ኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር(አቡ ዓማር)


Channel's geo and language: Ethiopia, Amharic
Category: not specified


የአላህ  መልዕክተኛ (ﷺ)  እንዲህ  ብለዋል፦
(ከሰዎች መካከል የመልካም በር ከፋች የሆኑና የመጥፎ በር ዘጊዎች የሆኑ አሉ ፤ እንዲሁም ከሰዎች መካከል የሸር  በር ከፋች የሆኑና የመልካም በር ዘጊ የሆኑ አሉ። አላህ የመልካም በር መክፈቻ ቁልፍ በእጁ ላደረገለት ‘ጡባ’ አለለት ፤  አላህ  የመጥፎ  በር መክፈቻ  ቁልፍ  በእጁ  ላደረገለት  ‘ወይል’ አለለት።)
[ኢብኑ ማጃህ (237) ዘግበውታል። 

Related channels  |  Similar channels

Channel's geo and language
Ethiopia, Amharic
Category
not specified
Statistics
Posts filter


🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿

ኢትዮጵያ ውስጥ መቻቻል እንዳለ ለማሳየት ፖለቲከኛውም፣ ጋዜጠኛውም፣ አር ቲስቱም፣ አክቲቪስቱም፣ መሀይሙም፣ ምሁሩም እንቁጣጣሽ፣ ጥምቀትና ገና የሚያከብሩ "ሙስሊሞችን" ማቅረብ መጥቀስ የተለመደ ነው። በተቃራኒው የሙስሊም ዒዶችን የሚያከብሩ ክርስቲያኖችን ግን ሲያቀርቡ ወይም ሲጠቅሱ ገጥሞኝ አያውቅም። ለምን? ሙስሊሙ የእምነቱን ህግጋት ጥሶ የነሱን በአላት ማክበሩ ከመቻቻል ትርጓሜ ጋር ምን የሚገናኝ ነገር አለው?

እውነት ይሄንኑ የተንሻፈፈ አረዳድ መቻቻል አድርገው ካሰቡት ለምን ሙስሊሞችን ብቻ ነጥለው ያቀርባሉ? እንዲህ አይነቱ "ከባልሽ ባሌ ይበልጣል ሽሮ አበድሪኝ" አይነት የብልጠት ጨዋታ አይደብርም ወይ? ደግሞ'ኮ ሙስሊሙ የገዛ ወገኑን ከእንዲህ አይነት ተግባራት እንዲርቁ ሲያስተምር እንደ ማክረርና ፅንፈኝነት ሊቆጥሩ ዳር ዳር ሲሉ ማየት ነው የሚገርመው።

✍IbnuMunewor

https://t.me/ibnukedir


📤📤📤📤📤📤📤

🌿የጁሙዓ ኹጥባ ቁ፡55


🔖 ማንቂያው እና መዳኛው
   

🎙 በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🔻ሊደመጥ የሚገባ ወቅታዊ ኹጥባ!


💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር!


🕌  ቃሊቲ ቶታል ነስር መስጂድ

https://t.me/ibnukedir


Video is unavailable for watching
Show in Telegram
🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿

     ዘመኑ የስጋት እና የፊትና መሆኑን ቀጥሏል

እውነተኛው ነብይ እንዳሉት፦
«لم يبق من الدنيا إلا بلاء وفتنة»
«ከዱንያ በላእ እና ፊትና እንጂ የቀረ የለም።»

   ከላይ የተያያዘው ቪዲዮ ዛሬ ምሽት በሀገራችን በተለያዩ ቦታዎች የታየ "ምንነቱ ያልታወቀ በራሪ እሳት የሚመስል ነገር ነው።" ተብሎ የተሰራጨ ነው። እውነታው አላህ ይወቀው።

በነገራችን ላይ፦
  ዛሬ በአስፈሪ የሰደድ እሳት እየታመሰች ያለችዋ ኣሜሪካ ከሳምንታት በፊት "ሰማይ ላይ ምንነታቸው ያልታወቁ በራሪ የሆኑ አብሪ ነገሮች እያተዩ ነው" ተብሎ በብዛት ሲቀረፅ እና ሲሰራጭ ነበር። የሀገሪቱ መንግስት ግን ህዝቡን ለማረጋጋት "ምንም ይሁን ምን ህዝባችንም ይሁን ሀገራችን ላይ የሚያመጣው ጉዳት የለም" እያለ ሲያረጋጋ ነበር። ከታዩ ነገሮች ጋ ግንኙነት ይኑረው አይኑረው ባይታወቅም ይኸው ዛሬ እንዲህ እየነደደች ነው።

