Housing in Addis Ababa የአዲስ አበባ ቤቶች


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


The interest of this Channel is giving continuous information about housing projects (40/60&20/80) & other Real Estates Updates. This page is not a gov't page.

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


"ይሄ ማ በቅቅል ብቻ አይታለፍም"😂


በአዲስ አበባ ከተማ 18 ሄክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ ሊቀርብ ነው

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ፤ በጥቅሉ 18 ሄክታር ስፋት ያላቸው 427 ቦታዎችን ለሊዝ ጨረታ ሊያቀርብ ነው። በመዲናይቱ ዘጠኝ ክፍለ ከተሞች የሚገኙት እነዚህ ቦታዎች፤ ለመኖሪያ እና ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ መሆናቸው ተገልጿል።

በከተማይቱ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመሬት ዝግጅት እና ባንክ ጥበቃ ዳይሬክተር አቶ ሀብታሙ ተስፋዬ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” እንደተናገሩት፤ ለጨረታ የሚቀርቡት ቦታዎች “በተለያየ አግባብ ወደ መሬት ባንክ የገቡ ይዞታዎች” ናቸው። በአሁኑ ዙር ጨረታ በቦሌ እና ልደታ ክፍለ ከተሞች የሚገኙ የመሬት ይዞታዎች እንዳልተካተቱ ዳይሬክተሩ ገልጸዋል።

ለጨረታ የሚቀርቡት ቦታዎች ዝርዝር፤ “አዲስ ልሳን” ጋዜጣ ማግኘት እንደሚቻል የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ይህንን ተከትሎ የጨረታ ሰነድ ሽያጩ “ከእጅ ንኪኪ በጸዳ መልኩ” ከመጪው ሰኞ መጋቢት 1 እስከ መጋቢት 12 ድረስ ባሉት ቀናቶች የሚከናወን መሆኑንም ጠቁሟል።

🔴ዝርዝር ዘገባውን ለማንበብ ➡️ https://ethiopiainsider.com/2025/15278/

22.1k 0 196 16 130

ለአዲስ አበባ ባለጓሮዎች

በ2016 ዓ.ም በተሻሻለው የአዲስ አበባ የህንፃ መመሪያ መሰረት በከተማ አስተዳደሩ ክልል ውስጥ የሚገኙ አርሶ አደሮች በይዞታቸው ላይ ማልማት የሚችሉበትን ህጋዊ አሰራር ያሳያል፡፡
በመመሪያው ከገጽ 34 እስከ 36 በተገለፀው መሰረት ከ1,000 ካሬ በታች ላሉ ይዞታቸው ስፋት 80 በመቶ ያልበለጠ፣
ከ1,001 እስከ 2,000 ካሬ ሜትር ላሉ ይዞታዎች የይዞታው 70 በመቶ ያልበለጠ፣
ከ2,001 እስከ 3,000 ካሬ ሜትር ላሉ ይዞታዎች የይዞታው 50 በመቶ ያልበለጠ፣
ከ3,001 እስከ 4,000 ካሬ ሜትር ላሉ ይዞታዎች የይዞታው 25 በመቶ ያልበለጠ፣
ከ4,001 እስከ 5,000 ካሬ ሜትር ላሉ ይዞታዎች የይዞታው 20 በመቶ ያልበለጠ እንዲሁም
ከ5,001 ካሬ ሜትር በላይ ላሉ ይዞታዎች የይዞታው 20 በመቶ ያልበለጠ
ነገር ግን አጠቃላይ ግንባታው ከ2,000 ካሬ ሜትር በላይ መብለጥ የለበትም ሲል ይደነግጋል፡፡

ይህ ማለት ቀደም ብሎ አርሶ አደሩ ማልማት የሚችለው 5% በሚል ተቀምጦ የነበረው አሰራር ከላይ በተዘረዘሩት አገላለፆች ተቀይሯል ማለት ነው፡፡

የአርሶ አደር ማቋቋምና ሬጉላቶሪ ዘርፍ ም/ኮሚሽነር ወ/ሮ ሎኮ ዳለቻ አርሶ አደሩ ለረጂም ጊዜ ሲጠይቅ የነበረው ጥያቄ መልስ ያገኘ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ነገር ግን ሌብነትና ብልሹ አሰራርን መከላከል ይገባል ብለዋል፡፡
አያይዘውም በየደረጃው ያሉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች መመሪያው ሳይሸራረፍ መተግበር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የአርሶ አደር ማቋቋምና ልማት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረጋሣ ባይሳ በበኩላቸው መመሪያውን ለክፍለ ከተሞች እንዳወረዱ፤ በባለሙያም አተገባበሩ ላይ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡
በአዲስ አበባ አርሶአደርና ከተማ ግብርና ልማት ኮሚሽን

