕትና ተራ ሲጠብቅ አድሮ ሌሊት ፲ [10] ሰዓት ላይ ደረሰውና ሊጠመቅ ቀረበ::

አሥር ሰዓት መሆኑም ርግብ [መንፈስ ቅዱስ] ሲወርድ ሰዎች ሥጋዊት ርግብ ናት ብለው እንዳይጠራጠሩ ነው:: ርግብ በሌሊት መንቀሳቀስ አትችልምና::

መድኃኒታችን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ ሲጠጋ አምላክነቱን ተረድቶ "እንዴት ፈጣሪየ ወደ እኔ ትመጣለህ? እንዴትስ በእኔ እጅ ትጠመቃለህ?" አለው:: ትህትና ለእናትና ልጅ ልማዳቸው ነውና:: ጌታ ግን "ጽድቅን ሁሉ ልንፈጽም ይገባል" ሲል እንዲያጠምቀው ፈቀደለት::

ቅዱስ ዮሐንስም "ስመ አብ በአንተ ሕልው ነው:: ስመ ወልድ ያንተ ነው:: ስመ መንፈስ ቅዱስም በአንተ ዘንድ ሕልው ነው:: በማን ስም አጠምቅሃለሁ?" ሲል ጠየቀው::

ጌታ "ወልዱ ለቡሩክ ከሣቴ ብርሃን ተሣሐለነ:: አንተ ካህኑ ለዓለም በከመ ሲመቱ ለመልከ ጼዴቅ" እያልክ አጥምቀኝ አለው:: ትርጉሙም "የቡሩክ አብ የባሕርይ ልጁ : ብርሃንን የምትገልጥ ሆይ ይቅር በለን! አንተ እንደ መልከ ጼዴቅ ሹመት የዓለም ካህኑ ነህና" እንደ ማለት ነው::

ከዚያም ጌታ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ ባሕር አይታ ደነገጠች : ሸሸችም:: [መዝ.፸፮፥፲፮ , ፲፩፥፫] ዮርዳኖስ ጨንቆት ግራ ቀኝ ተመላለሰ:: እሳተ መለኮት ቆሞበታልና ውኃው ፈላ:: በጌታ ትዕዛዝ ግን ጸና::

ጌታ ተጠምቆ: ሥርዓተ ጥምቀትን ሠርቶ: ዮርዳኖስን ብርህት ማሕጸን አድርጐ: የእዳ ደብዳቤአችንንም ቀዶ ከወጣ በኋላ ሰማያት ተከፈቱ:: ማለትም አዲስ ምሥጢር ተገለጠ::

አብ በደመና ሆኖ "የምወደው: የምወልደው: ሕልው ሆኜ ልመለክበት የመረጥኩት የባሕርይ ልጄ ይህ ነው!" ሲል በአካላዊ ቃሉ ፍጹም ተዋሕዶን መሰከረ:: መንፈስ ቅዱስም በአምሳለ ርግብ ወርዶ በራሱ ላይ ተቀመጠ:: ራሱንም ቆንጠጥ አድርጐ ያዘው:: በዚህም የሥላሴ አንድነቱ: ሦስትነቱ ታወቀ: ተገለጠ::

ቅዱስ ዮሐንስ "መጥምቀ መለኮት" የሚባልበትን ታላቁን ክብር ሲያገኝ ዮርዳኖስ የልጅነት መገኛ ቅዱስ ባሕር ሆነ::


🕊  † ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ †  🕊

ቅዱስ ወንጌል ላይ ቅዱስ ሉቃስ "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: [ ሉቃ.፩፥፮ ]

እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር:: እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ ፺ [90] የዘካርያስ ደግሞ ፻ [100] ደርሶ ነበር::

ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት [ኢሳ.፵፥፫ , ሚል.፫፥፩] ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም ፳፮ [26] ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ፮ [6] ወራት ራሷን ሠወረች:: በ፮ [6] ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ [ሰገደ]:: ከዚህ በኋላ ሰኔ ፴ [30] ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

ቅዱስ ዮሐንስ ከተወለደ ፪ ዓመት ከ፮ ወር በሆነው ጊዜ ሰብአ ሰገል በመምጣታቸው በእሥራኤል ምድር የሚገኙ ሕፃናትን ሔሮድስ ቁዝ አስፈጀ:: ትንሽ ቆይቶም አይሁድ ለሔሮድስ ስለ ቅዱሱ ሕፃን ነገሩት:: "ሲጸነስ የአባቱን አንደበት የዘጋ: ሲወለድ ደግሞ የከፈተ 'ዮሐንስ' የሚባል ሕፃን አለና እሱንም ግደል" አሉ::

እናቱ ቅድስት ኤልሳቤጥ ይዛው ስትሸሽ ካህኑን ዘካርያስን ግን በቤተ መቅደስ መካከል ገድለውታል:: አረጋይት ኤልሳቤጥም ሕፃኑን እያሳደገች በገዳመ ዚፋታ ለ፫ [፭] ዓመታት ቆይታለች:: ቅዱስ ዮሐንስ ፭ [፯] ዓመት ሲሞላው ግን እዚያው በበርሃ እናቱ ዐረፈች:: ከሰማይ ዘካርያስና ስምዖን ወርደው ቀበሯት::

ሕፃኑ ዮሐንስ ሲያለቅስ ድንግል ማርያም ስንት አገር አልፋ ሰማችው:: እርሷም ስደት ላይ ነበረችና:: ከጌታ ጋር በደመና ሒደው ድንግል አቅፋ አጽናናችው:: ጌታንም "እንውሰደው ይሆን?" አለችው:: ጌታችን ግን "ለአገልግሎት እስክጠራው እዚህ ይቆይ" አላት:: ባርካው: አጽናንታውም ተለያዩ::

ቅዱስ ዮሐንስ ከዚህ በኋላ በዚያ ቆላ የግመል ጠጉር ለብሶ: ጠፍር ታጥቆ ተባሕትዎውን ቀጠለ:: ለ፳፭ [፳፫] ዓመታትም በንጽሕና ሲኖር ከምድር አራዊትና ከሰማይ መላእክት በቀር ማንንም አላየም:: ይሕችን ዐመጸኛ ዓለምም አልቀመሳትም::