እንዲሁም…………
  ሰሞኑ ጎረቤታችን ኬንያ ውስጥ እንዲሁ ምንነቱ ያልታወቀ ትልቅ ክብደት ያለው ቁስ ነገር ከሰማይ መውደቁ ተዘግቦ ነበር።

የሆነው ሆነና…………
   ዘገባዎቹ እውነትም ይሁኑ   ውሸት ለመጨረሻው ዘመን የተቃረብን መሆኑ ግን እውነት ነው። ለቂያማ በተቃረብን ልክ አስፈሪ ክስተቶች እና አስደንጋጭ አደጋዎች ይበዛሉ።

ጉዳዩ ይህ ከሆነ…………
   መረበሽ እና መጣበብ ሳይሆን ፈርተንና ተደናግጠን ወደ አላህ መመለስ አለብን!! አላህ ይወፍቀን🤲

የተወሰደ

https://t.me/ibnukedir


🌿አዲስ ደርስ


📚ሱለሙል ውሱል


🎙ክፍል፡18


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🔻በዓቂዳ ዙሪያ የሚያጠነጥን!


🕌 በኢማሙ ነወዊይ የሂፍዝ ማዕከል የተሰጠ።

https://t.me/ibnukedir


🌿አዲስ ደርስ


📚ረውደቱል አንዋር


🎙ቁጥር፡30


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🕌  አቃቂ ዑመር መስጂድ የተሰጠ

@ibnukedir


📚የቁርአን ተፍሲር ቁ፡207


📖ሱረቱ-ዙመር
        

🎙ክፍል፡4


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🕌  አቃቂ ቢላል መስጂድ የተሰጠ

@ibnukedir


📤📤📤📤📤📤📤

🌿የጁሙዓ ኹጥባ ቁ፡54


🔖 የረጀብ ወር ትሩፋት እና ዒባዳ!
   

🎙 በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🔻ሊደመጥ የሚገባ ወቅታዊ ኹጥባ!


💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር!


🕌  ቃሊቲ ቶታል ነስር መስጂድ

https://t.me/ibnukedir


🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿

አህባቢ አምላካችን አላህ ወደእርሱ እንድንመለስና ልባችንን እንድንፈትሽ በዚህና በመሰል ክስተቶች እየገሰፀን ነው ።በንዝረቱና በመንንቀጥቀጡ ስንዘናጋ ይኸው ሌላ ደውል!።ግን ምን ያህል ልባችን ቢደርቅ ነው እንደዚህ አይነት ክስተቶችን እንኳን እያየን እራሳችንን የማንመረምረውና ለልባችን መፍትሄ የማንፈልገው?እስኪ ከስር በተዘረዘሩት ነጥቦች እራሳችንን መርምረን አቋቋማችንን እናስተካክል።አላህ ያግራልን ይድረስልን።አሚን🤲

