እነዚህ ናቸው ስለ ዑለማእ ክብር የሚደሰኩሩት
~
ሰሞኑን በሰዑዲ ዐረቢያ የሃሎዊን በዓል መከበሩን ተከትሎ የኢኽዋንና የአሕባሽን ጥምር ዘመቻ ስናይ ነበር። ከላይ ያያያዝኩት በዘመቻው ላይ ከፊት ረድፍ ከተሰለፉት ውስጥ ነው፡፡ ፅሑፉ በጥላቻና በድንቁርና የተለወሰ ነው። ነጥብ እየመዘዝኩ ምላሽ እሰጣለሁ፦
1- "ሳዑዲ የሚለው ስያሜ ከ1932 ጀምሮ የመጣ እንጂ ኢስላም ውስጥ የሌለ ቢድዓ እንደሆነና በነብያችን (ሰዐወ) ወቅት ስሟ ሒጃዝ እንደነበር ... " ይላል።
መልስ፦
ሀ. እንደምታዩት የሃገራትን ስያሜ ሱናና ቢድዐ እያለ ሊከፍል እየዳዳው ነው። ስለ ቢድዐ ያለው ግንዛቤ ይሄው ነው በቃ። ከአቅምህ በላይ ስለሆነ ጉዳይ ከመፈትፈት ይልቅ ቢያንስ የቢድዐን መሰረታዊ ግንዛቤ ብትለይ ይሻልህ ነበር።
ለ. "ሳዑዲ የሚለው ስያሜ ቢድዐ ነው" ሲል የቢድዐ አደጋ የሚያስጨንቀው አይመስልም? በየትኛው ቢድዐ ላይ ነው ስትዘምቱ የታያችሁት? በሺርክ የተጨማለቁ ድግሶችን አይደልንዴ በትንንሽ ነገር መለያየት የለብንም እያላችሁ የምትከላከሉት? የቀርዷዊ ዓለም አቀፍ ማህበርኮ ምክትሎቹ ሺዐና ኻሪ-ጂ ናቸው። እኮ እናንተም ስለ ቢድዐ?
ሐ. ደግሞም ሳዑዲ ማለት ለሒጃዝ የተሰጠ አቻ ስያሜ አይደለም። ከ1932 በፊትም በኋላም ሒጃዝ ሒጃዝ ነው። ሒጃዝ ከ0ረቢያ ልሳነ ምድር ውስጥ አንድ ክልል እንጂ ድፍን አካባቢውን የሚገልፅ አይደለም። ሒጃዝ በዛሬዋ ሰዑዲያ ምዕራባዊ ክፍል ያለው ግዛት ነው። ሰዑዲያ የሚለው ስያሜ ከዚህ ግዛት በብዙ እጥፍ የበዛ ነው። በሰዑድ ስም መሰየሙም በጥላቻ ስለተሞሉ እንጂ ይህን ያህል የሚያነጋግር አልነበረም። ሁሌ የምትዘምሩለት የኦቶማን ተርክ ኤምፓየር እኮ በመስራቹ ዑሥማን ጋዚ ስም ነው የተሰየመው። ለማንኛውም ስለምታወሩት ጉዳይ እንኳ ያለምንም የእውቀት እርሾ በባዶ አትፃፉ። ጥላቻ እውቀት አይሆንም።
2- "ስዑድ የአንድ አምባገነን ቤተሰብ ስም መሆኑ ልብ ይሏል" ይላል።
መልስ፦
ሀ- አዎ ይሄ ስያሜ ዛሬ ላለው ሃገር በመጠሪያነት የዋለው በመስራቹ ንጉስ ዐብዱልዐዚዝ ዘመን ነው፣ ረሒመሁላህ። ከነ ክፍተታቸው ጀግና ናቸው፣ የጀግና ቤተሰብ። ከየትኛውም ሀገርና ቡድን በተለየ ለተውሒድ፣ ለኢስላም ሰፊ ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ከሃገራቸው አልፈው በመላው አለም ተውሒድን ለማሰራጨት እጅግ ብዙ ገንዘብ ያፈሳሉ። ጠላት ሳይቀር ይህን ተገንዝቦ "የሳዑዲ ፔትሮ ዶላር" እያለ እያላዘነ ነው። ከመላው አለም ወጣቶችን እየተቀበሉ በዩኒቨርሲቲዎቻቸው ያስተምራሉ። ኢስላማዊ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች፣ ኢስላማዊ ጉዳዮች፣ ደዕዋና ኢርሻድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ በመልካም ማዘዝ ከመጥፎ መከልከል ባለስልጣን መስሪያ ቤት፣ የታላላቅ ዑለማዎች ምክር ቤት፣ የሐጅ እና ዑምራ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት፣ ወዘተ ለኢስላም ምን ያክል ትኩረት እንደሚሰጡ ህያው ምስክር የሆኑ በመንግስት የሚመሩ የሀይማኖት ተቋማት ናቸው። እስኪ በየት ሀገር ነው የነሱን የሚያህሉ እንዲህ አይነት ተቋማት ያሉት?