ከዚህ በኋላ ፴ [ 30 ] ዘመን ሲሞላው እግዚአብሔር ከሰማይ ተናገረው:: "ሒድ! የልጄን ጐዳና ጥረግ" አለው:: ነቢያት ስለዚህ ነገር ተናግረው ነበርና:: [ኢሳ.፵፥፫, ሚል.፫፥፩] አባቱ ዘካርያስም "ወአንተኒ ሕፃን ነቢየ ልዑል ትሰመይ: እስመ ተሐውር ቅድመ እግዚአብሔር ከመ ትጺሕ ፍኖቶ" [ሉቃ.፩፥፸፮] ብሎ መንገድ ጠራጊነቱን ተናግሮ ነበርና::

ቅዱስ ዮሐንስ በዚያ ጊዜ በኃይለ መንፈስ ቅዱስ እየገሰገሰ ከበርሃ ወደ ይሁዳ መጣ:: ያዩት ሁሉ ፈሩት: አከበሩት:: ቁመቱ ቀጥ ያለ: ጽሕሙ እንደ ተፈተለ ሐር የወረደ: ጸጉሩ የቁራ ያህል የጠቆረ: መልኩ የተሟላ: ግርማው የሚያስፈራ ገዳማዊ ነውና::

ፈጥኖም ሕዝቡን ለንስሐ ሰበከ: ለንስሐም በርካቶችን አጠመቃቸው:: በዚህ አገልግሎት ለ፮ ወራት ቆይቶ ጌታችን ወደ እርሱ ዘንድ መጣ:: ዮሐንስ ሰማይን ከነግሱ: ምድርን ከነልብሱ የያዘ ፈጣሪ "አጥምቀኝ" ብሎ ሲመጣ ደነገጠ:: የሚገባበትም ጠፋው::

" እንቢ ጌታየ ! አንተ አጥምቀኝ " አለው:: ጌታ ግን "ፈቅጄልሃለሁ" አለው: አጠመቀው:: በዚህ ምክንያት ይሔው እስከ ዛሬም "መጥምቀ መለኮት" ሲባል ይኖራል:: ቅዱስ ዮሐንስ በመጨረሻ ሔሮድስን ገሰጸው:: ንጉሡም ተቀይሞ ለ፯ ቀናት አሠረው::


Forward from: ገድለ ቅዱሳን




Forward from: ገድለ ቅዱሳን
🕊

[    እ ን ኳ ን   አ ደ ረ ሳ ች ሁ ! !   ]

ያን ጊዜ ጌታ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ። ❞ [ ማቴ ፫÷፲፫ ]

🕊                      💖                      🕊

❝ ክርስቶስ በዮርዳኖስ ወንዝ በመጠመቁ ምክንያት ጥምቀትን በእርሱ ጥምቀት ባርኮ ሰጠን። ክርስቶስ የተጠመቀበት የዮርዳኖስ ወንዝ መለኮታዊውን ብርሃን ለበሰ። በእርሱ ጥምቀት ወንዞች ፣ ጅረቶች ፣ ምንጮች ፣ ሁሉ ተቀደሱ። ... መድኅናችን ሆይ በአንተ ጥምቀት የውኃ ምንጮች ሁሉ ተቀደሱ ፤ ስለዚህም ውኃ የመንፈሳውያን ልጆች መገኛ ማኅፀን ሆነች። ❞

[  ቅዱስ ኤፍሬም   ]


❝ ጥምቀትን ለኃጢአት ሥርየት ሰጠን እንዲሁም በዚሁ ጥምቀት ከፍዳ እንድንድንና መንግሥቱን እንድንወርስ አደረገን፡፡ ❞

[ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ]

🕊

ከንግግር ይልቅ ተግባር የገለጸሽ
   ፍኖተ ክርስቶስ ተዋሕዶ አንቺ ነሽ !  ]


🕊                      💖                      🕊


Forward from: ገድለ ቅዱሳን




Forward from: ገድለ ቅዱሳን
🕊

"በስመ አብ  ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን"።

ጥር ፲ [ 10 ] ቀን።

† እንኳን ለገሀድ [ ጋድ ] ጾመ ፣ ለከተራ በዓልና ለአባ ታውብንጦ ለዕረፍት በዓል በሰላም አደረሰን። በተጨማሪ በዚች ከሚታሰቡ ፦ ከሰማዕት ከጠምያኒ ፣ ከኪናርያና ከንግሥት በጥሪቃ ከመታሰቢያቸው ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን። †



- የዕለቱ ሰላም ፦ "ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ ሃሌ ሉያ ፤ ወረደ ወልድ እምሰማያት ውስተ ምጥማቃት ፤ በፍሥሐ ወበሰላም"። [ቅዱስ ያሬድ በድጓው ላይ]

+ + +

- በዚች ዕለት ምንም ምን መብልን ሰይቀምሱ ምእመናን ሁሉ እስከ ምሽት ይጾሙ ዘንድ ከእኛ አስቀድመው የነበሩ ታላላቅ ሊቃውንት የቤተ ክርስቲያን መምህራን ሥርዓትን ሠሩ በምሽትም ቢሆን በታላቁ ጾም ከሚበላው በቀር ጥሉላትን እንዳይቀምሱ። በዚች ዕለት ምእመናን እስከ ምሽት እንደመጾሙን ያዘዙበት ምክንያቱ ይህ ነው የልደትና የጥምቀት በዓል በዓል በረቡዕ ወይም በዓርብ ቀን ቢሆን በበዓለ ኃምሳ የሚበላውን የጥሉላት መብል በጥዋት በመብላት ምእመናን ሁሉ በዓሉን እንዲአከብሩ የከበሩ አባቶቻችን ሐዋርያት አዝዘዋል እሊህ ሁለቱ የእግዚአብሔር ታላላቅ በዓላቶቹ ናቸውና።

- እኛ በዚህ በኅላፊው ዓለም ተድላ ደስታ ደስ የሚለን ለሌሎች እንዳይመስላቸው እንደ አይሁድና እንደ አረማውያን በዓል በመብልና በመጠጥ ብቻ እንዳናደርግ ስለዚህ ከልደትና ከጥምቀት በዓል በዋዜማ ያሉትን ሁለቱን ዕለታት እንድንጾም አዘዙን የልደትና የጥምቀት በዓል በረቡዕና በዓርብ ላይ በሚሆን ጊዜ በረቡዕና በዓርብ ፈንታ እንድንጾማቸው ይገባልና በዚህም ሁለት ሥራ ይፈጸምልናል የጾም ሥራና የበዓል ማክበር ሥራ ነው። እንዲሁም በግብፃውያን አብያተ ክርስቲያን የተሠራ ነው።