❤️የልብ መድረቅ ምልክቶች

🔻 ልቡ የደረቀ ሰው ሐራም መዳፈር ያበዛል።

🔻ወንጀል እየፈፀመ አይደነግጥም።

🔻የሰው ሐቅ መዳፈሩ አያስጨንቀውም።

🔻ዒባዳው ለዛ ያጣል።

🔻 የዒባዳውን አሻራ አይፈትሽም።

🔻ተውበት ከመከጀል ሃጢያት መዳፈር

🔻ዒልም ኑሮት አለመተግበር

🔻ስራን ያለ ኢኽላሰ መስራት

🔻የአላህን ሪዝቅ እየበሉ አለማመሰገን

🔻የአላህን ቀድር አለመውደድና አለመቀበል

🔻የሞተን ሰው እየቀበሩ አለማሰተንተን

❤️የልብ ድርቀት ምክንያቶች

🔻የአላህን ትዕዛዝ መራቅ

🔻ወንጀሎችን ማብዛት

🔻በዱንያ ላይ ልብን ማንጠልጠል

🔻ረዥም ምኞትን መመኘት

🔻 አኼራን ፍፁም መዘንጋት

🔻ቁርአንን አለማንበብና አለመሰማት እንዲሁም አለመተግበር

🔻መጥፎ ጓደኛ መያዝ

🔻በመጥፎ ማህበረሰብ ውሰጥ መኖር

🔻ሞትን መርሳት

❤️የልብ ድርቀት መድኃኒቶች

🔻አላህን አብዝቶ ማውሳት

🔻እስቲግፋር ማዘውተር

🔻ቁርአንን በማስተንተን ማንበብ

🔻ራስን መመርመር እና መተሳሰብ

🔻ከመጥፎ ጓደኞች መራቅ እና ጥሩ ጎደኛ መያዝ።

https://t.me/ibnukedir


🌿አዲስ ደርስ


📚ተይሲሩ አህካሚ ተጅዊድ


🎙ክፍል፡17


🔻የመጨረሻ ክፍል


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🔻በተጅዊድ ዙሪያ የሚያጠነጥን!


🕌 በኢማሙ ነወዊይ የሂፍዝ ማዕከል የተሰጠ።

https://t.me/ibnukedir


🌿አዲስ ደርስ


📚ሱለሙል ውሱል


🎙ክፍል፡17


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🔻በዓቂዳ ዙሪያ የሚያጠነጥን!


🕌 በኢማሙ ነወዊይ የሂፍዝ ማዕከል የተሰጠ።

https://t.me/ibnukedir


🌿አዲስ ደርስ


📚ረውደቱል አንዋር


🎙ቁጥር፡29


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🕌  አቃቂ ዑመር መስጂድ የተሰጠ

@ibnukedir


📚የቁርአን ተፍሲር ቁ፡206


📖ሱረቱ-ዙመር
        

🎙ክፍል፡3


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🕌  አቃቂ ቢላል መስጂድ የተሰጠ

@ibnukedir


📤📤📤📤📤📤📤

🌿የጁሙዓ ኹጥባ ቁ፡53


🔖 ዑመር አል-ፋሩቅ ማነው!
   

🎙 በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🔻ሊደመጥ የሚገባ ኹጥባ!


💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር!


🕌  ቃሊቲ ቶታል ነስር መስጂድ

https://t.me/ibnukedir


🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿

ካለመማር የማይሻል መማርማ አለ
~
አዎ አለመማር ያሳፍራል፣ ያስቆጫል እንጂ አያኮራም። በተለይ በዚህ ዘመን ያለው አለመማር ቀደም ባለው ዘመን ከነበረው አለመማር የከፋ ጉዳት አለው። ቆም ብሎ ያስተዋለ ብዙ ሰበዞችን መምዘዝ ይችላል።
መማር የአስተሳሰብ አድማስን ያሰፋል። የማስተዋል አቅምን ያዳብራል። ሌላው ቀርቶ በሃገራችን ተጨባጭ የዲን ሰዎች እንኳ አካደሚ ትምህርት በመማራቸው ይህንን ካላገኙት የተሻለ ብስለትና አቀራረብ ሲንፀባረቅባቸው፣ ያልተማሩት ደግሞ በዚህ ረገድ የጎላ ክፍተት ሲታይባቸው ያጋጥማል። ሁሉን ማለቴ አይደለም።
ግን መማር ምንድነው? ካምፓስ ደርሶ መመለስ ነው መማር? ዲግሪ መቁጠር ነው መማር? እንግሊዝኛ መቀላቀል ነው መማር? መማር ምንድነው?
በርግጥ መማር ብዙ እርከን አለው። ቀለም መቅመስ፣ ክፍል መቁጠር፣ ዲግሪ መደርደር ብቻውን መማር አይደለም። መማር መልለወጥ ነው። መማር ለህይወት ዋጋ መስጠት ነው። መማር በህሊና መኖር ነው። መማር ለወጡበት ማህበረሰብ ቅን መሆን ነው። መማር ለራስ የማይወዱትን ነገር ሌሎች ላይ አለማድረስ ነው። ይሄ ደግሞ ጥልቅ ንባብ፣ ማሰላሰል፣ አእምሮን ማስፋት፣ የተማሩትን ሆኖ መገኘት ይጠይቃል። በሃገራችን ተጨባጭ አብዛኛው "ምሁር" በዚህ ረገድ ሲታይ ተምሯል ለማለት ይከብዳል።

