በምዕራብ ወለጋ በ142 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን ገለጸ።
በርኖስ ሚዲያ /ህዳር 9/2013 ዓ.ም
የኦሮሚያ ፖሊስ ኮሚሽን በምዕራብ ወለጋ ጉሊሶ ወረዳ በኦነግ ሸኔ ቡድን የፈጸመውን ጥፋት ተከትሎ እርምጃ እየወሰደ መሆኑን ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
በ142 የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ እንደተወሰዳባቸው፣48 ታጣቂዎች በቁጥጥር ስር እንደዋሉና፣ 64 ደግሞ በህብረተሰቡ ውስጥ ከተበታተኑ በኋላ መለቀማቸውን ኮሚሽነሩ ገልጸዋል።
አክለውም ለኦነግ ሸኔ አባላት የሎጂስቲክስና ስልጠና ሲሰጡ የነበሩ 1341 ግለሰቦችም በቁጥጥር ስር መዋላቸውንና ከእነዚህ ውስጥም 104ቱ የህወሃት ቡድን አባላት መሆናቸው ተገልጿል፡፡
በተወሠደዉ እርምጃም 57 የእጅ ቦንቦችና ክላሾች፣ 681 ጥይቶች፣ 600ሺህ ብር ጥሬ ገንዘብና የተለያዩ የጦር ሜዳ ሬድዮዎችና የጦር መነጽሮች በቁጥጥር ስር መዋሉንም ገልጸዋል።
በምዕራብና በደቡብ ኦሮሚያ አካባቢዎች አንፃራዊ ሰላም እንደሰፈነም ኮሚሽነር አራርሳ መርዳሳ በመግለጫው ወቅት ጠቅሰዋል፡፡
@bernosmedia24