37.1k 0 163 6 159

አያት መንግሥት ባለበት አገር የገዙትን ሱቅ አላስረክብም ብሎ ለ18 ዓመታት እያሰቃያቸው መሆኑን ገዥዎች ተናገሩ

የሚመለከተው የመንግሥት አካል መፍትሔ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል
‹‹ያሉትን ችግሮች በንግግር እንፍታ ብለናቸዋል››

አያት ሪል ስቴት
ከአያት አክሲዮን ማኅበር ከ18 ዓመታት በፊት የንግድ ሱቆችን ግዥ ሲፈጽሙ በገባው ውል መሠረት ሙሉ ለሙሉ ገንብቶ በ18 ወራት ሊያስረክባቸው ስምምነት የፈጸሙ ቢሆንም፣ የተለያዩ ምክንያቶችን በመስጠትና ምላሽ በመንፈግ ላለፉት 18 ዓመታት እያሰቃያቸው መሆኑንና ሊያስረክባቸው እንዳልቻለ ገልጸው፣ መንግሥት ባለበት አገር መበደል ስለሌለባቸው የሚመለከተው አካል መፍትሔ እንዲሰጣቸው ገዥዎች ጠየቁ፡፡
በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ አሥር አያት ባቡር ጣቢያ አካባቢ ከ550 በላይ የንግድ ሱቆች...

ተጨማሪ ያንብቡ: https://www.ethiopianreporter.com/138841/


(ዘ-ሐበሻ ዜና) ከአያት ሪል ስቴት ሱቅ የገዙ ሰዎች በድርጅቱ ላይ አቤቱታ አሰሙ፡፡ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 አያት ሾፒንግ ሞል በሚል በተገነባው ህንፃ ውስጥ ሱቅ የገዙት የዛሬ 16 አመት እንደነበር አቤቱታ አቅራቢዎቹ ገልፀዋል፡፡ በወቅቱ ድርጅቱ በሁለት አመት ውስጥ ግንባታውን አጠናቆ እንደሚያስረክባቸው ቃል እንደገባላቸውም አስረድተዋል፡፡

የአያት ሞል ሱቅ ባለቤቶች ማህበር ፀሀፊ ሩት ግርማይ ስትናገር ‹‹እኛ የማህበሩ አባላት በህጋዊ መንገድ ሱቅ የገዛንና ውል የፈፀምን ነን፡፡ ነገር ግን ድርጅቱ ተገቢውን መሰረተ ልማት አሟልቶ ባለማጠናቀቁ ሱቃችንን ለመረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናችን ተዘግቶ ይገኛል›› ብላለች፡፡ እንደገለፀችውም በህንፃው ውስጥ ካልተጠናቀቁት መሰረተ ልማቶች መካከል መብራት፣ ውሀ፣ መፀዳጃ ቤት፣ መኪና ማቆሚያና ሊፍት ይገኙበታል፡፡ የህንፃው ግንባታ ረጅም ጊዜ በመቆየቱ አንዳንድ የማህበሩ አባላት በራሳቸው ወጪ አጠናቀው ስራ መጀመራቸውን ሩት ገልፃለች፡፡

ጉዳዩን ወደፍርድ ቤት ለመውሰድ ቢፈልጉም የገንዘብ እጥረት እንዳለባቸው ጠቅሳም በአሁኑ ወቅት ለሚመለከታቸው የመንግስት መስሪያ ቤቶች አቤቱታ በማቅረብ ላይ ቢሆኑም ምንም መፍትሄ አለማግኘታቸውን አስርታለች፡፡ የአያት ሪል ስቴት ቦርድ ምክትል ሊቀመንበር አቶ አብይ ማሞ ስለጉዳዩ ከዘሪፖርተር ተጠይቀው ሲመልሱ ‹‹እኛ ሱቅ ገዢዎቹን በመነጋገርና በውይይት ችግሩን እንድንፈታ ጠይቀናቸው ነበር፡፡ እነሱ ግን ጉዳዩን ወደተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች መውሰድን መርጠዋል›› ካሉ በኋላ ጉዳዩን ለመፍታት በሂደት ላይ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡


Video is unavailable for watching
Show in Telegram

43.7k 0 202 74 93

ማስታወቂያ በአዲስ አበባ ከተማ ለምትገኙ የሪል እስቴት አልሚዎች በሙሉ

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሪል እስቴት ልማት ስራ ላይ የተሰማራችሁ አልሚዎች በሪል አስቴት ልማት እና የማይንቀሳቀስ ንብረት ግብይትና ግመታ አዋጅ እንዲሁም ይህንን ለማስፈጸም በወጣው ረቂቅ ደንብ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ስለሚካሄድ የካቲት 22 ቀን 2017 ዓ.ም ባምቢስ አጠገብ በሚገኘው በዲል ኦፖል ሆቴል ከጠዋቱ 2፡00 ሰአት ጀምሮ ባለቤቶች ወይም ህጋዊ ወኪል የሆናችሁ ሁሉ በመገኘት የውይይቱ ተሳታፊ እንድትሆኑ ጥሪ እናሰተላልፋለን፡፡ 

የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ

38.8k 0 128 10 88

ችሏል

36.1k 0 115 32 191

#CapitalNews የመንግስት ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ስራ ባለመጠናቀቁ ቤቶቹ በህገወጥ መልኩ ወደ ግለሰቦች እየዞሩ ይገኛል ተባለ

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ
የመንግስት ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ ስራ አለመጠናቀቁ ቤቶችን በህገወጥ መልኩ ወደግለሰቦች እንዲዞሩ በር እየከፈተ እንደሚገኝ አስታውቋል።

የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ ሙሉ በሙሉ
ባለመጠናቀቁና አዳዲስ ውል ምዝገባዎች መረጃ እየተለዩና እየተደራጁ ባለመሆኑ ስራዎችን በተቋሙ የመረጃ ቋት ላይ ለመጫን ክፍተት እየፈጠረ እንደሚገኝ ቢሮዉ ገልጿል።

ለካፒታል የደረሰዉ መረጃ እንደሚያመላክተዉ አሁን ላይ ከ150 ሺህ በላይ የመንግስት መኖርያና የንግድ ቤቶች መረጃ በለማው ቴክኖሎጂ ወደ መረጃ ቋት ማስገባት እንደተቻለ እና ከነዚህ ውስጥ 93 ሺህ 350 የሚሆኑ ቤቶች የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ እንደተሰራላቸው ተጠቁሟል።

የተቋሙ የ 6 ወር ሪፖርት እንደሚያሳየዉ እስከአሁን ባለው ጊዜ ከ 495 ሺህ 745 በላይ ቤቶችን የአከራይ ተከራይ ውል ምዝገባ ተከናዉኗል።

48.9k 0 10 14 124

Forward from: Capitalethiopia
#CapitalNews የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣራና የግድግዳ ግብርን የመሰብሰብ ስልጣን ያለው መሆኑን ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታወቁ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የጣራና የግድግዳ ግብርን የመሰብሰብ በአዋጅ የተሰጠው ስልጣን ያለው ሲሆን፣ ይህን ግብር ከመሰብሰብ የሚከለክል ምንም አይነት ህጋዊ አካል እንደሌለ ከንቲባ አዳነች አቤቤ አስታውቀዋል።

ይህንን የተናገሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን እየተካሄደ ባለበት ወቅት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ ነው።

ከንቲባዋ የጣራና የግድግዳ ግብርን በተመለከተ የምክር ቤት አባላት ላነሷቸው ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ፣ የጣራና የግድግዳ ግብር አዋጅ በ1968 ዓ.ም የወጣ አዋጅ መሆኑን አስታውሰዋል።

በወቅቱ የነበረው አሰራር አሁንም እንደቀጠለ ነው ያሉት ከንቲባዋ፣ ነገር ግን የተለወጠው ወቅቱን ያገናዘበ የዋጋ ተመን ብቻ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም አዋጁ ሲወጣ የነበረው የኪራይ ዋጋ እና አሁን ያለው የኪራይ ዋጋ እኩል ባለመሆኑ አሁን የጨመረው ኪራዩ መሆኑን ጠቁመዋል።

የከተማ አስተዳደሩ የሚያስከፍለው ግብር ግን በትክክለኛ ዋጋው ሳይሆን ለመኖሪያ ቤት የዋጋውን ግማሽ እንዲሁም ለንግድ ቤቶች 75 በመቶ ብቻ እንደሆነ ከንቲባዋ አብራርተዋል።