የትምህርት ስርአታችን በራሱ በሳል ትውልድ የሚመረትበት ከመሆን ይልቅ ለሃገር ፀር፣ ለወገን ጠንቅ የሆኑ መርዛማ ትውልዶችን ወይም ሻል ካለ ካንገት በላይ ሳይሆን ካንገት በታች የሰፉ ሆድ አደር አድር ባይ የሃገር ሸክሞችን ነው እያመረተ ያለው። የትምህርት ስርአታችን አባት አጥቷል። የተቋቋመበትን አላማ ዘንግቷል። በርካሽ ጥቅማጥቅም ፍትህ እየሸጠ ያለው ዳኛ፣ ethicሱን የረገጠው ሃኪም፣ የህዝብ እንባ የማይገርመው civil servant፣ የሃገርን እድገት በራሱ የተንጣለለ ቪላ እና የተንደላቀቀ ህይወት የሚመዝን ሹመኛ፣ ጥላቻ እየቸርቸረ በህዝብ ስም የሚነግድ የደም ነጋዴ የሆነ ፖለቲከኛ፣ ሚዲያን ያክል ትልቅ የለውጥ መሳሪያ ይዞ ሳለ ድባቡን እንዳለ በክፋት፣ በአድር ባይነት፣ በአርቲቡርቲ የሞላው ጋዜጠኛ፣ ... የትምህርት ስርአታችን እንዲህ አይነት ጃርቶችን ነው ያፈራውና እያፈራ ያለው።

የማህበረሰብን ለዘመናት የዘለቀ በሰላም አብሮ የመኖር እሴት የሚንድ፣ ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጭ፣ በህዝብ መሃል መርዝ የሚዘራ መርዝ ትውልድ ቢማርም አልተማረም። ይህ ለተማሪዎቹ ዘር እየመነዘረ ውጤት የሚሰጥ "ምሁር" ተምሯል ሊባል አይችልም። ይሄ ሃይማኖት እየለየ ታዳጊ ልጆችን ከትምህርት ገበታ እየገፋ ያለው ገ ልቱ ፍጡር ለስሙ ካምፓስ ተመላልሷል እንጂ አእምሮው የሸረሪት ድር ያደራበት ኦና ቤት ነው። አልተማረም። የገዛ ወገኑ በኑሮ ስንክሳር ጎብጦ፣ በመከራው ላይ መከራ፣ በችግሩ ላይ ችግር የሚደራርብ ህሊና ቢስ ፖለቲከኛ ከተማሩት የሚቆጠር አይደለም። ወጣቱ ወደ ተሳሳተ አቅጣጫ ሲሄድ እየተመለከተ እውነቱን የማይጋፈጥና መንጋ የሚፈራ አድር ባይ ምሁር ከመሀይም አይሻልም። ከወጣበት ማህበረሰብ ይልቅ ለአላፊ ስርአት ጥብቅና እየቆመ በወገኑ መከራ ላይ አይኑን ጨፍኖ ምናባዊ የተድላ ዓለም ያለን ያህል ሰርክ የሚደሰኩር "ሊቅ" ምኑን ተማረው?! ይሄ መደ ንቆር እንጂ መማር አይደለም።

እና ምን ለማለት ነው? ሰው በሃገራችን ተጨባጭ መማርን ቢወቅስ አትፍረዱበት ለማለት ነው። ሃሳቡ ልክ ባይሆንም ጤነኛ ምሳሌ ሳስቶበታል። ከተማሩት የሚያየው ግራ የሚያጋባ ነው። የመማር ትርጉሙ ምን እንደሆነ እንዲደበዝዝበት ተደርጓል። ተምሯል፣ ተመራምሯል፣ ለሃገር ለወገን ይጠቅማል ብሎ ተስፋ የጣለበት አካል ጭራሽ ተስፋውን የሚነጥቅ ሲሆንበት እንዴት ግራ አይጋባ?!
"እዩልኝ ስሙልኝ ሰው ይፈርዳል በኔ
በግንቦት አግብቻት ወለደች በሰኔ" አለ ግራ የገባው። ግራ የገባው ሰው ብዙ ይላል። እውነት ለመናገር የኢትዮጵያ ምሁር ነገር ላልተማረው ቀርቶ ህሊና ላለው ሁሉ ግራ የሚያጋባ ነው። እና ያልተማረው ምን ያድርግ? ባየው ፈረደ።
ቢሆንም! ቢሆንም! ቢሆንም አለመማር አያኮራም። አለመማር ይሻላል እያልክ በነውርህ እንዳትመፃደቅ። አለመማር ስንኩልነት እንጂ ጌጥ አይደለም።

✍IbnuMunewor

https://t.me/ibnukedir


🌿አዲስ ደርስ


📚ተይሲሩ አህካሚ ተጅዊድ


🎙ክፍል፡16


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🔻በተጅዊድ ዙሪያ የሚያጠነጥን!