- በይረሙን በእሑድ ወይም በአይሁድ ሰንበት ቀን ቢሆን ይህም ጌታ የተገለጸበት ጥር ዐሥራ ቀን ነው በዋዜማው ዐርብ እስከ ምሽት ይጹሙ አስቀድመን እንደተናገርን ጥሉላት አይብሉ የልደትና የጥምቀት በዓልም ሰኞ ቀን ቢሆን በሰንበት ቀን ይጾም ዘንድ አይቻልም ነገር ግን ጥሉላትን ከመብላት ይጠበቁ።

- በጥምቀትም ዕለት ከእኵለ ሌሊት በፊት ተነሥተው በውኃው ላይ ይጸልዩና ይጠመቁ ሕፃናትም በሚጠመቁ ጊዜ በውኃ እንዳይገድፉ ካህናቱም ከመንጋቱ በፊት ቀድሰው ቊርባኑን ያሳርጉ እጅግም ማልደው በጥዋት ከቤተ ክርስቲያን ይውጡ በከበረ ሥርዓታቸው ጌቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙ።

- የመለካውያን ወገኖች ግን የልደትና የጥምቀት ዋዜማ በቅዳሜ ቀን ወይም በእሑድ ቀን ቢሆን በሦስት ሰዓት ይቀድሳሉ ከወደዱም የተባረከ ኅብስት ተመግበው ውኃ ይጠጣሉ ከዚህም በኋላ ካህናቱ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሁነው በየሰዓቱ በመጸለይ ለበዓሉ የሚገባውን የነቢያትን ትንቢቶች ያነባሉ በዚያች ቀን በምሽት ይኸውም ጥር ዐሥር ነው በውኃው ላይ ይጸልያሉ ይህም አባቶቻችን ሐዋርያት እንዳዘዙት አልሆነም። እርሳቸው የኤጲፋንያን በዓል እንዲአክብሩ አዘዋል ይኸውም መድኃኒታችን የተገለጠበት ካኑን በሚባል በሮም ሁለተኛ ወር በሰባት ይህ ጥር ዐሥራ አንድ ቀን ነው።

- መለካውያን ግን የከበሩ አባቶች የቤተ ክርስቲያን መምህራን ያዘዙትን ይተላለፋሉ በልደትና በጥምቀት በዓል ዓርብም ረብዕም ቢሆን አስቀድመው በርሱ ፈንታ ሳይጾሙ በጥዋት ተነሥተው ይበላሉና። እኛንም ከበደላችን ያነጻን ዘንድ በዮርዳኖስም ወንዝ እንደ ተገለጸ የጌትነቱን ክብር በልቡናችን ይገልጥልን ዘንድ የክብር ባለቤት የሆነ ጌታችንን ኢየሱስ ክርስቶስን እንለምነው ጌትነት ክብር ስግደት ለእርሱ ይገባልና ከቸር አባቱ ጋር ይቅር ባይ ከሆነ መንፈስ ቅዱስም ጋር ዛሬም ዘወትርም ለዘላለሙ አሜን።

+ + +

- አባ ታውብንጦስ ፦ ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ ጀምሮ አባ ታኡና በሚባል በሮሜው ሊቀ ጳጳሳት ቤት አደገ እርሱም የምንኵስናን ልብስ አለበሰው። መንፈሳዊ ዕውቀትና ኃይል እንደተሰጠው አይቶ ከእስክንድርያ አገር ውጭ ስሙ ጤናዲራን በሚባል ቦታ ኤጲስቆጶስነት ሹሞ የገዳም አበ ምኔት አደረገው ከእርሱ ሥር ያሉ መነኰሳትም ሰባት መቶ ናቸው።

- ከዚህም በኋላ ከእርሱ ጋር ላሉ መነኰሳት አለቃ የሆነ ኤጲስቆጶስ ታውብንጦስ ከከሀዲ ንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ስለሆነው ሁከት በሰማ ጊዜ ሸሽቶ ወደ ደብረ ሲሐት ገዳም ሒዶ እግዚአብሔርን ከምትፈራ ከአንዲት ድንግል ዘንድ ተቀመጠ። በእርሷ ቤትም ብዙ ዘመናት ኖረ በመጀመሪያ ወደርሷ በገባ ጊዜ ግን ንጉሡን ስለ መፍራት ጣዖትን ስታመልክ አገኛትና የክብር ባለቤት ጌታችን ክርስቶስን ወደ ማመን መለሳት።

- ከዚያም ተርኑጥና መርኑስ ወደ ሚባሉ ገዳማት ሔደ የአብያተ ክርስቲያናትን ወሬ ይሰማ ዘንድ ፈልጎ በጾም በጸሎት ሌሊትም በመትጋት እያገለገለ በአንዲት ገዳም ውስጥ ሁለት ሦስት ቀን ተሠውሮ ያድር ነበር። የመንፈስ ቅዱስም ጸጋ በላዩ እንዳደረ እግዚአብሔርም በእጆቹ ድንቆች ተአምራቶችን እንዳደረገ ከወንበዴዎችና ከዓመፀኞች ብዙዎችን መነኰሳትን አድርጎ ለክርስቶስ ወደ መገዛት እስከ መላሳቸው ድረስ መነኰሳቱ ሁሉ መሰከሩለት።

- ከዚህም በኋላ ፈጽሞ በአረጀ ጊዜ የሚሞትበትን ቀን ዐወቀ ልጆቹንም የክርስቶስ በሆነች በቀናች ሃይማኖት እንዲጸኑ ትእዛዙንም እንዲጠብቁ አስተማራቸው ወዲያውኑ ጥር ፲ [10] ቀን በሰላም ዐረፈ። ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በአባ ታውብጦስ ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋር ትኑር ለዘላለሙ አሜን።

[ ምንጭ ፦ የጥር ፲ ስንክሳር ]

+ + +

"ሰላም እብል ለጾመ ዕለት ዋሕድ። ዘስሙ ገሀድ። መምህራነ ሥርዓት አቀሙ ለዘይመጽእ ትውልድ። እመባልዕት ጥሉላት ወእምነ ቅሡም ማዕድ። አንስት ይትሀረማ ወይጹሙ ዕድ። ሊቁ አርከ ሥሉስ [ አርኬ ] የጥር ፲ [10]

+ + +

- የዕለቱ የማኅሌት ምስባክ ፦ "ለበስኩ ሠቀ ወኮንክዎሙ ነገረ። ላዕሌየ ይዛውዑ እለ ይነብሩ ውስተ አናቅጽ። ወኪያየ የኀልዩ እለ ይሰትዩ ወይነ"። [ መዝ.፷፰፥፲፩ ] የሚነበበው ወንጌል [ ማር.፩፥፩-፱ ]