በከተማዋ በግብር ስርዓት ውስጥ ያልነበሩ በርካታ ነዋሪዎች እንደነበሩ ያስታወሱት ከንቲባ አዳነች፣ በከተማዋ ካሉ 800 ሺህ ህንጻዎችና ቤቶች ግብር ይከፍሉ የነበሩት 120 ሺህ ብቻ እንደነበሩ ገልጸዋል።

በኢያሱ ዘካሪያስ

44.9k 0 26 18 225



እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ሲንሸራሸር ያገኘሁት መረጃ ነው። አንዱ የ400 ብር የመብራት አገልግሎት ቻርጅ ለማድረግ መብራት ኋይል ሄዶ የገጠመው የሰርቪስና የታክስ ብዛት ይህንን ይመስላል።

ሰርቪስ ቻርጅ 15.65
የተቆጣጣሪ ክፍያ 1.95
የኢቢሲ ቴሌቭዠን 10
ቫት ዶሜስቲክ 336.32
ቫት ሰርቪስ ቻርጅ 2.35

በድምሩ ከ 400 ብር ላይ በርካታ ታክሶችና ቅንስናሾች 366. 27 ከፍሎ ለመብራት አገልግሎት ብር 33 ከ73 ቻርጅ ተደርጎለት ተመልሷል። (መረጃው ተያይዟል)

የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል ይሏችኋል ይሄ ነው። በቻርጅ ላይ ቻርጅ፣ በቫት ላይ ቫት፣ በታክስ ላይ ታክስ፣ በክፍያ ላይ ክፍያ! እንዲህ ያለ ነገር የየትኛው ሀገር ተመክሮ ይሆን ?

እንደኔ እንደኔ ግን ከዚህ ሁሉ ውጣ ውረድ በየወሩ መጨረሻ በመገናኛ ብዙሃን ጥሪ እየተደረገልን ቤታችን ሳንገባ አንድም ሳንቲም ሳናጎድል ደመወዛችንና ገቢያችንን ለወረዳ ፋይናንስ ብናስረክብ የሚሻል ይመስለኛል ?!

ማለቴ፣ እኛንም እናንተንም ከማሰብ፣ ከመጨነቅ ከውጣ ውረድና ከድካም ይገላግለናል። ደረሰኝ ምናምንስ ለምን ያስፈልጋል። "ኪሳችን ኪሳችሁ። ቤታችን ቤታችሁ እንዲያውም አንድ አምሳልና አንድ አካል ሆነን የለ ¡¡¡"

ያለ ገቢ መኖር እንዴት እንደሚቻል በጾም በጸሎት እስኪገለጽልን ደረስ ደመወዛችንን ብቻ ሳይሆን በነካ እጃችሁ ቤተሰቦቻችንንም ጭምር መረከቡን እንዳትረሱ። ሲመቸንና ስራ በሌለን ጊዜ፣ በበዓልና በእረፍት ቀን እየመጣን እንጠይቃቸዋለን ።
Mush Semu

61.8k 0 207 45 393

በኮሪደር ልማት የተሳተፉ ከ400 በላይ ኮንትራክተሮች መንግስት ክፍያ ሊፈፅምላቸው እንዳልቻለ ተናገሩ

(መሠረት ሚድያ)- በኮሪደር ልማት ምክንያት እንደ ካዛንችስ ካሉ ቦታዎች ለተነሱ ሰዎች በፍጥነት የተዘጋጁ የጋራ መኖርያ ቤቶችን ያዘጋጁ ከ400 በላይ ኮንትራክተሮች ክፍያቸውን መንግስት እንደያዘባቸው ገልፀው ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዳሉ ተናገሩ።

ኮንትራክተሮቹ ለመሠረት ሚድያ በሰጡት መረጃ መሰረት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ኮንትራክተሮቹ በግዴታ ከ3 ሺህ በላይ ቤቶችን ለኮሪደር ተነሺዎች እንዲገነቡ ካደረገ በኋላ ክፍያ መፈፀም አልቻለም።

"በጥቃቅን እና አነስተኛ የተደራጀን እኛ ኮንትራክተሮች ከ3 ሺህ በላይ የ40/60 የጋራ መኖርያዎች ውስጥ ያሉ ለንግድ ተብለው የተሰሩ ክፍሎችን ወደ መኖርያነት ቀይረን ገንብተን ብንጨርስም መንግስት ክፍያችንን ከልክሎናል" የሚሉት ኮንትራክተሮቹ አብዛኞቹ በብድር ወስደው ስራውን ቢሰሩም አሁን ትርፉ ቀርቶ ብድራቸውን ለመክፈል ተቸግረው እንዳሉ አብራርተዋል፣ አንዳንዶቹ ብድሩን ለመክፈል የግል ንብረታቸውን ለመሸጥ እየተገደዱ እንደሆነ ተናግረዋል።

