እሳት የማያቃጥላት ዕፅ፦
እሳት ከነደደ የማያቃጥለው ዛፍ የለም። ነቢዩ ሙሴ ግን እሳት እየነደደባት እሳት የማያቃጥላት ፅፀ ጳጦስ የተባለች ዛፍ በደብረ ሲና አይቶ ተደንቆ ነበር። ያቺ ዕፀ ጳጦስ የድንግል ማርያም ምሳሌ ናት።
እሳቱ ከዛፏ ጋር እየነደደ ቢታይም እንዳላቃጠላት ሁሉ፥ ድንግል ማርያምም ጌታችን ክርስቶስን ጸንሳ በወለደች ጊዜ እሳተ መለኮቱ አላቃጠላትም።
አንድም፥እሳት የተባለ ሞት ነው።
ሁሉንም ዛፎች ማውደም የሚችለው እሳት ዕፀ ጳጦሷን ማቃጠል እንዳልቻለ ሁሉ፥ የአዳምን ልጆች በሙሉ የሚበላውና የበላው ሞትም፥ በእርሷ በእመቤታችን ላይ በእሳት አምሳል ታይቷል፤ አፍርሶ አበስብሶ ያስቀራት ዘንድ ግን አልተቻለውም።
እሳተ መለኮት ያላቃጠላትን ጳጦስ፥
አዳም በዕፀ በለስ ያነደደው እሳት/ሞት እንዴት ያቃጥላት ዘንድ ይቻለዋል?
✝️እንኳን አደረሳችሁ✝️
© የኔታ ሥሙር አላምረው