"የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ መስዋዕትነት ከፍሎ ነጻ ያወጣቸውን ህዝቦቹንና ግዛቶቹን መልሶ ለትግራይ ክለል አስተዳደር የሚሰጥበት ምክንያት የለም።"
ዶ/ር ሲሳይ መንግስቴ
በርኖስ ሚዲያ /ህዳር /9/2013 ዓ.ም
የወልቃይት ጠገዴና የራያ ጉዳይ አሁንም አነጋጋሪ ሆኖ መቀጠሉን የሚያመላክቱ ሀሳቦች እየተራመዱ ነው። እስካሁን ባለው ሁኔታ በወልቃይት ጠገዴ ተወላጆች መካከል የተከሰተ የተለየ ነገር ባይኖርም የራያ ህዝብ አሁንም በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስር እንዲቆይ የሚፈልጉ ጉዶች/ከሀዲዎች መኖራቸው ግልጽ እየሆነ መጥቷል።
አሳዛኙ ነገር የራያም ሆነ የወልቃይት ጠገዴ አካባቢና ህዝብ በትህነግ ተገዶ ወደ ትግራይ በመሄዱ ምክንያት እንደቅደም ተከተሉ ላለፉት 35 እና 28 አመታት ሲሰቃይ መቆየቱ እየታወቀና የአማራ ልዩ ሀይል፣ ሚሊሻና ፋኖ ክቡር መስዋዕትነት ከፍሎ በጀግንነት ነጻ እንዳወጣቸው ግልጽ ሆኖ እያለ እነዚህ አካባቢዎች በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስር እንዲቆዩ የሚል አቋም መያዝ ፍጹም ሀላፊነት የጎደለውና የአማራን መስዋዕትነት መናቅ የመሆኑ ጉዳይ ነው።
በቅርቡ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ሆነው በጠቅላይ ሚኒስሩ የተሾሙት ዶ/ር ሙሉ ነጋ ስለወልቃይትና ራያ ሁኔታ ተጠይቀው የሰጡት ምላሽ አካባቢዎቹ በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ስር ቆይተው ጥያቄያቸው በከስተዳደር ወሰንና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ሊታይ እንደሚችል ገልጸዋል። ይህም ከእሳቸው የሚጠበቅ ስለሆነ ከዚህ በላይ ከዶ/ር ሙሉ ነጋ መጠበቅ የዋህነት ነው።
ይኸ በዚህ እንዳለ የወልቃይት ጠገዴ፣ ጠለምትና ራያ ጉዳይ መታየት ያለበት በሀይል ተወስደው ስለነበር በሀይል እንዲመለሱ ተደርገዋል። እናም የአማራ ልዩ ሀይልና ሚሊሻ መስዋዕትነት ከፍሎ ነጻ ያወጣቸውን ህዝቦቹንና ግዛቶቹን መልሶ ለትግራይ ክለል አስተዳደር የሚሰጥበት ምክንያት የለም።
ከሁሉም በላይ ግን ይኸ ህዝብ ማንም እየመጣ ፍላጎቱን የሚጭነበት ሁኔታ ስለማይኖር በአማራ ክልል ውስጥ ሆኖ ሀሳቡን በነጻ የሚገልጽበት አሰራር ነው መመቻቸት ያለበት። በዚህ ረገድ የአማራ ክልል መንግስና ገዥው ፓርቲ የአማራ ብልግና ግልጽ አቋም በመያዝ ከፌዴራል መንግስቱ ጋር መነጋገር ይኖርበታል። በፍጹም ያ ታሪካዊ ስህተት መደገም አይኖርበትም።
@bernosmedia24