+ + +

- የዕለቱ የቅዳሴ ምስባክ ፦ "ሣህል ወርትዕ ተራከባ። ጽድቅ ወሰላም ተሰዐማ። ርትዕሰ እምድር ሠረፀት"። [ መዝ.፹፬፥፲ ]የሚነበቡት መልዕክታት [ ገላ.፫፥፳-ፍጻሜ ] ፣ [፩ኛ ዮሐ.፬፥፲፬-፲፰] እና [የሐዋ ሥራ.፲፫፥፳፬-፴ ] የሚነበበው ወንጌል [ማቴ.፫፥፩-፲፫] ። የሚቀደሰው ቅዳሴ ቅዳሴ እግዚእነ ነው። መልካም የጾም ቀንና የከተራ በዓል ለሁላችንም ይሁንልን።

🕊

[  † ጥር ፲ [ 10 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ጾመ ገሃድ
፪. አባ ታውብንስጦስ ዘሲሐት
፫. ቅዱስ ኪናርያ
፬. ቅድስት ጠምያኒ

[   † ወርሐዊ  በዓላት   ]

፩. ቅዱስ ናትናኤል ሐዋርያ
፪. ቅዱስ ኒቆላዎስ ዘሃገረ ሜራ
፫. አቡነ መልክዐ ክርስቶስ
፬. ቅዱስ ያዕቆብ ሐዋርያ [ወልደ እልፍዮስ]
፭. ቅድስት ዕሌኒ ንግስት
፮. ታላቁ ቅዱስ ቆስጠንጢኖስ
፯. ቅዱስ እፀ መስቀል

" እነርሱ እሥራኤላውያን ናቸውና:: ልጅነትና ክብር: ኪዳንም: የሕግም መሰጠት: የመቅደስም ሥርዓት: የተስፋውም ቃላት ለእነርሱ ናቸውና:: አባቶችም ለእነርሱ ናቸውና:: ከእነርሱም ክርስቶስ በሥጋ መጣ:: እርሱም ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው:: አሜን::" [ሮሜ.፱፥፬]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖






Forward from: ገድለ ቅዱሳን
- እርሱ አነጋግሯቸው: ባርኩዋቸው ዐርጉዋል:: ለምልክትም በዓታቸው እንደ ተሰነጠቀ ቀርቷል:: ዘወትርም በዕለተ ሰንበት ይገለጥላቸው ነበር:: ቅዱሳን አባ ገዐርጊና አባ አብርሃም በርካታ ተአምራትን ሲሠሩ ኑረዋል::

- አባ አብርሃም ጥር ፱ [ 9 ] ቀን ሲያርፉ አባ ገዐርጊ ግንቦት ፲፰ [18] ቀን ዐርፎ ተቀብሯል:: በዓታቸው በግቢግም ዛሬ ድረስ በምድረ ግብጽ አለች::

አምላከ ቅዱሳን አበው በፍቅሩ ይገለጥልን:: ከአባቶቻች ጸጋ በረከትም አይለየን::

🕊

[  † ጥር  ፱ [ 9 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት  ]

፩. አባ አብርሃም ገዳማዊ
፪. አባ ገዐርጊ ጻድቅ
፫. ቅዱስ ዲዮስቅርስ ዘሮሜ
፬. አባ ኪናፎርያ

[    †  ወርሐዊ በዓላት    ]

፩. ቅዱሳን ፫፻፲፰ [318]ቱ ሊቃውንት
፪. አባ በርሱማ ሶርያዊ [ ለሶርያ መነኮሳት ኁሉ አባት ]
፫. አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
፬. የብሔረ ብፁዐን ጻድቃን
፭. አባ መልከ ጼዴቅ ዘሚዳ
፮. ቅዱስ ዞሲማስ ጻድቅ

" በረከት በጻድቅ ሰው ራስ ላይ ነው:: የኀጥአንን አፍ ግን ግፍ ይከድነዋል:: የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው:: የኀጥአን ስም ግን ይጠፋል:: " [ ምሳ.፲፥፮ ]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖


Forward from: ገድለ ቅዱሳን
🕊

†  በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ፩ አምላክ ፡፡ አሜን ።  †

" እንኩዋን ለአበው "ቅዱሳን አባ አብርሃም ወአባ ገዐርጊ" ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ "

🕊  † ቅዱሳን አብርሃም ወገዐርጊ †  🕊


†   ተጋድሎተ ቅዱሳን   †

- ቅዱሳኑን የመሰሉ አባቶች "መስተጋድላን" ይባላሉ በግዕዙ:: ለሃይማኖታቸው እስከ ደም ጠብታና እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ መጋደላቸውን የሚያሳይ ነው:: መጋደል ጐዳናው ብዙ ዓይነት ነው::

- ከራሱ ጋር የሚጋደል አለ:: ከዓለም ጋር የሚጋደልም አለ:: የቅዱሳኑ ተጋድሎ ግን በዋነኝነት ከ፪ አካላት ጋር ነው:: በመጀመሪያ ፍትወታት እኩያትን [ ኃጣውዕን ] ከሚያመጡ አጋንንት ጋር ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ "ሃይማኖቸታችሁን ካዱ: ለጣዖትም ስገዱ" ከሚሉ ከሃድያን ጋር የሚደረግ ትግል ነው::

- በተለይ ፪ኛው እስከ ሞት የሚያደርስ ውሳኔን ይጠይቃል:: የዚህን ቅዱስ ሕይወት ለመረዳት ግን አንድ ነገርን ልብ እንድትሉልኝ እፈልጋለሁ::

- ያለንበት ዘመን ክርስትና በራድ [ ቀዝቃዛ ] በመሆኑ የቀደሙ አባቶች የጸና ተጋድሎ አንዳንዴ ግራ ሲያጋባን ተመልክቻለሁ:: ቅዱሳኑ ሁሌም አንድ ነገርን እያሰቡ ይኖራሉ:: ይኼውም በዘመኑ በርካቶቻችን የረሳነው: ወይም ማስታወስ የማንፈልገው ነገር ይመስላል::

- ሰማያዊው አምላክ ከዙፋኑ ወርዶ በተዋሐደው ሥጋ በቃል ሊገለጽ የማይችል መከራን ስለ እኛ ተቀብሏል:: ክርስትና ማለት ቀራንዮን በልብ ውስጥ መሳል ነው:: ፍቅረ መስቀሉን: የጌታንም ውለታ የሚያስብ ማንኛውም ሰው: የትኛውም ዓይነት መከራ ቢመጣበት አይታወክም::

