ኢናሊላሂወኢናኢለይሂራጂዑን!!
መጨረሻችን የት ነው?
ይህ ትውልድ ወዴት እያመራ ነው?
ኳስ ዘመናዊ ጣዖት: ኳስ የዘመናችን ወጣት ልብ የተቆጣጠረ: ኳስ ወደ ዲን ቀርቤያለሁ የሚለው ሳይቀር የተፈተነበት በሽታ።
እግር ኳስ መመልከት ከመጀመሪያው እስከ መጨረሻው ጥፋትና መዓት ብቻ። ነው። ምክንያቱም ይበሳጫል: ይወራጫል: ይናደዳል: ቡድንተኝነት ይዘዋል: ሌላም ሌላም።
ተጫዋቾቹ የራሳቸው የሆነ እብደት ያሳያሉ። ወይ በደስታ ወይ በብስጭት። አስቡት አንዴ ቲሸርት ሲያወልቅ: አንዴ ሲወድቅ: አንዴ መሬት ሲመታ: አንዴ ተመልካች ሲሰድብ: መጮኽ: ጭፈራ: ያለ ቅጥ መደሰትና መማረር:መበሳጨት ያለበት የፈሳድ ሜዳ። ይህ ሁሉ ቆም ብሎ ላሰበውና ትንሽ የዲን እውቀት ለቀሰመ: ጥፋትነቱ አይሰወረውም።
ግን ለምን ጭፍንተኛ ሆንን? ለምን ፈረንጅ በተራገጠበት እኛ ወገንተኝነት ያዘን?
ደጋፊዎችና ተመልካቾች ሳይቀሩ: ልብሳቸውን ይቀዳሉ። ቅጥ ያጣ ደስታ ውስጥ ይገባሉ። ቅጥ ያጣ ብስጭት ውስጥ ይገባሉ። ከቤተሰብ ይጣላሉ። እቤታቸው ምግብ አንበላም እስከማለት ይደረሳሉ። ይህ ሁሉ የኳስ በሽታ የያዛቸው ደዩሶች ስራ ነው። እኔ አንዳንድ ሰዎች ይገርሙኛል: ምንም ሳያፍሩ; ወደ ዲን ቀርበው; ሰለፊይ ነን እያሉ: ፂማቸው አሳድገው: ሱሪያቸው ቆርጠው: "እኔ የእገሌ ደጋፊ ነኝ" ይላል። አኡዙቢላህ። ኧረ ልክህን እወቅ?? በኳስ መለከፍ ማለት ሳይታወቅ በኩፍር መለከፍ ነው። ኳስ የዘመናችን ህዝብ በዘመናዊነት የሚያመልከው ጣዖት ነው" አያፍሩም ደግሞ የተጫዋች ፎቶ ፕሮፋይል አድርገው ዘና ሲሉ። ኳስ ጊዜህ: አቅልህ: እድሜህ: እምሽክ አድርጎ ሚበላ የሰይጣን ጥሪ ነው። የሰው ልጅ አዕምሮ: ጭንቅላቱ ሁለት ተቃራኒ ነገር መያዝ አይችልም። ወይ ቁርአንና ሃዲስ ወይ ፊልም: ሙዚቃ ኳስ: ምርጫው በእጅህ ነው። ተውሒድ የተረዳ ፈፅሞ በእንዲህ አይነት ሰይጣናዊ ስራ አይገባም። እንዴ የተውሒድ ባለቤት አላህን የሚያስቆጣ ስራ ይሰራል?
90 ደቂቃ ነገ አላህ ሲጠይቅህ: ምን አረኩባት ልትለው ነው።
መዓት ተጫዋቾች ሃፍዘሃል!!
እስቲ ነብይህ ታውቃቸዋለህ?
የስንት ሶሐቦች ስም ታውቃለህ?
ታቢኢዎችስ: አኢማዎችስ?
ይህ የምልበት የራሴ ተሞክሮ ስላለኝ ነው። (ወላሂ) አራቱ ኸሊፋዎች ማናቸው ብትለው- ኧረ ተወው አራቱም ስማቸው ጠቅሰህ ማናቸው እነዚህ ሶሐቦች ብትለው ማያውቅ: ግን እያንዳንዱ አለም ላይ በሰፊው የሚታወቁ ክለቦች ከነ ተጫዋቾቻቸው ያውቃል። የት እንደተሸጠ: ስንት እንደተሸጠ: እንዴት እንደተሸጠ ብቻ ስለእያንዳንዱ ተጫዋች ያውቃል። ግን ሐዋሪያቶች የማያውቁ መዓት የቁም ሙቶች ሞልተዋል: በኳስ ተበልተዋል። ኳስ የሰው ነብስ ያጠፋል: ወንድም ለወንድም ያቀያይማል: እልህ ያሲዛል ብቻ የሙስሊሙ ባህሪ ጭራሽ የራቀ ነው። ሙስሊሞች ከዚህ የሸይጧን በሽታ መራቅ አለባቸው። አሁን ከወንዶች አልፎ ሴት እህቶቻችንም እዚህ ቆሻሻ ውስጥ ተንቦራጭቀዋል። የዘንድሮው ደግሞ በጣም ሚያሳዝነው: ሚያስለቅሰው የወንጀላችን ጥግ: የአላህ ቤት መስጅድ ውስጥ ኳስ ሲታይ።
TG https://t.me/iliyasNassir/4792
Facebook ላይ የሸይኽ አብዱራዛቅ አል በድር ሃፊዘሁላህ አጭር ምክርም አለበት። ገብታቹ ተመለከቱ። https://fb.watch/h_pddyi4hN/
ይህ ነገር ብዙዎች ቢያስደነግጥም ሃታ!! ኳስ አፍቃሪዎችም ቢደነግጡም: ግን ይህ ነገር የመጣው በኔ ምክንያት ነው ብለው አለመደንገጣቸው ነው። ዝሙት በአንድ ቀን አይፈፀምም: ቀናት: ወራት ሊያስቆጥር ይችላል። ኳስ ወደ ሙስሊሙ ወጣት ልብ ሲገባ ቀስ-በቀስ ነው። ዘንድሮ መስጅድ ውስጥ ሲታይ ብዙዎች ደነገጡ። ቀጣይ ከተደገመ: ይለመዳል። መደገንጥ ብቻ መፍትሔ አይደለም: በቃ በኔ ሰበብ ነው ይህ ፈሳድ የመጣው ብለህ ኳሱን ተወው። "አንተም-ቤተሰብህም-የዲንህም ክብር አስጠብቅ- "ኳስ እኮ ሙስሊሞችም ያያሉ" ሲባል ወላሂ ያሳፍራል። ምንም ካልተሰማህ: አንተ የገዛ አዕምሮህ ለሰይጣን አስረክበሃል ማለት ነው። በነገራችን ላይ ኳስ መመልከት የልብ በሽታና የተያያዙ ሌላም እስከሞት የሚያስከትል በሽታ ያመጣል። "cardiovascular mortality and proarrhythmic effect" ይጨምራል ይላሉ።(ዶክተሮች)
በመጨረሻም ለሌላ ባታስብ ለነፍሲያህ እዘንላት።