ንጉስ አልፎ ሌላ ንጉስ በተተካ ቁጥር ደስ የማይል መላላት በየዘመኑ እያየን ነው። በዚህ ነገር ውስጣችን እጅጉን ይደማል። ከመሆኑም ጋር እነሱን በማብጠልጠል ላይ የተሰማሩት የኢኽዋንና የአሕባሽ አንጃዎች ከነሱ ሊሻሉ ነው? አመድ በዱቄት ይስቃል!
ለ- በተረፈ አምባገነን ስርአት ነው ስትሉ ምንድነው የምትፈልጉት? ዲሞክረሲ የለም ልትሉ ነው? እንኳንም አልኖረ። በኢስላም መመዘኛ ዲሞክረሲ ፈፅሞ ከአምባገነን ስርአት የተሻለ አይደለም። ደግሞስ ሰርክ የምትዘምሩለት የኦቶማን አስተዳደር የለየለት አምባገነን እንደነበር ማን በነገራችሁ?
3- "የቀብር አምልኮ (ሽርክ ከመሆኑ ጋር) ላይ ብቻ የሚጮኹና ቤተ-መንግስት ውስጥ ያሉ ህያው አምባገነኖችን ቀዳሽና አወዳሽ አላህ ላይ ያለምንም ስልጣን አሻራኪ የነበሩ፣ በባለስልጣናት ዙፋን አስጠባቂ ዓሊሞችና እስር ቤት ለዓመታት እንዲማቅቁ ተደርገው የሚሞቱ ዓሊሞች መሃል ያለውን ልዩነት ማስተዋል ያሻል።"
መልስ፦
ለትናንቱም ለዛሬውም ፅሑፌ ቀዳሚው መነሻዬ ይሄን መሰል እርኩስ ውንጀላ ነው። ደጋግሜ እንደገለፅኩት የነዚህ ነውረኛ አካላት ዋናው ማጠንጠኛ የሳዑዲ ስርአት አይደለም። የሳዑዲ ዑለማዎች እንጂ። እንደምታዩት ዑለማዎቹን ነው "አምባገነኖችን ቀዳሽና አወዳሽ አላህ ላይ ያለምንም ስልጣን አሻራኪ" እያለ የሚገልፀው። በዚህ መልኩ ቆሻሻቸውን ሲደፉ እያየ "ዑለማዎቹን ማን ነካ?" የሚል እንቅ -ልፋም አለ። ከዚህ በላይ ምን ይበላቸው?! እኮ እነ ኢብኑ ባዝ፣ ዑሠይሚን፣ ፈውዛን፣ ዐባድ፣ ... ናቸው አምባገነኖችን እያመለኩ በአላህ ላይ የሚያሻርኩት?! በኢስላም ታሪክ እንደዚህ የኢኽዋን ቡድን ባለጌና ነውረኛ መንጋዎችን የሰበሰበ መኖሩን እጠራጠራለሁ።
4- "ሸሪዓ ቁረጠው ፍለጠውና ቅፍደዳ አይደለም። እንደዚያ አለመሆኑን ሐረሞቻችን ላይ የተጠመጠው ይህ ቤተሰብ ህዝቡን አፍኖ ጥቂት ነፃነት ሲሰጠው በቀጥታ እንደታየው የሸይጣን አምላኪ ባልሆነ ነበር። ከዚህ ስርዓት ይልቅ ምዕራቡ ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች ስለ ሸሪዓ አብዝተው ይሰራሉ" ይላል።