- ቅዱሳኑም የፍቅራቸውና የትእግስታቸው ምሥጢር ይኼው ነው:: ጌታችን "የሚወደኝ ቢኖር የሞቱን መስቀል ተሸክሞ ይከተለኝ" [ማቴ.፲፮፥፲፰] እንዳለው ቅዱሳኑ ይህንን ቃል በቃል ሲፈጽሙት እነሆ እንመለከታለን::

†  ገዳማዊ ሕይወት  †

- ገዳማዊ ሕይወት ጥንቱ ብሉይ ኪዳን ነው:: በቀዳሚነትም በደብር ቅዱስ አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ደቂቀ ሴት እንደ ጀመሩት ይታመናል:: ሕይወቱ በጐላ: በተረዳ መንገድ የታየው ግን በታላቁ ጻድቅ ሄኖክ: ከዚያም በቅዱሱ ካህን መልከ ጼዴቅ አማካኝነት ነው::

- ቀጥሎም እነ ቅዱስ ኤልያስ ነቢይ: እነ ኤልሳዕ ደቀ መዝሙሩ ኑረውበታል:: በሐዲስ ኪዳን ደግሞ ሙሉ ሕይወቱን በገዳም [ በበርሃ ] ያሳለፈው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ቅድሚያውን ይይዛል::

- ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና መድኃኒታችን ክርስቶስ በገዳመ ቆረንቶስ ለ፵ [ 40 ] ቀናት በትሕርምት ኑሮ ገዳማዊ ሕይወትን ቀድሷል: አስተምሯል:: በዘመነ ስብከቱም ያድርባት የነበረችው የደብረ ዘይቷ በዓቱ [ ኤሌዎን ዋሻ ] በራሷ ለዚህ ሕይወት ትልቅ ማሳያ ናት::

- ከጌታ ዕርገት በሁዋላም ክርስቲያኖቹ የዓለም ሁካታ ሲሰለቻቸው: አንድም በንጹሕና በተሸከፈ ልቡና ለፈጣሪያቸው መገዛትን ሲሹ ከከተማ ወጣ እያሉ ይኖሩ እንደ ነበር የታሪክ መዛግብት ያሳያሉ:: አኗኗራቸውም በቡድንም: በነጠላም ሊሆን ይችላል::

- ዋናው ነገር ግን በጾምና በጸሎት መትጋታቸው ነው:: ይሕም ሲያያዝ እስከ ፫ኛው መቶ ክ/ዘመን ደረሰ:: በዚህ ዘመን ግን አባ ዻውሊ የሚባል አንድ ንጹሕ ክርስቲያን ይሕንን ሕይወት ወደ ሌላ ደረጃ ከፍ አደረገው:: ለ፹ [ 80 ] ዓመታት ሰው ሳያይ ተጋድሎ "የባሕታውያን አባት" ተባለ:: ደንብ ያለው ተባሕትዎም ጀመረ::

- ይህ ከሆነ ከ፳ [ 20 ] ዓመታት በሁዋላ ደግሞ አባ እንጦንስ የሚባሉ ደግ ክርስቲያን ይህንን ገዳማዊ ሕይወት በሌላ መንገድ አጣፈጡት:: በቅዱስ ሚካኤል አመንኩዋሽነት ገዳማዊ ሕይወት በምንኩስና ተቃኘ:: ስለዚህም አባ እንጦንስ የመነኮሳት አባት ተባሉ::

- እርሳቸውም ሕይወቱን ለማስፋፋት ከተለያዩ አሕጉር ደቀ መዛሙርትን እየተቀበሉ አመንኩሰዋል:: ቅዱሳን የአባ እንጦንስ ልጆችም ወደየ ሃገራቸው ተመልሰው: ሕይወቱን በተግባር አሳይተው ገዳማዊነትን አስፋፍተዋል::

- አባ እንጦንስ አባ መቃርስን: አባ መቃርስ አባ ዮሐንስን ወልደዋል:: አባ ዮሐንስም የታላቁ ገዳመ አስቄጥስ አበ ምኔት ሆነው በጸጋ አገልግለዋል:: አስቄጥስ በምድረ ግብጽ የሚገኝ: በስፋቱና ብዙ ቅዱሳንን በማፍራቱ ተወዳዳሪ የሌለው የዓለማችን ቁጥር አንድ ገዳም ነው::

- ሕይወተ ምንኩሰናም ወደ መላው ዓለም የተስፋፋ በዚህ ገዳም መናንያን አማካኝነት ነው:: በዚህ ገዳም ላይ የሚሾሙ አበው ደግሞ በብዛት መንፈስ ቅዱስ ያደረባቸውና አባታቸውን ቅዱስ መቃርስ ታላቁን የመሰሉ ናቸውና ኃላፊነቱ እጅግ ከባድ ነው::

- በ፭ [5] ኛው መቶ ክ/ዘመን በምድረ ግብጽ ተወልደው ያደጉት አባ ዮሐንስ ከመነኑባት ዕለት ጀምረው በፍጹም ተጸምዶና ተጋድሎ ለፈጣሪያቸው ስለ ተገዙ የታላቁ ገዳም አበ ምኔት ሊሆኑ ተገባቸው::

- በአበ ምኔትነት ዘመናቸውም መንጋውን ይጠብቁ ዘንድ ብዙ ደከሙ:: በተለይ ቅዱስ ቃሉን ያስተምሩ ዘንድ ተጉ:: ሕይወተ መላእክትንም ያሳዩ ዘንድ በቃል ብቻ ያይደለ በተግባር ሆነው : ከመንፈሳዊ አብራካቸው ብዙ ቅዱሳንን ወለዱ::

- ከዋክብቱ አባ ገዐርጊ: አባ አብርሃም: አባ ሚናስ: አባ ዘካርያስ . . . የአባ ዮሐንስ ፍሬዎች ናቸውና:: ጻድቁ በዘመናቸው ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: ከዕረፍታቸው በሁዋላ እንኩዋ መግነዛቸውና የልብሳቸው እራፊ ብዙ ድውያንን ፈውሷል::

†  🕊  ቅዱሳን አብርሃም ወገዐርጊ  🕊  †

- እነዚህ ፪ ቅዱሳን በግብጽ በርሃ ያበሩ የቅዱሱ አባ ዮሐንስ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቹ ናቸው:: አስቀድሞ ወደ በርሃ የወጣ አባ አብርሃም ሲሆን እርሱም በምድረ ግብጽ የተባረኩ ሰዎች ልጅ ነው::