እነዚህ ለተነሺዎች በኮንትራክተሮቹ የተዘጋጁ ቤቶች በአያት፣ አራብሳ፣ ቡልቡላ እና አስኮ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

"ቤቶች ልማት እና ፋይናንስ ቢሮዎችን ስንጠይቃቸው ምላሻቸው ገንዘብ የለንም ነው፣ ታድያ ገንዘብ ከሌላቸው ለምን እኛን አሰሩን?" የሚል ጥያቄ የሚያነሱት እነዚህ አነስተኛ እና ጥቃቅን ኮንትራክተሮች አንዳንዶቹ ቤተሰባቸው ጭምር ችግር ላይ እንደወደቀ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ከኮንትራክተሮቹ ጋር መረጃ ይለዋወጥበት የነበረ የቴሌግራም ግሩፕን ስራው ካለቀ በኋላ ሰው መረጃ እንዳይቀያየርበት መቆለፉን ለማየት ችለናል።

የቤቶች ልማት ኮንትራክተሮቹን ወደ ስራ ሲያስገባ ምንም አይነት ቅድመ ክፍያ እንዳይጠይቁ አስፈርሞ እንደነበር መሠረት ሚድያ የተመለከተው አንድ ሰነድ ያሳያል።

"ወደን ሳይሆን በግዴታ ነው ካለ ቅድመ ክፍያ ተስማምተን የገባነው፣ እንደዛ ካልተስማማን ወደፊት ምንም ስራ ከተማ ውስጥ መስራት አትችሉም ተብለን ማስፈራርያ ተሰጥቶን ነበር" ያሉት ግለሰቦቹ አሁን ላይ ለሁሉም ስራ ሳይከፈል የተከማቸው ገንዘብ 4.4 ቢልዮን ብር ገደማ እንደሆነ ጠቁመዋል።

መሠረት ሚድያ በዚህ ዙርያ ባደረገው ተጨማሪ ከ3 ሚልዮን ብር እስከ 42 ሚልዮን ብር የተያዘባቸው ኮንትራክተሮች እንዳሉ የተረዳ ሲሆን ከነዚህ ኮንትራክተሮች ውጪም በኮሪደር ልማት ዙርያ የመንገድ ግንባታ የተሳተፉ አቅማቸው ከፍ ያለ ኮንትራክተሮችም ክፍያ ተነፍጓቸው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችላል።

51k 0 170 28 180





#CapitalNews በኢትዮጽያ ያለውን የቤት ፍላጎት ከአቅርቦቱ ጋር ለማመጣጠን በዓመት በአማካኝ 471 ሺህ  ቤቶችን መገንባት ያስፈልጋል ተባለ

የፖሊሲ ጥናት ኢንስቲትዩት እንደገለፀው በከተሞች ያለውን የቤት አቅርቦት ችግር ለመፍታት በዓመት በአማካኝ 471 ሺህ ቤቶችን መገንባት ይጠይቃል ብሏል።

ኢንስቲትዩቱ ተመራማሪ የሆኑት ሰለሞን ጥላሁን የቤት ልማት የፍይናንስ ስረዓት ላይ ያቀረቡትን ጥናት ዋቢ አድርጎ ኢፕድ እንደዘገበው በኢትዮጵያ  68 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ቤት ለመስራት የብድር አገልግሎት እንደሚያስፈልግ ተመላክቷል።

ይህን ተከትሎ የሀገሪቷ መንግስት በ10 ዓመት እቅዱ 4 ነጥብ አራት ሚሊዮን ቤቶችን ለመገንባት እየሰራ መሆኑና በአማካኝ የሚያስፈልገውን 471 ሺህ ቤት የሚያሟላ ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል ።

48.7k 0 28 21 170

የቢሮው ማሳሰቢያ!!

በተለምዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራው የቤትና ቦታ ግብር ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ በመሆኑ ግብር ከፋዮች ከወዲሁ እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተለመዶ የጣራና ግድግዳ እየተባለ የሚጠራ የቤትና ቦታ ግብር የሚከፍሉ ግብር ከፋዮች ግብሩ ያለቅጣትና ወለድ የሚከፈልበት ጊዜ እየተጠናቀቀ መሆኑን በመገንዘብ ከወዲሁ ግብራቸውን እንዲከፍሉ ተጠየቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቢሮ የገቢ አወሳሰንና አሰባሰብ ዳይሬክተር አቶ ወንድማገኝ ካሳዬ እንደገለፁት በመዲናዋ 429 ሺህ 829 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር ክፍያ እንዲፈፅሙ ይጠበቃል፡፡
ይሁንና እስካሁን ባለው ሂደት 228 ሺህ 222 ግብር ከፋዮች የቤትና ቦታ ግብር መፈፀማቸውን በመግለፅ ይህም የዕቅዱ 51 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
አክለውም የቤትና ቦታ ግብራቸውን ከከፈሉ ግብር ከፋዮችም 2 ነጥብ 24 ሚሊዮን ብር መሰብሰቡን ተናግረዋል፡፡
እንደሚታወቀው የቤትና ቦታ ግብር ከአዋጅ ከ1968 ጀምሮ በተለምዶ የአፈር፣ የቤትና ጣሪያ በሚሉና መሰል ስያሜዎች እስከ የካቲት 30 ድረስ የሚሰበሰብ የግብር አይነት መሆኑ ይታወቃል፡፡
(አዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ)

54.5k 0 213 56 225

አዲሱ የብልጽግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በአጠቃላይ 45 አባላት ያለው ሲሆን 10 ሴቶችን አካቷል።

#ኦሮሚያ_ክልል

1. ዶክተር ዐቢይ አህመድ
2. ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ
3. ኦቦ አወሉ አብዲ
4. ኦቦ ፍቃዱ ተሰማ
5. አዴ አዳነች አቤቤ
6. አዴ ጫልቱ ሳኒ
7. ኦቦ ሳዳት ነሻ
8. ኦቦ ከፍያለው ተፈራ
9. ዶክተር ተሾመ አዱኛ
10. ዶክተር እዮብ ተካልኝ

#አማራ_ክልል

11. አቶ ተመስገን ጥሩነህ
12. አቶ መላኩ አለበል
13. ወ/ሮ አይናለም ንጉሴ
14. አቶ አረጋ ከበደ
15. አቶ ይርጋ ሲሳይ
16. ዶክተር አብዱ ሁሴን
17. አቶ ጃንጥራር አባይ
18. ዶክተር ሙሉነሽ ደሴ

#ሶማሌ_ክልል

19. አቶ አደም ፋራህ
20. አቶ ሙስጠፌ መሃመድ
21. አቶ አህመድ ሺዴ
22. ወ/ሮ ሃሊማ ዋሽራፍ

#ትግራይ_ክልል

23. ዶክተር አብርሃም በላይ
24. አቶ ታዜር ገብረ እግዚአብሔር

#ሀረሪ_ክልል

25. አቶ ኦርዲን በድሪ
26. ወ/ሮ አሚና አብዱልከሪም

#አፋር_ክልል

27. ሀጂ አወል አርባ
28. መሀመድ ሁሴን አሊሳ
29. መሀመድ አህመድ አሊ

#ደቡብ_ምዕራብ_ኢትዮጵያ_ክልል

30. ዶክተር ኢንጂነር ነጋሽ ዋጌሾ
31. አቶ ፍቅሬ አማን

#ሲዳማ_ክልል

32. አቶ ደስታ ሌዳሞ
33. አቶ አብርሃም ማርሻሎ
34. ዶክተር ፍፁም አሰፋ

#ጋምቤላ_ክልል

35. ወ/ሮ አለሚቱ ኡሞድ
36. ዶዶክተር ካትሏክ ሩን ናቸው።

#ቤኒሻንጉል_ጉሙዝ_ክልል

37. አቶ አሻድሊ ሀሰን
38. አቶ ጌታሁን አብዲሳ

#ማዕከላዊ_ኢትዮጵያ_ክልል

39. አቶ እንዳሻው ጣሰው
40. ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል
41. ዶክተር ዴላሞ ዶቶሬ

#ደቡብ_ኢትዮጵያ_ክልል

42. አቶ ጥላሁን ከበደ
43. ወ/ሮ ⁠ሸዊት ሻንካ
44. ዶክተር ተስፋዬ ቤልጅጌ
45. ዶክተር አበባየሁ ታደሰ

26.3k 0 87 14 211

Video is unavailable for watching
Show in Telegram
ወይ አዲስ አበባ...

42.2k 0 143 31 137

Video is unavailable for watching
Show in Telegram
አዲሱ የቤቶች ፋይናንስ ስረአት

20 last posts shown.