መልስ፦
ተመልከቱ ይህንን የተሳከረ ትንታኔ! በመጀመሪያ ሃሎዊን ያከበሩት የሳዑዲን ህዝብ 1% አይሆኑም። እንዴት እነዚህን መነሻ አድርጎ ህዝብን በጅምላ "የሸይጣን አምላኪ" ብሎ ይገልፃል? ጥላቻ አውሮት እንጂ አሁን ይሄ ለህፃን የሚሰወር ጉዳይ ነው? ደግሞስ ተመሳሳይ ስሌት ተጠቅሞ የቱርክን ህዝብ "የሸይጣን አምላኪ" ብሎ ይገልፃል? እኮ ከሳዑዲ በበለጠ ምዕራቡ ውስጥ ያሉ ሙስሊሞች ስለ ሸሪዓ አብዝተው ይሰራሉ? ምን የሚሉት ፍርደ ገምድልነት ነው? በዚህ ቅጣምባሩ በጠፋው ግንዛቤህ ነው ህዝብን ከህዝብ የምትመዝነው?
5- "ተስፋ አስቆራጭና የቂያማ ነገ መሆንን ብቻ ሳይሆን እንደ ኡማ ፈሳድና ጃሂሊያን ታግሎ ልክ እንደ ኳታር የኢስላምን መርሆች ዳግም ማምጣትን ማሰብም ከአንድ ሙስሊም የሚጠበቅ የድል ተስፈኝነት ምልክት ነው" ይላል።
መልስ፦
ሀ. ሳዑዲን ያብጠለጠለው ብእር ለኳታር የሚጨፍርበትን ምክንያት እናውቀዋለን። ይሄ አስመሳይ አካሄድ ከቁንጮዎቹ የተወሰደ ድግምት ነው። እንዲህ የንፍቅና አካሄድ እየሄዱ ነው ስለ ድል የሚዘምሩት። "እናያለን" አለ እውር!
ለ. አንዳንዶች "እንዴት ሳዑዲንና እነ ቱርክና ኳታርን ታወዳድራለህ?" ብላችኋል። መቼ ስራ ፈታሁና! የማይወዳደር ነገር ላይ ምን አደከመኝ?! "እና ከሳዑዲ ለመከላከል ለምን እነሱን ትጠቅሳለህ?" ነው ሎጂካችሁ። እያወዳደርኩ ቢሆን ስለ ቱርክ አንድ መፅሐፍ እፅፍ ነበር። የማላደርገው የሚይዝ ይዞኝ ነው። እውነቱን ለመናገር ክፉም አልመኝላቸውም። ስማቸውን የምጠቅሰው ሳዑዲን ለመተቸት የሚያነሱት ጥፋት ሁሉ በነዚህ ሃገራት ውስጥ በሰፊው ከመኖሩ ጋር በሳዑዲ ዑለማዎች ላይ የሚዘምቱት የኢኽዋን መንጋዎች የነዚህ ሃገራት ቀዳሽ አወዳሽ ስለሆኑ ነው። ስለሆነም የትችታቸው እውነተኛ መነሻ ለዲን መቆርቆር ሳይሆን ቡድናዊ ጥላቻ የወለደው እንደሆነ ለማሳየት ነው የምጠቅሰው። በዚያ ላይ እያወዳደሩ ያሉት ራሳቸው ናቸው። በልጁ ፅሑፍ ላይ ራሱ ማወዳደሩን ታያላችሁ።