- ወላጆቹ በፈቃደ እግዚአብሔር እርሱን ከወለዱ በሁዋላ ብዙ በጐነትን አሳይተዋል:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ [ የችግርና የረሃብ ጊዜ ] ነበርና ሃብታቸውን በምጽዋት ጨርሰዋል:: የሚገርመው የቅዱሱ አባት "ነዳያን እየተራቡ ዝም አልልም" ብሎ እየተበደረ ያበላቸው ነበር::

- እርሱ ባረፈ ጊዜም የተባረከች ሚስቱ መልካምን እየሠራች ብዙ ተፈትናለች:: ለባርነት ተማርካ እስክትሔድ ድረስም ታግሣለች:: ቅዱሱን ልጇን አብርሃምንም እንደሚገባ አሳድጋ "ሚስት ላጋባህ" አለችው::

- እርሱ ግን "እናቴ ሆይ! እኔ ይህንን ዓለም አልፈልገውም" ሲል መለሰላት:: ይህንን ስትሰማም ሐሴትን አድርጋ አብርሃምን ወደ በርሃ ሸኘችው:: አባ አብርሃምም ወደ ገዳመ አስቄጥስ ሔዶ በደብረ አባ መቃርስ መነኮሰ:: ተጋድሎንም በዚያው ጀመረ::

- ሲጾም: ሲጸልይ: ሲጋደልም ዘመናት አለፉ:: በዚህ ጊዜም ታላቁ አባ ገዓርጊ ከዓለም ወደ በርሃ መጥቶ መነኮሰ:: የአባ ዮሐንስ የመንፈስ ልጆች ውስጥም እንደ አንዱ ተቆጠረ:: አባ ገዐርጊን የተመለከተው አባ አብርሃምም ስለ ወደደው አብረው መኖር ጀመሩ::

- ፪ቱ ቅዱሳንም "በግቢግ" በምትባል በዓታቸው በፍቅር ለፈጣሪያቸው ሲገዙ ዘመናት አለፉ:: በነዚህ ዘመናትም በርካታ ቅዱሳን ከመንፈሳዊ አብራካቸው አፈሩ ከቅድስናቸው ብዛትም ከሰንበት በቀር እህልን አይቀምሱም ነበር::

- የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አንድ ቀን ከዓለት በተወቀረች በዓታቸው ውስጥ በጸሎት ላይ ሳሉ ወረደላቸው:: የበዓታቸውን ዓለት ሰንጥቆ ሲገባ ታላቅ ግርማና ብርሃን አካባቢውን ዋጠው:: ቅዱሳኑም ለመድኃኒታችን ተደፍተው ሰገዱ::






Forward from: ገድለ ቅዱሳን
- ቅዱስ ሚክያስ ቁጥሩ ከ፲፪ [12]ቱ ደቂቀ ነቢያት ሲሆን ዘመነ ትንቢቱም ቅ.ል. ክርስቶስ በ፰ መቶ [800] ዓ/ዓ አካባቢ ነው:: "ደቂቀ ነቢያት" ማለት በጥሬው "የነቢያት ልጆች" ማለት ነው:: አንድም የጻፏቸው ትንቢቶች ሲበዙ ፲፬ [14] ምዕራፍ: ሲያንስ ፩ ምዕራፍ ያላቸው ናቸውና ደቂቅ ይላቸዋል::

- ሚክያስ ትውልዱ ከነገደ ብንያም ሲሆን አባቱ ሞራት [ሞሬት] ይባላል:: ሚክያስ ማለት "መኑ ከመ አምላክ-እንደ እግዚአብሔር ያለ ማን ነው!" ማለት ነው:: አንድም "መልአከ እግዚአብሔር" ማለት ነው:: የአባቶቻችን ሁሉ ስማቸው እግዚአብሔርን የሚሰብክ ነው::

- ቅዱሱ ነቢይ ልጅ እያለ መላእክት ያነጋግሩት ነበር:: በዚህ ምክንያት ከሰው አይቀርብም:: ትክ ብለው ሲያዩት በፊቱ ላይ ብርሃን ቦግ ቦግ እያለ ይታይ ነበር:: በወጣትነት ዘመኑ እግዚአብሔር ለትንቢት ሲጠራው በእሺታ ታዘዘ:: በ3ቱ ነገሥታት [በኢዮአታም: አካዝና ሕዝቅያስ] ዘመንም ትንቢቶችን ተናግሯል:: ሕዝቡን: መሣፍንቱን: ነገሥታቱን አስተምሮ ገስጿል::

- አንድ ቀን በቤተ ልሔም ሲያልፍ የዳዊት ከተማ ፈት ሁና: ዳዋ በቅሎባት ቢመለከት አዘነ:: ወዲያውም ትንቢት ተናገረላት::
"ወአንቲኒ ቤተ ልሔም ምድረ ኤፍራታ: ኢትቴሐቲ እምነገሥተ ይሁዳ: እስመ እምኔኪ ይወጽዕ ንጉሥ::"
[አንቺም የኤፍራታ ምድር ቤተ ልሔም: የይሁዳ ነገሥታት ከነገሡባቸው ከተሞች ከቶ አታንሺም:: ወገኖቼን እሥራኤልን የሚጠብቃቸው ንጉሥ ካንቺ ዘንድ ይወጣልና] አለ::

- ይኸውም አልቀረ ለጊዜው ከሚጠት በሁዋላ ደጉ ዘሩባቤል ነግሦባታል:: በፍጻሜው ግን የባሕርይ ንጉሠ ነገሥት ኢየሱስ ክርስቶስ ከንጽሕት ድንግል ማርያም ተወልዶባታል::

- ቅዱስ ሚክያስ ወገኖቹን ሲያስተምርና ሲመራ ኑሮ: ፯ [7] ምዕራፎች ያሉትን ሐረገ ትንቢት ተናግሮ: በመልካም ሽምግልና በንጉሡ ሕዝቅያስ ዘመን ዐርፏል:: ወገኖቹም ቀብረውታል:: ጌታም በክብረ ነቢያት ከልሎታል::

አምላከ አበው ቅዱሳን ለተፋቅሮ ይበለን: ከበረከታቸውም ይክፈለንና

🕊

[   † ጥር ፰ [ 8 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት   ]

፩. ታላቁ ቅዱስ መቃርስ
፪. ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ
፫. አባ እንድራኒቆስ ሊቀ ዻዻሳት
፬. አባ ብንያሚን ሊቀ ዻዻሳት

[     †  ወርሐዊ በዓላት      ]

፩. ቅዱስ ሙሴ ሊቀ ነቢያት
፪. ኪሩቤል [አርባዕቱ እንስሳ]
፫. አባ ብሶይ [ቢሾይ]
፬. አቡነ ኪሮስ
፭. አባ ሳሙኤል ዘደብረ ቀልሞን
፮. ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ [ከ፲፪ቱ ሐዋርያት]