🕌 በኢማሙ ነወዊይ የሂፍዝ ማዕከል የተሰጠ።

https://t.me/ibnukedir


🌿አዲስ ደርስ


📚ሱለሙል ውሱል


🎙ክፍል፡16


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🔻በዓቂዳ ዙሪያ የሚያጠነጥን!


🕌 በኢማሙ ነወዊይ የሂፍዝ ማዕከል የተሰጠ።

https://t.me/ibnukedir


🌿አዲስ ደርስ


📚ረውደቱል አንዋር


🎙ቁጥር፡28


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🕌  አቃቂ ዑመር መስጂድ የተሰጠ

@ibnukedir


📚የቁርአን ተፍሲር ቁ፡205


📖ሱረቱ-ዙመር
        

🎙ክፍል፡2


💺በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🕌  አቃቂ ቢላል መስጂድ የተሰጠ

@ibnukedir


📤📤📤📤📤📤📤

🌿የጁሙዓ ኹጥባ ቁ፡52


🔖 የተቅዋ ፍሬ!
   

🎙 በኡስታዝ ሙሐመድ ኸድር


🔻ሊደመጥ የሚገባ ወቅታዊ ኹጥባ!


💫የአጅሩ ተካፋይ እንድንሆን ሼር!


🕌  ቃሊቲ ቶታል ነስር መስጂድ

https://t.me/ibnukedir


🌿🌿🌿🍃ጥቆማ🍃🌿🌿🌿

የአጠያየቅ አደብ
~
ጥያቄ የእውቀት ቁልፍ ነው። ስርአት ሲያጣ ዋጋውን ያጣል። ብዙ ሰዎች ግን አጠያየቅ በራሱ ስርአት እንዳለው ይዘነጋሉ። ወይም ደንታ አይሰጣቸውም። በስርአት የመጠየቅ ፍላጎቱ ከሌለን ከነ ጭራሹ ጥያቄው ቢቀርብን መልካም ነው።

🔻1- ሞገደኛ የሆነ፣ መፈታተን ያለበት፣ ሹፈት ያዘለ፣ ... አጠያየቅ ለጭቅጭቅ ስለሚጋብዝ እንዲሁም ራስንም ሌሎችንም ወንጀል ላይ ሊጥል ስለሚችል መራቅ ይገባል።

🔻2- የቀረበን ትምህርት ተመርኩዘን ሌላ ነጥብ ውስጥ የምንጠይቅ ከሆነ በቅድሚያ የቀረበውን ትምህርት በሚገባ እንረዳ። ከፊት ያለውን በቅጡ ሳይረዱ ለሌላ ጥያቄ መቸኮል ደክሞ ማድከም ነው።

🔻3- ጥያቄያችን በሌሎች ቀድሞ ተጠይቆ ተመልሶ ስለሚችል ኮሜንቶችን ወይም የቀደሙ የቅርብ ፖስቶችን ቃኘት ማድረግ ጥሩ ነው። ይሄ ጠያቂውንም ሌሎች ተከታታዮችንም ከማሰልቸት ያተርፋል።

🔻4- ጥያቄያችን የተሳሳተ ጭብጥ እንዳያሲዝ ፍንትው፣ ቅልብጭ አድርገን ሳናዝረከርክ እናቅርብ። ጥያቄው በፅሑፍ የሚቀርብ ከሆነ ለማንበብ የማያስቸግር አድርገን እንፃፍ።

🔻5- ጥያቄያችን ወይም የጥያቄው መልስ ለቦታው የማይመጥን፣ ፊትና የሚያስነሳ፣ በታዳሚውም ላይ ይሁን፣ በመላሹም ላይ ይሁን፣ በትምህርቱ ዘላቂነትም ላይ ይሁን ጥሩ ያልሆነ ውጤት የሚያስከትል ከሆነ ባደባባይ ሳይሆን በግል እንጠይቅ።

✍IbnuMunewor

https://t.me/ibnukedir

20 last posts shown.