" ምን ይዤ ወደ እግዚአብሔር ፊት ልምጣና በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ? የሚቃጠለውን መስዋዕትና የአንዱን ዓመት ጥጃ ይዤ በፊቱ ልምጣን? እግዚአብሔርስ በሺህ አውራ በጐች: ወይስ በእልፍ የዘይት ፈሳሾች ደስ ይለዋልን? . . . ሰው ሆይ! መልካሙን ነግሮሃል:: እግዚአብሔርም ከአንተ ዘንድ የሚሻው ምንድር ነው? ፍርድን ታደርግ ዘንድ: ምሕረትንም ትወድ ዘንድ: ከአምላክህም ጋር በትሕትና ትሔድ ዘንድ አይደለምን ? " [ሚክ.፮፥፮]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖


Forward from: ገድለ ቅዱሳን
🕊

[  እንኩዋን ለቅዱሳን አበው "አባ መቃርስ" እና "ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።  ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !

🕊  † ታላቁ ቅዱስ መቃርስ †   🕊

- ታላቁ ቅዱስ መቃርስ [ ቅዱስ መቃሬ ] "ጽድቅ እንደ መቃርስ" የተባለለት የመነኮሳት ሁሉ አለቃ: ከ፹ [80] ዓመታት በላይ በበርሃ የኖረ: በግብፅ ትልቁን ገዳም [አስቄጥስን] የመሠረተ: ከ፶ ሺህ [50,000] በላይ መነኮሳትን ይመራና ይመግብ የነበረ ፍፁም ጻድቅ ነው::

- በ፬ [4] ኛው መቶ ክ/ዘ አርዮሳውያን ደጉን ታላቅ አባት በሰንሰለት አስረው ከግብፅ ወደ እስያ በርሃ ከጉዋደኛው ቅዱስ መቃርዮስ እስክንድርያዊ ጋር አሰድደውታል:: በዚያ ለ፪ [2] ዓመታት ስቃይን ከተቀበሉ በሁዋላ በአረማውያን ፊት ድንቅ ተአምር አድርገው አረማውያንን ከነ ንጉሳቸው አጥምቀዋል::

- በተሰደዱባት ሃገርም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ [ስም አጠራሩ ይክበርና] እመቤታችንን: ቅዱሳን ሐዋርያትን: አዕላፍ መላእክትን: በተለይ ደግሞ ቅዱሳኑን ዳዊትን: ዮሐንስ መጥምቁንና ወንጌላዊውን: ማርቆስን: ዼጥሮስን: ዻውሎስን አስከትሎ ወርዶ ተገልጦላቸዋል:: በቅዱስ አንደበቱም የምሕረት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል::

- ታላቁ ቅዱስ መቃርስና ባልንጀራው መቃርዮስ ከ፪ [2] ዓመታት ስደትና መከራ በሁዋላ ስደት በወጡባት ዕለት መልዐኩ ኪሩብ በክንፉ ተሽክሞ ወደ ግብፅ መልሷቸዋል:: በወቅቱም ጻድቁን ለመቀበል ከ፶ ሺህ [50,000] በላይ የሚሆኑ ልጆቻቸው መነኮሳት በዝማሬ ወጥተዋል::

- ቅዱስ መቃርስ ካረፈ በሁዋላ ከክቡር ሥጋው ብዙ ተአምራት ይታዩ ነበርና የሃገሩ [የሳስዊር] ሰዎች ሊወስዱት ፈለጉ:: ሳስዊር ማለት ቅዱሱ ተወልዶ ያደገባት ወላጆቹ [አብርሃምና ሣራ ይባላሉ] የኖሩባት ቦታ ናት:: የምትገኘውም ግብጽ ውስጥ ነው::

- በምድረ ግብጽ: በተለይም በገዳመ አስቄጥስ የአባ መቃርስን ያህል ክቡርና ተወዳጅ የለምና የሃገሩ ሰዎች የነበራቸው አማራጭ መስረቅ ነበር:: መሥረቅ ኃጢአት ቢሆንም እነሱ ግን ስለ ፍቅር: አንድም ለበረከት አደረጉት::

- ወደ ሳስዊርም ወስደው: ቤተ ክርስቲያን በቅዱሱ ስም አንጸው በክብር አኖሩት:: በዚያም ለመቶዎች ዓመታት ተቀመጠ:: በ፯ [7] ኛው መቶ ክ/ዘመን ግን ተንባላት [እስላሞች] መጥተው ቤተ ክርስቲያኑን አጠቁ:: በዚህ ጊዜም ሕዝቡ የጻድቁን አጽም ይዘው ሸሹ:: በሌላ ቦታም እንደ ገና በስሙ ቤተ ክርስቲያን አንጸው በዚያ አኖሩት::

- በእነዚህ ሁሉ ዓመታት የመንፈሳዊ አባታቸውን ሥጋ ያጡት የገዳመ አስቄጥስ ቅዱሳን ያዝኑ ይጸልዩ ነበርና ልመናቸውን ፈጣሪ ሰማ:: አባ ሚካኤል ሊቀ ዻዻሳት በነበረበት ዘመን: ከገዳሙ ለሌላ ተግባር ወደ ሳስዊር የተላኩ አበው ከታላቁ አባት ቤተ ክርስቲያን ሲደርሱ ሰውነታቸው ታወከ::

- ይዘው ለመውሰድ ሙከራ ቢያደርጉ ሊሳካላቸው አልቻለም:: ምክንያቱም የቤተ ክርስቲያኑ ጠባቂ ደወል ደውሎ ሕዝቡን ሁሉ ጠርቶ ነበርና:: ሕዝቡና ሃገረ ገዢው የሆነውን ሲሰሙ "የቅዱሱን ሥጋ ብትነኩ እንገላቹሃለን" ብለው ሰይፍ: ዱላ: ጐመድና ጦር ይዘው መጡባቸው::

- መነኮሳቱ ግን ባዷቸውን ሊመለሱ አልፈቀዱምና ሌሊቱን ሲያለቅሱና ሲጸልዩ አደሩ:: መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜም ታላቁ መቃርስ በግርማ ወርዶ መኮንኑን "ለምን ወደ ልጆቼ እንዳልሔድ ትከለክለኛለህ?" ሲል በራዕይ ተቆጣው:: በዚህ ምክንያትም መነኮሳቱ የቅዱሱን ሥጋ ተቀበሉ::

- ሕዝቡም በዝማሬና በማሕኅሌት: ከብዙ እንባ ጋር ሸኟቸው:: ታላቁ መቃሬ ወደ ገዳሙ ሲደርስም ታላቅ ደስታ ተደረገ:: ቅዱሳን ልጆቹ ከመንፈሳዊ አባታቸው ተባርከው በክብር አኑረውታል::

- ይህቺ ዕለት ቅዳሴ ቤቱ ስትሆን የተቀደሰችውም በ7ኛው መቶ ክ/ዘ በአባ ብንያሚን እጀ ነው::


🕊  † ቅዱስ ሚክያስ ነቢይ †   🕊

- ነቢይ ማለት በቁሙ ኃላፍያትን [አልፎ የተሠወረውን ምሥጢር] : መጻዕያትን [ገና ለወደ ፊት የሚሆነውን] የሚያውቅ ሰው ማለት ነው:: ሃብተ ትንቢት የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ሲሆን እርሱ ለወደደው ደግሞ በጸጋ ይሰጠዋል:: እነዚህም ከጌታ ሃብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባቶችና እናቶች "ቅዱሳን ነቢያት" በመባል ይታወቃሉ::

- ዘመነ ነቢያት ተብሎ የሚታወቀው ብሉይ ኪዳን ቢሆንም እስከ ምጽዓት ድረስ ጸጋውን እግዚአብሔር ለፈቀደላቸው አይነሳቸውም:: በሐዋርያት መካከልም ቅዱስ አጋቦስን የመሰሉ ነቢያት ነበሩ:: [ሐዋ.፲፩፥፳፯]

- ቅዱሳን ነቢያት ከእግዚአብሔር እየተላኩ ሰውን ከፈጣሪው እንዲታረቅ ይመክራሉ: ይገስጻሉ:: ከበጐ ሃይማኖታቸውና ንጽሕናቸው የተነሳም እግዚአብሔርን በተለያየ አርአያና አምሳል አይተውታል::
"እስመ በአንጽሖ መንፈስ ርዕይዎ ነቢያት ለእግዚአብሔር:: ወተናጸሩ ገጸ በገጽ::" እንዳለ አባ ሕርያቆስ:: [ ቅዳሴ ማርያም ]

- የብዙ ነቢያት ፍጻሜአቸው መከራን መቀበል ነው:: እውነትን ስለ ተናገሩ: አንዳንዶቹም በእሳት: አንዳንዶቹም በሰይፍ: አንዳንዶቹም በመጋዝ ተፈትነዋል:: ሌሎቹ ለአናብስት ሲጣሉ ቀሪዎቹ ደግሞ በድንጋይ ተወግረዋል::

- ስለዚህም መከራቸው ለቤተ ክርስቲያን መሠረት ተብለዋል:: ጌታም ለደቀ መዛሙርቱ "ሌሎች ደከሙ: እናንተ በድካማቸው ገባችሁ" ብሎ የነቢያቱን መከራ ተናግሯል:: [ ዮሐ.፬፥፴፮ ]

- ነቢያት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስና እና ድንግል እናቱን ለማየት ብዙ ጥረዋል: ሽተዋልም:: "ብዙ ነቢያትና ጻድቃን እናንተ የምታዩትን ሊያዩ ሹ" እንዳለ ጌታ በወንጌል:: [ማቴ.፲፫፥፲፮, ፩ዼጥ.፩፥፲] ዛሬ ግን በሰማያት ጸጋ በዝቶላቸው: ክብር ተሰጥቷቸው ሐሴትን ያደርጋሉ::

- ቅዱሳን ነቢያት በዋነኝነት ፲፭ [15] ቱ አበው ነቢያት: ፬ [4]ቱ ዐበይት ነቢያት: ፲፪ [12]ቱ ደቂቀ ነቢያትና ካልአን ነቢያት ተብለው በ፬ [4] ይከፈላሉ::

- ፲፭ቱ [ 15ቱ ] አበው ነቢያት" ማለት :-

- ቅዱስ አዳም አባታችን
- ሴት
- ሔኖስ
- ቃይናን
- መላልኤል
- ያሬድ

- ኄኖክ
- ማቱሳላ
- ላሜሕ
- ኖኅ
- አብርሃም
- ይስሐቅ
- ያዕቆብ
- ሙሴና
- ሳሙኤል ናቸው::

- ፬ቱ [ 4 ]ቱ ዐበይት ነቢያት

- ቅዱስ ኢሳይያስ ልዑለ ቃል
- ቅዱስ ኤርምያስ
- ቅዱስ ሕዝቅኤልና
- ቅዱስ ዳንኤል ናቸው::

- ፲፪ ቱ  [ 12 ] ቱ ደቂቀ ነቢያት"

- ቅዱስ ሆሴዕ
- አሞጽ
- ሚክያስ
- ዮናስ
- ናሆም
- አብድዩ
- ሶፎንያስ
- ሐጌ
- ኢዩኤል
- ዕንባቆም
- ዘካርያስና
- ሚልክያስ ናቸው::

- " ካልአን ነቢያት " ደግሞ :-

- እነ ኢያሱ
- ሶምሶን
- ዮፍታሔ
- ጌዴዎን
- ዳዊት
- ሰሎሞን
- ኤልያስና
- ኤልሳዕ ሌሎችም ናቸው::

ነቢያት በከተማም ይከፈላሉ::

- የይሁዳ [ ኢየሩሳሌም ] :
- የሰማርያ [ እሥራኤል ]ና

- የባቢሎን [ በምርኮ ጊዜ ] ተብለው ይጠራሉ:: በዘመን አከፋፈል ደግሞ :-

- ከአዳም እስከ ዮሴፍ [ የዘመነ አበው ነቢያት ] :
- ከሊቀ ነቢያት ሙሴ እስከ ነቢዩ ሳሙኤል [የዘመነ መሳፍንት ነቢያት]

- ከቅዱስ ዳዊት እስከ ዘሩባቤል ያሉት [የዘመነ ነገሥት ነቢያት]:
- ከዘሩባቤል ዕረፍት እስከ መጥምቁ ዮሐንስ ያሉት ደግሞ [የዘመነ ካህናት ነቢያት] ይባላሉ::
- ስለ ቅዱሳን ነቢያት በጥቂቱ ይህንን ካልን ወደ ዕለቱ በዓል እንመለስ::


Forward from: ገድለ ቅዱሳን
🕊                        💖                      🕊

[ ጥር ፯ [ 7 ] ]


እንኩዋን ለአጋእዝተ ዓለም "ሥላሴ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።     
                        


                 †       †       †
🕊                        💖                      🕊



20 last posts shown.